ክፍል አንድ
እርግጠኛ ነኝ ይህ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የፃፈው በይበልጥ ለመምህር ግርማ መፃፉን እገነዘባለሁ። ይህ የመልስ ጽሁፍ ብዙ ሐሳዊያን ስላሉ ፣ባህታዊያን ነን ብለው ብዙ ችግር የሚፈጥሩትን የሚያታልሉትን በድጋፍ መልክ አይወክልም ። ወንድማችን በሐሳብህ እነሱን ብለህ ከሆነ በጣም ጥሩ ነው ጥሩ ብለሐል በርታ … ነገር ግን እንደምረዳውም እሳቸውን መምህር ግርማ የሚያጠቁም መሆኑን ስለተረዳሁ ይህን ጽፌልሀለሁ :: ይህ ጽሁፍ ስለ መምህር ግርማ እና በንጹ መንፈስ ለሚያገለግሉ ሁሉ ነው
ለእይታዎችህ በየተራ ቁጥሩ መልስ ለመስጠት ያህል :-
ቁ1/ A/ መምህርን እንድታውቃቸው ያህልትንሽ ልንገርህ ብዙዎቻችን አንተም ሳትወለድ በፊት
A.1/ መምህር ግርማ ዲያቆን ሆነው ለረጅም አመታት በባሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በምግባር በታዛዝነት በጽናት እግዚአብሔርንና ቤተክርስቲያንን ምእመንን አገልግለዋል
A.2/ እንደማንኛውም ሰባኪ ለዘመናት ከዲቁና ጀምሮ እግዚአብሔር እንደገለጠላቸው ህዝበ ክርስቲያናችንን በመንፈሳዊ ስብከት በዚያን ግዜ ጅምሮ አገልግለው ። ፍሬው ያማረ ከብዙሺህ የሚቆጠር ምእመንን ለንስሐና ለቅዱስ ቁርባን አብቅተዋል፣ ክርስቶስን እንዲያውቁ አርገዋል ፣ሕዝቡ የቤተክርስቲያን ሀብት እንዲሆን አርገዋል።
A.3/ ሌላው ልነግርህ የምፈልገው ነገር አንተ አቡነ ጎርጎሪዩስን ሳታውቃቸው በፊት ከብዙ አመታት በፊት መምህር ግርማ የአቡነ ጎርጎሪዩስ በፍቅር ተወዳጅ ተማሪ እንደነበሩ እወቅ። በጣም የሚዋደዱ አባትና ልጅ እንደነበሩ ለእውቀት ያህል እንድትረዳ እፈልጋለሁ። ማለት ምኑንም ሳትጀምሩት መምህር ግርማ የመንፈሳዊ ትምህርትና የጸሎት ብርታ እንደነበራቸው ከአቡነ ጎርጎሪዩስ ጋር የጠነከረ የጠራ የአባትና ልጅ የፍቅር እንደነበራቸው ተረዳ።
ተቺና፣ነቃፊ ስላልሆኑ፣ተንኮል ስለሌላቸው፣በድብቅ ሌላውን ለመጉዳት የማይጠነስሱ ስለሆነ እሳቸው ፍቅር ስላላቸው በጎነታቸውን ስላየ መንፈሳዊ ጉዛቸውን ክርስቶስ ስለወደደው እሱ አብዝቶ ሰጣቸው
እርግጠኛ ነኝ ይህ ሁሉ አልታየህም ያየህው በምን አይን እንደሆነ አልገባኝም
B/ የጸሎት ሕይወት ላልከው መንፈስህ ከፈቀደልህ ጠጋ ብለህ ጠይቃቸው እያቸው ። እግዚአብሔር እረድቶአቸው ምን ያህል በጸሎቱ ህይወት እንደረዳቸው ግንዛቤ ታገኝ ይሆናል
C/ ሌላው ነገር ወገንህ ምን ያህል በእርኩስ መንፈስ እንደተወጠረ የገባህ አይመስለኝም። መሰበኩን ብዙ ትናገራለህ እንጂ የልቡን ጭንቀት ለማየት የተጠጋህ እንካን አልመሰለኝም። አንተ እንዳልከው ማጥመቅ ስራው የሆነ የለም ብለሃል ይህ ያንተ አባባል ነው ። እግዚአብሔር ከተያዘውና ካለቀው ትውልድ አንፃር እንዲያገለግሉ ከወደደላቸው አንተ ምን አስቀናህ አገባህ ።
ክርስቶስ ልጆቹ ይድኑ ዘንድ ፍላጎቱ ነው ። እውነት እልሃለሁ በኔ እይታ ደግሞ አንተ ያልከው የመዳንን በር የሚዘጋ አባባል ነው ፣ ትውልድ በሰይጣን ተጨንቆ ይኑር ብዙ ግልፅ የሆነ ጥምቀትና መናፍስትን ማስወጣት ጥሩ አይደለም ይበቃል የሚል አባባል ያዘለ ይመስላል::
D/ የመንፈስ ቅዱስን አሰራር ከመረጃ ፍለጋ ልታገኘው አትችልም በፍጹም ልትደርስበት አትችልም ካልተፈቀደልህ
E/ ላንተ ጥያቄ … ክርስቶስ ሲመርጣቸውና ሲያድርባቸው ላንተና አልገባ ላላቸው መንገር ነበረበት እንዴ??
አንተን መጠየቅ ነበረበት ወይ?? ይህን በእውነት ከመለስከው ግራ ሊያጋባ ለፃፍከው ነግር ብዙው መልስ ይሆንሃል
ቁ2/ A/ ሌላው ነገር ለምሳሌ አንተ ….. ከመምጣትህ በፊት ዳንኤል ክብረት ሊመጣ ነው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተብሎ ከወር በላይ አይደል እንዴ ጥሪውና ዝግጅቱ … ምን አለበት ታዲያ መምህርም በተሰጣቸው ጸጋ የወንጌልና የፈውስ ግልጋሎት ማዘጋጀቱ ምኑጋር ነው ችግሩ? ባይሆን ጥላቻ ካልሆነ
B/አንድ ነገር ልንገርህ ክብሬ ይገለጣል ብለህ ከምትሸሽ ። ተገልጠህ ነፍሳትን ማዳን ወደ ክርስቶስ ማምጣት እንደሚበልጥ እርግጠኛ ሆኜ እነግርሃለሁ።
C/ ሌላው ስለሌሎች ክብር መገለጥ መጨነቅህና ስብከትህ በዚያ ዙሪያ ማጥፋትህ ጥሩ አይደለም ። ያአንድ ግለሰብ መምህር ራሳቸውን ጠንቅቀው ከክርስቶስ ጋር ስለሚያውቁ ብዙ አትድከም። በቅድስና ላይ ብታተኩር ይሻላል
D/ ስለመሸጥ ተናግረሃል .. ልጠይቅህ ጥንት አባቶቻችን መጸሐፍ መሸጥ የሚባል ነገር አልነበረም ። አንተ ወይም ሌሎች ለምን መጸሃፍ ትሸጣላቹሁ? ይህን ከመለስክ መምህር ለምን እንደሚሸጡ መለስክልን ማለት ነው።
E/ብዙ ነገሮችህ ቅዱሳኖችን እየጠራህ እነሱ እንዲ አያረጉም ነበር እነዚህ ግን እንዲህ ነው ትላለህ ። አሁንም ልጠይቅህ … የድሮዎቹ ሰባኪ ለአገልግሎታቸው ብር አይቀበሉም ነበር ። ልምንድነው አንተም ሌሎችም ግን የግልጋሎት ዋጋ በብር ይሰጣቹሃል ለምን ይመስልሃል? … ይህን ከመለስክ መምህር ለምን እንደሚሸጡ መለስክልን ማለት ነው። በተጨማሪ ላሳውቅህ የምፈልገው መምህር ሁሉ ጋር በነፃ በፍቅር ነው የሚያገለግሉት ሰዎች አስገድደው ዋጋ ካልተቀበሉ ብለው ያስገድዳሉ እንጂ
ቁ3/ በኢየሱስ አልወጣም በማሪያም ነው ብለሃልይህ? እዚህ ጋር እንደመናፍቅነት እይታህ የጎላ ነው ። ይህ በስህተት እይታ ያየ ፣ የሰይጣንን ቃል ሰምተህ እንጂ መምህር ጋር እንዲህ አይደለም ። እይታህ ለመንቀፍ ችኩል እንደሆነ እረዳለሁ።
አጋንንት በሚካኤል ስም ቢወጣ ። የክርስቶስን ክብር ዝቅ ማረግ አይደለም ።በሚካኤል ስም ቢወጣ የጌታ ፈቃዱ ሆኖ መሆኑን ዘንግተሃል። በየትኛው አይን እና ህሊና እንዳየህው እራስህን ጠይቅ?
ቁ4/አንተ በመቁጠሪያ ይወጣል ይላሉ ብለሃል:: እይታህ በጣም መሳሳቱን እይ ። እሳቸው እንዲህ አላሉም ከሄዱበት መንፈሳዊ መንገድና ጉዞ አንፃር የተደበቀ መናፍስትን በክርስቶስ ስም ማድከሚያ የእኛ ጦር መሳሪያ ነው። አሁንም ላይገባህ ይችላል ግን ምን ማረግ ይቻላል ለብዙዎች ግን ጦር መሳሪያችን ነው እወቀው።
ቁ5/ያ ግዜና ይህ አንድ አይደለም ለምሳሌ በዚያ ግዜ ከ200 ሰው 1 ስው በመናፍስት የተጎዳ ነበር አሁን ግን ከ200 ሰው በትንሹ 190 ሰው የተጠቃ ነው።
ሌላው ደግሞ መተተኞቹና አስማተኞቹ በጣም በዝተው ። ትውልዱን ከዲያብሎስ ጋር አንድ ሆነው በስውር የጨረሱበት ዘመን ነው ።ሰይጣንን ለአላማቸው ጠርተው ሂድ ይህን አድርግልኝ የሚሉ ብዙ እንዳሉ እኔ ላንተ አልነግርህም ። አይ አላውቅም ውሸት ነው ካልክ የቆሎ ተማሪ የሆነን ሰው በተወለድክበት ቦታ ጠይቃቸው በጣም ብዙ ይነግሩሃል።
አንተ እንዳልከው ይህ የሰይጣንን ኃይል የሚያሳይ ነው ብለሃል ። እየውልህ እይታህ በተሳሳተ መንገድ መቆሙን አየን ።የእኛ እይታ ደግሞ ደግሞ የሰይጣን ደካማና አልቃሻ ነቱን በክርስቶስ እንዴት እንደሚባረር ተረዳን መምህር ግርማ አስተማሩን ።
ይህ ሁሉ ሰው በሰይጣን ሲያዝ ክርስቶስ የለምን ጥምቀቱና ቁርባኑ አይሰራምን ብለህ ጠይቀሃል
ጥያቄ ላንተና የተመሳሰለ ሃሳብ ላላቸው
በመፃህፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙዎች ተይዘው የተጎዱ አሉ ። ለምን ይመስልሃል ሲያዙ ዝም የተባለው? ይህን ከመለስክ አሁንም መልሱን አግኝተሃል።
ክርስቶስ ነፃነት ሰጥቶናል ግን በራሱ እጅ ሰው ይያዛል። ጥምቀቱና ቅዱስ ቁርባል ታላቅ የክርስቶስ ልጅነትና ኃይልን አሲዞን ነበር ነገር ግን በራስ እጅ የዲያብሎስ እጅ ውስጥ እየገባን እንጂ
ቁ6/ክፉ የሚሰሩ ሰዎች ይጋለጡ ዘንድ ለነሱና ለዲያብሎስ አጋዝ የሆነ አስተያየት መሆኑን እገነዘባለሁ። ሰይጣን ውሸታም ነው ። የክፉዎች መረብ የመታቾች ተንኮል የነቃና ይፈርስ ዘንድ የማይፈቅድ ጥንቃቄ ያለበት አባባል ይመስላል
ቁ7/መምህር ግርማ ይህ ቅድስና ነው አላሉም ። ለክርስቶስ መንጋ እንዲያገለግሉ ክርስቶስ ሾማቸው እንጂ። በክርስቶስ ሹመት አንተ ምንም አያገባህም ። ብትችል ከበረከታቸው ተካፈል እንጂ እንዲህ ነው እንዲህ ነው ልትል አቅሙም ስልጣኑም የለህም ። ገዳምም ይሁን ከተማ በክርስቶስ ምርጫና አሰራር የሚያገባህ አይመስለኝም።
ቁ8/አንተ የወደፊቱን አሳች እያሰብክ እየፈራህ ዛሬ ክርስቶስ የመረጣቸው የጠራቸውን መምህር ግርማን ወቃሽና አዋራጅ ለመሆን ምክንያት ትደረድራለህ ። ከሩቅ ሆነህ መረጃ ሰብስበህ ያወሩልህን እውነት ብለህ ከምትነዛ ቀረብ ብለህ ትምህርታቸውን ተማር በጣም ብዙ ትምህርት ታገኝበትና እይታህ ይቃናል የክርስቶስ ሐዋሪያ መሆናቸውን ትረዳለህ። ለዚህ እድል ክርስቶስ ይርዳህ።
ቁ10/ ከክርስቶስ ይልቅ መምህር ግርማ አልጎሉል አልከበሩም ይህ እይታህ እዚህ ጋር እንደመናፍቅነት እይታህ የጎላ ነው ። በመምህር ግርማ ስብከትና ፈውስ ክርስቶስ ከበረ ክርስቶስ ሰራ እንጂ እኔ ያሉበት ቦታ አላየሁም ።ሌሎች ሌላ ነገር ብለውክ ይሆናል በራስህ ቀርበህ ከማየት ይልቅ።
በአጠቃላይ በመምህር ግርማ ዙሪያ ላወጣህው ድብቅ ገላጭ ጽሁፍ ወንድማችን እይታህ እንደተሳሳተ እነግርሃለሁ ሕዝቡም አይቶት ይመሰክራል
ሁሉ ሰው እንደ እምነቱና እንደገባው መጠን መርከስም መቀደስም ተፈቅዳል ስለዚህ መቀበልም አለመቀበልም እንደዚሁ ። እኔ ለምን መምህር ግርማን አልተቀበላቹሁም አይደለም ነገር ግን
ልክ ለሌላው ሊድን ሲል ከሰይጣን ሰንሰለት ሊላቀቅ ሲል ግን ብዙዎች አወቅንልህ ብለው የሚከለክል የዲያብሎስን ያህል ምክር ይመክራሉ … ሰውየው ግን ተይዞ ለዘመናት ሲያነደው ማንም ትንፍሽ ያላለ …. የመዳኛው ሰአት ሲደርስ ግን … ሁሉ የሞት ሽረት ላንተ ጠበቃ ሆኖ ሲከለክልህ ግራ ሲያጋባህ ይታያል ። ይህም ያስጠይቅሀል….
“ሉቃ 11፥52
እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ወዮላችሁ ራሳችሁ አልገባችሁም የሚገቡትንም ከለከላችሁ”
የሌላውን ሰይጣን ያሰረበትን ሰንሰለት እንዳይበጠስ ወደ መዳን የሚገቡትን ከልካይ ሆነህ መቀመጥህን አስተውል
አስተውል ልኡል እግዚአብሔርን ዝም ብለህ ተቃዋሚ ሆነህ መቆምህን እንድትረዳ ልብህን መርምረው። አንተ ክፍ ትውልድ ልኡል እግዚአብሔር ያነሳውን ባለሞል ልታሰናክል እንደማትችል እነግርሀለሁ ።ባይሆን በምኞትህ እንደምትወድቅ የጌታ መለኮታዊ ቃሉ ይነግረናል:: ከመደፋፈርህ በፊት አስተውል ከቻልክ ቅዱስ መንፈስ ካለብህ በፀሎት ጌታን ለምን!!
እግዚአብሔር መምህር ግርማን ሀይሉን ፍቅሩን ለመንጋው የገለጠባቸው የሚገልጥባቸው ታማኝ ባለሟል ከሆኑት ውስጥ ስለሆኑ ።(ይህንንም ስል በሌሎች በጣም ብዙ አባቶቻችን ገልፃል ይገልፃልም ማለቴም ነው)እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሳቸው በኩል ስለሚገስፀን የጌታን ቃል እንማራለን እናድጋለን ። ግን ሌሎች በቅናት ልቦና ቆመው ሆይ ሆይ እንደሚሉት “አድናቂና ዝምብሎ ተከታይ ቲፎዞ ግን አይደለንም”
መንፈሳዊ ወገኖቼ አምላካችን ክርስቶስ በባለሞሉ በመምህር ግርማ በኩል ሊያሳስበን የፈለገውን መንፈሳዊ ንቃት ያስተዋላቹሁ ። አይዛቹሁ በርቱ አብዝቶ ይግለፅልን በሀይማኖት ምግባር ፍቅር እምነት በርቱ ”ፊሊጽሲዮስ 1፥ 28-29 በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ” ሳያውቁ ግራ ለተጋቡብን ወገኖቻችንም በፀሎታቹሁ አሳስቡላቸው ወደማስተዋል ህሊና እንዲኖሩ
በወደደን በክርስቶስ እንሻገራለን!!
በክፍል ሁለት እንገናኝ!
ከኢያሱ ሚካኤል