June 1, 2013
13 mins read

Health: የመራራው ሎሚ ጣፋጭ ጠቀሜታዎች

ከቅድስት አባተ

ምንጭ፡ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 51

የሎሚ ስረ መሰረት ባይታወቅም፣ የመጀመሪያዎቹ ዛፎች በደቡባዊ ህንድ፣ ሰሜናዊ ምያንማር (በረማ) እና ቻይና እንደበቀሉ ይገመታል፡፡ በሎሚ ስረ መሰረት ዙሪያ የተደረገ ጥናት ፍሬው የመራራ ብርቱካንና የባህረ ሎሚ ድቃይ እንደሆነ አመላክቷል፡፡

ሎሚ ወደ አውሮጳ የገባው በጥንታዊት ሮም ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ በአንደኛው ምዕተ ዓመት በደቡባዊ ጣልያን ነው፡፡ ይሁን እንጂ፣ በወቅቱ በሰፋት አልተተከለም፡፡ በቀጣይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፋርስ ከገባ በኋላ ወደ ኢራቅና ግብፅ ተሰራጭቷል፡፡ ሎሚ ለመጀመሪያ ጊዜ በስነ ጽሑፍ ላይ ሰፍሮ የምናገኘው በ10ኛው ምዕተ ዓመት በአረብኛ ቋንቋ በእርሻ ዙሪያ በተፃፈ አንድ ጽሑፍ ላይ ነው፡፡ ሎሚ በቀደምት የሙስሊም አፀድ ውስጥ በጌጥ ተክልነት ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡ በ1000 እና 1150 ዓ.ም መካከል ባሉት ዓመታት ደግሞ በዐረቡ ዓለምና በሜዲትራኒያን ክልል በስፋት ተሰራጭቷል፡፡

የመጀመሪያው የሎሚ መጠነ ሰፊ እርሻ በአውሮጳ የተጀመረው በ15ኛው ምዕተ ዓመት አጋማሽ በጀኖዋ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ክሪስቶፈር ኮለምበስ በባህር ጉዞዎቹ የሎሚ ዘርን ወደ ሂስፓኒዮላ በወሰደበት 1493 ዓ.ም ከምዕራቡ ንፍቀ ክበብ ገብቷል፡፡ ስፔናውያን አዲሱን ዓለም በወረራ ማስገበራቸው የሎሚ ዘሮችን ስርጭት አግዟል፡፡ ሎሚ በምዕራቡ ንፍቀ ክበብ በአብዛኛው ጥቅም ላይ ይውል የነበረው እንደ ጌጥ ተክልና ለመድሃኒት ነበር፡፡ ሎሚ በ18ኛውና 19ኛው ምዕተ ዓመት በስፋት በፍሎሪዳና ካሊፎርኒያ ግዛት ይተከል ነበር፡፡

ጀምስ ሊንድ የተባለው እንግሊዛዊ ሐኪም በ1747 ዓ.ም በእስከርቪ በሽታ በሚሰቃዩ መርከበኞች ላይ ባደረገው ጥናት የሎሚ ጭማቂ በመጠቀም በአመጋገብ ስርዓታቸው ላይ ቪታሚን ሲ ጨምሮ ውጤታማ መሆን ችሏል፡፡

ጥቅሞች

የሎሚ ዘይት ለአሮማቴራፒ ያገለግላል፡፡ የኦሃዩ ግዛት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የሎሚ ዘይት ሽታ በሰው ልጅ የቅስሙ ተፈጥሮ መከላከያ ስርዓት ላይ ተፅዕኖ ባያሳድርም፣ ስሜታዊ ሁኔታን ሊያሻሽል እንደሚችል ደርሰውበታል፡፡

በፍሌት (Fermentation) ላይ የተመሰረቱ ሂደቶች ከመዳበራቸው ቀደም ብሎ ሎሚ ዋነኛው የሲትሪክ አሲድ ምንጭ ነበር፡፡ ብዙ የገንዘብ ኖት የሚቆጠሩ የባንክ ገንዘብ ከፋዮችንና ገንዘብ ተቀባዮችን የመሰሉ ሰራተኞች ጣታቸውን ለማርጠብ ለሁለት የተከፈለ ሎሚ ይጠቀማሉ፡፡

የሎሚ ጭማቂ ለማጽጃነት ሊያገለግል ይችላል፡፡ ለሁለት የተከፈለ ሎሚ በጨው ወይም ሶዲየም ባይካርቤኔት (baking powder) ውስጥ ነከር አድርጎ ከመዳብ የተሰራ ድስትና መጥበሻ መሰል የወጥ ቤት ቁሳቁሶችን እስኪያንፀባርቁ ድረስ ለመወልወል ይውላል፡፡ የሎሚው አሲድ ቆሻሻውን ሲያስወግድ፣ ጨው ወይም ሶዲየም ባይካርቦኔቱ በማጽዳቱ ሂደት ያግዛሉ፡፡ የሎሚ ጭማቂው መልካም ጠረን ሊሰጥ፣ ቅባትን ሊያስወግድ፣ ቆሻሻን ሊያነጣና ጀርሞችን ሊያስወግድ ይችላል፡፡

ከሶዲየም ባይካርቦኔት ጋር ሲደባለቅ ደግሞ ከፕላስቲክ ሰራሽ ምግብ መያዣ እቃዎች ላይ ቆሻሻን ያስወግዳል፡፡

የሎሚ ልጣጭ ዘይትም እንዲሁ የተለያዩ ጥቅሞች አሉት፡፡ የመሟሟት ባህርዩ የቆየ ሰም፣ የጣት አሻራ፣ ላብና አቧሯ ለማሟሟት ጥቅም ላይ በሚውልበት ለዕንጨት ማጽጃነትና መወልወያነት ያገለግላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ የሎሚ ልጣጭ ዘይት መርዛማ ላልሆነ ፀረ ተባይ መድሃኒት ማምረቻነት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

ተመራማሪዎች ኤሌክትሮዶችን ከሎሚ ጋር በማያያዝና ኤሌክትሪክ ለማመንጨት እንደ ባትሪ የተጠቀሙበት አንድ ሙከራ ተካሂዷል፡፡ ምንም እንኳን አነስተኛ ኃይል ቢያመነጩም፣ በርካታ ሎሚ ሰራሽ ባትሪዎች አንድ አነሰተኛ ዲጂታል ሰዓት ለማንቀሳቀሰ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፡፡ ይህ አይነቱ ሙከራ በሌሎች ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ጭምር ሰርቷል፡፡ የሎሚ ጭማቂ አንዳንድ ጊዜ በትምህርታዊ የሳይንስ ሙከራዎች በአሲድነት ጥቅም ላይ ይወላል፡፡

ሎሚ በህንድ ለባህላዊ ህክምና ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የህንድ ባህላዊ ሐኪሞች ሎሚን እንደ ጠቃሚ ፍራፍሬ በመመለከት ባህርያቱን ያደንቃሉ፡፡ የሚኮመጥጠው፣ የሚሰነፍጠውና የአካልን ህብረ ህዋሳት የሚያኮማትረው ሎሚ የሐሞትን ከመጠን ያለፈ ፍሰትን ይቆጣጠራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ አፍን ያፀዳል፡፡ አክታን ከማስወገድ ባለፈ ያስገሳናል፡፡ በምግብ መንሸራሸር ሂደት እገዛ የሚያደርገውና የሆድ ድርቀትን የሚያስወግደው ሎሚ፣ ትውከትን፣ የጉሮሮ ችግርን፣ አሲዳማነትንና ቁርጥማትን ይከላከላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ የአንጀት ትላትሎችን ያሰወግዳል፡፡

የሎሚ ጭማቂ ጠንካራ ፀረ ባክቴሪያ ነው፡፡ የወባ፣ የኮሌራ፣ የታይፎይድና የሌሎች ገዳይ በሽታዎች ባክቴሪያ በሎሚ ጭማቂ እንደሚጠፋ በሙከራ ተረጋግጧል፡፡ ሎሚ የተወሰነ ቪታሚን ኤ እና ከሰው ሰራሹ የበለጠ ውጤታማ የሆነ ቪታሚን ሲ በውስጡ ይዟል፡፡ በሎሚ ጭማቂ ውስጥ ያለው ቪታሚን ሲ ከቪታሚን ቢ ጋር ስለሚጣመር ይበልጥ ፍቱን ነው፡፡ ሎሚ ከቪታሚን ሲ በተጨማሪ ቢ ኮምፕሌክስ ቪታሚኖችን በአነስተኛ መጠን ይዟል፡፡

የሎሚ ጭማቂ ከመጠጣቱ በፊት በውሃ መቅጠን አለበት፡፡ ንፁህ የሎሚ ጭማቂ የጥርስን ጥሩር (መስተዋት መሰል ክፍል) የሚጎዳ አሲድ አለው፡፡

ጠዋት በባዶ ሆድ ከቀዝቃዛ ውሃና ማር ጋር የተደባለቀ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት የውስጥ አካላችንን ያፀዳልናል፡፡ የሆድ ድርቀትን ለማስወገድ ከፈለግን አልፎ አልፎ ቀዝቃዛውን ለብ ባለ ውሃ መተካት እንችላለን፡፡

የሎሚ ጭማቂ እንፍሎዌንዛን፣ ወባንና ጉንፋንን ይከላከላል ወይም እንዳይጠናከር ያግዛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ ትኩሳትን ያቃልላል፡፡ ከውሃ ጋር የተደባለቀ የሎሚ ጭማቂ የስኳር ህመምተኛን የውሃ ጥም ለመቁረጥ ይጠቅማል፡፡ ለሆድ ዕቃ ችግሮች ፈጣን ማስታገሻ ነው፡፡ ሎሚ ለነርቮችና ለልብ የማረጋጋትን ሚና ይጫወታል፡፡

ሎሚ በተለይ ለቪታሚን ሲ ጥቅም እጅጉን ይፈለጋል፡፡ ቫስኮ ዳ ጋማ በደቡብ አፍሪካ፣ የመልካም ተስፋ ርዕሰ ምድር በኩል አድርጎ ከፖርቹጋል ወደ ህንድ በተጓዘበት ወቅት ከመርከበኞቹ መካከል ሁለት ሶስተኛው ያህሉ በእስከርቪ በሽታ ሳቢያ ሞተውበታል፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን ሎሚ በስፋት ጥቅም ላይ በመዋሉ እንዲህ አይነቱ ጥፋት አይከሰትም፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው መርከበኞች ሎሚን በመጠቀም ሕይወታቸውን መታደግ ችለዋል፡፡

በሎሚ ዙሪያ የተደረጉ ምርምሮች እንዳሳዩት፣ የሎሚ ዘይት የማረጋጋት ባህርይ ስላለው ድካምን፣ ዝለትን፣ መጫጫንን፣ ጭንቀትን፣ ስጋትንና ውጥረት በመቀነሱ በኩል እገዛ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ የሎሚ ዘይትን በአፍንጫ መማግ ማስተዋልንና ንቁነትን ሊያሳድግ ይችላል፡፡ ስለዚህም፣ የሠራተኞችን ቅልጥፍና ለማሳደግ በቢሮ ውስጥ እንደ ፍሬሽነር ሊያገለግል ይችላል፡፡ የመንፈስ ጭንቀት ከተሰማን ጥቂት የሎሚ ዘይት መሐረባችን ላይ በማድረግ በአፍንጫችን መማጉ ጥሩ ነው፡፡

ሎሚ የተወሰኑ ቅመማ ቅመሞችን፣ አልኮል መጠጥ ወይም ሲጋራ ከወሰድን በኋላ፣ አሊያም በቂ ምራቅ በማጣት ሳቢያ የሚፈጠረውን መጥፎ የአፍ ጠረን ያሰወግድልናል፡፡ ጥሩ የአፍ ጠረን እንዲኖረን ከፈለግን የአንድ ሎሚ ጭማቂ ከአንድ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃ ጋር በመደባለቅ አፋችንን በተደጋጋሚ መጉመጥመጥ እንችላለን፡፡ ምግብ ከበላን በኋላ ሎሚ መምጠጡም እንዲሁ እገዛ ያደርጋል፡፡

ቃር፣ የኩላሊት ወይም የፊኛ ችግር ወይም የሲትረስ አለርጂ ካለብን ሎሚ ከመብላታችን ወይም ከመጠጣታችን በፊት የጤና ባለሙያ ማማከር ይኖርብናል፡፡ የጥርሳችንን ጥሩር ለመከላከል ሎሚ ከተጠቀምን በኋላ ጥርሳችንን ቢያንስ ለግማሽ ሰዓት መቦረሽ የለብንም፡፡ በሎሚ ጭማቂ ማሸት ወይም የሎሚ ጭማቂ መጠጣት ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት አይመከርም፡፡ S

tenaadam.comን ይጎብኙ

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop