May 26, 2013
9 mins read

እርማት ለጃዋር መሐመድ፡ በነጭ ውሸት ላይ የተመሰረተ ትንተና የት ያደርሰን ይሆን?

በቴዎድሮስ በላይ

አቶ ጁዋር ሲራጅ መሃመድ በቅርቡ ከአቶ ደረጀ ደስታ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ (http://ethsat.com/video/esat-yehager-lij-activist-juwar-mohamed-10-may-2013/) በአጽንኦት ተከታትያለሁ። የሰውየው ግለ ታሪክና ያደረጋቸው ጉዞዎች መሳጭ ቢሆኑም አንዳንድ እርማት የሚያስፈልጋቸው የተሳሳቱና የተዛቡ ታሪኮችን እንደገና እንዲፈትሽ፤ ሆን ብሎ እያራገበው ከሆነም ቆም ብሎ እንዲያስብበት ለመጠቆም ወደድኩ። የተሳሳተ መረጃ መረጃ ራስንም ሌላውንም ክፉኛ ይጎዳል። ሊዘህ መነሻ የሆነኝ፤ ስለ ኦሮሞ ጭቆና መነሻውን ሲገገልጽ፤ አማራዎቹ የአውሮፓን መሳሪያ ቀድመው ስላገኙ የሚል፤ መሰረት የለሽ ውንጀላው ነው።
ጋዜጠኛ ደረጀ ስለ ኦነግ አመሰራረት ሲጠይቀው፤ ጁዋር እንዲሚከተለው መለሰ። “እንግዲህ በመቶ አመታት ወደዃላ ሂደን ስናይ አካባቢው በቡድን ግጭት የተሞላ ነበር-በተለይ ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ። ከዚያ በፊት አብዛኛው የሐይማኖት ነበር። በሐይማኖት ስር የተደራጁ መንግስታት ነበር ሲጋጩ የነበሩት። ከዚያ በዃላ ግን የብሔር ግጭቶች ነበሩ። ይህ የብሔር ግጭት፤ በአማራ፣ በኦሮሞና በትግሬ የተካሄደው ነው-ኢትዮጵያን የወለደው። በዚህ ግጭት ውስጥ ቀድሞ የአውሮፓን መሳሪያ ሊያገኝ የቻለው የአማራው ሀይል አሸንፎ፤ በበላይነት አሁን የምናውቃት ኢትዮጵያን ፈጠረ። “ እጅግ በጣም የገረመኝ መልስ ነው። በእርግጥ አቶ ጁዋር ብቻ አይደለም ፤ በቅርብ ጊዜ የምሰማው ከመሰሎቹ የኦሮሞ ወንድሞቼ የዕለት ከዕለት ውንጀላ ሆኗል። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል፤ እንዲሉ የዚህ አይነቱን ነገር እንደ እውነት ሳይወስዱት አልቀረም።
ይሄ መልስህ፤ ብዙ ጥያቄዎችን አጭሮብኛል፡
• በውኑ ኢትዮጵያን የወለደ ከ14ኛው አመት በዃላ ያለው የብሔር ግጭት ነው?
• ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበሩት የሐይማኖች ግጭቶች፤ የኦሮሞ ሕዝብ የት ይሆን የነበረው?
• በውኑ አማራው ነው የውጭዎቹን መሳራያውን ቀድሞ ያገኘው? ማረጋገጫ ልትሰጠኝ ትችላለህ? እኔ ያነበብሁትና የማውቀው ሌላ ነው።
ለምን የፈጠራ ውንጀላ ውስጥ በተለይ ማንበብና መጻፍ ከምንችል ሰዎች መካከል እንደምንዘፈቅ አይገባኝም። ሁለቱን ጥያቄዎች ለአቶ ጁዋር ትቼ፤ ለውንጀላ የተጠቀምህበትን ሶስተኛውን ጥያቄ እኔው ካነበብሁት እመልሳሃለሁ። ስህተት ከሆነ ማስረጃ ያቅርብና እንከራከርበት። ኢትዮጵያውያን እርስ በራሳቸው፤ በአካባቢያቸው በሰሩት መሳሪያ ይዋጉና አሸናፊው ይገዛ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። በዚህ እርሱ እና እኔም እንስማማለን። እንዲህ አይነቱ ልማድ በሌሎቹም አለም ሲደረግ የኖረ ሃቅ ነው። ነገር ግን የአለም ሁኔታ ተቀይሮ፤ አንዱ የሌላውን ሃብት ድምበር አቋርጦ ለመዝረፍ ሲባል፤ ጠመንጃ መሳሪያን ይዘው ብቅ አሉ። በመሰረቱ የጠመንጃ መሳሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ14ኛው ክፍለ ዘመን በቻይናዎች ነው። ወዲያውኑም ወደ ሩቅ ምስራቆችና አውሮፓዎቹ ተዛመተ። አውሮፓውያንና ሩቅ ምስራቆች፤ በሐይማኖት ሰበብ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭትን አስነሱ፤ የጠበንጃ መሳሪያውንም ይዘው ተነሱ። በኢትዮጵያም ይኸው ሆነ። በወቅቱ፤ ከክርስቲያኖች ጋር ለተጣላው ግራኝ አህመድ፤ ቱርኮቹ ልዩ ሰልጠና ሰጥተው የጦር መሳሪያ አስታጥቀው፤ ከሰለጠነ ወታደር ጋር ወደ ኢትዮጵያ አስገቡት፤ በ11529 ጀምሮ ኢትዮጵያን በይፋ ወረረ። በጦርና በጨበጣ ብቻ የመዋጋት ልምድ የነበራቸው ኢትዮጵያውያን፤ የጠመንጃ መሳሪያ የታጠቀውን መሃመድን በምንም መልኩ ሊቆጣጠሩት አልቻሉም። ብዙ የሰው ህይወትና የአገር ሃብት አወደመ። በወቅቱ የነበሩ ገዥዎች፤ እርሱን ለመቋቋም፤ ክርስቲያን ክፍል የሆኑትን ፓርችጋሎችን በመማጸን የመሳሪያና የሰው ሃይል እርዳታ አግኘተው፤ ተዋግተው አሸነፉ። ይህ ነው የጠመንጃ መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ አመጣጡ። ይሄን እውነታ ቀይሮ አማሮቹ መሳሪያ ቀድሞ ስላገኑ የሚለው አካሄድ፤ ምን አይነት የፓለቲካ ትርፍ ያመጣ ይሆን? በመሰረቱ፤ የግራኝ ጦርነትን ተከትሎ ሰሜኑን የወረረው ማን ነው። የኦሮሞዎች ወረራና በቀላሉ ሰፊውን የሃገሪቱ ክፍል የመያዝ ውጤቱ፤ በግራኝ አማካኝነት የተካሄደው ጭፍጨፋ ከፍተኛ የሆነውን የአማራ ሕዝብ ስለጨረሰ ነው። ለዚህ መከራከሪያ ምላሹን ከአቶ ጁዋር እፈልጋለሁ። የኦሮሞ ማህበረሰብ በወቅቱ የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም፤ የሰሜኑን ክፍል ወርሮ ያሸነፈው ብቸኛው ምክንያት ይሄው ነው። የጦር መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ መግባት የጠቀመው፤ አቶ ጁዋር እንደጠቀሰው አማራውን ሳይሆን ኦሮሞውን ነው። ከቆላማው ወደ ደጋማውና ለም የሃገሪቱ ክፍል እንዲገቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጎላቸዋል። ይሄን ጥሬ ሃቅ ክዶ፤ በወቅቱ የተሰራን ግፍ ወደ ሌላው መለከክ፤ ከአንድ የፓለቲካ ተንታኝ፣ ያውም ሌሎቹን እያሰለጠነ ካለ በፍጹም አይጠበቅም።
በወንድሜ፤ በአቶ ጁዋር አካሄድ ቢተነተን፤ እስላምና በኢትዮጵያ ምድር ለመስፋፋት አስተዋጽኦ ያደረገው፤ የጠመንጃ መሳሪያ የሙስሊሞቹ መሪ የነበረ በመጀመሪያ በእጁ በቱርክ በኩል ከልዩ ስልጠና ጋር ስለገባ፤ ብዙውን ሰው አሰለመ ወደሚለው ያደርሰናል። እናም፤ ሙስሎሞች ጥፋት ስላጠፉ…..የሚል ጭልጥ ያለ ውንብድና ውስጥ ይከተናል። እኔ ግን ይሄን አልቀበለውም። ምንም ይሁን ምን፤ ደካማ ጎናችንን በመጠቀም፤ የውጭ ሃይሎች የጫኑብን መከራ ነበር ብዬ ነው የማልፈው። ለዛሬ ችግራችንም መጥቀስን አልፈልግም። ምክንያቱም፤ በእነሱ ተንኮል ስር እንደገባሁ ስለምቆጠርው። እናም ጁዋር፤ የኦሮሞ ችግር በውኑ በአማራው የደረሰብት መከራ ነበርን ለማት ታሪኩን፤ መሳሪያ ከመግባቱ በፊት የነበረውን ሁኔታ በጥልቅ እንዲያነቡና ለሁላችን የሚያስማማ፤ እያንዳንዱ ዜጋ የተከበረባት ኢትዮጵያን ለማዬት እጅግ ወሳኝ ነው እላለሁ።
አበቃሁ።

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop