October 16, 2014
10 mins read

Health: ሐኪሞች እንዴት በዘር ፍሬዬ አለመኖር ይደናገጣሉ? ችግሬ ከአዕምሮ ዝግመት ጋር ይያያዝ ይሆን?

አንድ ጥያቄ ነበረኝ፡፡ ይህ ጥያቄዬ ደግሞ ወጣት እንደመሆኔ መጠን የየዕለት ሃሳብና ጭንቀት ሆኖብኛል፡፡ ወንድነቴ እያሳፈረኝ መጥቷል፡፡ ይኸውም ከዘር ፍሬዎቼ አንዱ የለም፡፡ ይህ ደግሞ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለመሮጥና አንዳንዴ እንደ ኮሌጅ ተማሪነቴ ለጥናት ብዙ ሰዓት መቀመጥ እየከለከለኝ ነው፡፡ አሁን አሁንማ ፍርሃት ፍርሃት እያለኝ ስለመጣ እባካችሁ፡-
1. ይህ ነገር ከምን እንደሚመጣ ንገሩኝ? ምክንያቱም የአባላዘር በሽ እንዳልል ምንም የፈፀምኩት ነገር የለም፡፡
2. ሐኪም አማክሬ እንደዚህ አይነት ነገር እስካሁን አላጋጠመኝም ስላሉኝ ነው፡፡ ምን ይሻላል?
ሳሚ ነኝ

መልስ:- ውድ ሳሚ የአንደኛው የዘር ፍሬህ አለመኖር ሐኪሞችን ማስደንገጡ እኛንም አስደንግጦናል፡፡ ምክንያቱም ዘር ፍሬ በተለመደው ስፍራው ውስጥ አለመኖር በአንተ ላይ ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ሳይሆን ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ ችግር ነው፡፡ በሕክምናው ዓለም ተለይቶ የታወቀ በመሆኑም ያማከርካቸው ሐኪሞች ማስደንገጡ ገርሞን ነው ‹‹የደነገጥነው››
የአዕምሮ ‹‹ዝንጉነት›› ብለህ የጠቀስከው ችግር በአንተ ላይ የተከሰተ ባይመስልም እና ከዘር ፍሬዎች አለመኖር ጋር እምብዛም የተያዘ ባይሆንም ወደ ኋላ ላይ ዘርዘር ባለ መልኩ እንመለከታለን፡፡

በእርግጥ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬዎች (testicles) በተለመደው /በተገቢ/ ስፍራ፣ ማለትም በቆለጥ ውስጥ የሉም ማለት ፍፁም አልተፈጠሩም ማለት አይደለም፡፡ የዘር ፍሬዎች ያልተፈጠሩለት ወንድ ልጅ የለም ለማለት ይቻላል፡፡ በተለመደው ስፍራቸው ማለትም በቆለጥ ውስጥ አለመገኘታቸው ግን የተለመደ እና ከአንድ ሺ አዋቂ ወንዶች መካከል በአስሩ የሚያጋጥም ክስተት ነው፡፡

ወደ ታዳጊነት የዕድሜ ክልል ስንመጣ ችግሩ የሚታይባቸው ህፃናት ቁጥር የበለጠ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በርካታ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከአንድ ሺ ታዳጊ ህፃናት መካከል ሃያ ያህሉ የዚህ ችግር ሰለባዎች ናቸው፡፡
ታዲያ የተፈጠሩት ግን የሌሉት የዘር ፍሬዎች ምን ዋጣቸው? በእናቱ ማህፀን ያለ እና ገና ያልተወለደ ጽንስ የዘር ፍሬዎቹ የሚገኙት በቆለጡ ውስጥ ሳይሆን በሆዱ ውስጥ ነው፡፡ የመወለጃው ቀን እየተቃረበ ሲሄድም ፍሬዎቹ ከሆድ መውጣት ይጀምሩና መጨረሻ ላይ ሙሉ በሙሉ ተገፍተው ቆለጥ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ይህ የዘር ፍሬዎች ከሆድ ወደ ውጭ የመውጣቱ ሂደት በተለያዩ ሁኔታዎች ሊደናቀፍ የሚችል ሲሆን፣ በዚህ የተነሳም ከአንድ ሺ አዲስ የተወለዱ ህፃናት መካከል እስከ አርባ

የሚደርሱት የዘር ፍሬያቸው ከውጭ አይታይም፡፡ ሆዳቸው ውስጥ ቀርቷል ማለት ነው፡፡
እናም ሁኔታው ከአፈጣጠር ጋር የተያያዘ እንጂ ከአባላዘር ህመሞች ጋር የተገናኘ አለመሆኑን ለመግለፅ እንፈልጋለን፡፡ አንተም ከግብረ ስጋ ግንኙነት ርቀህ መኖርህ ከዘር ፍሬ አለመኖር ይልቅ የበለጠ ጎጂ ከሆነው ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንደሚጠብቅህ በመረዳት ይህንን አቋምህን ወደፊትም እንድትቀጥልበት ለማስታወስ እንወዳለን፡፡

ወንድ ልጅ የልጆች አባት ይሆን ዘንድ የሚየስችሉት የዘር ፍሬዎቹ እንደሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ከእነዚህ ፍሬዎች መካከል አንዱ እንኳን በተገቢው ቦታ የሚገኝ ከሆነ የመካንነት አደጋው አይኖርም፡፡ ሆኖም በዚህ ሁኔታ ወደ አዋቂነት ዕድሜ ከተዘለቀ ቦታውን ያልያዘው የዘር ፍሬ ለሌሎች አደጋዎች የተጋለጠ ይሆናሉ፡፡ በተለይም በታችኛው የሆድ ክፍል በማይመች ስፍራ በሚቆይበት ወቅት በቀላሉ ለአደጋዎች የተጋለጠ ነው፡፡ በሆድ ውስጥ የሚገኝ የዘር ፍሬ ለካንሰር የተጋለጠ በመሆኑ እና እጢ ቢፈጠርበት እንኳን በቀላሉ ለማወቅ አያስችልም፡፡

ውድ ሳሚ፡- ከደብዳቤህ መንፈስ ለመረዳት እንደቻልነው የኮሌጅ ተማሪ ነህ፡፡ በአሁኑ ዕድሜህ ደግሞ ተገቢ ስፍራውን ያልያዘው የዘር ፍሬህ ጤነኛ ሆኖ የመገኘቱ ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፡፡ ከላይ በጠቀስናቸው ምክንያቶች የተነሳም በቀዶ ጥገና ዘዴ መውጣት ይኖርበታል፡፡

ዕድሜህ ከስምንት ዓመት ከዘለለ በኋላ የዘር ፍሬዎች ሆድ ውስጥ ከቆዩ ስራቸው ይስተጓጎላል፡፡ እጢዎችን የመያዛቸው ዕድልም የሰፋ ነው፡፡ ስለዚህ ኦፕራሲዮን ተደርገው ስምንት ዓመት ከመሙላቱ በፊት መከናወን አለበት ማለት ነው፡፡ ከስምንት ዓመት ዕድሜ በፊት በቆለጥ ውስጥ የተቀመጠዓመት ዕድሜ በፊት በቆለጥ ውስጥ የተቀመጠ እንደሆነ፣ የዘር ፍሬው ጤንነቱ የተጠበቀና ስራውንም የማያቋርጥ ይሆናል፡፡

የአዕምሮ ዘገምተኝነት መንስኤዎች አሉት፡፡ በአጠቃላይ ግን ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች እንዳሉት ታውቋል፡፡ በማህፀን ውስጥ በሚፈጠሩ ችግሮች የተነሳ የሚመጣው የአዕምሮ ዘገምተኝነት አንዱ ሲሆን፣ ከእነዚህ ባልተናነሰ ሁኔታ ደግሞ በወሊድ ወቅት በፅንሱ አንጎል ላይ የሚከሰቱ ህመሞች ደግሞ ሌላኛው ነው፡፡

ነፍሰጡር እናት የወሰደቻቸው መድሃኒቶች፣ ተላላፊ ህመሞች እንዲሁም ‹‹በዝርያ ፍልሰት›› /ክሮሞዞማል አብኖርማሊቲ/ የተነሳ በጽንሱ አንጎል ላይ የሚደርሱ ህመሞች ለብዙዎቹ የአዕምሮ ዘገምተኞች መነሻ ችግሮች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ባልተናነሰ ሁኔታ ደግሞ በወሊድ ወቅት በጽንሱ አንጎል ላይ የሚከሰቱ መታፈን እና አየር ማጣት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

እንደ ማጅራት ገትር ያሉ አንጎልን የሚያጠቁ ተላላፊ ህመሞች በሀገራችን ውስጥ በተለይም ዕድሜያቸው አንድ ዓመት ያልሞላቸው ህፃናትን በስፋት እንደሚያጠቃ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ህመሞች ያልዘገየ እና የተሟላ ህክምና እና ክትትል ካልተደረገላቸው ግን መጠነ ሰፊ ጉዳት የሚያስከትሉ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የአዕምሮ ዝግመት ነው፡፡
እጅግ ከገፋም በኋላ ቢሆን የአዕምሮ ዝግመት እንደ አዲስ ሊከሰት ይችላል፡፡ በተለይም ከፍተኛ የሆነ የጭንቅላት አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ለዚህ ችግር የተጋለጡ ናቸው፡፡

ውድ ሳሚ፡- የአዕምሮ ዝግመት ያለባቸው ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ከአንደኛ ደረጃ የዘለለ ትምህርት አይኖራቸውም፡፡ አንተ ደግሞ ይህን አልፈህ የኮሌጅ ተማሪ ነህ፡፡ ስለዚህ ችግሩ አንተን ሊመለከት አይችልም፡፡ የዘር ፍሬህን ችግር ግን ነገ ዛሬ ሳትል በአቅራቢያህ የሚገኝ ሆስፒታል በመሄድ እንዲስተካከል ማድረግ ትችላለህ፡፡ መልካሙ ሁሉ እንዲገጥምህ እንመኛለን፡፡

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop