October 16, 2014
2 mins read

በኢትዮጵያ ተከታታይ ፍንዳታዎች ይደርሳሉ የሚለው ስጋት አይሏል * ደህነቶች እና የኢምባሲ አታሼዎች በስብሰባ ተወጥረዋል

በኤምባሲዎች የደህንነት አታቼዎች እና በወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት መካከል ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው
በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ ምእራባውያን ዲፕሎማቶች ዘንድ የሚደርሱ እናፈነዳለን መረጃዎች ከፍተኛ የሆነ ስጋት እየፈጠሩ መሆኑን በአዲስ አበባ የሚገኙ እና ለደህንነት አታቼዎች ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሰዎች እንደሚናገሩት መሃል አገርን እና ምስራቅ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪት ክልሎች ይደረጋሉ የተባሉ ፍንዳታዎች ከአልሸባብ የመጡ ማስጠንቀቂያዎች ናቸው ቢባልም በአልሸባብ ውስጥ በተደረገ የመረጃ ማጣራት አልሸባብ ይህንን መረጃ እንዳልበተነ በአዲስ አበባ የአሜሪካን የደህንነት አታቼ ለማረጋገጥ ያደረጉት ሙከራ በከፊል ባይሳካም የሁኔታውን አሳሳቢነት አስመልክቶ በምእራባውያን የኤምባሲ ዲፕሎማቶች የደህንነት አታቼዎች እና በወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል።

ከወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር ይደርሳሉ የሚባሉ ፍንዳታዎች ምዕራባውያን ላይ ያነታጠሩ በመሆኑ የሰጉት የሃያላኑ ዲፕሎማቶች ሁኔታው ከመከሰቱ በፊት ለመቆጣጠር ሲሉ አስፈላጊውን የዲፕሎማቲክ ሩጫ እያደረጉ መሆኑ ሲታወቅ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ከሆነ ምርጫ እየደረሰ ስለሆነ ተቃዋሚዎችንና ያልያዛቸውን ጠንካራ ሰዎች ለማፈስ ወያኔ የሚጠቀምበት ስልት ነው። ህዝቡን እያስፈራራ የውጭ አገር መንግስታትንም እንዲሁ አሸባሪ ለመዋጋት እያለ እራሱ የቀበራቸውን ፈንጂዎች ያስጮህብናል። የፈለገውንም ይገድላል። ስለዚህ ህዝቡ ነቅቶ መጠበቅ የግድ ይለዋል።

3 Comments

  1. ደደብ ሁሉ ነገር ለናንተ የፖለቲካ ቁማር ነው አዬ ተቃዋሚ …………..?ህውሃት በከፍተና ሁነታ ጥንክሩዋል!

  2. በበኩሌ መልሱ የመጨረሻው 3 መስመር ላይ የሠፈረው ሃሳብ ነው::
    “….አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ከሆነ ምርጫ እየደረሰ ስለሆነ ተቃዋሚዎችንና ያልያዛቸውን ጠንካራ ሰዎች ለማፈስ ወያኔ የሚጠቀምበት ስልት ነው። ህዝቡን እያስፈራራ የውጭ አገር መንግስታትንም እንዲሁ አሸባሪ ለመዋጋት እያለ እራሱ የቀበራቸውን ፈንጂዎች ያስጮህብናል። የፈለገውንም ይገድላል። ስለዚህ ህዝቡ ነቅቶ መጠበቅ የግድ ይለዋል።”

Comments are closed.

Mhbere Kidusan
Previous Story

ማኅበረ ቅዱሳን የመንግሥት ተቃዋሚ ሆኖ አያውቅም!!! – 10ሩ የኔ ወሳኝ ነጥቦች ስለማህበሩ

ask your doctor
Next Story

Health: ሐኪሞች እንዴት በዘር ፍሬዬ አለመኖር ይደናገጣሉ? ችግሬ ከአዕምሮ ዝግመት ጋር ይያያዝ ይሆን?

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop