ድምጻዊት አበበች ደራራ አረፈች

/


አርቲስት ደበበ እሸቱ በፌስ ቡክ ገጹ እንደዘገበው፦
ለረጂም ዓመታት በራስ ቴአትር በድምጻዊነት ስትሰራና ለአድማጮችዋ ዜማዎችን ስታቀርብ ኖራ በስተመጨረሻው ወደ እስራኤል ሀገር ከትማ ስትኖረ የነበረችው ታዋቂዋ ድምጸ መልካሟ አበበች ደራራ ዛሬ ሜይ 16 ቀን ባደረባት ህመም ሳቢያ ሕይወቷ አልፏል፡፡
አበበች ደራራ በሕመም ተይዛ ለበርካታ ወቅት በአልጋ ላይ ከመቆየቷም ባሻገር ጨርሶ ከሰዎች ጋር ግንኙነት አቋርጣ በሽታዋን ለብቻዋ ስታስታምም እንደነበረች በቅርብ የሚያውቋት ይናገራሉ፡፡
የአበበች ደራራ አስከሬን በኖረችበት የቴል አቪቭ ከተማ በዛሬው እለት ከቀኑ 3.00PM ላይ ወደ ቀብር በወዳጅ ዘመዶች ታጅቦ በመሄድ ሥርአተ ቀብርዋም ይፈጸማል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: ለኢትዮጵያ ይሰልላል የተባለ ሱማሊያዊን አልሸባብ ገደለ፤ * በአሶሳ የተገደሉ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን አስከሬን መቀሌ ገባ

5 Comments

    • Yagerachinin ena yehzb lijoch yehonu birqyewochin enkuan mastamem bewegu meqber alemechalachin yangebegibal

  1. አበበችን የምታክል ብርቅዬና አንጋፋ የጥበብ ሰው በሀገሯ መድረሻ አጥታ በስደት ኖራ በስደት መሞቷ ሳያንስ ሬሳዋ እንኳን በሀገሯ ማረፍ አለመቻሉ እነዴት ያሳዝነናል? በቃ ይች ሀገር እንደመለስ ላሉ ባንዳዎች ካልሆነ በቀር ቦታ የላትም ማለት ነው።

Comments are closed.

Share