July 12, 2014
7 mins read

Health: ቃር እያሰቃየኝ ነው፣ መፍትሄውን ንገሩኝ

እንዴት ናችሁ? እኔ ከሰሞኑ ከሚያሰቃየኝ ቃር ውጪ ደህና ነኝ፡፡ ይህ ነው የሚባል የጨጓራ ችግር እስካሁን የለብኝም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከምበላው ነገር ይሆን ወይ? ብዬ ምግቦችን እየለዋወጥኩ መመገብ ጀምሬ ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ ልቤን መፋቁ እና ቃር ሊተወኝ አልቻለም፡፡ እስቲ ስለቃር ምንነት እና መከላከያ ከዚያም ህክምና አማራጭ ካለ በዝርዝር አስረዱኝ፡፡

ሰላም ውድ የአምዳችን ተከታታይ፤

ብዙዎቻችን ጋር አልፎ አልፎ መጠነኛ የልብ መቃጠል እና ምቾት ማጣት ሊከሰት መቻሉ የጤንነት እጦት አይደለም፡፡ ይሁንና እኛ በተመልዶ ‹ቃር› የምንለው ችግር በሳምንት ከሁለት ጊዜ በላይ ሲከሰት እና በቀላል መድሃኒቶች ማስታገስ ሳይቻል ሲቀር እንደ አሳሳቢ የጤና ችግር ይወሰዳል፡፡ በህክምናው ይህ የቃር እና የልብ ማቃጠል ‹ጋስትሮኢሶፋጂያል ሪፍለክስ ዲዚዝ› ተብሎ ይጠራል፡፡ ቃር የሚለው ቃል ሁኔታውን በሙሉ ባይገልፀውም ለመግባባት እንዲቀለን ቃር በሚለው መግለጫ እንቀጥላለን፡፡
ቃር በደረት አካባቢ የሚፈጠር እና የሚያቃጥል ስሜት ሲሆን ወደ አፍ ውስጥና ጉሮሮ አካባቢም ወደላይ ወጥቶ የሚሰማ ህመም ነው፡፡ ችግሩ በደረት ህመም፣ ለመዋጥ በመቸገር፣ ደረቅ ሳል፣ የጉሮሮ መጎርነን እና አንዳንድ ጊዜ የምግብ መጓጎጥ ስሜትን እና ምልክቶች በማሳየት ይገለፃል፡፡

ቃር የሚከሰተው በሆድ መቅረት ያለበት የምግብ መፍጫ አሲድ ወይም ቅባት ነክ ምግቦችን የሚፈጨው ሀሞት ከአንጀት ተነስቶ ሽቅብ ወደ ጉሮሮ ሲመጣ እና ማቃጠልን ሲፈጥር ነው፡፡ በተፈጥሮ ምግብ ስንውጥ የታችኛው የጉሮሮ መጨረሻ ላይ ያሉ ጡንቻዎች ፈታ ይሉና ምግብና ፈሳሽ ወደ ሆድ እንዲወርዱ መንገድ ይከፈታል፡፡ ምግብና ውሃው ወደ ሆድ ከገቡ በኋላ ጡንቻዎቹ ይዘጋሉ፡፡ ይሁንና ይህ የጡንቻዎቹ መክፈቻና መዝጊያ ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ሲዳከም የሆድ ውስጥ አሲዶች ሆድን አልፈው ወደ ጉሮሮ ሽቅብ መምጣት ይጀምራሉ፡፡ የደረት እና ጉሮሮ አካባቢን ማቃጠል (ቃር) የሚፈጥሩትም እነዚሁ አሲዶች ናቸው፡፡

ማንም ሰው ቃር የሚታመም ቢሆንም በተለይ ወፍራም ሰዎች፣ ሲጋራ አጫሾች፣ ኸርኒያ ያለባቸው እና አስም ታማሚዎች የበለጠ ለቃር ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ቃር ለጊዜው ጉዳት የለሽ ጊዜያዊ እክል ቢመስልም ለረጅም ጊዜ መፍትሄ ሳይሰጠው ከቆየ ከበድ ያሉ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከእነዚህም መካከል የጉሮሮ መጥበብ፣ የጉሮሮ ቁስለት መሰል መብላትና መጠጣትን የሚከለክሉ ችግሮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ቃርን ለማስታገስ እና ጊዜያዊ የሆነ ፀረ አሲድ መድኃኒቶችን ከፋርማሲ በመግዛት መጠቀም ቢቻልም በቃሩ ምክንያት ቁስለት የተፈጠረበት ጉሮሮ ከሆነ መፍትሄ አይሆንም፡፡ አንቲ አሲድ መድኃኒቶችንም አለአግባብ ደጋግሞ መጠቀም የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉት የባለሙያ ምክር የሚታከልበት እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ ሌሎች ጠንከር ያሉ መድኃኒቶችን በባለሙያ ካልታዘዙ በቀር መሞከርም ተገቢ አይደለም፡፡

ውድ ጠያቂያችን ቃሩ የቅርብ ጊዜ ችግርህ ስለሆነ ከበድ ያሉ ህክምናዎች የሚጠይቅህ አይመስለንም፡፡ መጀመሪያ ከምግብ መጠጥ እና አጠቃላይ አኗኗር ዘዬህ ጋር የተያያዙ ለውጦችን በማድረግ ችግሩን ለማሻሻል ብትሞክር ጥሩ ነው፡፡ በእነዚህ ለውጦች መካከል ክብደትህ በጤናማ ክልል ውስጥ እንደሆነ ማድረግ አንዱ ነው፡፡ ክብደት ሲበዛ ሆድን በመግፋት የሆድ አሲዶች ሽቅብ እንዲወጡ ያደርጋል፡፡ ወገብ አካባቢ የሚያጣብቁ ልብሶችን ማስወገድ፣ የማቃጠል ተፈጥሮ ያላቸውን እንደ የተጠበሱ ምግቦች፣ አልኮል መጠጥ እና ሽንኩርትን እንዲሁ መቀነስ ጠቃሚና ቃርን ማስወገጃ መንገዶች ናቸው፡፡ አንተ ራስህ ደግሞ ስትበላ ምቾት የሚነሱና የሚያቃጥሉህን ምግብና መጠጦች በደንብ ተከታትለህ ለያቸው እና በተቻለ መጠን አርቃቸው፡፡ ከመተኛትህ በፊት ቢያንስ ከሁለት ሰዓት በፊት መመገብ ሌሊት ላይ ቃር እንዳያስቸግር ያደርጋል፡፡ ስትተኛ ትራስህን ከፍ ማድረጉም በግራቪቲ እሳቤ አሲዱ እዚያው እታች እንዲቀር ይረዳል፡፡ ሲጋራ ማጨስና አልኮል መጠጥ አዘውታሪ ከሆንክ ከዚህም ብትርቅ መልካም ይመስለናል፡፡ የሚያጨናንቁ እና ውጥረት ውስጥ የሚከቱት ሁኔታዎችም አባባሽ የቃር ምክንያቶች የሚሆኑባቸው አጋጣሚዎችም ጥቂት አይደሉምና ይህንን አስብበት፡፡ የነገርንህ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ሞክራቸው፡፡ በአጭር ጊዜ መፍትሄ ካላገኘህ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ጋር ቀርበህ ምርመራና ህክምና ማድረግን እንመክራለን፤ ጤና ሁን!

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop