July 12, 2014
58 mins read

‹የፈራሁት ነገር መጣ ድሆ ድሆ› (ብስራት ደረሰ)

ብስራት ደረሰ (ከአዲስ አበባ)

 

የፈሩት መድረሱ፣ የጠሉት መውረሱ ያለና የነበረም ነው፡፡ አንድን ነገር በሩቅ እያለ መዐዛው ሲያውድህ ወይም ቅርናትና ግማቱ ሲያጥወለውልህ በምናባዊ የስሜት ህዋስህ እየተሰማህ ስሜቱ ገና ላልተሰማቸው ልታስታውስና የማንቂያ ደወል ልታሰማ ትችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንዳለመታደል ይሆንና ሰሚ ታጣለህ ወይም ከጉዳይ የሚጥፍህ አይኖርና እንዲሁ ደክመህ ትቀራለህ፡፡ የመጨረሻው መጨረሻ ሲመጣና በምናብህ የታየህ ነገር የሁሉንም ቤት መቆርቆር ሲጀምር ግን ቀዳሚው ዕይታህ እውነትና የማይቀርም መሆኑን አንተ ራስህም እንደሌላው እየተደመምክ ጊዜ ባለውሉን ታደንቃለህ፡፡ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታፈንና ለትግሬው ነፃ አውጪ ወያኔ በቅጽበት ተላልፎ መሰጠት ሳቢያ ሰሞኑን እያስተዋልነው ያለነው ሀገራዊ ክስተት ይህን ነው የሚመስለው፡፡

በባህላዊ ዘፈኖቻችን በአንደኛው ውስጥ የመጀመሪያውን ስንኝ ለጊዜው ዘነጋሁት እንጂ በርዕሴ ላይ የጠቀስኩትን የመሰለ ተከታይ ስንኝ አለ፡፡ የሚፈራ ነገር ጊዜ ይፍጅ እንጂ መድረሱ የማይቀር መሆኑን ይጠቁማል፡፡ እኔም የፈራሁት፣ ብዙዎች ሩቅ ተመልካች ኢትዮጵያውያንም የፈሩት፣ ቀደም ካለ ዘመን ጀምሮ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን የትንቢት መዛግብት ውስጥም የተቀመጠውና በእጅጉ የተፈራው ነገር በቅርብ ሊፈጸም እንደሆነ ከዳር ዳርታው እየተረዳን በመሆናችን የፈራነው ነገር ድሆ ድሆ ስለመምጣቱ ቅንጣት መጠራጠር አይገባም፡፡ ለምንድንስ ነው የምንጠራጠረው? እንኳንስ ዘረኛው የትግሬ መንግሥት ከሆዳምነታቸውና ከጨካኝነታቸው በስተቀር በአንጻራዊ ሁኔታ ለሀገራቸው አንድነትና ለሕዝባቸው ደኅንነት ይተጉ የነበሩ የቀ.ኃ. ሥላሴንና የአፄ መንግሥቱ ኃ/ማርያምን የመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን መንግሥታትስ ጊዜያቸውን ጠብቀው ወደታሪክ መዝገብነት ተለውጠው የለም እንዴ? ታዲያ የወያኔን ወረደ መቃብር መዳረስ ለምን እጠራጠራለሁ? የወያኔ የባሕርይ አባቶች ናዚው ሂትለር፣ ፋሽስቱ ሙሶሊኒ፣ አምባገነኖቹ መንግሥቱና ሞቡቱ፣ ኢድ አሚንና ጋዳፊ ወዘተ. ተራቸውን እየጠበቁ ወደማይቀረው ሞት ተጉዘዋል፡፡ የመለስ ዜናዊ ወያኔም የማይቀርለትን ዕዳ ሊወጣ ቁልቁለቱን በከፍተኛ ፍጥነት እየተንደረደረ ነው፡፡ ውሃ ውስጥ ገብቶ እየሰመጠ የሚገኝ ሟች ደግሞ የሚያድነው እየመሰለው ፊላና ሣር እንዲሁም የሚንሳፈፍ የወፍ ላባ ሳይቀር ይጨብጣል፡፡ ሞቱ ታሪካዊና የማይቀር የሆነው ወያኔ ደግሞ የሚድን እየመሰለው ይጨብጠውንና ይለቀውን አጥቶ በሚያሳዝን የኅልውና ሁኔታ ውስጥ ይገኛል – ጣረሞታዊ ኅልውናውን ኅልውና ካልነው፡፡

እርግጥ ነው – ወያኔ በመሞት ላይ ነው ስል የነጋበት ጅብ ብዙ ምናልባትም ሊጠገን የማይችል እጅግ ብዙ ጉዳት ማድረሱ እውነት እንደመሆኑ ወያኔም በዚህ የአመሻሽ ሰዓቱ – በዚህ የጣዕረ ሞት ቅጽበቱ ለግምት የሚከብድ ጠባሳ እንደሚያስከትል በተግባር እያየነው ነው፡፡ ስለዚህም ትግልን በተቻለ መጠን በጥንቃቄ ማድረጉ ብዙ ኪሣራ ውስጥ ላለመግባት ጠቃሚ ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ይህን ስልም የወያኔ ሞት ይቀራል ማለት እንዳልሆነ ላሰምርበት እፈልጋለሁ፡፡ የወያኔ ሞት ወያኔ ስለጠላው ወይም እኛ ስለወደድነው የሚቀር ወይም የሚመጣ አይደለም፤ ታሪካዊ ሞት ስለሆነ ማንም ሊያግደው የሚችለው አይደለም፡፡ የወያኔ ሞት በተቃዋሚዎች መጠንከር ወይም መልፈስፈስ የሚወሰን አይደለም፤ ሁሉም የራሱ ጊዜ አለውና ወያኔ ከየትም አቅጣጫ በሚነሣ ወጀብና ሕዝባዊ ዐውሎ ንፋስ ይገረሰሳል፡፡ ዕዙ ከፈጣሪ በመሆኑ፣ መነሻው የሕዝብ ዕንባና ደም በመሆኑ የወያኔ ኅልፈት በማንም ምድራዊ ኃይል አይስተጓጎልም፡፡ ማዘግየትና ማፋጠን ግን ይቻል ይሆናል፡፡ ስለሆነም የትግል ሥልትን አዋጭ በሆነ መንገድ መቀየሱ ጉዳዩ ይበልጥ ከሚመለከታቸውና የእምዬ ኢትዮጵያን ነፃነት ለማዋለድ ታሪክ ከመረጣቸው ዜጎች ብዙ ይጠበቃል፡፡ እርግጥ ነው – የኢትዮጵያን ነፃነት እውን ለማድረግ በትንሹ ኢትዮጵያዊነት እንጂ የድርጅት አባልነት የግድ እንዳልሆነም መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ሀገር የጋራ ናት፤ ፓርቲና ቡድን ግን የግል ናቸው – ሃይማኖትም፡፡ በመሆኑም ሁሉም የቻለውን ያድርግ፡፡ (የጠምባሮ ብሄረሰብ ብሂል ናት – አንድ ሰው የሞላ ወንዝ ዳር ቆሞ ወንዙ እስኪጎድልለት ድረስ ይጠብቃል – ሊሻገር፡፡ በዚህ መሀል ግንዱንና ደንጋዩን እያንከባለለ ከሚወርደው ጎርፍ ላይ ያ ሰውዬ ጠላቱን ያያል፡፡ በደስታ በመሞላትም አክ ይልና ምራቁን አጠረቃቅሞ እጎርፉ ላይ እንትፍ ይላል፡፡ የርሱ ምራቅ በጎርፉ ላይ ተጨምሮ ጠላቱን “ጠራርጎ” እስከመጨረሻው የወንዙ መዳረሻ እንዲወስድለት መሆኑ ነው፡፡ ልክ ነው! እኛም የዚህን ሰው አርአያ መከተል ይኖርብናል፡፡ የዋህነታችንና ፍርሀታችን በቃል ለማይገለጽ ውርደት ዳርጎናልና፡፡)

በዚህን ወቅት የሥልጣን ሱስ ሰለባውን፣ የፍቅረ ንዋይ ምርኮኛውን፣ ሰው መሣይ ድንጋይ ራሱን፣ አደናጋሪውን፣ አዘጥዛጩን፣ አሽቃባጩን፣ አስመሳዩን፣ አድር ባዩን፣ ከርሳሙን፣ ቂጥኛሙን፣ ውርዴውን፣ ነቀርሣውን፣ … መጠንቀቅ ይገባል፡፡ በዚህ በተዘበራረቀ ማኅበረሰብ ውስጥ ማንን ከማን ለይቶ ማመንና አለማመን ስለሚከብድ ብዙ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ በተረፈ የወያኔ ሞት ከላይ እንጂ ከታች ብቻ ስላልሆነ እውን መሆኑ የግድ ነው፡፡ በሥነ ቃሉም “እንዲህ ጨሶ ጨሶ የነደደ እንደሆን፤ ያመዱ ማፍሰሻ ሥርፋው ወዴት ይሆን፡፡” መባሉ ለዜህ ነው፡፡

ማን ያውቃል፡፡ የአንዳርጋቸው በዚህ ባልተጠበቀ ሁኔታ ውስጥ መገኘት ለበጎ ቢሆንስ? የርሱን መሰዋት ግዴላችሁም ብዙም አንጥላው፡፡ ስንዴ ካልሞተች ለሌሎች ስንዴዎች ትንሣኤ መነሾ አትሆንምና – ድል ያለ መስዋዕት እንደማይጣፍጥም ይነገራልና የአንዳርጋቸው በወያኔ ወጥመድ ውስጥ መግባት ፈጣሪ ወዶና ፈቅዶ ያደረገው ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው “አታሞ በሰው እጅ ታምር ሲይዟት ታደናግር” እንዲሉ ነውና ይህ ክስተት በኔና ባንተ ቢሆን ሊከብደን ይችላል፡፡ ይሁንና አንዳርጋቸው በነዚህ ጭራቆች እጅ መግባቱ ለበጎ ነው የምልባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ይሄውና ለዓመታት ሲጎሻመጡና ዐይንህ ላፈር ሲባባሉ የነበሩ አንዳንድ ተቃዋሚዎች – በቡድንና በድርጅትም በግለሰብም ደረጃ – የአንድነት መንፈስ ያሳዩት በዚህ ሰሞን ነው፡፡ ወያኔዎች ለአገዛዝ እንዲያመቻቸው ባዘጋጁት የክፍፍል አባዜ ሳይዘናጋ ወይም በቋሚነትም ይሁን በጊዜያዊነት ወደጎን በመተውና ግንቦትና ሚያዚያ ሳይባባል ምድረ አበሻ ከጫፍ እስከ ጫፍ የተነቃነቀው በዚህ ሰሞን ነው – የሚያስቀና ነውና ያዝልቅልን፡፡ “የትም ብኖር ለካንስ ወያኔ ከፈለገ አንገቴን ጨምድዶ እንደፈለገው ሊያደርገኝ ይችላል” ከሚል ስሜት በመነሳት ይመስላል አበሻ ሁላ መከፋፈሏን እየናቀች ወደጋራ መድረክ የመጣችው በዚሁ ሰሞን ነው – እንዳንዳንዶቻችን ግምት ለጊዜያዊ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሊሆን ይችላል ብለን ብንጠራጠርም፡፡ ሌላም ሌላም፡፡ እንደዚህ ሰሞኑ ትብብርና መተሳሰብ ቢሆን ኖሮ ወያኔዎች ወደደደቢታቸው ከተመለሱና ከናካቴውም ከከሰሙ በትንሹ 30 ዓመታትን ባስቆጠሩ ነበር – ግና የኛ ኃጢኣትስ በምን ሥርየትን ያግኝ? እንዴትስ ይከፈል? ሁሉም ነገር ለበጎ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ታዲያን የአንዳርጋቸው ጭዳነት ለመልካም ፍጻሜ ቢሆንስ? ፈጣሪ ሌላ መንገድ ከመፈለግ ይልቅ ይህኛውን የወዲያው መንስኤ (immediate cause) ፈቅዶትስ ቢሆን? አላውቅም፤ ግን እንዲህ ያለ ነገር ይሰማኛል – ስሜት የድርጊትን ያህል ከባድ ባይሆንም፡፡ በታሪክ ትምህርት ለአንድ ኹነት መነሾ ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች እንዳሉ ይነገራል – fundamental and immediate causes ይሏቸዋል – መሠረታዊና የወዲያው መንስኤዎች ልበላቸው፡፡ የአንደኛውን ይሁን የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ያስነሳችው በሰው ማሣ የገባች አንዲት ቀበጥ ዓሣማ እንደሆነች ሲነገር ሰምቻለሁ፡፡ ለአንድ የቦካ ቂም እውናዊ ትንሣኤ አንዲት ቀጭን ሰበብ ታስፈልጋለች ማለት ነው፤ የአንዳርጋቸው ግን ከቀጭንም በላይ እርፍ እሚያህል ነውና በቃላት ብቻ የሚያልፍ እርግማንና ቁጣ ሰቆቃን ከማባባስ ውጪ የሚፈይደው ነገር እንደሌለ መረዳት ይኖርብናል፡፡

አንዳርጋቸው በአረመኔዎቹ እጅ ከገባ በኋላ በደከመ አንደበት “blessing in disguise” ሲል ሰምቻለሁ፡፡ በወያኔዎቹ ትርጓሜ እንዲህ ማለቱ “መያዜ ዕረፍት ሰጥቶኛልና ከእንግዲህ እኔ እንዳረፍኩና ሰላም እንዳገኘሁ እናንተም አርፋችሁ በመቀመጥ ሰላማችሁን አረጋግጡ” ለማለት እንደፈለገ እንዲገባን የፈለጉ ይመስለኛል፡፡ እውነተኛውን ትርጓሜ ጊዜ ይነግረናል፡፡ አንዳርጋቸው ግን የቆርጦ ቀጥሎቹን ወያኔዎች ምኞት የሚያስተናግድ ንግግር እንደማያደርግ ከግምት የሚልቅ እምነት አለኝ፡፡ ለነገሩ እንደዚያም ቢሆን አይገርመኝም፡፡ ወያኔዎችን ለሚረዳ ሰው፣ አንድን ሰብኣዊ ፍጡር ከሰይጣንም በላይ ሰይጣን በመሆን እንዴት እንደሚያሰቃዩና በዘመናዊ መንገድ ሂፕኖታይዝ በማድረግም ጭምር ከአንድ አእምሮ ምን ዓይነት ግብኣት ጨምረው ምን ዓይነት መረጃ ሊያወጡ እንደሚችሉ እረዳለሁ፡፡ ዘመኑ በስይጣኔ (በስልጣኔ አላልኩም) እጅግ የተራቀቀ ነው፡፡ በአርትዖት (ኤዲቲንግ) መቁረጥ መቀጠሉ እንዳለ ሆኖ እንደፈረንጆቹ ከሆነ በአእምሮን መቆጣጠሪያ ዘዴ (ማይንድ ኮንትሮል ሲስተም) የአንድን ሰው አእምሮ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የፈለጉትን መረጃ ከትተው ሲያበቁ ሰውዬው ያንኑ እንዲናገር የማድረግ ሰይጣናዊ ችሎታ አላቸው፡፡ ደርግም በጊዜውና ቤት ባፈራለት የማሰቃያ መንገዶች  “አልጋችን ሥር ታንክ ደብቀናል” የሚያስብል ወፌላላና የዘይት ጥብሳት እንደነበረው እናስታውሳለን – አለመታደላችን ግን ምን ያህል የበረታ ነው! ወያኔማ ከዚያ የሚብስ እንዴት አይኖረው! ለማንኛውም በበኩሌ የአንዳርጋቸውን ፈረንጃዊ ፈሊጥ ለኔ በሚስማማኝ መልኩ በመጋራት ይህ ሁኔታ ለኢትዮጵያ “mixed blessing” ነው እላለሁ፡፡ ከእንግዲህ መጨነቅ ለኛው ነው፡፡ አንዳርጌ ግዳጁን ተወጥቷል፡፡ ስለሱ ማላዘንም ይብቃ፡፡ በአንዳርጋቸው እጅ መዛል ምክንያት ከእጁ ያመለጠችዋን ባንዲራ ተረክቦ መታገል ይገባናል፡፡ ልቅሶና ዋይታ ሆድ ከማስባስና ወደኋላ ከመጎተት በስተቀር ማንንም አይጠቅምም፡፡ ሀበሻነትን ለጊዜው ገታ አድርገን ፈረንጅ እንሁንና ጥርሳችንን ነክሰን አቀበቱን እጅ ለእጅ ተያይዘን በኅብረት እንውጣ፡፡ ባይሆን ሁሉም የዚህ ቲያትር ተካፋይ የየራሱን ሒሳብ የሚያወራርድበትን ቀመር አዘጋጅቶ ማስቀመጥ ነው፡፡ የመንም፣ ወያኔም፣ … በዚህ ቆሻሻ ተግባር የተሳተፈ ሁሉም ፍጡር ዋጋውን እንደሚያገኝ በበኩሌ ጥርጥር የለኝም፡፡ የኢትዮጵያውያን ጊዜ ሲመጣ የ”ለለአሃዱ በበምግባሩ” ፍትህ ይበየናል፡፡

ወያኔዎች ጨካኞች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ በአንዳርጋቸው ላይ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉም በጣም ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ማስታወስ የሚገባን ነገሮች አሉ፡፡ የትግራይ ወንበዴዎች ትግሉን ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ያኮላሹ መስሏቸው አንዳርጋቸውን ሊገድሉት ይችላሉ – ምድር ላይ ገና ባልተሞከሩ የማሰቃያ ሥልቶች ማሰቃየታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡ አሰቃዩትም ገደሉትም ከእንግዲህ ዕዳው የነሱና የኛ እንጂ የአንዳርጋቸው አይደለም፡፡ አንዳርጋቸው ከዕዳው ነፃ ነው የምለው ሥራውን ጨርሷል በመባሉ አይደለም፡፡ በእጅህ የገባን ብርጭቆ ስትፈልግ መስበር፣ ሳትፈልግ ማስቀመጥ ያለብህ አንተ ስለሆንክ አንዳርጋቸውን እንደፈለጉ የማድረግ ዲያብሎሳዊ መብትና ሥልጣን ያላቸው ወያኔዎች ብቻ ናቸው፡፡ ለምን አስያዙት ብሎ መቆጣትም ሞኝነት ነው፡፡ እንዲያውም ቂልነት፡፡ አንዳርጋቸው ዓለምን የሚዞረው ለወያኔዎች ዕቅፍ አበባ ለማበርከት አለመሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ከዚህ አኳያ ለምን ያዙት ብሎ መናደድ ጉንጭ አልፋና ለትዝብትም የሚዳርግ ነው፡፡ የሚያናድደው የተያዘበት አኳኋን ነው፡፡ ያመኑት ፈረስ በደንደስ መጣሉ ነው እጅግ የሚያበግነው፤ ዓለም አቀፍ ህግ መጣሱ ነው የሚያንጨረጭረው፤ ሊያስቀሩት ይቻል በነበረ የአደጋ ሥጋት አጉል መስዋዕትነት መክፈሉ ነው የእግር እሳት፡፡ በጦርነት ቢሆን እሰዬው ነው – የአሁኑን ያህል ቁጭትና ንዴት የለበትም፡፡ ለዚያ ሰሞኑን ለደረሰው ጥፋት ደግሞ የአንድ ወገን ብቻ ሣይሆን የብዙ ወገኖች ጥፋት ይመስለኛል – ትምህርቱ ቆንጣጭና አስቆጪ መሆኑ ከፋ እንጂ ይህ ክስተት መማሪያ ነው፡፡ ደግሞም ከፍ ሲል ለመጠቆም እንደሞከርኩት የፈሰሰ አይታፈስምና ስህተትን በመከፋፈልና በመጸጸት ጊዜን ማባከን ተገቢ አይደለም፡፡ የሆነው ሆኖኣል – የሆነውም ሊሆን ግድ ስለሆነ መሆኑን ማመን ይገባል፡፡ የማይሆን ቢሆን ኖሮ ቀድሞውንም አይሆንም ነበርና፡፡ እናም ጉዞ ወደፊት እንጂ ወደኋላ የለምና ይልቁንስ የተሰዋው ወንድማችን አስተዋፅዖ ከግቡ እንዲደርስ እንጣር፡፡ ተሰዋ ስልም በርግጥም እስካሁኒቷ ሰዓት ተሰውቷል ለማለት ሳይሆን የወያኔ እጅ የገባ ሰው የድመት ምርኮኛ የሆነ ያህል ስለሚሰማኝ ነው፤ እንጂ ከንፍሮ ጥሬ ይወጣልና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አንዳርጋቸውም የነገን ጣይ ሊያይ የሚችልበት ጠባብ ዕድል ሊኖር ይችል ይሆናል – ወያኔዎች ማሰብ ከጀመሩ፣ አሁን ዘግይተውም ቢሆን በመጨረሻ ሰዓታቸው ወያኔዎች ሰው መሆን ከጀመሩ ይህም ቀላል ነው፡፡ ተያይዞ ከመጥፋት ቢያንስ ለትውልዳቸው ሊያስቡ ከፈለጉ እያንዣበበ የሚገኘውን የጥፋት ደመና ከወዲሁ ሊያስቀሩት ይችላሉ፡፡ እኔ ግን አይመስለኝም፡፡

ወያኔዎች ወደፊትን መመልከት የማይችሉ ደናቁርት መሆናቸው ከአንዳርጋቸው ሕይወት አንጻር ያሳዝነኛል፡፡ የሚያሳዝነኝ አንዳርጋቸው ሳይሆን የወያኔዎች ድንቁርና ነው፡፡ የሁልጊዜ ትምክህታዊ መርሆኣቸው “ማን ምን ያደርገናል? ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ…” የሚለው አፄያዊና ደርጋዊ ትዕቢታቸው ነው፡፡ አሁንና ከአሁን በኋላ ግን ይህ ትምክህት አይሠራም፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ ለመፍራት ጊዜ አለው – ለመጀገን ጊዜ አለው፤ ተስፋ ለመሰነቅ ጊዜ አለው – ተስፋ ለመቁረጥ ጊዜ አለው፤ ለመለያየት ጊዜ አለው – ለመተባበር ጊዜ አለው፤ ለመጣላት ጊዜ አለው – ለመታረቅ ጊዜ አለው፡፡ ይህን ነባራዊ ዘመን የማይሽረው እውነት ቅዱሳት መጻሕፍትም ቀድመው አስቀምጠውታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ለወትሮው በፈሪነትና በልዩነቶች ተከፋፍሎ በመራኮት ዘመን አመጣሽ ወያኔ ወለድ ጠባዩ ወያኔዎች ይፈርጁት የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ቀደመው አንድነቱ እየመጣና ቁጭቱን ለመወጣት መንገድ አመላካች ሙሤ እየፈለገ ነው፡፡ ስለዚህ አንዳርጋቸውን መግደል ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን እነሱ ባይገባቸው የምናውቅ ወገኖች ጠንቅቀን እናውቃለን – ይህን ስል እንዳይገድሉት በውስጠ ወይራ ለመለማመጥ አይደለም – ወያኔዎች ልምምጥና ልመና እንደማይገባቸው አውቃለሁ፤ ወያኔዎች ያሸነፉትን በመግደል የሚረኩ ጅሎች እንጂ አንድም የጀግንነትና የመሐሪነት መንፈስ እንደሌላቸውም አውቃለሁ፡፡ ጅብ ለማንም እንደማይራራ ወያኔም ከጅብ በበለጠ የራሱን ተጋዳዮች ሳይቀር እየቀረጠፈ ነው እዚህ የደረሰው፡፡ ጅብ እንኳን ጓደኞቹ ሲቆስሉና ሲሞቱ ነው አሉ እሚበላቸው፡፡ ወያሜዎች ግን አንድን ሰው ለመብላት በተቃዋሚነት መጠርጠርና በጠላትነት መፈረጅ ብቻ በቂያቸው ነው፡፡

ሴትዮዋ “መንግጌ አባስኩሽ” እንዳለችው ነው፡፡ የወያኔዎች የኅልውና ማስጠበቂያ ሥልቶች በሙሉ ታኝከው አልቀዋል – ባለፉት ሠላሳ ምናምን ዓመታት ዕድሜያቸው የመግዥያ ሥልቶቻቸውን አንድ በአንድ አኝከው በልተው ጨርሰዋቸዋል፡፡ መግደልም፣ ማሰርም፣ ማሰቃየትም፣… ሁሉም ፋሽኑ አለቀ፡፡ የሞተን ሰው የማትገድልበት፣ የሞተን ሰው የማታስርበት፣ የሞተን ሰው የማታሰቃይበት ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል ማወቅ ይኖርብሃል – እንደዚያ ያለ ሰው ከሆንክ፡፡ እርግጥ ነው – ወያኔዎች የሚያሰማሯቸው የሕወሓት ወጠምሻ ድንጋይ ራሶች ሆዳቸው እስከሞላ ድረስ አንጎል የሚባል ነገር ስለሌላቸው ከመግደልና ከማሰቃየት ወደኋላ አይሉም – በዚያ ላይ እንዲያደፋፍሯቸው የሚጠቀሙባቸው አንዳንድ ንጥረ ነገሮች ሳይኖሩ እንደማይቀሩ እገምታለሁ – ለምሳሌ ሀሺሺንና ጫትን መጠጥንም የመሳሰሉ፡፡ ደግሞም ብዙ ትግሬ ካድሬዎች – ስታዘባቸው – ቂላቂል ናቸው፡፡ ለድርጅታቸው ያላቸው ታማኝነት የማምለክ ያህል ነው – ከዚያም በላይ፡፡ በየመጠጥ ቤቱ በጣራ መለስ ጩኸት ሲያውካኩ ስትሰማ – በዚያም ጩኸት ኢትዮጵያዊነትን የሚያራምዱ ወገኖችን እንዴት ሲሳደቡና ሲወርፉ ስታዳምጥ በርግጥም እነዚህ ሰዎች ወያኔ እስከወዲያኛው በሥልጣን ፀንቶ እንደሚኖር የሚያምኑና አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ያለማቅማማት እንደሚያደርጉ ትገነዘባለህ – ተገንዝበህ ብቻ አታበቃም – ካዘንክባቸው በኋላ ታዝንላቸዋለህም፡፡ “አንድ ሰው ምን ያህል አእምሮው ከሥራ ውጪ ቢሆን ነው በሰው ስቃይ የሚደሰተው?” ብለህ ራስህን ስትጠይቅ የዓለም ወቅታዊ ቅርጽ ከሦርያ እስከ ሶማሊያ ፊትህ ላይ ድቅን ሊልብህ ይችላል – ሊያውም ለዘመናት አብሮ በኖረው ወገኑ ላይ፡፡ ችግሩ የሚከፋውና ተስፋህን የሚያሟጥጥብህ ደግሞ ድርጅታቸውን በጭፍን ስለሚወዱና – ይህም ለሆድና ለዘውጋዊ የዓላማ ጽናት ሲሉ ነው – ኢትዮጵያዊነትን ፈጽመው እንዲጠሉ ስለተደረጉ ከነዚህ ሰዎች ጋር መነጋገርም ሆነ መደራደር የማይቻል የማይሞከርም የመሆኑ መጥፎ አጋጣሚ ነው፡፡ ሰው ግን በስንት ይበደላል!

አንዳርጋቸው ቢገደል አፈር አያሟሽም፡፡ አንዳርጋቸውን ቢገድሉት አንድ ነገር ይቀርበታል፡፡ ያም በጉጉት ይጠብቃት የነበረችዋን የኢትዮጵያን ነፃነት ሊያይ አለመቻሉ ብቻ ነው፡፡ ወያኔዎች ቢገድሉት ይህን የአንዳርጋቸውን ጉጉት ባጭር ለማስቀረት ካላቸው ፍላጎት እንጂ ዕድሜያቸውን ለማርዘም የርሱ ሞት ጠቃሚ ሆኖ እንዳልሆነ እስካሁን ካላወቁት አሁኑኑ ሊያውቁት ይገባል- በቃ፤ እውነቱ ይህ ነው፡፡ እንጂ አንዳርጋቸውን በመግደል የኢትዮጵያን ነፃነት እናስቀራለን የሚል አስተሳሰብ አሁንም ካላቸው በርግጥም በዱሮው ጅልነታቸው እንደታሰሩ ናቸው ማለት ነው፡፡ የተቆረጠን ቀን የአንድ ሰው መሞት አለመሞት አይመልሰውም፡፡ አያድርግበትና ቢገድሉት እንዲያውም ኢትዮጵያ ትጠቀማለች፤ ወያኔ ግን ክፉኛ ይጎዳል፡፡ አንዳርጋቸው በአንዳርጋቸውነቱ ቢሞት ባይሞት ምንም ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው – ወንድ ሲናገር ዛሬ ጧት ከኢሳት እንደሰማሁት አንዳርጋቸው በሕይወቱ የደላው ሰው አልነበረም – በሀገሩ ፖለቲካዊ ቀውስ ሳቢያ ከገሞራው ኃይሉ(ኃይሉ ገሞራው?) ብዙም ያልተሻለ ሕይወት ይመራ እንደነበር ተገንዝቤያለሁ፤ ኢትዮጵያን ያለ – ስለኢትዮጵያ አብዝቶ የተጨነቀ ተጠቅሞ አያውቅም – ምን ሩቅ አስኬደኝ … ነገን በተስፋ ሲጠብቁ ይህች ቅጽበታዊ ምድራዊ ዕድሜያቸው እየከዳቻቸው ያሉ በየሽርንቁላው ተወትፈው ቅዳሜን እሁድ ለማድረግ የሚታትሩ በርካታ ልጆች አሏት – ኢትዮጵያ፡፡ አንዳርጋቸው የሚለየው ጥሪውን ተቀብሎ የድርሻውን አበርክቷል – እናም አይቆጨውም፡፡

የርሱ ነገር መንጠልጠያው በትንሹ የሰባና የሰማንያ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡ አንዳርጋቸውን ሲገርፉ ኢትዮጵያን እየገረፉ ነው፡፡ አንዳርጋቸውን ሲያሰቃዩ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን እያሰቃዩ ነው፡፡ የአንዳርጋቸውን ጥፍር ሲነቅሉ የኔንም ጥፍር እያወለቁ ነው – ልዩነቱ የኔ በስሜት ነው – የርሱ ግን በውነት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የዞረ ድምር አለው፡፡ ዛሬ አንዳርጋቸውን የሚያሰቃዩ ሰዎች ደናቁርት ይሁኑ እንጂ እነሱም የሚሰቃይና የሚሞት ሰብኣዊ አካል ወይም ሰውነት አላቸው፤ ቤተሰብ አላቸው፤ ቀጣይ ትውልድ አላቸው፤ ሀብት ንብረት አላቸው፤ ባያምኑበትም ኢትዮጵያዊ ማንነትና ሥረ መሠረት አላቸው፡፡ ስለሆነም በነገይቷ ኢትዮጵያ በነሱና የነሱ በሆነ ነገር ላይ ሁሉ ምን ሊደርስ እንደሚችል ከአሁኑ ሊገምቱ ካልቻሉ በርግጥም ኅሊናቸው ታውሯል፤ አንጎላቸውም ተሰውሯል ማለት ነው፡፡ ዘመድ የሚያስፈልገው ይሄኔ ነው፡፡ መካሪ ያስፈልጋል፡፡ አንዳርጋቸውን መግደል ያዋጣ የነበረው ዛሬ አይደለም – ቀደም ሲል ቀረ፡፡ እርሱን ከመግደልም ይልቅ የዐዋቂዎችን ምክር ሳይንቁ ቢሰሙና ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ እያደረጉ የመጡትን ዘግናኝ አፍራሽ ነገሮችን ባያደርጉ፣ ለሕዝብ ስሜት ቢገዙ፣ የሕዝብን ፍላጎት ቢያከብሩ አንድ አንዳርጋቸውንና ከርሱም በፊት ያረዷቸውን ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ሳይረፈርፉ ከኢትዮጵያውያንና ከከራማዋ ጋር ታርቀው በቀላሉ በሰላም መኖር በቻሉ ነበር፡፡ አሁን ግን በጣም መሽቷል፤ ድንግዝግዝ ብሎባቸዋል – ከፈጣሪና ንጹሓን ፍጡሮቹ ጋር ደም ተቃብተው ከሰማዩም ከምድሩም ጋር ክፉኛ ተቀያይመዋል፡፡ አንዳርጋቸው ሌላ ኃጢኣትና ወንጀል ኖሮበት ሳይሆን በትንሹ የሚከተሉት ነገሮች እንዲወገዱ ነው የታገለው፡፡ እንደማሣረጊያ ከመቶ የትግሬ ወያኔ ጥፋቶች ዜሮ ነጥብ ዜሮ ዜሮ አንዱን ብቻ እዚህ ላይ ማስታወስ ፈለግሁ፡፡ ቀናና የመልካም ሥነ ምግባር ባለቤት የሆን ትግሬዎች በዚህ የወያኔዎች ዕኩይ ድርጊት ልናዝን እንጂ ባላደረግነው ነገር የቀያችን ልጆች ስላደረጉት ብቻ ልናፍር አይገባም፡፡ ክፉ ሥራና ኃጢኣት በዘርና በጎሣ አይተላለፍም፡፡ ሁሉም እንደሥራው እንጂ በጎጣዊ ማንነቱ ፍርድን አይቀበልም፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያን ከእግር እስከራስዋ ወርረው እስከመቅኒዋ ድረስ እየመጠመጡ የሚገኙ ሰዎች ኅሊና ብሎ ነገር፣ ሀፍረት ብሎ ነገር፣ ይሉኝታ ብሎ ነገር አልፈጠረባቸውምና አንዳርጋቸውን ቆራርጠው ቢበሉት ለጊዜውና አሁን የአማርኛውን ጉድ “ጉድ!” ከማለት ውጪ ሌላ ቃል የለንም፡፡ የነገውን ግን አንድዬ ነው የሚያውቅላቸው፡፡

አዲስ አበባ ውስጥ የአንድ ቀበሌ ሥራ አስፈጻሚ ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ ከበላዮቹ  ለአንድ ሹመት አንድ ባለዲግሪ መርጠህ ላክ ይባላል፡፡  ይህ ሰው ባለዲግሪ ትግሬ ቢያፈላልግ ያጣል፡፡ ምሥጢሩን የተረዳ አንድ ከርታታ አማራ “እኔ የሚፈለገው ዲግሪ አለኝ አይደለም እንዴ ለምን አትልከኝም?” ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ምን መለሰለት መሰላችሁ – “ያንተን ዲግሪ ለሽንት ቤት ተጠቀምበት!”፡፡ ያ ቆፍጣና ካድሬ አንዷን ባለዲፕሎማ ትግሬ ላከና ዐረፈው፡፡ ትግሬ ሁን እንጂ፣ በዚያም ላይ ታማኝነትን ደርብበት እንጂ መማር አለመማርህ ዋጋ የለውምና ሥራ ለመያዝ በባለዲግሪዎች የሌሎች ዘውጎች ተቀጣሪ አሽከሮችህ ላይም ለመዘባነን የሚያሳስብህ ነገር የለም – ተዓምር ነው፤ ከተዓምርም በላይ፡፡ የዚህ ሁሉ ጎጠኝነት መንስኤ ሥራ በትክክል ተሠራ አልተሠራ ወያኔን የማያስጨንቀው መሆኑ ነው – የሚያስጨንቀው ፖለቲካውንና ጥቅሙን ከወያኔ ትግሬ ውጪ ሌላ ኢትዮጵያዊ መያዙ ነው፡፡ ያ ያንገበግበዋል፡፡ ኢትዮጵያ ማለት ትግሬ፣ ትግሬ ማለት ኢትዮጵያ ሆናልሃለች፡፡ በሁሉም የመንግሥት መ/ቤቶች በአዛዥ ናዛዥነት እንደልቡ የሚፈነጥዘው ትግሬ ወያኔ ነው፡፡ ሌላው ባይተዋር ነው – ጨዋ ኢትዮጵያዊ ትግሬም ጭምር፡፡ በተለይ አማራ ለዘበኝነትም የማይታመን ሆኖልሃል ወዳጄ! አማራ “የሥራውን ነው ያገኘው፤ እሰይ! እንኳን!” እንዳልል ይህ ዘውግ በዚህን (ወያኔዎች በሚያሳዩት ደረጃ) ያህል ድፍረትና በዚህን ያህል ክትሩን የለቀቀ ጀብድ ኢትዮጵያን በግሉ ተቆጣጥሮ የጋጠበት፣ ሌሎችን በዚህን ያህል ደረጃ ያዋረደበት አንድም የግል ተሞክሮም ይሁን ታሪካዊ የጽሑፍ ማስረጃ ላገኝ አልቻልኩም፤ እናም ለመፍረድ ተቸገርኩ፡፡ እዚያው አጠገባቸው ስለምኖር ይህን አውቃለሁ፡፡ ፍርድ ለራስም ነውና በምለው ነገር እርገጠኛነቴን አትጠራጠር፡፡ እንዲህ የምለው ለዲያስጶራው እንጂ የዚሁማ የዚሁ ነው፡፡ እዚህ ያለውማ ነጋ ጠባ የተለማመደውን መራር እውነት እኔ ላረዳው ይቻለኛልን?

አንድ የኢሕአዴግ አባል የሆነ አማራ ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ ይህ ሰው እንዲህ የሚል የቅጥር መመሪያ በውስጥ ማስታወሻ ይደርሰዋል፡- “ ስትቀጥር 50 በመቶ ትግሬ፣ 25 በመቶ ደቡብ፣ … 1 በመቶ አማራ …” ይህ አባል ትግሬ መስሏቸው ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል – ብዙዎቹ ትግሬ ካድሬዎች ይሉኝታ ስለሌላቸው ጅሎች መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡ ያ የኢሕአዴግ አማራ ካድሬ ብልጥ ነበርና አመልካቾች ሲመዘገቡ አማራ ነን የሚሉትን በጆሯቸው ጠጋ እያለ “ሃድያ ነኝ ብለህ ተመዝገብ”፣ “ጠምባሮ ነኝ በል”፣ “ኮንሶ ብለህ ተመዝገብ” … በማለት ምድረ አማራን በደቡብ ስም ከደቡቦቹ ጋር እያዛነቀ ቀጠረ አሉ፡፡ ምን ያድርግ፤ ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ ይባል የለም? በዚህ መልክ ብቀጥል አውሎ ያሳድረናል፡፡ ይህንን ዐይን አውጣ የወያኔ ዕኩይ ተግባር ለማስተካከል መሞከር ሽብርተኛ ካሰኘ የነሱ ምን ሊባል እንደሚችል ራሳችሁ ገምቱ፡፡ ጎበዝ፣ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ እንደወያኔ ከሆነ ባፍንጫየ ይውጣ፡፡ ከእንስሳትም ወረዱብኝ፡፡ …

ተዓምረ ወያኔ ከዚህም ከዚያም

  • ኃ/ማርያም ደሳለኝ የትሮይ ፈረስ ሆኖ በውስጡ ያሉት እነሐጎስና እነግደይ ናቸው፡፡ ኃ/ማርያም ከሁለቱ የኢትዮጵያ መንግሥታት የአንደኛው አሻንጉሊት ነው – ኢትዮጵያ የኅቡዕና የግልጽ ሁለት መንግሥታት እንዳላት የማያውቅ መቼም የለም – የነጎይቶምና የነአብረኸት የመጋረጃው በስተጀርባ መንግሥትና የነደቻሳና የነስንሻው የምስለኔና እንደራሴ የውክልና መንግሥት፡፡ የኃ/ማርያም አሻንጉሊትነት “ኢትዮጵያ ከደቡብ ሕዝቦች የመጣ ጠ/ሚኒስትር አላት” የሚል ቅባት በተለይ ለደቡቡ ሕዝብና ለውጪው ዓለም ማደናገሪያነት መቀመጡ ነው፡፡ እንጂ ስለኢትዮጵያ የወቅቱ አስተዳደር ቅንጣት አያውቅም – እንዲያውቅም አይደረግም፤ ለታይታ ካገለገለ እርሱ ምን ቤት ሆነና! ግን ወግ አይቀርምና በሚዲያቸው “ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ከቻይናው አቻቸው ከቺንግቹዋ ቹንግ ጋር ተወያየ፡፡ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከግብጹ አቻቸው ከፕሬዚደንት አልጉልቤ ሲሲ ጋር ተነጋገሩ …” ይባልልኛል፡፡ ቂቂቂቂቂ ….. አለች ያቺ ጋዜጣ ጽሑፋዊ ሳቋ አምልጧት፡፡ የቃሉ አጠራር በጠያፍነቱ ምክንያት ባያስነውረኝ ኖሮ ኃ/ማርያምን “ኮንዶም ነው” ባልኩና ደስ ባለኝ፡፡
  • የአደባባይ ምሥጢር፡፡ መከላከያ፣ ውጭ ጉዳይ፣ ፖሊስ፣ ደኅንነት፣ ጉምሩክ፣ የመንግሥት ባንኮችና ኢንሹራንሶች፣ መብራት ኃይል፣ ቴሌ፣ የትምህርት ተቋማት፤ ገቢና ወጪ ንግዶች፣ የግንባታና የልማት ድርጅቶች፣ ፋብሪካዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ክፍለ ከተማዎች፣ ወረዳዎች፣ አነስተኛና ጥቃቅኖች፣ ሱቆች፣ መጋዘኖች፣ ማከፋፈያዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ኢንዱስትሪዎች፣ ወዘተ. ሙሉ በሙሉ በትግሬ ወያኔዎች ቁጥጥር ናቸው – የሌሎች ዘውጎች አባላት በታዛዥነት መኖራቸው አያስገርምም – ከተላላኪነትና ከእንደራሴነት የዘለለ ሚና የላቸውም ግን፡፡ ኢትዮጵያ በትግሬ ወያኔዎች የወለድ አግድ ማነቆ ሥር ናት፡፡ ተናደድ፤ መናደድ ባንተ አልተጀመረም፡፡ ስትናደድ ወደ ለውጥ የሚያመራ መንፈስ ይመጣልሃል – ምናልባትም ጥሩ መንፈስ፡፡
  • በግል ትምህርት ቤቶች በውድ ዋጋ ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል በግምት ከመቶ 95 የሚበልጡት ወላጆቻቸው ትግሬዎች ወይም ኢሕአዴግ ከሚባለው የወያኔ ዋሻ አንዳች ፍርፋሪና ዳረጎት የሚጣልላቸው ውዳቂ ዜጎች ናቸው፡፡ ደግሞም ለትምህርት ዋጋ የማይሠጡ ደናቁርት ናቸው፡፡ ልጆቻቸው ቢማሩ ባይማሩ ደንታቸው አይደለም፡፡
  • በየትም ሥፍራ በተለይም በአዲስ አበባ ከሚሠሩ ህንፃዎችና የልማት አውታሮች ውስጥ አሁንም በግምት ከ80 ከመቶው የሚበልጡት የትግሬዎች ናቸው፡፡
  • አዲስ አበባና መቀሌ ልዩነታቸው ፍጹም እስከሚጠፋ ድረስ ሁሉም የአዲስ አበባ ንግድ ቤቶች በትግሬ ወያኔዎች ቁጥጥር ሥር ሊገቡ የቀራቸው ጊዜ ግፋ ቢል ከአሁን በኋላ አሥር ዓመት ቢሆን ነው – እንዲያውም ከዚያም ያንሳል፡፡  የትም ሂዱ፣ የትም ግቡ ባለሱቁና ባለመኪናው ባለሀብቱና ባለቀብራራ ኑሮው ትግሬ ነው፤ ገንዘቡን የሚመነዝረው ትግሬው ነው፤ ለሚስቱ ብቻ ሳይሆን ለየውሽማውም ሳይቀር የሀገራችንን ሀብት መኪናና ቤት በመግዛት የትም የሚረጨው ትግሬው ነው፤ ሕዝብ ቆሼ ተራ ሀብታም በጣለው ፍርፋሪ ላይ ሲራኮትና ዜጋ በየመንገዱ ወድቆ በርሀብ አለንጋ ሲገረፍ ወያኔ ትግሬዎች በልጆቻቸው የልደት ቀን በሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ለድግስና ለስጦታ ያወጣሉ – ድንቁርና ከዚህ በላይ ካለ ንገሩኝ፡፡ ዜጎች በርሀብ እየወደቁ፣ ተማሪዎች በርሀብ ምክንያት መማር እያቃታቸው በምሣ ሰዓት በየትምህርት ቤቱ ኮሪደር እየተዘረሩ፣ የለማኙ ቁጥር ከመጽዋቹ ቁጥር በልጦ ኢትዮጵያ የቧጋቾች ሀገር ሆና ጥቂት ወያኔ ትግሬዎችና አንፋሽ አከንፋሾቻቸው ለራሳቸው እንደምትመጥን አድርገው በፈጠሯት አዲሲቷ የወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ልዩ ምድረ ገነት ፈጥረዋል፡፡ የሌሎች ዘውጎችን ነጋዴዎች የቤት ኪራይ በመቆለልና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ግብር በመጣል ከንግዳቸው አባርረው፣ መኖሪያ ቤታቸውንም እንዳመቺነቱ በዘረፋና ወይም በግዢ ነቅለውና ፈንቅለው የአሁኑ የአዲስ አበባ ጠረን ትግሬ ትግሬ የሚል ሆኗል፡፡ ቦሌም ግባ ጉለሌ “ጥሩ ጥሩ ለትግሬ” በሚል ሥውር ዐዋጅ ሌላው ከሥሩ ተፈንቅሎ ለስደትና ለማራሪነት ሲዳረግ ወያኔዎች ገብተው ይዝመነመኑበታል – ይህንን ሁሉ ግፍ የማይቆጥርና ዕዳን የማያስከፍል ፈጣሪ የለም የምትሉ ከሆነ እኔ የለሁበትም፡፡ የፍርድ ቀን ከመምጣቱ በፊት ወያኔ ትግሬዎች ሆይ አቅል ጀባ!
  • ምሥኪን ዜጎች ብሶታችንን እንዳንናገር እንኳ ንግግርን፣ አስተሳሰብንና ሃሳብ ማውጠንጠንን ራሱን በሽብርተኝነት የሚያሳስር ወንጀል እንደሆነ አስደርገው በወኪሎቻቸው የመንግሥት ወያኔ ትግሬዎች አማካይነት በሚያስወጧቸው የወሮበሎች ህግጋት በቁማችን መቀመቅ ሰደውናል፤ እንዳንታሰር እንፈራለን – ስለምንፈራም ፀጥ ረጭ እንላለን፤ ፀጥ ረጭ ስንልም ወደንና ፈቅደን የምንገዛላቸው ይመስላቸዋል፡፡ ገደብ የለቀቀውን “ትግስታችንን”ም እንደፍርሀት በመቁጠር እላያችን ላይ ይጸዳዱብናል፡፡ የመጸዳዳታቸው ውጤት የሆነው ክርፋትና ጥምባት ግን ፈጣሪን አስቆጥቶት ይሄውና … ቆይማ ብቻ፡፡ አሁን ምን አስቀባጠረኝ!
  • ሌላው ዜጋ በልዩ ልዩ ዘዴ ያፈራው ሀብት እንኳን ቢኖረው በሰቀቀንና በፍርሀት ተጀቡኖ በሁለተኛና ሦስተኛ ዜጋነት ነው የሚኖረው – ያሳዝናችኋል፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ እንደልቡ የሚኖረው ደንቆሮ ትግሬ ብቻ ነው፡፡ ዕድሜ ለወያኔዎች ሩቅ ተመልካች ትግሬ ሳይቀር ነገን በማሰብ አቀርቅሮ እንዲኖር የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሌት ከቀን የሚዝናናው፣ በመኪናው ውስጥ በሚከፍተው የሙዚቃ ድለቃ በደረቅ ሌሊት ሕዝብን እንቅልፍ የሚነሳው፣ በየቡና ቤቱ እየዞረ ትግርኛ ካልተከፈተልኝ በማለት ሌላውን ዘፈን በነፍጠኛነት የሚፈርጀውና የሚያስፈራራው ጠግቦ እየዘለለ የሚገኘው ትግሬ ወያኔና አሽከሮቹ ናቸው፡፡ የሚገርመው ጠጪዉና ተዝናኙ ትግሬ ብቻ ነው ተብሎ በአዋጅ የተነገረ ይመስል በየመዝናኛውና በየምሽት ክበቡ የሚከፈተው ዘፈን ከሞላ ጎደል ትግርኛ ብቻ ነው፡፡ ትግርኛ ካልከፈታችሁ ቡና ቤታችሁ ይዘጋል የተባለ ይመስል አዳሜ ከገዢው ወገን ጋር የተዛመደ እየመሰለው የሚከፍተው ሙዚቃ ትግርኛ ብቻ የሚሆንበት አጋጣሚ ሞልቷል፤ ሁሉም ነገር የብሔር ተዋፅዖ በሚለው የወያኔ አስመሳይ ፍልስፍና እየተመራ(ከስልሳ የጦር ጀኔራል ስልሳውንም ትግሬ አድርገው ሲያበቁ እኮ ነው – አያስቁም? ድንቄም ተዋፅዖ!) ለምሳሌ የሞቀ ኦሮምኛ ተከፍቶ በምትጨፍርበት ሠርግ ላይ ሳታስበው ድንገት ትግርኛ ወይም ወላይትኛ ሊከፈት ይችላል – ያኔ የውዝዋዜ ሥልትህን በቅጽበት ትቀይርና በኩኑ ከማሆሙ ነባር ኢትዮጵያዊ ብሂል አንተም አለውድ በግድህ ሰሜነኛ ወይም ደቡብኛ ውዝዋዜውን ታስነካዋለህ – በአቅጣጫና በቁጥር ስያሜዎች አለቅን እኮ፡፡ አለዚያ “ይህን አይወድም፣ ይህን ይነቅፋል ወይ ይጠላል” በሚል ኢመደበኛ ግምገማ የሰው ዐይን ውስጥ ልትገባ ትችላለህ – በዚያም ሰበብ የምታጣው ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ እስከዚህን የወረድን ሕዝብ ሆነናል – በዘፈን ምርጫ ሰውን መገምገም የሚዳዳባት ሀገር፡፡ እዚህ ላይ ትግርኛ መከፈቱ አስከፍቶኝ ሳይሆን ራስን ያለመሆን ጠባይ እየጎላ መምጣቱ ግን አስገርሞኝ ነው፡፡ በየትምህርት ቤቱማ ብታዩ ታሪኩ ብዙ ነው፡፡ በየቦታው የምትሰሙት ሙዚቃ አስመሳይነትን እንጂ እውነተኛ ፍላጎትንና ምርጫን አያመለክትም፡፡ ገበያን ለመሳብ ብቻ እንዴት የአንዲት ከተማ ቡና ቤቶች ተመሳሳይና የተሰለቹ ዘፈኖችን አንድን ወቅት እየጠበቁ (የስካርና የመዝናኛ) ይከፍታሉ? ወረተኝነት ከምን ጊዜውም በላይ እየተስፋፋ ነው፡፡ ነገ ደግሞ የሽናሻ መንግሥት ቢመጣ ቡና ቤቱ ሁሉ ሽናሽኛ ዘፈን እየለቀቀ ካለተዝናኙ ፍላጎት ሊያደነቁረው ነው ማለት ነው፡፡ ትንግርቱ ብዙ ነው፡፡ ይህን የምለው በጥራዝ ነጠቅ የማውቃት የሥነ ልቦና ትምህርት ግንዛቤየ እየታወሰችኝ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች ለምን፣ እንዴትና መቼ እንደሚያደርጉ ወይም እንደማያደርጉ የጫረብኝ አስጠሊታ ምስል ነው፡፡ ሰው ግን ምን ያህል አስመሳይ ፍጡር ነው!? ምን ነካን? ብንወርድ ብንወርድ እስከዚህ እንውረድ?
  • አዲስ አበባ ውስጥ ከሚዝመነመኑ ግሩም አውቶሞቢሎች ከአሥሩ በትንሹ ሰባቱ የትግሬዎች ናቸው ቢባል ስህተቱ ለኩነኔ አያደርስም፡፡ የንግድ መኪናውን ብትመለከትም እውነቱ ከዚህ ብዙም አይለይም፡፡ ትግሬ ግን ከኢትዮጵያ ሕዝብ አጠቃላይ ብዛት ግፋ ቢል 8 በመቶ ቢሆን ነው፡፡ የጥንቱን ስድስት በመቶውን አሁን እርሱት – አዲስ አበባ ላይ የሚርመሰመሰው ወያኔ ብቻውን ከአምስት በመቶ የሚያንስ አይመስለኝም – ለቁጥር ያለኝ ቀረቤታ እንደበውቀቱ ሥዩም እስከዚህም ቢሆንም፡፡ አማራው ቀንሷል – ትግሬው ጨምሯል፤ በምናውቃቸውም በማናውቃቸውም ምክንያቶች የተነሣ፡፡ ዘር ማብዣ ማዳበሪያ ወደትግራይ – ዘር ማምከኛ በስሪንጋ የሚሰጥ ብልቃጥ መርዝ ወደአማራ፡፡ ታሪክ ይፋዊ የምሥክርነት ቃሉን ሊሰጥ በቋፍ ላይ ነውና በትግስት እንጠብቅ፡፡ አለ ገና – ብዙ ነገር ይታያል፡፡ ዕድሜና ጤና መለመን ነው፡፡ አንድዬ የሚሳነው ነገር የለምና ያቆየን፡፡ የምመክራችሁ እንድትናደዱ ነው፤ ስትናደዱ ወደመፍትሔው ትጠጋላችሁ፡፡ አሪቬዴርቺ፡፡

 

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop