June 1, 2014
21 mins read

ልማታዊ-ሱሰኞችና ትዉልድ-አምካኙ መንግስት

ናትናኤል አባተ
ከኖርዌይ
19 06 2014

ናትናኤል አባተ
ልማታዊ-ሱሰኞችና ትዉልድ-አምካኙ መንግስት 1

በሃገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቁ እጅግ በጣም የሚያሳፍሩና መረን የለቀቁ ከሃገራችን ባህል ጋር የሚጻረሩ ድርጊቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተበራከቱ መጥተዋሉ፣፣ ሃይማኖተኛዉና ፈሪሃ-እግዚያብሄር  ያለዉ የሃገረ ሰው፣ እንደ ቀድሞ ሃይማኖቱን፣የሃይማኖት ትምህርቱን የሁሉም መሰረት የሆነዉን ኧምላኩን መፍራት በመተዉ እነዚህ አሳፋሪና ትዉልድ የሚያመክኑ ድርጊቶች ተካፋይ ሆነዋሉ፣፣

በትላልቅ ከተሞች እንደ አሸን የፈሉና ሃገርቱን ከታች እስከ ላይ እንደበረሃ አንበጣ የወረሩ ሱስ ቤቶች፣ስዉር የራቁት ጭፈራ ቤቶችና ተቆጣጣሪ የሌለዉ የአልኮል ገበያ  ከሃገሪቱ ድህነት ጋር ተዳምሮ እጅግ በጣም አስጊ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሰዋል፣፣ የእነዚህ ተቋማት አስጊነታቸዉ፥ በብዛት በተቋማቱ የሚገለገሉ ወጣቶችንና ገና በአፍላ ዕድሚያቸዉ የሚገኙ ልጆችን ኧእምሮ በሱስና ምግባረ ብልሹነት ማምከናቸዉ እንድሁም ብቁ ዜጋ እንዳይሆኑ ማድረጋቸው ነው፣፣ አብዛኞቹ ተገልጋዮች ልጅነት የሚጠቃቸዉና ገና ያልበሰሉ በመሆናቸዉ፥ እነዚህን ተቋማት አዘዉትሮ መጠቀም የሚያስከትሏቸዉን  ችግሮችንና ዉጠታቸዉን በጥልቀት ማገናዘብ የማይችሉ ናቸዉ፣፣ የሃገሪቱን ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ መቀየር የምችሉ ወጣቶችና የነገይቱን ኢትዮጵያ ተረካቢ ህጻናት በእንድህ አይነት ክፉ ወጥመድ ዉስጥ መዉደቃቸዉ ችግሩ ለወደፍት ሃገሪቱ ምን ያህል አስጊ እንደሆነ ያመላክታል፣፣

በየትኛዉም አለም በስነምግባር የታነጸ ትዉልድ ለወደፍት የሃገር ህሊዊና ወሳኝ መሆኑ እሙን ነው ፣፣በተቃራኒዉ ሱሰኛና ምግባረ ብልሹ ትዉልድ ለሃገር ዉድቀትም ትልቅ ሚና ይጫወታል፣፣ የሃገራችን ጉዳይ ከዚህ የተለየ ባለመሆኑ ዉሸታሙ ልማታዊ መንግስታችን ባለፉት 23 ዓመታት ልማታዊ ሱሰኛ ትውልድ ከማፍራቱም በላይ በሃገርቱ ሱሰኝነት እንድበዛ ሱስ የሚያስይዙ ነገሮችን  በልማታዊ መንገድ እየነገደ ይገኛል፣፣ ልማታዊ ሱስ ቤቶች በብርሃን ፍጥነት በትላልቅ ከተሞች እየተበራከቱ የመጡ ሲሆኑ አንዳንዶቹን እንደምከተለዉ አስቀምጣለዉ፣፣

1, ጫት ቤትና በዉስጡ የሚገኙ ነገሮች:-

ሀ, ሲጋራ፥ሺሻ፣ ጋንጃ፣ኮከይንና ሌሎች አደንዛዥ እጾችን ይይዛል፣፣

ለ, አሻሻጭና አጫዋች ኮረዳ እንድሁም አስፈላጊ ሲሆን ከወንድ  ጋር የሚትወጣ፣፣

1.1, የቤቱ ባለቤትነት:-አብዛኛዉን የመንግስት ካድረ ምስጥር በሆነ መልኩ ወይም በዘመድ ስም፣ የመንግስት አባል የሆነና የመንግስትን በፖለቲካዊ ተልኮ መወጣት የሚችል ነጋዴ፣፣

1.2, ተገልጋዮች:-ወጣቶች፣አፍላ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ህጻናት፣ አንስተኛ ቁጥር ያላችዉ አዋቂዎችና የመንግስት ሰላዮች

የጫትቤት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ያለ የገበያ መስክ ስሆን፥ ከላይ እንደጠቀስኩት አብዛኞቹ ተገልጋዮች የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህት ቤት አፍላ ህጻናት ተማሪዎች፣የሃይ እስኩል፣ኮሌጅና ዩንቨርሲቲ ተማሪዎችና በለሎች መስክ የተሰማሩ ወጣቶች ናችዉ፣፣ በርግጥ ዉስን ቁጥር ያላቸዉ ጎልማሳዎች እንደምጠቀሙ አይካድም፣፣ ጫት ቤት ዉስጥ በጫት ስም የሚነገዱ አደገኛ አደንዛዥ እጾች፣ ሺሻ በጉዳቱ ከስጋራ በ200 እጥፍ የሚበልጥ ፣ ሲጋራና ሴተኛ አዳሪዎች ይሸጣሉ ይለወጣሉ ያለማንም ቁጥጥር፣፣ እንደ ዘመናዊነት እየተቆጠረ ወጣቶች በሰፍው የሚጠቀሙት ሺሻ ለጤና ጠንቅ ከመሆንም በላይ ከስጋራ በመቶዎች እጥፍ የሚበልጥ ጤናዊ ጉዳት እንድሚያደርስ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ያመላክታሉ፣፣ አደንዛዥ እጽዎች በከፍል  በሃገር ዉስጥ የሚመረቱ ሲሆን ከፍሉ ደግሞ በልማታዊዉ መንግስታችን  ባለስልጣናት አማካኝነት በህገ/ወጥ መንገድ ከዉጭ ይገባሉ፣፣ እንድሁም አንዳንድ ሙያዊ ስነምግባር የጎደላቸዉ ልማታዊ ሃኪሞች ከህክምና ተቋማት በህገወጥ መንገድ አዉጥተዉ እንደምሸጡ ዉስጥ  አዋቂዎች ይመሰክራሉ፣፣ ከጫት ቤት ተጠቃሚዎች  መሃከል በእጅጉ የሚጎዱ ህጻናትና ወጣቶች ሲሆኑ ገና በልጅነታቸዉ ብዙ ነገር መማርና መቅሰም ባለባቸው ዕድሜ የሱስ ሰለባ ሆነዉ ወደ ሁዋላ ይቀራሉ፣፣ በሱስ የተጠመደ ኧእምሮ ወደፍት የማለም፣የማቀድና የማሰብ ብቃቱን  ያጣል፣፣ የዚህ ኧእምሮ ትልቁ ስራ የእለት ሱስ መሸፈንና የመሸፈኛዉን ዜዴ ማሰብ ብቻ ይሆናል፣፣ እነዚህ ሱሰኞች የአምራችነት አቅማቸው የሚቀንስ ከመሆኑም አልፈዉ ማህበራዊ፥ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በበቂ ሁኔታተሳትፈዉ ለዉጥ ለማምጣት ስለማይጥሩ የሃገርና የህዝብ ሸክም ይሆናል፣፣ ከዘረዘርኳቸዉ የጫት ቤቶች ምስጥራትን ጎን ለጎን መንግስት በእያንዳንዱ ጫት ቤት ዉስጥ ሰላዮችን በመመደብ ያስሰልላል፣፣ አንዳንድ ጊዜ የጫትቤቱ አስተናጋጅ ዉብ ኮረዳዎች ሰላዮች ሲሆኑ የተላኩበትን ተልእኮ ለመፈጸም እንስትነታቸዉ ጉልህ አስትዋጽኦ እንዳለዉ ይነገራል፣፣ ለዚህም እንደምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ወያነ አድስ አበባ ዉስጥ በየካፌዉ ሰላይ አስተናጋጆችን እንዳሰለፈ ማስታወስ ይቻላል፣፣

ከጫት ቤቶች ቀጥሎ የብዙዎችን ጎጆ ያፈረሰ፣ የወጣቶችን ኧእምሮ የበከለና የስነምግባር ጸር የሆነ የራቁት ጭፈራ ቤቶች  ይገኛል፣፣ በአንድ ወቅት ልማታዊዉ ወያነ አስዘጋለዉ ብሎ ተነስቶ እንደገና በስዉር ራሱ የከፈተው፥ይህ የጭፈራ ቤት የተለያዩ ለአቅሜ ሄዋን ያልደረሱ ጉብል ልጃገረዶች ከተለያዩ የሃገቱ ክፍሎች በደላላ በኩል ለባለስልጣናት የሚቀርቡበትና የብዙ ባለትዳሮች ማማገጫ ስፍራ ነዉ፣፣ ህሊና የሌላቸዉ እነዚህ ሰዎች የስንቱን ህልም አጨለሙት፣የስንቱን ጎጆ አፈረሱት፣፣ በእነዚህ ቦታዎች፣ኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ሰብዓዊ ክብር የጠፉበት፥ህሊናቸዉን የከዱ ሰዎች ያሉበትና፣ ለማየት የምሰቀጥጡ፣ ከባህል፣ ከወግና እምነት የወጡ ድርጊቶች የሚፈጸሙበት ሲሆኑ የሴት ልጅ ክብሩዋ ተገፎ  እንደእቃ አገልግሎት የምትሰጥበት ስፍራ ነዉ፣፣ እንግድህ ይሄን ዲያብሎሳዊ የርኩሰት ስፍራ የመዝናኛ ስፍራ ብለዉ መጥራታቸዉ የሚያስገርም ሆኖ እያለ የሴት ልጅ ክብሩዋን እየገፈፉ ስራዋ ነዉ ማለታቸዉ ምንያህል ኢሰብዓዊ ድርጊት እየፈጸሙ እንደሆኑ ያሳያል፣፣

ሌላኛው በሰፍዉ ብዙዎች የሚገለገልሉት አልኮሆል በትላልቅ ከተሞች እንደአሸን የፈላ ሲሆን እንደሌሎች ሃገሮች የተጠቃሚዎች እድሜ ላይ ቁጥጥር ስለማይደረግ መረን የለቀቀና ልክ ያጣ የአልኮል ተጠቃሚነት ይታያል፣፣ በትላልቅ ከተሞች መሸትሸት ስል ዞር ዞር ያለ ሰው በግርምት የተጠቃሚዎችን ብዛት ያለእድሜ ወሰን ሊገነዘብ ይችላል፣፣ በሃገርቱ የይስሙላ ህግ የአልኮል መጠቀሚያ እድሜ ብደነግግም ህጉ በስራ ላይ ባለመዋሉ በአፍላ እድሜ ላይ የሚገኙ ህጻናት በሰፍዉ ስጠቀሙ ይታያሉ፣፣ ይህ የአፍላ ልጆች አልኮል መጠቀም ለHIVና ለሎች አባለዘር በሽታዎች መስፋፋት ሰፍዉን ድርሻ ይወስዳል፣፣እንግድህ እነኝህ ያለእድሜያቸዉ ልማታዊ ሱሰኛ የሆኑ ዜጎች ለሱሳቸዉ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት በማህበረሰቡ ላይ ማንኛዉን አይነት ወንጄል ለመፈጸም ወደኋላ የማይሉ፣የማይራሩ ጨካኞች፣ ደም የጠማቸዉ ወንጀለኞች ሆነዉ ይወጣሉ፣፣

ከላይ ለመዳሰስ የሞከርኳቸዉ የወጣቶች ሱሰኝነት ኢትዮጵያ ዉስጥ በሰፍዉ የሚታይ ሲሆን የሱስ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም በዋናነት አንግበዉ የሚንቀሳቀት አላማ ትዉልድን ማምከን፣ የወጣቶች ማሰብያ ብቃት መቀነስ፣ በሃገርቱ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት የሚሳተፍ የወጣት ሃይልን ማጥፋት ነው፣፣ይህ ሆን ተብሎ ታስቦበት ፖለቲካዊ መልእክት ይዞ የሚደረግ የወያነ ሴራ ነው፣፣ የወጣቱ መድከምና በሱስ መጠመድ ለአደገኛዉ ቦዘነ ኢህአዴግ መንግስት የእድሜ ማስረዘሚያ ዜዴ ከመሆኑም አልፎ የደነዘዘ ወጣት ለስልጣኑ ስጋት ስለማይሆነው ደስታውን ታላቅ ያደርገዋል፣፣ እንደ ወያነ እምነት ለአገዛዙ ስጋት ያልሆነ እንድሁም ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ መብቱን የማይጠይቅ ሰው የፈለገዉን ማድረግና መሆን ይችላል፣፣ ወያነ ስለ ነገይቱ ኢትዮጵያ የሚገደዉ ነገር የለዉም፣፣ ስለዚህም ነው ብዙ ወጣቶችን እያሳደደ ሃገር ጥለዉ እንድጠፉ፣እንድታሰሩ፣ እንድሰቃዩ፣በሱስ የተጠመዱና የተበላሹ ዜጎች እንድሆኑ ቀንና ሌሊት የሚተጋው፣፣ በጠቅላላዉ ስታይ በሃገርቱ በሰፍዉ የምታየዉ የወጣቶች የሱሰኝነትና የሱስ ተቋማት መብዛት የመንግስት ስራ መሆኑ ገሃድ ነዉ፣፣ ወያነ በሱስ የተጠመደ ወጣት ለአገዛዙ እንደማያሰጋና ሁለንተናዊ ለዉጥ ብዙም እንደማያሳስበዉ ጠንቅቆ  ያዉቃል፣፣ በመሆኑም ሱስና ሱሰኝነትን ለመቀነስ ምንም አይነት እርምጃ አይወስድም፣፣ በርግጥ በአንድ ወቅት የጫት ቤትንና የራቁት ጭፈራ ቤት አስዘጋለሁ ብሎ ማስፈራሪያ ጀምሮ  የነበረ ብሆንም ሌሎች ነጋዴዎችን በማስዘጋት፥ የካድሬዎቹን እንደገና በሁለትና በሶስት እጥፍ እንድከፍቱ አድርጎ በየጫት ቤቱ የሰላይ መዓት መደበዋል፣፣ እነዚህ ቃማቴ ሰላዮች፥ ወዳጅ መስለዉ ቀርበው ስራቸዉን ይሰራሉ፣፣

ትዉልድ አምካኙ ወያኔ መራሽ ኢህአዴግ፥ በሃገርቱ ፖሊቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታዎች ብቻ ላይ ሳይሆን አሉታዊ ተጽእኖ  ያሳደረዉ፣ በማህበረሰቡ ሃይማኖታዊና፣መንፈሳዊ ህሊዉናም ላይ ነዉ፣፣ ሃይማኖት የአንድን ሃገር ዜጋ በስነምግባር ለማነጽና ጠንካራ ትዉልድ ለመፍጠር ትልቅ ድርሻ እንዳለዉ ይታዎቃል፣፣በተለይ በሃገራችን ኢትዮጵያ፣፣ ወያነ ከብዙዎቹ ሃይማኖታዊ ተቋማት መሪዎች ጋር በመመሳጠርና ቀንደኛ አጫፋሪ በመሆን እንድሁም በቀጥታና በተዘዋዋሪ በሃይማኖት ተቁዋማት ዉስጥ እጅ በማስገባት፣ መንፈሳዊ ተቋማትን የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ማስከጃ ስፍራ በማድረጉና የሃይማኖት መሪዎች ፖለቲከኝነት፣ዉሸታምነት፣ ለመንግስት መቆምና ብልሹ ስነምግባር ወጣቱን ተስፋ አስቆርጧል፣፣  ይህ ድርጊት ከትዉልዱ ላይ ፈርሃ እግዚያብሄር በማጥፋት መንፈሳዊነትን አድክሞ ሱሰኝነትን እንድንሰራፋ የበኩሉን አድርጓል፣፣ ትውልዱን ተስፋ ያስቆረጠው ምክንያት ለአምላክ ቅርበት ያላቸዉ የሃይማኖት መሪዎቹ የሚፈጽሙ እኩይ ፣እርኩስና አስጸያፊ ድርጊት ያያሉ፣ ምንም ነገር እንደማይደርስባቸዉም ይመለከታሉ፣፣ ከዚህም የተነሳ ተከታዮቹ አስር እጥፍ ክፉ ለመስራት የፈጠኑ ይሆናሉ፣፣  አብዛኞቹ አስመሳይ ሃይማኖተኞ ች ይሆኑና  ቀን እያስቀደሱ፣እየሰገዱና እየጸለዩ ይዉሉና ማታ ወንጀለኞች፣ሱሰኞች፣አስጸያፊ ድርጊት የሚፈጽሙ  ነዉረኞች ፣ልማታዊ ሃይማኖተኞች ናቸዉ፣፣ ለወጣቶቹ መንፈሳዊ ድክመትና ሱሰኝነት ቀጥተኛ ተጠያቂዎች የሃይማኖት መሪዎች ድርጊት ሲሆን በተጨማሪም የሃይማኖት መሪዎች ከምግባሬ ብልሹ የወያነ መንግስትጋር መመሳጠራር ራሳቸዉ የስነምግባር ዝቅጠት ዉስጥ በመዝፈቃችው ለተከታዮቹ መዉደቅ ትልቅ መንስኤ ነው፣፣

ለወጣቶች ሱሰኝነት ሃይማኖታዊ ተቋማት ጉድለት የራሱ ሚና ቢኖረዉም ትንሹን ድርሻ ይወስዳል፣፣ ትልቁን ድርሻ የሚወስደዉ  መንግስትና የመንግስት ፖሊሲ ነዉ፣፣ መንግስት ለወጣቶች መዝናኛ በቂ ትኩረት ያለመስጠት ያስከተለው የመዝናኛ እጦት፣ ያሉት የመዝናኛ ስፍራዎች የቅንጦት ሆነው ዉድና የድሃዉን አቅም ያላገናዘቡ መሆናቸዉ፣ የወጣቶች የኳስ መጫዎቻ ቦታዎች ተሽጠዉ ማለቃቸዉ በዋነኛ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ፣፣ ሆዳሙ መንግስታችን ከእኔ በኋላ ሰርዶ አይብቀል በማለት የተገኘዉን  መሬት ሁላ ከኳስ ሜዳ እስከ ገበሬዉ ማሳ ፣ ከግጦስሽ መሬት እስከ ገዳማትና ደብር ድረስ እየቸበቸበ ገንዘቡን በክሱ ያደርጋል፣፣ በገንዘቡ የእነሱ ልጆች ተንደላቀዉ አሜሪካና አዉሮፓ ሲማሩና ሲዝናኑ ታድያ የድሃዉ ልጅ የት ይሂድ ???ሱሰኛ ቢሆንስ ምን ይገርማል!!!!!!የድሃ ልጆች እንደባለስልጣናቱ ልጆች በድሎት በፈረንጅ ሃገር ቪላ ተገዝቶላቸው ተንፈላስሰው መማር ስላልቻሉና የመዝናኛ ስፍራቸዉ ስለተሸጠባቸዉ ሱሰኞች ቢሆኑ ብዙም አይገርምም፣፣

ድምዳሜ

በስነምግባር የታነጸ፣ከሱስ የጸዳ፣አርቆ አሳቢ፣ሃገር ወዳድና በሃገርቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና፣ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት የሚሳተፍ ጠንካራ ዜጋ  ለማፍራት በስልጣን ላይ ያለዉ ስነምግባረ ብልሹና ትዉልድ አምካኙ ስርዓት መወገድ አለበት፣፣ ወያኔ በሃገርቱ ሃይማኖታዊ፣ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ ገጽታዎች ላይ እያደረሰ ያለዉ ክስረት ከባድ ነው፣፣ይሄ እኩይ ተግባሩና የሃገርቱ ዉድቀት እንድቀጥል ወጣቱን በሱስ በማደንዘዝ፣ወጣቱ ለዉጥ እንዳይፈልግ፣ጥያቄ እንዳያስነሳ በተዘዋዋሪና በቀጥተኛ መንገድ የወጣቶችን ኧእምሮ እያመከነ ይገኛል፣፣ በመሆኑም ይንን ትዉልድ የሚያመክን፣ሃይማኖት የሚቀይርና ሃገር የሚሸጥ ባዕድ ገዥ ለማስወገድ በአንድነት እንነሳ ፣፣

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!!!!

ኢትዮጵያ ትቅደም!!!!!

አስተያየትዎን በዚህ ይላኩልኝ E-mail[email protected]

Facebook Nathy De Saint

Twitter  @nathysaint

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop