13ቱ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች 3ት የመከላከያ ምስክራቸውን አሰሙ፤ ሙሐመድ ሰዒድ እርቃኑን ተገርፏል

June 30, 2014

(ፎቶ ከፋይል)
13ቱ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች 3ት የመከላከያ ምስክራቸውን አሰሙ፤ ሙሐመድ ሰዒድ እርቃኑን ተገርፏል 1
የአዛን አንቲ-አህባሽ የመረጃ መረብ እንደዘገበው

ላለፉት ረጅም ጊዜያት በእስር እየተንገላቱ የሚገኙት 13ቱ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬ ሰኔ 23ት ዕለተ ሰኞ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋሉ።

የፌደራል ኣቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ እና ሐሰተኛ ምስክር ዙሪያ መርምሮ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ጥፋተኛ ናቸው ወይም ነፃ ናቸው በማለት ብይን ለመስጠት ለግንቦት 26/2006 በቀጠረው መሰረት የፌደራል አቃቤ ህጉን ክስ ተቀበሎ ተከሳሽ ንፁሃን ወንድሞቻችንና እህታችንን እንዲከላከሉ መወሰኑ ይታወቃል።

እስከ ሰኔ 19 ዕለተ ሐሙስ በነበረው የመከላከያ ምስክርነት (የዕምነት ክህደት ቃል)

1ደኛ ተከሳሽ እስማዔል ኑሪ
2ተኛ ተከሳሽ እህት ፈቲያ 3ተኛ ተከሳሽ ኑሪዬ ቃሲም
4ተኛ ተከሳሽ ያሲነ ፈያሞ
5ተኛ ተከሳሽ ሙሃመድ አሚን
6ተኛ ተከሳሽ ሙሐመድ ሰዒድ
7ተኛ ተከሳሽ ዩሱፍ ከድር
8ተኛ ተከሳሽ ጣሂር ሙሃመድ
9ተኛ ተከሳሽ ሙሃመድ ሰዒድ
10ተኛ ተከሳሽ ሰዒድ ኢብራሂም
11ተኛ ተከሳሽ አብደላ ሙሃመድ
12ተኛ ተከሳሽ አብዲ ሙሃመድ
13ተኛ ተከሳሽ ኢብራሂም የሱፍ የተከሳሽነት ቃላቸውን በተናጥል ሰጥተዋል።
በቀነ ቀጠሯቸውም መሰረት 13ቱ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎቸ የሰው የመከላከያ ምስክራቸውን ከሰዐት በዋለው ችሎት አቅርበዋል።

የመከላከያ ምስክር ሆኖ የቀረበው በዚሁ መዝገብ 12ተኛ ተከሳሽ የሆነው አብዲ ሙሃመድ ሲሆን ምስክርነቱንም የሰጠው ለ 6ተኛ ተከሳሽ ለሆነው ለሙሃመድ ሰዒድ ነው።

12ተኛ ተከሳሽ ከሰዐት በዋለው ችሎት “ከሁለት ወር በላይ አብረው እንደነበሩና ባሳለፉት ሁለት ወር ውስጥ የተከሳሽነት ቃሉን ስድስተኛ ተከሳሽ ሙሃመድ ሰዒድ በግዳጅ እንደሰጠ ፣ አብረው በነበሩበት ወቅት ከእጂ መዳፍ እስከ ክርኑ፤ ከቁርጭምጭሚቱ እስከ ታፋው፤ ከመቀመጫው እስከ ጀርባው መጨረሻ ድረስ አካላዊ ድብደባ እንደሚፈፀምበት ፣

እርቃኑን እንደሚገረፍ፣ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞበት ሲመለስ አካሉን በቫዝሊን እንደሚያሽለት፣ 6ተኛ ተከሳሽ ሰውነቱ ከሰንበር አንስቶ እስከቁስለት ደረጃ ድረስ እስኩደርስ መደብደቡን፣ አብረው ከታሰሩበት ክፍል 6ተኛ ተከሳሽ በሰላም ወደ ምርመራ ከሄደ በሗላ ሲመለስ አካሉ ደክሞና ጉዳት ደርሶበት እንደሚመለስና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን በማዕከላዊ እስር ቤት የሚፈፀሙ ግፎችን አስረድቷል።
2ተኛ የ 13ቱ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መስካሪና 8ተኛ ተከሳሽ ጧሂር ሙሃመድም በከሰዐቱ ችሎት ለ 6ተኛ ተከሳሽ ሙሃመድ ሰዒድ የመከላከያ ምስክርነት ቃሉን የሰጠ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ቃሉን ተገዶ እንደሰጠ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

3ተኛ የ 13ቱ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መስካሪና 9ኛ ተከሳሽ የሆነው በተመሳሳይ መልኩም ሙሃመድ ሰዒድ ዩሱፍ ለ6ተኛ ተከሳሽ ሙሃመድ ሰዒድ በማዕከላዊ ስለደረሱበት እንግልትና ድብደባ እንዲሁም ቃሉን በግዳጅ እንደሰጠ የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱም ቀጣይ የመከላከያ ምስክርነት ሂደት እንዲቀጥል ለ ለሰኔ 30 ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፍትህ ለተማሪዎቻችን!

2 Comments

  1. በታም ያሳዘናልል መን እያሆነ እንዳለ መሰማት በራሱኡ የዘገነናል እግዘአብሀር ያወታችሁ!!!!!ከምረረ አገዛዘ ያሰትረፋችሁ!!!!

  2. ይህ ድርጊት እኮ ዛሬ ኢትዮጵያ በምንላት አገር ውስጥ ለመብታቸው በቆሙ ሁሉ ላይ የሚፈጸም የእለት ተእለት ግፍ ከሆነ ቆይቶአል እኛ ግን ገና አልባነንም :: እያንዳንዳችን ላይ እስኪደርስ የምንጥብቅ ይመስላል :: ሙስሊሙ ክርስቲያኑ ወንዱ ሴቱ ሙሁሩ ገበሬው ሰራተኛው ወዘተ …ሁሉም ላይ ግፉ በየተራ እየደረሰ ነው :: በአጠቃላይ ጤነኛ አእምሮና እንደሰው ማሰብ በሚችል ዜጋ ላይ ሁሉ ግፉ ይቀጥላል :: ወያኔ የሚሰራውና የሚለውን ሁሉ ትክክል ነው ብለን እስካልተቀበልን ድረስ ::

Comments are closed.

Previous Story

የሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ኪሳራ በሚነሶታ!  እውን አላሙዲ የገንዘብ ድጋፋቸውን ይቀጥሉ ይሆን?

Next Story

ዐማራውም በደል አልመረው አለ! ጠላቶቹም የላም አሸናፊ ሆኑ!

Go toTop