የዳቦና የዱቄት ጉዳይ እያወዛገበ ነው

በጸጋው አለሙ

በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት መንግስት ለተወሰኑ ዱቄት ፋብሪካዎችና ዳቦ አቅራቢዎች የድጎማ ስንዴን በማቅረብ ዳቦን በቁርጥ ዋጋ ለተጠቃሚው እንዲያቀርቡ ሲያደርግ ቢቆይም ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ ግን ቃሉን ጠብቆ የስንዴ ምርቱን እያቀረበ ባለመሆኑ ችግር ላይ መውደቃቸውን አንዳንድ በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል። መንግስት የተወሰነ ዱቄት ፋብሪካዎችና ዳቦ አምራቾችን በራሱ የአቅርቦት ትስስር ውስጥ በማስገባት ባለፉት አመታት የዳቦ ግራምን ወስኖ ባስቀመጠው ዋጋ እንዲሸጡ ሲያደርግ ቆይቷል።

ሆኖም መንግስት ለዳቦ ቤቶችና ለዱቄት ፋብሪካዎች ስንዴን በማቅረቡ ረገድ እስካለፉት አራት ወራት ድረስ ቢቀጥልም ካለፉት አራት ወራት በኋላ ግን በገባው ቃል መሰረት በቂ ስንዴ ማቅረብ ባለመቻሉ የዳቦ እጥረት እየፈጠረ መሆኑን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ገልጸውልናል። እንደነጋዴዎቹ ገለፃ መንግስት በአሁኑ ሰዓት እያቀረበ ያለው የስንዴ መጠን መቅረብ ከሚገባው ሁለት ሶስተኛን እጅ በመቀነስ ነው።

በዚሁ ዙሪያ ካነጋገርናቸው በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል አንዱ የሆኑት የሮዚታ ዳቦ መጋገሪያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተሾመ ተዘራ መንግስት በገባው ቃል መሰረት የተፈለገውን የስንዴ መጠን ሊያቀርብላቸው ባለመቻሉ ከተቀመጠው ዋጋ በተጨማሪ 5 መቶ ብር በኩንታል አውጥተው ከግለሰብ አቅራቢዎች ስንዴ ለመግዛት መገደዳቸውን ገልፀውልናል። በዚህም አንዳንድ ዳቦ ፋብሪካዎች ክስረት እየደረሰባቸው በመሆኑ ከዘርፉ ለመውጣት እየተገደዱ መሆኑን አንዳንድ ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችም ገልፀውልናል።
መንግስት ባስቀመጠው የዋጋ ተመን መሰረት ዳቦ ቤቶች ምርታቸውን እንዲሸጡ ቢገደዱም ግን መንግስት በገባው ቃል መሰረት በቂ የስንዴ አቅርቦትን ባለማቅረቡ ከሌላ ነጋዴ በ1300 ብር እየገዙ በተተመነው ዋጋ ዳቦ መሸጣቸው በቀን የዘጠኝ ሺ ብር ክስረት እየደረሰባቸው መሆኑን አቶ ተሾመ ገልፀውልናል። መንግስት በገባው ቃል መሰረት አንድ ኩንታል ዱቄትን በ796 ብር ሲያቀርብ የቆየ መሆኑ ታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከሰዓት በኋላ በመዲናዋ በጣለው ከባድ ዝናብ የተከሰተው ጎርፍ በሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ

በነጋዴዎቹና በመንግስት የስንዴ አቅርቦት መካከል የተፈጠረውን ክፍተት ተከትሎ በአዲስ አበባ በድጎማ ለህብረተሰቡ የሚቀርበው የአንድ ብር ከሃያ ዳቦ እጥረት እየታየበት ነው።
በዚህ ዙሪያ ያነጋገርናቸው በንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማከል ይማም መንግስት በአንድ ወቅት የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ስንዴ በድጎማ ማቅረብ የጀመረበት ሁኔታ ቢኖርም በዘለቄታው ግን በዚህ ይቀጥላል የሚል አስተሳሰብ መያዝ የሌለበት መሆኑን አመልክተዋል።

እንደ አቶ አማከል ገለፃ ዳቦ አቅራቢዎች በሁለት ተከፍለው ሊታዩ የሚችሉ ናቸው። የመጀመሪያዎቹ መንግስት በአንድ ወቅት የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት በስንዴ አቅርቦት ትስስር ውስጥ በማስገባት የተደጎመ ዳቦ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ የተደረጉ ሲሆኑ ከዚህ ውጪ ያሉት ግን የድጎማ ስንዴን ስለማይወስዱ ዳቦን በፈለጉት ዋጋ የሚያቀርቡ ናቸው። በትስስሩ ውስጥ የገቡት የዳቦ ቤት በአሰራሩ አምነውበት መሆኑን የገለፁት አቶ አማከል መንግስት የሀገር ውስጥ ስንዴ አቅርቦት የተረጋጋ በሚሆንበት ወቅት የውጪ የስንዴ ግዢውን የሚቀንስበት ሁኔታ መኖሩን ገልፀውልናል።

ነጋዴዎቹ ከሰርን ቢሉም ነጋዴው እየከሰረ መሸጥ ስለሌለበት መድረኮች ተፈጥረው ውይይት ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ መኖሩንም አቶ አማከለ ገልጸውልናል። በነጋዴዎቹ ከሚገለፁት ቅሬታዎች መካከል አንደኛው መንግስት የዳቦ ተመኑን ሲያወጣ ታሳቢ ያደረገው የስንዴ ዋጋን ብቻ ሲሆን ይሁንና ከዚህ ውጭ ግን የእርሾና ተያያዥ ግብአቶች ዋጋም በየጊዜው እየናረ የመሄድ ጉዳይ ታሳቢ ያልተደረገ በመሆኑ ይህ ሁኔታ ለተጨማሪ ክስረት የዳረጋቸው መሆኑን ነጋዴዎቹ ተናግረዋል። አቶ አማከል በበኩላቸው በአጠቃላይ ነጋዴዎቹ ላቀረቡት ጥያቄ መንግስት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በመጀመሪያ ጥናት መደረግ ያለበት መሆኑን አመልክተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ በሚጠራው ሰልፍ ላይ 100ሺህ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

1 Comment

  1. Hewohat Amaran Le- madakem be keyesew stratagey meseret semonun Bademe genbar ymegagnw ye-ma eikelawy eize(commands) commander yeneberuten Letanal general Abebaw Tadesse ne- kehalafenet yabrerachew sehon. Lelochunem berkata Ye- Amara mekonenoch( officers) be- metekakat sem Ke-serawit eyekenese new. Abebaw kesamora ketelo teleku baleseltan neber. ahun hewohat ye- serawetun amerar bemulu kelay eseke tach be-tigregna tenagary asyezo bechachewn eyemeru -new.

Comments are closed.

Share