ተስፋ (ከዘላለም ገብሬ)

በሃሳብ ተኝተሽ
ሃሳቡን ጸንሰሽ
ጽንሱን አሳድገሽ

የሃሳብ ልጅ አርገሽ

እርግዝናው ሞቆሽ እናትነት ሰቶሽ

የእናትነት ፍቅርን ሃሳብ አስረክቦሽ

ጭንቅ ብሎሽ እርግዝናው ከብዶሽ

መራመድ አቅቶሽ

መውለጃሽ ሲቃረብ

ምጡ ሲጠናበሽ ጩኽትሽ በርትቶ

መውለድም ሲከብድሽ

ተወለድ! አልወለድም ክርክሩ ገጥሞሽ

የእናትነት ጥማት ልጅሽን ተጠምተሽ

የተስፋ ልጅ ይዘሽ ከቶ ማያገኙት

ወልደው የማያዩት ምጡንም አመጠው

በሃሳብ ተክዘው በጭንቀት ተጠበው

የተስፋ ልጅ ይዘው

ነገን ተስፋ አድርገው

በተስፋ ላይ ታዝለው

ተ…….ስ……ፋ…. እያሉ ሲያቆለጳጵሡት ሲያሞጋግሱት

እውነት ህይወት መስለሽ እንዲህ ያደረገሽ

የነገን ሰንቆ ዛሬ ህልም አስይቶሽ

ባዶነት መኖሩን ምኑንም ሳይነግርሽ

ልብሽን ወጥሮ አእምሮሽን ሰብሮ

በደስታ ፍሬ የዘርፍሬ አጭደሽ

በተስፋ ማእበል የህልም ጉዞ ሄደሽ

መቼም ላትመለሽ አስፍሮ አስኮብልሎሽ

በባዶ ሜዳ ላይ ይሄው አንጓሎ ጣለሽ !

ተስፋ `ያሉ ሚሉት ካንቺው ጋር ተጣብቶሽ

ከአንቺው ተወልዶ

አንቺን አስጨንቆ በምጥ አሰቃይቶ

የነገን ላትኖሪ በነገ ተስፋ ነገን አሳይቶሽ

ተስፋ

ይህ ጽሁፍ የተጻፈው ለሜሮን አባተ ለጻፈችው የግጥም ጽሁፍ መልስ ስለሆነ እሱዋን እንድጽፍ ስላደረገችኝ አመስግኑልኝ !

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሕገ መንግሥት ለውጥ - ለኢትዮጵያዊነት የሚያስፈልግ መሠረታዊ ጉዳይ - ኪዳኔ ዓለማየሁ
Share