ከማን.ዩናይትድ ጋር የተያያዙ 10 አነጋጋሪ የወሲብ ቅሌቶች

የሪያን ጊግስን ወሲባዊ ቅሌት የሚጠቁሙ መረጃዎች በተከታታይነት በመውጣት ላይ ናቸው፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት በብሪታኒያ ፓርላማ ውስጥ የመነጋገሪያ ርዕስ ለመሆን የቻለው ኢሞጋን ቶማስ ጋር ፈፅሟል በተባለው ወሲባዊ ግንኙነት ሳይሆን ስሙ በማንኛውም ሁኔታ እንዳይገለፅ በፍርድ ቤት እስከማሳገድ በመድረሱና አንዳንድ ሰዎችንም ለማስፈራራት በመሞከሩ ነበር፡፡ የሚስጢራዊው ፉትቦለር ስም በፓርላማው ከተጠራ በኋላ በርካታ ጋዜጦች የጊግስን ቅሌት በስፋት ዘግበውታል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው ከገዛ ወንድሙ ሚስት ጋር መማገጡ የተወራው፡፡ ሌሎች ከእሱ ጋር መማገጣቸውን የሚገልፁ ሴቶችም ተከስተዋል፡፡ እናም የጊግስ ጉዳይ ትልቅ የታብሎይድ ታሪክ ለመሆን ችሏል፡፡ ግን ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የተያያዙ ሌሎችም የወሲብ ቅሌቶች ተመዝግበዋል፡፡ በጣም አነጋጋሪ የሆኑት አስሩ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ቶማስ ዶቸሪ እና የፊዚዮው ሚስት፡-
ይህንን ታሪክ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ዛሬም ድረስ ባስታወሱት ቁጥር ይሸማቀቁበታል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ቶሚዶቸሪ ለአምስት ዓመታት ከቆየበት የአሰልጣኝነት ስራው በጁላይ 1977 ባይባረር ኖሮ ክለቡ በ1970ዎቹ እና በ1980ዎቹ የነበረውን የሊቨርፑልን ኃያልነት መረከብ ባልቻለ ነበር ይላሉ፡፡ በእርግጥም ቶማስ ዶቸሪ በክለቡ ኃላፊዎችም ሆነ በደጋፊዎቹ በኩል በእጅጉ የሚወደድ በመሆኑ በገዛ ቅሌቱ ባይወገድ ኖሮ ለተጨማሪ ረጅም ዓመታት በኦልድትራፎርዱ አለቅነቱ መቆየት በቻለም ነበር፡፡ ለጀፈሪ ከማን፣ዩናይትድ አሰልጣኝነት መባረር በዋነኝነት የተጠቀሰው ምክንያት ደግሞ የክለቡ ተጨዋቾች ሚስቶች በወቅቱ ዩናይትድ ሊቀመንበር ለነበሩት ሉዊስ ኤድዋርድስ የፃፉት ደብዳቤ ነው፡፡ በእርግጥም ዶቸሪ አንድ አሳፋሪ ቅሌት ፈፅሞ ነበር፡፡ ይኸው ሚስቱንና አራት ልጆቹን ትቶ የክለቡ የአካል ብቃት አሰልጣኝ ሚስት ከሆነች ሴት ቅልጥ ብሎ መክነፉ ነበር፡፡ ዶቸሪ ከፊዚዮው ሚስት ጋር ወሲባዊ ግንኙነት የፈጸመው ለ1977 ኤፍ.ኤ ዋንጫ ፍፃሜ ማን.ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጋር በተጫወተበት ዋዜማ ሲሆን ይህ ቅሌት አነጋጋሪ የሆነው ከማግስቱ ጀምሮ ነው፡፡ በመጨረሻም የክለቡ ተጨዋቾች ሚስቶች ለሊቀመንበሩ በፃፉት ማመልከቻ ዶቸሪ ከነቅሌቱ ከማን.ዩናይትድ ሊባረር ችሏል፡፡ በጣም የሚገርመው በወቅቱ የአሰልጣኙ ሚስት የሆነችው ሜሪ ዶቸሪ እሱን ከፈታች በኋላ ትዳር መስርታ እስካሁንም ድረስ ላለፉት 30 ዓመታት ከሁለተኛው ባለቤቷ ጋር የቆየች መሆኗ ነው፡፡ የቶማስ ዶቸሪ ቅሌት ግን ዛሬም ድረስ በአሳፋሪነቱ የሚጠቀስ ነው፡፡
2. ማርቲን ኤድዋርድስ እና የተሰበረው የመፀዳጃ ቤት በር
የማንቸስተር ዩናይትድ ሊቀመንበር የነበሩት ማርቲን ኤድዋርድስ እንደ እድለኛ ሰው ሲቆጠሩ ቆይተዋል፡፡ በወቅቱ በእሳቸው ቁጥጥር ስር የነበረውን የክለቡን አክሲዮን ለመሸጥ ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም፡፡ እናም በብራዚል እና በስዊዘርላንድ ውስጥ ራሳቸውን በሚያዝናኑበት ወቅት ከተለያዩ ዝነኛ ሴቶች አዳሪዎች ጋር ተኝተው ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ሴቶችም ‹‹የአያቴን ያህል ሽማግሌ ነው›› በማለት ቀልደውባቸዋል፡፡ ሰውዬው ይህንን ድርጊት የፈጸሙት በ1996 ቢሆንም ቅሌታቸው ይፋ የሆነው ግን በ2002 ማለትም ከ6 ዓመት በኋላ ነበር፡፡ ዕድለኛ የተባሉትም በዚሁ ነው፡፡ የማርቲን ኤድዋርድስ ወሲባዊ ቅሌት ዘግይቶም ቢሆን ይፋ የሆነው ደግሞ የሴቶች መኝታ ቤት የመፀዳጃ ቤት በርን ሰብረዋል በሚል ክስ የፖሊስ የመጥሪያ ወረቀት ከደረሳቸው በኋላ ነው፡፡ የኤድዋርድስ ወሲባዊ ቅሌት ይፋ ከሆነ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ማለትም በ2003 ማርቲን ኤድዋርድስ የማንቸስተር ዩናይትድን ቦርድ የለቀቁ ሲሆን በክለቡ ውስጥ የነበራቸውን አክሲዮን በ80 ሚሊዮን ፓውንድ ሸጠውታል፡፡
3. ሪያን ጊግስ እንደ ታይገር ውድስ
‹‹እኔ ይህንን ማመን አልችልም፣ ጊግስ እኮ ቤተሰባዊ ህይወት ያለው ሰው ነው›› ያለው የፉትቦለሩ ወኪል ሀሪ ስዌልስ ናቸው፡፡ ስዌልስ ይህንን አስተያየት የሰጡት ወሲባዊ ቅሌቱ እንዳይወጣና ስሙ እንዳይጠቀስ በፍርድ ቤት ያሳገደው ሰው ሪያን ጊግስ መሆኑ ይፋ ከሆነ በኋላ ነው፡፡ የሪያን ጊግስ ገበና እርቃኑን የቀረው ደግሞ ፉትቦለሩ ከገዛ ወንድሙ ሚስት ጋር ለስምንት ዓመታት የዘለቀ ምስጢራዊ ወሲባዊ ግንኙነት እንዳለው ከተገለፀ በኋላ ነው፡፡ ሌላዋ ሶስተኛ ሴትም ብቅ ብላለች፡፡ ለዚህም ነው አንዳንድ ሚዲያዎች የፉትቦለሩን ቅሌት ከጎልፉ ሚሊየነር ታይገር ውድስ ጋር የሚያነፃፅሩት፡፡ የሪን ጊግስ ስም ለመጀመሪያ ጊዜ በፓርላማ ውስጥ ከተጠራ በኋላ ቅሌቶቹ በተከታታይነት በመውጣት ላይ ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት የግል የህዝብ ግንኙነት ሠራተኛው /PR/ ከነበረችው ከሮሊን ስተንበር ጋር ወሲባዊ ግንኙነትም እንደነበረው ተገልጿል፡፡ በማንቸስተር ከተማ ‹‹የጊግስ ኮርነር›› (Giggsy Corner) የሚባልና ለፉትቦለሩ የሚሆኑ ሴቶች የሚወሰዱበት ቦታ እንዳለም እየተወራ ነው፡፡
4. ጆርጅ ቤስት እና ሚስ ወርልድ
በ1970ዎቹ ውስጥ የማንቸስተር ዩናይትድ ድንቅ ተጨዋች የነበረው ጆርድ ቤስት ሁለት ግል ክበቦችን አቋቁሞ ነበር፡፡ ስላክ አላይስ እና አስካርስ ወደተባሉት ክለቦች ከሚመጡት ቆነጃጅቶች ከአንዳንዶቹ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ይፈፅም እንደነበረም ተገልጿል፡፡ ከቤስት ጋር አንሶላ ተጋፋለች ተብላ ከምትጠረጠረው ሴት መካከል አንደኛዋ ደግሞ የዝነኛው ጠበቃ ጆርጅ ካርማን ሚስት ነበረች፡፡ ‹‹ጆርጅ ቤስት አንተ መጥፎ ሰው፣ ከሚስቴ ጋር መማገጥህን ደርሼበታለሁ›› የሚለውን ኃይለ ቃል ጠበቃው ለጆርጅ ቤስት መናገሩንም አንዳንድ ፕሬሶች በወቅቱ ገልፀውታል፡፡ ይህም ሆኖ ቤስት በእጅጉ የሚታወቅበት ቅሌት ሆኖ የተመዘገበው በወቅቱ በቁንጅና ‹‹ሚስ ወርልድ›› ተብላ ከተመረጠችው ማርጆሪ ዋላስ ጋር የፈፀመው ነው፡፡ ቆንጆዋ ሴት በወቅቱ ፎርሙላ ዋና ተብሎ የሚጠራው የመኪና እሽቅድምድም ተወዳዳሪ የሆነው ፒተር ሪብሰን እጮኛ ነበረች፡፡ ሁለቱ ዝነኞች የሚፈፅሙት ድርጊት ይፋ የሆነው ደግሞ ተጣልተው ወደ ለንደኑ ውድ ሌን የፖሊስ ጣቢያ ከመጡ በኋላ ነው፡፡ በወቅቱ ቤስት የዋላስን አፓርትማ ሰብሮ በመግባት 2,000.00 ፓውንድ የሚያወጡ ኮትና ጌጣጌጦችን በመዝረፍ ወንጀል ተከሶ ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ቤስት በዚሁ ወንጀል ምክንያት ፍርድ ቤት ከመቅረቡ ከአምስት ቀናት በፊት የቆንጆዋ እጮኛ ለደቡብ አፍሪካው ግራንድ ፕሪክስ ሲለማመድ በደረሰበት አደጋ ህይወቱ አልፏል፡፡ የጆርጅ ቤስት ቅሌት በወቅቱ በስፋት የመወያያ ርዕስ ለመሆን ችሎ ነበር፡፡
5. የዋይኒ ሩኒ፡- የወጣቱ ቅሌት
የአጥቂው ፀጉር በወጣትነት ዕድሜው መመለጡ አያስገርምም፡፡ ምክንያቱም ዋይኒ ሩኒ ከወጣትነት ዕድሜው ጀምሮ ማሳጅን የሚወድ በመሆኑ ነው፡፡ የኤቨርተን ተጨዋች በነበረበት ወቅት ፓርሎ ወደ ዲቫስ የተባለው የሊቨርፑል ማሳጅ ደምበኛ እንደነበር የሚነገርለት ሩኒ ለአንዲት ሴት የላከው መልዕክት አስገራሚ ነበር፡፡ ‹‹I shagged you on December 26. Loads of Love›› በሚል በዚህ መልዕክቱ አማካኝነት መግለፅ የፈለገው በዲሴምበር 26 በፈፀሙት ድርጊት ትልቅ እርካታ ተሰምቶት የነበረ መሆኑን ነው፡፡ ሩኒ ቀድሞውኑ ከሴቶች ጋር መማገጥ የሚወድ ነው፡፡ ከኮሊን ማክላፊን ጋር ቀለበት ካሰረ በኋላ ግን በተቻለው መጠን ጨዋ ለመሆን ሞክሯል፡፡ ይሁን እንጂ ባለፈው መስከረም ወር ይፋ የሆነው ሚስጢር የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎችን አንገት አስደፍቶ ነበር፡፡ ኮሊንሩኒ ነፍሰ ጡር በነበረችበት ወቅት አጥቂው 1200 ፓውንድ በመክፈል ከጄኒፈር ቶምፕሰን እና ከጓደኛዋ ሄለን ውድ ጋር የፈፀሙት የሶስትዮሽ ወሲባዊ ድርጊት ይፋ ከሆነ ሲሆን ሩኒ ለማስተባበል እንኳ አልሞከረም፡፡ በእርግጥ እንግሊዛዊው አጥቂ በአሁኑ ወቅት ከባለቤቱ ጋር ያለው የትዳር ህይወት ጤናማና በፍቅር የተሞላ ይመስላል፡፡ ወሲባዊ ቅሌቱ ግን መቼም ቢሆን የሚረሳ አይደለም፡፡
6. ሮናልዶ፣ አንደርሰን እና ብዚላዊቷ ሴት
‹‹ቴሌቪዥን በባህር ዛፍ ላይ ከፍ አድርጎ መስቀልና ኳስን እያስተካከሉ ወደ እሱ መምታት በእጅጉ የምደሰትበትና የምዝናናበት ነገር ነው›› ክርስቲያኖ ሮናልዶ ይህንን አስተያየት የሰጠው የማንቸስተር ዩናይትድ ኮከብ በነበረበት ጊዜ ሲሆን ከ2007 መስከረም በፊት ይህ ሮናልዶን እንደሚያዝናና ብቸኛው ነገር እንደነበር ይቆጠር ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ነው የፖርቹጋላዊው የክንፍ ተጨዋች ቅሌት ይፋ የሆነው፤ ሮናልዶ ሁለቱን የቡድን ጓደኞቹን አንደርሰንና ናኒን ቲሻየር በሚገኘው ቤቱ እንዲመጡ ይጋብዛቸዋል፡፡ በወቅቱ በግዙፍ ቤት ውስጥ አምስት ሴተኛ አዳሪዎች ነበሩ፡፡ ብራዚላዊቷ ሴተኛ አዳሪ ጁሊያና ባልትረቮች በወቅቱ ስለፈፀመችው ድርጊት ስትናገር ‹‹በናኒ ላይ ወሲባዊ እንቅስቃሴን አደረኩ፤ ከዚያም ከሮናልዶ ጋር ወሲብ ቀስቃሽ ዳንስ ደነስኩ፡፡ ከዚያም ከአንደርሰን ጋር ገደብ የሌለው ወሲባዊ ድርጊት ፈፀምኩ›› ብላለች፡፡ ብራዚላዊው የመሀል ሜዳ ተጨዋች አንደርሰን ከሮናልዶ መኖሪያ ቤት ውስጥ ያንን ድርጊት ከመፈፀሙ ከአንድ ዓመት በፊት ሲሆን ሆውተን ከተባለች ሞዴል ጋር በሽንት ቤት ውስጥ ወሲብ መፈፀሙን በፍንደቃ ይለፈልፍ እንደነበር ሞዴሏ ገልፃለች፡፡
7. ፈርጊ እና የማይነካው ጉልበት
ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከባለቤታቸው ካቲ ጋር የተዋወቁት ሁለቱም በአንድ የታይፕ ራይተር ፋብሪካ ውስጥ ይሰሩ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ እና ጥንዶቹ ለ45 ዓመታት በትዳር ህይወት በአንድ ላይ ቆይተዋል፡፡ የፈርጉሰን የትዳር ህይወት በእግርኳስ ዓለም ውስጥ ከታዩት ጠንካራ ትዳሮች ውስጥ የሚጠቀስ ቢሆንም በኦክቶበር 2002 አንዲት የ21 ዓመት የሶፍትዌር ቴክኒሽያን የተናገረችው ነገር የዩናይትድን ደጋፊዎች አስበርግጎ ነበር፡፡ ናዲያ አብርሃምስ ትባላለች፣ ቴክኒሽያኗ የምትለው ፈርጉሰን ወሲባዊ ትንኮሳ የፈፀሙባት መሆናቸውን ነው፡፡ ‹‹በኬፕ ታውን አካባቢ ከሌሊቱ በ8፡00 ሰዓት መኪናዬ ውስጥ እንዲገቡ የጋበዝኳቸው የእሳቸው መኪና የትራፊክ ግጭት ስላጋጠማት ነበር፡፡ እናም ከጎኔ በተቀመጡ ጊዜ ጉልበቴን በመደባበስ ወዳረፉበት የሆቴል ክፍል እንድመጣ ጋብዘውኛል፡፡›› ያለችው ናዲያ አብርሃምስ ፈርጉሰንን በወሲባዊ ትንኮሳ በመክሰስ አቤቱታዋን ያቀረበችው ለደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የሀገሪቱ ፖሊስ የቴክኒሻኗን ክስ ውድቅ አድርጎታል፡፡
8/ የፓርሞግራፊው ንጉስ፡- ድዋይት ዮርክ
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ድዋይት ዮርክ በኦገስት 1998 በወቅቱ ትልቅ በሚባል የ12.6 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ወደ ኦልድትራፎርድ በገባበት ወቅት የቡድኑ ደጋፊዎች ጉድ ተሰኝተው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አጥቂውና በቪላ ፓርክ የቡድን ጓደኛው የነበረው ማር ቦስኒሽ ከአራት ሴቶች ጋር የፈፀሙት ድርጊት በቪዲዮ ተቀርፆ ለህትመት የበቃው አጥቂው ወደ ዩናይትድ ከመጣ ከአንድ ወር በኋላ ነበር፡፡ የቪዲዮ ምስሉ የሚያሳየው በረኛው ከአንዲት ፀጉረ ወርቃማ ሴት ጋር ተያይዞ ሲላፋና አጥቂው ደግሞ ከጓደኛዋ ጋር ግልፅ ወሲብ ሲፈፅም ነበር፡፡ ይህ የቪዲዮ ምስል ድዋይት ዮርክን የመጀመሪያ ጥቂት ወራቶች የዩናይትድ ቆይታ ፈተና ውስጥ የከተተው ሲሆን በቀድሞ የፍቅር ጓደኛው ቪላ ድድሊ ጋር የተጋጨውም በዚሁ ምክንያት ነበር፡፡
9. ክሌበርሰን እና ታዳጊዋ ሙሽራ
በ2003 ክሊበርሰን ከአትሌቲኮ ፓራናኢንሲ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ሲመጣ ሁለት ነገሮች ገሀድ ሆነዋል፡፡ እነሱም ልክ እንደሱ በዚያኑ ወቅት የፈረመውን የክርስቲያኖ ሮናልዶን ያህል ጥሩ ብቃት እንደሌለውና ባለቤቱም ገና ታዳጊ መሆኗ ነበር፡፡ ብራዚላዊው ከፍቅረኛው ጋር የፍቅር ግንኙነት የጀመረው እሱ የ21 እሷ ደግሞ የ14 ዓመት ታዳጊ በነበረችበት ወቅት ነበር፡፡ በ2002 ወደ ሊድስ ሊያደርገው የነበረው ዝውውር የተቋረጠውም በወቅቱ 15 ዓመት የነበራት ጓደኛው ያለ ወላጆቿ ፈቃድ ከሀገሯ ለመውጣት የማትችል በመሆኑ ነበር፡፡ ጥንዶቹ ጋብቻቸውን የፈፀሙት ጃላን ዊሊያምስ ገና የ16 ዓመት ታዳጊ በነበረችበት ጊዜ ነው፡፡ ከ10 ወራት ታዳጊ በነበረችበት ጊዜ ነው፡፡ ከ10 ወራት በኋላም የመጀመሪያ ልጃቸውን ወለደች፡፡ ታዳጊዋ ምጧ የመጣው ባሏ በብላክበርን ላይ ግብ ባስቆጠረበት ወቅት ወደ ላይ በመዝለል ደስታዋን ስትገልፅ ነበር፡፡
10. ጆን ኢቫንስ እና የቁራጭ ስጋ ፓርቲ
የማንቸስተር ዩናይትዱ ተጨዋቾች በ2007 ያዘጋጁት የገና በዓል የሁሉም ፓርቲዎች ማሳረጊያ ነበር፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከዚያ ቀን ወዲህ ተጨዋቾቹ ፓርቲ እንደማይኖራቸው በመግለፃቸው ነው፡፡ ከፓርቲው በኋላ የጋዜጦችን አምድ ያጨናነቀው ጉዳይ ደግሞ ወጣቱ ጆኒ ኢቫንስ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል በሀሰት መወንጀሉ ነበር፡፡ በወቅቱ በፓርቲው ላይ በተጋባዥ እንግዳነት ከተጋበዙት ሴቶች መካከል አንደኛዋ እንዲህ ብላለች፡፡ ‹‹በጣም አስደንጋጭ ነገር ነበር… አንደኛው ተጨዋች እኔና ጓደኞቼን እየገፋፋ ወደ መኝታ ክፍል ሊወስደን በመሞከር ላይ ነበር…፤ አይሆንም ብለውም ሊሰማኝ አልቻለም፡፡ በጣም ጠጥቷል፡፡ ሌሎቹም ተጨዋቾች ተሳክረዋል፡፡ ከዚያም ተጨዋቹ እየገፈተረ ከዋናው የፓርቲው ቦታ ሊነጥለኝ ሲሞክር እያለቀስኩኝ ነበር፡፡ ተጨዋቾቹ ሴቶቹን እንደ ቁራጭ ሥጋ ነው የሚመለከቱት›› ብላ ነበር፡፡ ይህ ዜና በዴይሊ ሚረር ከወጣ በኋላ በስፋት አነጋጋሪ ሆኖ ቢቆይም በፓርቲው ላይ እንደተጠቀሰው አይነት ድርጊት ያለመፈፀሙን በመግለፅ በወቅቱ ክለቡ አስተባብሏል፡፡µ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‹‹የማሸነፍ አዕምሮ›› የዘንድሮው የማንቸስተር ጠንካራ ጎን ሆኗል
Share