ጎሳዬ በ እናቱ ሞት የተነሳ በአትላንታው እግር ኳስ ውድድር ፌስቲቫል ላይ አይዘፍንም

June 30, 2011

(ሊሊ ሞገስ) በ28ኛው የኢትዮጵያውን የ እግር ኳስ ውድድር ላይ በአትላንታ ከተማ ጁላይ 3 ከ ኤፍሬም ታምሩ ጋር በመሆን ሊያቀርበው በነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ እንደማይገኝ አዘጋጆቹ አስቀድመው ለሙዚቃው አፍቃሪው ተናግረዋል። ለዚህም እንደምክንያት ያቀረቡት ድምጻዊው እናቱን በሕይወት ማጣቱን ነው።
2 አልበሞችን ለብቻው ያቀረበው ጎሳዬ “ሳታማሃኝ ብላ” የተሰኘው የሙዚቃ አልበሙ የመጀመሪያው የሚመስላቸው በርካታ ናቸው። ሆኖም ከዚህ ቀደም ምንም በማይታወቅበት ዘመን በመብረቅ ሙዚቃ ቤት አማካኝነት ካሴት አውጥቶ የነበረ ቢሆንም አይደለም ካሴቱ ሊደመጥ ከተማ ላይ እንኳ ፖስተሩ አልታየም ነበር :: ከዛም ጎሳዬ ”ቴክ ፋይቭ ” የተሰኘ ካሴት ከነበዛወርቅ ጋር ሰርቶ ይህ ካሴት ላይ ያሉት ዘፈኖቹ ሕዝብ ጋር አደረሱት ::ከዛም በ 1994 አመተ ምህረት መጨረሻ ላይ ከአለማየሁ ሄርጶ ጋር ያወጡት ”ኢቫንጋዲ ‘ የተሰኘው አልበማቸው እጅግ ተወዳጅ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም::
ድምጻዊው ከዚህ ቀደም በሚኒሶታ የሙዚቃ ኮንሰርት ከአቢይ ላቀው ጋር እንደሚያቀርብ ፖስተር ተበትኖ ባለቀ ሰዓት “አያቴ በመሞታቸው አልዘፍንም” ብሏል በሚል ኮንሰርቱ መሰረዙ ይታወሳል። አሁን ግን በአትላንታው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ጎሳዬ ባይገኝም አዘጋጆቹ በሙሉቀን መለሰ ዘፈኖች እጅግ ተወዳጅነትን ባተረፈው ብዟየሁ ደምሴ ተክተውታል። በዚህም መሠረት ኤፍሬም ታምሩና ብዟየሁ ደምሴ አብረው ይዘፍናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Previous Story

ብሶት የወለደው – ዋንጫውን ወሰደው

በነመራ ዲንሣ
Next Story

On the Democratization Process

Go toTop