ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)
ፕሪሚየር ሊግ ከመሰረቱት ከለቦች ዘንድሮ ያሉት 3 ናቸው፡፡ 2ቱ ዋንጫውን ወስደዋል፡፡ ቡና ነበር የቀረው፡፡ ዛሬ 12 ሰዓት ላይ ዋንጫውን አነሳ፡፡ ተጨዋቾቹ በክፍት መኪና ሆነው ዋና ዋና ጎዳና ላያ ይዘዋወራሉ ተብሎ ነበር፡፡ ሁኔታዎች ስላልተመቹ አልተሳካም፡፡ ምሽት ላይ ቦሌ አካባቢ ህብር የባህል ምግብ ቤት ራት በልተው ከተጨፈረ በኋላ አሁን ከምሽቱ 5 ሰዓት ወደ ኢንተር ኮንቲኔንታል እየሄዱ ነው፡፡ በየመንገዱ፣ በየቤቱ እየተጨፈረ ነው፡፡
አዲስ ቡድን
በፕሚየር ሊግ ለ13 ዓመት 3 ቡድኖች ብቻ ነበሩ ዋንጫ ያገኙት ፡፡ ጊዮርጊስ 9 ፣ መብራትና ሀዋሳ እኩል 2 አግኝተዋል፡፡ 4ተኛው ቡድን ቡና ሆነ፡፡ አዲስ ሆኖም ተመዘገበ፡፡
እድሉ እድለኛ
የቡናው አምበል እድሉ ደረጀ እንደስሙ እድለኛ ነው፡፡ በፕሪሚያር ሊጉ ለቡና የመጀመሪያውን ዋንጫ አንስቷል፡፡ እድሉ ቡና ውስጥ ረጅም አመት የቆየ ተጫዋች ነው፡፡ ጨዋታው አንዳለቀ ራሱን ይዞ ሜዳ ላይ ቁጭ አለ፡፡ የ32 ዓመቱ እድሉ ደረጀ በሰው ኃይል አመራር ማኔጅመንት ዘንድሮ ይመረቃል፡፡
አዳነ ሽጉጤ
ተቀማጭነቱ በምስማር ተራ ያደረገው ቀንደኛው አስጨፋሪ አዳነ ሽጉጤ ከምስማር ተራ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጥቶ ወደ ትሪቡን መጥቷል፡፡ ሜዳ ላይ የጭቃ ሸርተቴ ሲያሳይ ነበር፡፡ ዳንሱም ልዩ ነበር፡፡ አዳነ የስታዲየሙ አድማቂ ነው፡፡
መዳኔ ከፍቶ ዘጋው
17 ቁጥር ለባሹ የቡናው አጥቂ መዳኔ ታደሰ ቡና የመጀመሪያውን ጨዋታ ከሲዳማ ቡና ጋር ይርጋለም ላይ ሲጋጠም የመጀመሪያውን ጎል ያስቆጠረው እሱ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ 2ተኛውንና የመዝጊያውን ጎል የስቆጠረው እሱ ነበር፡፡ መዳኔ መጀመሪያውንና መጨረሻው የሱ ግብ ሆኗል፡፡
ኮሮላ መኪና
የቡና ደጋፊ ማህበር ክለባችን ዋንጫ ከወሰደ ለአሰልጣኙ ልዩ ሽልማት እንሰጣለን ብለው ነበር ፡፡ አሁን እንደሰማሁት ሽልማቱ መኪና ሲሆን አይነቱም ኮሮላ ነው፡፡
እንባችን ታበሰ
ዛሬ የቡና ደጋፊ ወደ ስታዲየም ይዞ የመጣው ጥቅስ ‹‹ሁሉ በእርሱ ሆነ›› እና ‹‹ እንባችን ታበሰ›› የሚል ነው፡፡ ለ13 ዓመት የወረደው እንባ ዛሬ ታብሷል፡፡
መሀል ሜዳ
ቡና ዘንድሮ ለውጤቱ ማማር ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉት መሀል ሜዳ ያሉ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ በተለይ ዳዊት ፣መሱድና ምንያህል ይጠቀሳሉ፡፡
አንድ ነጥብ
ቡና 61 ጊዮርጊስ 60 ነጥብ ሆነው ጨረሱ፡፡ ልዩነቱ 1 ነጥብ ነች፡፡ በአንድ ነጥብ 1ኛ ሆኖ ጨረሰ፡፡
የተማረ የሰው ኃይል
ቡና ውስጥ ተጨዋቾቹ ትምርትም ከፍ ያሉ ናቸው፡፡ በረኛው ወንድወሰን ዲግሪ አለው፣ ተስፋዬ ቢያቋርጥመ የሕክምና ተማሪ ነው፣ እድሉ በማኔጅመንት ዘንድሮ ይመረቃል፣ አራዶምም አንደዚሁ ቡና ዋንጫ ብቻ ሳሆን ትምሀርትም አለ፡፡ ‹‹ እየተማርን ዋንጫ እንበላለን›› ‹‹ እየተጫወትንም እንማራልነ››
እድለኛ ፕሬዘዳንት
ቡና ዘንድሮ በቦርድ አመራሩ ለውጥ አድርጓል፡፡ የቦርድ ፕሬዘዳት አቶ ኤሊያስ ኡመር ተመርጠዋል፡፡ አዲሱ ፕሬዘዳንት እድለኛ ናቸው፡፡ እግራቸው እንደረገጠ ዋንጫ ተገኝቷል፡፡
ደጋፊ ማህበር
አዲሱ ደጋፊ ማህበር ብዙ አሰራር ለውጥ ለማድረግ በደጋፊው ውስጥ ንቅናቄ በመፍጠር ለተጫዋቾቹ ትጥቅ በማቅረብ ሞረል በመስጠት ከደጋፊው ጋር በመሆን ለዋጫው መገኘት ትልቅ ምክንያት ሀኗል፡፡
ከለጋር እስከ ዲሲ
ቡና ለዋንጫ መድረሱ ለገሃር ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ስታዲያም አንሰቶ እስከ ዋሸንግን ዲሲ የቡና ደጋፊና የቀድሞ ተጨዋቾ ጨዋታውን በሬዲዮና በቲቪ በመከታተል ድሉን አጣጥመውታል፡፡
ሰኔ 20
ዋንጫ በመገኘቱ ይህቺን ቀን አንረሳትም በማለት አንድ የቡና ደጋፊ ‹‹ ሰኔ 20 የቡና የድል ቀን›› በሚል ቀኑ እንዲከበርና በካላነደር እንዲገባልን ብሏል፡፡