(ፎቶ ከፋይል)
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ (መድረክ) ዛሬ ያካሄደውን 5ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ዶክተር ሞጋ ፋሪሰን
ሊቀመንበር አድርጎ በመምረጥ መጠናቀቁን የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ምንጮች ከአዲስ አበባ አስታወቁ። ፓርቲው ዛሬ በዝግ ባካሄደው አምስተኛ ጠቅላላ ጉባኤው 6 ምክትል ሊቀ መንበራትም በስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ ውስጥ ተመርጠዋል።
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ምክትል ሊቀ መንበርና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፤ ዶክተር መራራ ጉዲና ምክትል ሊቀ መንበርና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ፣ አቶ ገብሩ አስራት ምክትል ሊቀ መንበርና የውጭ ጉዳይ ሃላፊ፣ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ምክትል ሊቀ መንበርና የፋይናንስ ንብረት አሰተዳደር ጉዳይ ሃላፊ ሆነው ያለው ዘገባው በጠቅላላ ጉባኤው ማጠናቀቀቂያ ላይ አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዳለው በቀጣይ አንድ አመት ትልቁ ስራችን የፖለቲካው ምህዳር የተመቻቸ እንዲሆን ማድረግ ነው ብሏል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በመኢሕአድ ፓርቲ ውስጥ ያለው ውስጣዊ አለመግባባት እየጨመረ መሄዱን ኢሳት የተባለው የመጀመሪያው ነጻ የኢትዮጵያውያን ቴሌቭዥን ጣቢያ ዘግቧል።