May 10, 2011
8 mins read

ቶሮንቶ በበቃ ተጠመቀች፤ ከተለያዩ ማህበረሰብ የተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን የተሳካ ስብሰባ አካሄዱ

በተክለሚካኤል አበበ
Ecadforum – ቅዳሜ ሜይ 7 ቀን በካናዳ የንግድ ከተማ፡ ቶሮንቶ ከተለያዩ ማህበረሰብ የተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን ተናጋሪዎችና ተሳታፊዎች የነበሩበት የተሳካ የበቃ ንቅናቄ ስብሰባ ተካሄደ። ተጋባዥ እንግዶቹም አብሮ የመስራትና የጋራ ዓላማን የሚያሳይ የአቋም መግለጫ አወጡ። በዚህ ስብሰባ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦጋዴን የአፋርና የኦሮሞ ብሄረሰብ አባላትና ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም የተገኙ ሲሆን፡ በመጨረሻም፡ ኢትዮጵያ አንድ ነች፡ አንድነታችን ግን በተለያዩ ማህበረሰቦች የተገነባ አንድነት ነው፡ እንዲሁም በዚህች ኢትዮጵያ ውስጥ የሰውነት የተፈጥሮ መብታችንን አስቀድሞ ማስከበር ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው ሲሉ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

በስብሰባው የመጀመሪያው ተናጋሪ የነበሩት፡ ከታላቁ የአፋር ብሄረሰብ የወጡት አቶ አሎ አይደሂስ፡ ሕወሀት/ኢህአዴግ በማሳ ውስጥ እንደበቀልና፡ እህሎቹን እንደሚያቀጭጭ አንድ አላስፈላጊ ዛፍ ነው ሲሉ መስለውት፡ አንድ ላይ አይቀመጡም፡ አይወያዩም፡ ብሎ ያስቀመጠን ተቃዋሚዎች ዛሬ ግን ባንድ ላይ መሰብሰባችን እጅግ እንዳስደሰታቸውና ወደፊትም መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል። በመጨረሻም ይህ ዛፍ መርዘኛ ስለሆነና እህሎቹን ስላቀጨጫቸው ከስሩ ለመነቀልና በአገራችን ፍትህና ርትእ ለማስፈን አብረን መስራት እንዳለብን አሳስበው ንግራቸውን ደምድመዋል።

ሁለተኛው ተናጋሪ ከኦጋዴን ማህበረሰብ የወጡት አቶ መሀመድ ሀሰን፡ እድሜ ልካችንን በማይረቡ ነገሮች ስንጨቃጨቅ ከምንኖር ይልቅ፡ የቋንቋ አንድነት፡ የሀይማኖት አንድነት፡ የአስተሳሰብ አንድነት፡ ሰይሆን የ“የምክንያት ወይንም የአላማ አንድነት (Unity of Purpose)” አንድነት ፈጥረን፡ አገራችንን እያጠፋ ያለውን ስርአት ማስወገድ አለብን ብለዋል። ሕወሀት/ኢህአዴግ ላለፉት አመታት በተለይም በኦጋዴን አካባቢ ከፍተኛ የሆነ እልቂት ሲፈጽም ገና ለገና ተገንጣይ ቡድኖች ናቸው ብሎ በማሰብና በመፍራት፡ በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በኦጋዴን የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተቃውመን በአንድነት አለመውጣታችን እጅግ እንደጎዳን ገልጸው፡ አሁንም ወያኔ ለምእራባዊያን የሚሸጠውን የፈጠራ ፖለቲካ ተባብረን ካልደመሰስነው በስተቀር፡ ርስ በርሳችን ስንባላ ያቺ የምንወዳት አገር ልትጠፋ እንደምንችል አሳስቦ፡ የጋራ ዓላማ ይዘን እንድንንቀሳቀስ አሳስቧል።

ሶስተኛ ተናጋሪ የሆነው አቶ አበበ በለውም፡ አሁን የስራ ጊዜ ነው፡ ጠላቶቻችን እያንዳንዱን ሰዓት አፈናም ይሁን ዝርፊያ በስራ ያሳልፉታል፡ እኛ ግን እስካሁን ከወሬ ደረጃ እንዳላለፍን ገልጾ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያንዱ ብሄር ችግር የዚያ ብሄር ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ በማሳሰብ የአብሮ መስራትን አስፈላጊነት ገልጿል።

አራተኛው ተናጋሪ ወጣት ጃዋር መሀመድ ሲሆን፡ ወጣት ጃዋር፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲን በማስፈን፡ የመፈረካከስ አደጋን ለማቆም ህዝቡና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ማድረግ ስለሚገባቸው ነገሮች ተናግሯል። ጃዋር፡ አሁን ባለው ሁኔታ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ህዝቡን ቀድመው መሄድና ማስተባበር ካልቻሉ፡ ህዝቡ ራሱ ቀድሞ በመተባበርና አብሮ በመስራት፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የፍትህና ስርአት ለውጥ እንዲመጣ፡ እንዲተጋ አሳስቧል። አሁን ባለው ሁኔታ ፖለቲከኞች ደጋፊ እናጣለን በሚል ፍራቻ የተነሳ ተፈራርተውና ተራርቀው እንደሚገኙ ገልጾ፡ ነገር ግን በመተማመንና በመተባበር ለመስራት፡ የአንድነትም ይሁን የነጻነት አራማጆች፡ ጽንፈኛነታቸውን ትተው ወደመሀል በመምጣት ነገሮችን አስታርቀው የመሄድ ባህል እንዲያዳብሩ ግድ እንደሚል ተናግሯል።

በመጨረሻም አቶ ኦባንግ ከራሱም ልምድና ከአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ሰፊ ማብራሪያ አሰምቶ፡ ሁላችንም ነጻ ካልወጣን አንዳችንም ነጻ እንደማንወጣ፡ ከብሄራችንም በፊት ሰውነታችን መቅደም እንዳበት አሳስቦ የአብሮ መስራትን አስፈላጊነት አበክሮ ገልጿል። አቶ ኦባንግ ጠላታችን ይሄ ብሄር ወይንማ ያኛው ብሄር ሳይሆን፡ ስርአት እንደሆነ ገልጾ፡ ያንን ስርአት ለመጣል እንድንታገል አደራ ብሏል።

በመጨረሻም “አንድነት ሀይል ነው” በሚል መፈክር የተጀመረው ስብሰባ፡ አምስቱም ተናጋሪዎች በጋራ ባወጡት “አንድነት ሀይል ነው” እንዲሁም መለያየት በቃ መግለጫ ተጠናቋል። በዚህ ስብሰባ ላይ ከታየው የህዝብ ስብጥር በተጨማሪ፡ የስብሰባው አስተባባሪና የመድረክ መሪ አወያይዋ፡ ወይዘሮ ፋሲካ ወልደሰንበት አስደናቂና አስደሳች የአወያይ ሚና ተጫውታለች። ተመሳሳይ ስብሰባና የበቃ እንቅስቃሴ በሚቀጥለው ሳምንትም የሚቀጥል ሲሆን፡ ዶ/ር ወንድሙ መኮንን፡ ዶ/ር ቡሻ ታአና አቶ መስፍን ተፈራ ንግግር በቶሮንቶ እንደሚያደርጉ ታውቋል።

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop