April 22, 2013
2 mins read

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት በፖሊስ ተከቦ ስብሰባውን አከናወነ

UDJ Images

ፍኖተ ነፃነት

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ አቶ ትግስቱ አወሉ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገሩት የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በፓርቲው ስትራቴጂክ እቅድ መሰረትየአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በመጪው አመት መስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ላይ እንደሚያካሂድ አስረድተዋል፡፡ በፓርቲው ደንብ ለሊቀመንበሩ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበሩትን ኢ/ር ዘለቀ ረዲን በስራ አፈፃፀም ብቃት ማነስ ምክንያት አንስተው በቦታው አቶ ስዩም መንገሻን መተካታቸውን ለምክር ቤቱ አሳውቀዋል፡፡ ምክር ቤቱም ሹመቱን አፅድቋል፡፡

አቶ ትግስቱ ጨምረውም ባለፈው ረቡዕ በሰንደቅ ጋዜጣ ለአንድነት ፓርቲ አሉታዊ አመለካካት ባለቸው አካላት የወጣውን መሰረተ ቢስ ውንጀላና በፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል በነበሩት ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ በተሰጠው የሀሰት መረጃ ዙሪያ ኢንጅነር ዘለቀ በተገኙበትና ሀሳባቸውን በነፃነት በገለፁበት ሁኔታ ሰፊውይይት መደረጉን አብራርተዋል፡፡

ምክር ቤቱ በሰጠው ውሳኔ መሰረትም ነገ ሰኞ ሰንደቅ ጋዜጣ ያወጣውን ሀሰተኛ መረጃ የሚያስተካክል መግለጫ እንዲሰጥ ኢ/ር ዘለቀን በሚመለከትም ጉዳዩ ለብሔራዊ ዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲመራ መወሰኑን የምክር ቤቱ ጸሀፊ ገልፀዋል፡፡ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ቅዳሜ ሚያዝያ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ስብሰባ ባደረገበት ወቅት ከአስር የበለጡ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ዙሪያ ከበባና ቅኝት ሲያደርጉ እንደነበር የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኞች ዘግበዋል፡፡

1 Comment

  1. What is the party, ‘andenet’ is there for in the first place? When is the party starting the struggle? why don’t these people find some other job and leave the field for the real fighters?

Comments are closed.

Previous Story

እዉነተኛና ዘላቂ ግንባታ

man 2
Next Story

የማንቸስተር ዩናይትድ አስገራሚ አቋም (ሻምፒዮን ሆነ)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop