እዉነተኛና ዘላቂ ግንባታ

አንዱዓለም (ከሰዊስ-Switzerland)

Andualem19@yahoo.com

አሁን አሁን ደግሞ ከገዢዉ ፓርቲ ሰዎች ጋርም ይሁን ባምሳላቸዉ ከሰሩዋቸዉ ደጋፊዎቻቸዉ ጋር ላንድ አፍታም ቢሆን ትነሽ ንግግር ሲጅመር ጭራሽ ደንቆሮ ይመስል አላግባባ ያለ አዲሰ ችግር ከተፈጠረ ሰነበት አለ፤ ግንባታ፣ግንባታ፣ግድብ፣ግድብ….ወዘተ የሚለዉ አሰልቺ ዘፈን ነዉ::ይህ አባባሌ ምናልባት አሁን ሁሉንም ንገር አጣመዉ ምዉስድ ለሚችሉበት የገዢዉ ፓርቲ አባላት ወይም የተሳሳቱ ደጋፊዎች ጣት የሚያስቀስርብኝ ኢነደሚሆን አምናልሁ::መገንዘብ ያልቻሉት ትልቅ ነገር ግን በጭራሽ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ወይም በሰዉ ደረጃ ራሱ ስዉ ያልሆነ ስዉ በቀር አንድን መሰረተ ልማት የሚጠላ ይኖራል በሎ ማመን በጣም ከባድ ነዉ ያዉም ለዘመናት ሲናፈቅ የቆየዉ ትልቁ አባይ ቀርቶ።

ትለቁ ጥያቄ ሆኖ መልስ የጠፋለት ግን ዓባይን የሚያክል ትልቅ ግድብ፣የባቡር ሃዲድን የሚያክል ትልቅ እና እሰየሁ የሚያስብል ስራ ለመስራት የቆረጠ ስርአት ወይም መንግስት በጣም ትንሽ እና መሰረታዊ የሆነዉን የሰዉ መበት/ነጻነት ማክበር ምነዉ ይሄን ያህል ተቸገረ?የትኛዉስ ነዉ ብዙ ውጪና ድካም የሚጠይቀዉ?ይሄ ሁሉ ድካምና ሩጫ ለህዝብ ነዉ ከተባለ በቅድሚያ ያ የሚደከምለት ህዝብ፣ያ የልማቱ ተጠቃሚ ይሆናል የሚባልለት ህዝብ ደህንነቱ፣ሰላሙ፣በልቶ ማደሩ፣ቢያንስ እንደ ሰዉ መኖሩ መታወቅ የለበትም ወይ?በቅድሚያ አንድ አካል በሰላም መኖሩ ሲታወቅ አይደለም ወይ ለዛ አካል ሌላ አንድ ተጨማሪ ነገር ያስፈልገዋል የሚባለዉ?ጤናዉ የተስተካከለና ሁኔታዎች በወጉ የተሟሉለት ቡድን ሳይኖር የመጫወቻ ሜዳ ብቻዉን መገንባቱ ከፈረሱ ጋሪዉ አይደለም ወይ?እዉነት እንነጋገር ከተባለ “እመራሀለዉ ወይም ቆሜልሀለዉ”ከሚባልለት ህዝብ ጋር ቀላል የሆነችዋን ሰላም/ፍቅር መገንባት ከሌላዉ አድካሚና “የእርዳታ ያለህ እየተበለ“በዓለም ዙሪያ ከሚያስጮህ ስራ ጋር እንዴት ይሆን የሚነጻጸረዉ!?ዘመናትን አስቆጥረዉ እስከ አሁን በመዝለቅ የኢትዮጵያ ኩራት የሆኑት የአክሱም ሃዉልት፣የላሊበላ፣የጎንደር፣የሃረር፣የጅማ…ወዘተ የግንባታ ዉጤቶች እኮ“ የአይ ኤም ኤፍ“እርዳታ ሳያስፈልጋቸዉ በህዝብ ፍቅር እና ጽኑ አንድነት በቀላሉ የተገነቡ በመሆናቸዉ እነሆ ለዘመናት ዘልቀዉ ዛሬም ዉበት ሆነዉናል::ህዝብ በፍቅር ሲያዝና ቀላል የሆነዉ መሰረታዊ መብቱ ሲጠበቅ በእንብርክኩም ሄዶ ቢሆን የተባለዉን ለማድረግ አያመነታም፤ያዉም ኢትዮጵያዊ!!!ለዚህም ነዉ በፍቀርና በጽኑ አንድነት ላይ የተመሰረተ ግንባታ ዘላቂነቱ ለጥያቄ የማይቀርበዉ።ገንቢዉም ጠባቂዉም ህዝብ ነዉ።በገንዘብ/እርዳታ ላይ የተመሰረተዉ ግን ገንዘቡ ሲቆም ይቆማል ወይም ገንዘቡ በሚያመጣዉ መዘዝ ይናጋል።ስለዚህ መሰረታዊ እዉነት መናገር ወይም ማሳሰብ በፍጹም ጸረ ልማት አያስብልም!”የምን አየነ-ደረቅ መልሶ….”እንደሚባለዉ ካልሆነ በቀር!።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግብጽ በየአቅጫው ሩጫ ላይ ና - መሳይ መኮነን

“መጽደቁ ቀርቶ በቀጡ በኮነነኝ” እንደሚባለዉ የሚያሳዝነዉ ግን የበፊት ቁስሎች ሳይሽሩ፤ለዚችዉ ለምናወራት ትንሸ ግን መሠረታዊ ስለሆነች የሰዉ ልጅ መብት በመጮሃቸዉ ዘብጥያ የተወረወሩ ሳይወጡ፤በደል የፈጸሙ(ለይስሙላ እንኳ) ለፍርድ ሳይቀርቡ፤እስቲ ዛሬም በሰላም እንሞክር ብለዉ በገዛ ሃገራቸዉ ለመሰባሰብ የሚሞክሩ ድርጅቶችና የፖለቲካ ፓረቲዎች አዳራሽ ሲከለከሉና በደህንነት ሰዎች ተዋክበዉ ለእሥር እና ለዱላ ሲዳረጉ፤እምነት አልባ ተሁኖ ከ ቄሱም ከ ሼኩም ሳይስማሙ አሁን ደግሞ “ባእንቅርት ላይ….”እንዲሉ ዜጎችን ማፈናቀል እንደ አዲስ ስልት ተግባራዊ እየሆነ ነዉ። “ማፈናቀል”ከሚለዉ ይልቅ “ማተራመስ”ወይም ”ፈፅሞ እንዳይሰክን አርጎ መበጥበጥ”በሚለዉ ቢተካ ይቀላል ምከንያቱም ይኸዉ ተመለሱም ተብሎ ተረጋግቶ የመኖራቸዉ ጉዳይ አደጋ ላይ ወድቛል፤አብረዉ ከኖሩት ህዝብ ጋር ሆድና ጀርባ ሆነዉ ስለወደፊቱ ምንም ዋስትና የላቸዉም።እንዲህ ነዉ እነግዲህ “የህዝብን በጋራ ተፈቃቅሮና ተከባብሮ፣አንድነቱን ጠብቆ እንዲኖር የማድረግ ራዕይ!!!!”ወይስ እኔ/እኛ አልገባንም?!

ብዙ ብዙ የተባለላቸዉ የሟቹ ጠ/ሚር ራዕይስ ይሄ ነበረ ወይ?ወይስ ስማቸዉ ከመቃብር በላይ በጥሩ እንዳይነሳ ራዕያቸዉን ማበላሸት ተይዟል!?ማሽሟጠጤ አይደለም እመኑኝ፤ግራ ገባኝ እኮ ምን ለድረግ!የሚወራዉና የሚሠራዉ አንድ አልሆን ሲለኝ!አሁን እነግዲህ አጭር እና ግልጽ ነገር አለ፤ይኸዉም የጠፋዉን ሁሉ በማረም፣ከህዝብ ጋር በመታረቅ፣ይቅር ለመባባል በመዘጋጀት….ወዘተ “እሰየሁ!! ለካስ የሄ ነበር ራዕዩ!!”ብለን እነድናመሰግን መድረግ ይህ ካልሆነና አሁን በተያዘዉ መንገድ ለመጓዝ ከሆነ ግን “እናንተንም በተቀደደዉ ቦይ ይዟችሁ ይሂድ ብለን እንጸልይ” “የማሞን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም!!”ማለት ግን ብልህነት ከመሆኑም በላይ ለልጅ ልጅም ዕዳ አለማቆየት ነዉ!!!እንዲህ አይነቱን ክፉ ራዕይ ለማሳካት ከሆነ ግን ጊዜ ይፍጅ እንጂ እንኳን መልዐክ ሰይጣንም ፈጽሞ አያሳካዉም!እንኳን ኢትዮጵያን የመሰለ ያአምላክ ጥበቃ የበዛላት ሀገር ቀርቶ!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቀጥ ብሎ ለመቆም የለገማችሁ የዘመኑ ካህናት ሆይ! ሰማእታት አባቶቻችን ከሰማይ ቤት እያዘኑ ነው!

ይልቅ ጊዜ ሳየረፍድ ወደ ልቦናችን እንድንመለስ ጥረት ማድረግ ነዉ።የቋጠርናትንም በወጉ እንድንበላ ሰላሟ የተጠበቀ፣የዜጎቿ ነጻነት የተረጋገጠባት፣ጥሎ ለመሰደድ ሳይሆን ቸኩሎ በናፍቆት የሚሮጥባት፣በቀንም ሆነ በምሽት ያለ ፍርሃት የሚኬድባት፣አንድነቷ የተረጋገጠ የጋራ ሀገር እንድትኖረን ቆም ብሎ ማሰብ ግድ ይላል።መንግስት አስተዳድርሃለዉ የሚለዉን ዜጋ ነጻነት እና መሰረታዊ መብት ማክበር፤ዜጎችም መንግስት የኔ ነዉ ብለዉ በነጻነት እና በኩራት መንቀሳቀሳቸዉ ለየትኛዉም ዓይነት ዘላቂ እና እዉነተኛ ግንባታ የማይናጋ መሠረት ነዉ።ይህ ሳይሆን የሚሮጥለት የድንጋይና የብረት ግንባታ ግን አንድ ድግሥ እስከሚያልፍ ከሚደረግ ጊዜያዊ ያዳራሽ ጌጥነት አያልፍም።

ልቦና ይስጠን!!እግዚአብሔር ኢትዮጵያንም ህዝቧንም የባርክ!!!

1 Comment

  1. betam tasazignalesh tsufun kejemru indalanebew tedergiyalehu……ginbata ketenakem min liwodes indehone silalgebagn…..yihene yetsafewun sew yemayreba poletikegna biyewalehu chaw

Comments are closed.

Share