ድብርትን (Depression) ለመዋጋት ፍቅርን ማሳደድ

January 1, 2013
9 mins read

ፍቅር የድብርት ጥሩ መድኃኒት ነው፡፡ ፍቅርን ማጣጣም ያልቻሉ ሰዎች በድብርት (ዲፕሬሽን) የመጠቃት እድላቸው የሰፋ ነው፡፡ bአለን ማክራዝ የተባሉ የስነ ልቦና ባለሙያ እንደፃፉት ኦክስጅን ለሰውነታችን የሚያስፈልገውን ያህል ፍቅር ደግሞ ለአዕምሯችን ወሳኝ ነው፡፡ ይህንን እውነት ሊቀይር የሚችል አንድም ነገር የለም፡፡ ፍቅርን በአግባቡ ባጣጣምነው ቁጥር አካላችን፣ አልፎ ተርፎም ስሜታችን የበለጠ ጤነኛነት ይሰማዋል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ከፍቅር በሸሸን ቁጥር መረጋጋት ይሳነናል፡፡ ፍቅርን የማያውቁም ሆነ በፍቅር ህይወታቸው ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች በህይወታቸው ድብርት ሲጫጫናቸው የመመልከት አጋጣሚው ሰፊ ነው፡፡ ‹‹የብዙ ሰዎች ድብርት ዋነኛው መንስኤ ፍቅር ማጣት ነው›› የሚሉት ባለሙያው አለን ‹‹ድብርትን መዋጋት ከፈለግን ፍቅርን ካለበት ማሳደድና ማጣጣም ነው›› ይላሉ፡፡
በድብርት ከተጠቁ ሰዎች አብዛኞቹ ራሳቸውን አይወዱም፡፡ አለፍ ሲሉም ሰዎች አይወዱንም ብለው ያስባሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ግለኛ አመለካከት የሚያጠቃቸው፣ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን የማይሞክሩና ፍቅርን የራሳቸው ለማድረግ የሚረዱ መንገዶችን ለመማር የማይጥሩ ናቸው፡፡ ፍቅር በአጋጣሚ የሚገኝ ነው ሲባል የሚሰሙ ሰዎች ቁጭ ብለው ፍቅርን እቤታቸው አንኳኩቶ እስኪመጣ ሲጠባበቁ ድብርት በላያቸው ላይ ይሰለጥናል፡፡  ፍቅር እንደሚባለው በአጋጣሚ የሚገኝ ሳይሆን የአፍቃሪውን ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡ አብዛኞቻችን የተለመደውን አመለካከት ተቀብለናል፡፡ ፍቅር በሰማይ ላይ የሚያንሳፍፈን እንደሆነ አምነናል፡፡ በዚህ እምነት የተጠቁ ሰዎች ፍቅርን ሲጀምሩ የተለየ ሁኔታ ሲገጥማቸው ድብርት ውስጥ ይገባሉ፡፡
ፍቅር ሲጀመር የሚገጥሙን መሰናክሎች በወሬ ከምንሰማው ሲለዩብን በቶሎ ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ በህሊናችን የተቀረፀው የፍቅር ስዕል የተሳሳተ መሆኑን ሳናውቅ ጓደኛችን የፈለገውን እንዲያደርግ ማስገደድ እንጀምራለን፡፡ ያኔ ድብርት ከነኮተቱ ጠቅልሎ ቤታችን ይሰነብታል፤ ላያችን ላይ ይሰፍራል፡፡ ከድብርት መሸሽ የፈለገ ሰው የፍቅር ስዕሉን ማስተካከል ግድ ይለዋል፡፡ በህይወታችን ማፍቀርንም ሆነ መፈቀርን ማጣጣም ከፈለግን የሚከተሉትን ስትራቴጂዎች መጠቀም ጠቃሚ ነው፡፡
1. ፍቅር የምትማረው ጥበብ መሆኑን ተገንዘብ፡-
ፍቅር ዝም ብሎ ስሜት ወይም የሆርሞኖች ጥምረት ውጤት ሳይሆን ጥበብ ነው፡፡ የፍቅርን ጥበብ ልትማረው ካልቻልክ በእርግጠኝነት የድብርት ተጠቂ ትሆናለህ፡፡ ጥበብን ካልተማርክ ከፍቅረኛህ ጋር የጠበቀ ግንኙነት መፍጠር አትችልም፡፡ ምክንያቱም የሚገጥሙህን የፍቅር ፈተናዎች ማለፍ ያቅትሃል፡፡
2. ጥሩ የመግባባት ችሎታ ማዳበር፡-
ጥሩ የመግባባት ችሎታ ከፍቅረኞቻችን ጋር የሚኖረንን ግንኙነት የሚፈጥሩ ሰዎች እርስ በእርሳቸው ስለሚተዋወቁና ስለሚግባቡ በድብርት የመጠቃት እድላቸው ጠባብ ይሆናል፡፡ ጥንዶች ምንም ያህል ጠንካራ ቅርርብ ሲፈጥሩ በመሀላቸው ልዩነት መኖሩ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ግንኙነታቸው በአግባቡ ከቀጠለ በጊዜ ሂደት ልዩነት ብልህ ሰዎች ልዩነታቸውን በመነጋገር ለማጥበብ ይችላሉ፡፡ ይህን ማድረግ የሚችሉት የፍቅረኛቸውን ባህሪይ በማጥናትና ራሳቸውን ለፍቅረኛቸው ግልፅ በማድረግ ነው፡፡ ልዩነቶቹ እንዲታወቁ ከፍቅረኞች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ በግልፅ በመነጋገር የጋራ አቋም ላይ ለመድረስ መጣር ያስፈልጋል፡፡
3. ለፍቅረኞች ትኩረት መስጠት፡-
ፍቅረኛችን ለእኛ የሚሆኑልን ወይም ለራሳችን የምናገኘው ጥቅም ላይ ከማተኮር ይልቅ የእሱ/ሷን ፍላጎት ለማወቅ ቅድሚያ እንስጥ፡፡ የፍቅር ተጓዳኛችንን በማጥናት የሚፈልጉት ምን እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ በምንገኝበት ምስቅልቅል ዓለም ውስጥ የሰዎችን የልብ ፍላጎት ለማወቅ ልዩ ችሎታ ይጠይቃል፡፡ የጓደኛን ፍላጎት ለማሟላት በምንጥርበት ወቅት ማንነታችንን ላለመርሳት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
4. ሌሎችን ለመርዳት የተዘጋጀን እንሁን
ድብርት ሰዎች ስለ ራሳቸው ብቻ እንዲያስቡ ስለሚያደርጋቸው ሌሎችን ማፍቀር እንዲያቅት ያደርጋል፡፡ ለሌሎች ትኩረት ሰጥተን ፍላጎታቸውን ማሟላት ከቻልን ፍቅርን ማጣጣም ያስችለናል፡፡
5. የማይጣጣሙ እውነታዎችን አቻችለን መኖር፡-
የፍቅረኛችንን ማንነት እንደ ራሳችን ቆጥረን ልንቀበለው ይገባል፡፡ ምን እንደሚፈልጉና ምን እንደሚሉ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ድብርት የሚያጠቃቸው ሰዎች የሌሎችን ስሜት የማይረዱና ራሳቸውን ብቻ የሚያዳምጡ ናቸው፡፡
6. ‹‹አይቻልም›› የሚል የውስጥ ስሜትን ታገሉ፡-
ሰዎች ሳይቀበሉን ስሜታችን በጣም የሚጎዳ ከሆነ ድብርት ውስጥ እንዳለን ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ በራሱ የማይተማመን ሰው የፍቅር ግንኙነቱ ላይ ችግር ከመፍጠሩም በላይ በማንነቱ ላይም ጥያቄ ያስነሳል፡፡ እንደዚህ የሚሰማን ከሆነ በእርግጥም የስነ ልቦና ህክምና ያስፈልገናል፡፡ ከፍቅረኛችን ጋር አለመስማማታችን የፈጠረብን ያለመፈላለግ ስሜት ከውስጣችን የፈለቀ እንጂ ውጫዊ አይደለም፡፡ ፍቅረኛ ለመያዝ ብቃት የለንም ብለን ስናስብ ድብርት ስራውን ጀምሯል ማለት ነው፡፡ ከውስጥ የሚሰማን ድምፅ ጠንካራ ቢሆንም እውነት አለመሆኑን ሁላችንም ማወቅ ይገባናል፡፡ ለሚሰማዎት ድምፅ ‹‹በርግጥ የተናቅኩ አይደለሁም፤ ከፍቅረኛ ዬ ጋር መጣላቴ የብቃት ችግር ሳይሆን በሰራሁት ስህተት ነው›› የሚል ምላሽ ይስጡ፡፡ ‹‹ፍቅሬ ያልሰመረው እኔ ብቁ ባለመሆኔ ሳይሆን ስህተት በመስራቴ በመሆኑ ለወደፊት እረሳዋለሁ›› በማለት ለራስዎ ቃል ይግቡ፤ ከመጀመሪያው የፍቅር ስህተት በመማር ነገሮችን ካስተካከሉ የሚፈልጉትን የተሳካ ፍቅር እንደ አዲስ መመስረት ይችላሉ፡፡ S

Previous Story

ትላንት ዋልድባ ታረሰ፣ ዛሬ የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሊፈርስ ነው፣ ነገስ ?

Next Story

‹‹ስሜቴን መግለፅ የምችለው በምሰራው ዜማ ነው›› (ቃለምልልስ ከድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ጋር)

Latest from Blog

እስክንድርን ለማውገዝ በፋኖ ስም የወጣ የመረጃ ቲቪ መግለጫ – መስፍን አረጋ

“በአራቱ ግዛቶች ያሉ የአማራ ፋኖዎች የጋራ አደረጃጀት እየመሰረቱ መሆኑ ይታወቃል” እያሉ፣ “ከአማራ ፋኖ በጎጃም፣ ከአማራ ፋኖ በጎንደር፣ ከአማራ ፋኖ በሸዋና ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ የጋራ መግለጫ” ማለትን ምን ይሉታል? ገና ያልተመሰረተ የጋራ ድርጀት የጋራ መግለጫ እንዴት ያወጣል? መግለጫው በጋራ ወጥቶ ከሆነስ፣ መግለጫውን በጋራ አወጡት የተባሉት ፋኖወች አዛዦች ስማቸውን በመግለጫው ሥር ያልዘረዘሩት ማንን ፈርተው ነው? ባለቤቱ ሾላ በድፍን የሆነ መግለጫ

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop