ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዬ ቅርጽና ይዘት የነበራቸው የእርስ በርስና ድንበር ዘለል ጦርነቶችን በየዘመናቱ አካሂዳለች፡፡ ኢትዮጵያ ይበልጥ የምትታወቀውም በዚሁ በአውዳሚ የጦርነት ባህል ነው፡፡ ይህ አላግባብ የምንኮፈስበት የጦርነት ባህል ባይኖርና ወደልማት ፊታችንን ብናዞር ኖሮ ይሄኔ የት በደረስን ነበር – እነማሌዥያንና ሲንጋፖርን ማሰብ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን በየክልልና በየጎጥ ተቧድነን በቢሊዮኖችና ትሪሊዮኖች በሚገመት ገንዘብ ሀብትና ንብረት የምናወድም በሚሊዮኖች የምንቆጠር ዜጎች ወደዬአቅላችን ብንመለስ ርሀብንና ድህነትን ታሪክ ባደረግን ነበር፡፡ ቁጥር ብቻ፡፡ 130 ሚሊዮን በአፍዝ አደንግዝ የተተበተበ ዜጋ በመከኑ አእምሮዎች እየተመራ የራሱን የመቀበሪያ ጉድጓድ ሲቆፍር ይውላል፤ ያድራልም፡፡ ይህም የሚያኮራ ሆኖ “ለአንድ ሽህ ዓመት ቢዋጉን አያሸንፉንም” እየተባለ በመሪ ተብዬው ጉራ ይነዛል፡፡ አሣፋሪ መሪ ከአሣፋሪ ሀገራዊ ፖለቲካዊ መቼት ጋር፡፡
ከ1967 የደርግ መንግሥት መባቻ ጀምሮ እስከ መውደቂያው 1983 ድረስ ጥርዥ ብርዥ የሚሉ የእርስ በርስ ጦርነቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከ1969 እስከ 1970 ደግሞ ከጎረቤት ሀገር የዚያድባሬዋ ሶማሊያ ጋር ሀገራችን ተዋግታ ጦርነቱን በድል አጠናቃለች፡፡
የኦሮሙማው መንግሥት በአቢይ አህመድ ተወክሎ የአራት ኪሎን መንበረ ሥልጣን ከተቆጣጠረ ወዲህ ግን በሀገራችን የእርስ በርስ ጦርነት ተወግዶ መታየት የጀመረው በዓይነቱ ልዩ የሆነና ዓለማችን አጋጥሟት የማታውቀው አዲስ የጦርነት ሥልት ነው፡፡ ይህ በዓይነቱ አዲስ የሆነ ጦርነት ከ2010ዓ.ም በፊት በየትኛውም የዓለም ሀገር ተከስቶ ስለማያውቅ ስም ለመስጠትም የሚቻል አይደለም፡፡ በተፈጥሮው አፍራሽና አውዳሚ የሆነው ጦርነት ዓይነቱና መጠኑ ቢለያይም አሁን በሀገራችን የሚገኘው ግን ተነጋግረንበትና ተስማምተን አዲስ ስያሜ ካልሰጠነው በስተቀር በአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ውስጥ ስለታዬ ብቻ በተለመደው አጠራር “በወንድማማቾች መካከል የሚካሄድ የእርስ በርስ ጦርነት” ብንል ለከፍተኛ ስህተት እንዳረጋለን፡፡ ለምን?
Let me entertain code shifting and use English for some time. What is civil war? Civil war is, “a war between organized groups within the same state. The aim of one side may be to take control of the country or a region, to achieve independence for a region, or to change government policies.” (Source: internet)
Now, you can see the purpose of Ormuma’s fighting with the partially armed or non-armed entire population of the Amara irrespective of their age, sex, residence, etc. The war imposed by Oromuma upon the Amara people is clearly GENOCIDE, not as such a civil war based on a need to ‘control a region, or achieve independence for a region, or change government policies.’ And as a matter of fact, the term genocide is not even alludingly mentioned in the definition of a civil war stated here above. Therefore, the mere interest of the owner of current `Ethiopia`, Oromuma, is massacring all the Amaras wherever they might be found, in or out of the region they are supposed to be confined. I hope I am clear.
ስለርስ በርስ ጦርነት ከፍ ሲል የተቀመጠው ብያኔ ወዳማርኛ ሲመለስ፤ “የእርስ በርስ ጦርነት ማለት የጦር መሣሪያ በታጠቁ የአንድ ሀገር ተቃራኒ ኃይላት መካከል የሚካሄድ ጦርነት ሲሆን ዓላማውም አንደኛው ወይ ሌላኛው የሀገርን ወይም የክልልን ሥልጣን ለመቆጣጠር፣ ለአንድ ክልል የግዛት ነፃነትን ለማስገኘት ወይም የመንግሥትን ፖሊሲዎች ለማስቀየር ነው፡፡” የኦሮሙማ ፍላጎት ደግሞ ከነዚህ ከተጠቀሱት አንዱም አይደለም፡፡
ውድ አንባቢያን በተለይም በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት እንዳለ የምታምኑ የዋሃን – አሁን ምን ተረዳችሁ? በኢትዮጵያ በእውኑ የእርስ በርስ ጦርነት አለ? መልሱ የለም ነው፡፡ ታዲያ ምንድን ነው ያለው?
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዬው አክራሪ ኦሮሞዎች በያዙት የኢትዮጵያ ታንክና ባንክ አምርረው የሚጠሉትን እጅግ አነሰ ቢባል ከ60 ሚሊዮን በታች የማይገመተውን አማራ የሚባል ነገድ ገድሎ በመጨረስ ሀገሪቱን አማራ-አልባና ሌላውን ነገድ እነሱ በሚፈልጉት መንገድ -(በሞጋሣ?)- ለውጠው የነሱ ታዛዥ ባርያ ማድረግ ነው፡፡ ይህን ሥራ ለመሥራት ደግሞ ብዙ ዓመታትን ፈጅቷል፡፡ ቅድመ ዝግጅቱ የጀመረው በቅኝ ግዛት ዘመን አካባቢ መሆኑም በስፋት ይነገራል፡፡ በተለይ ከመቶ ዓመታት በፊት ዐድዋ ላይ በተደረገው ጦርነት ነጮች ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቁሮች በመሸነፋቸው ሳቢያ አማሮች ቁርሾ ተይዞባቸው ለዚህ የዕልቂት ድግስ እንደተዳረጉ ታሪክ ይመሰክራል፡፡ ለዚያም ሲባል አማራን በሚመለከት በፈጠራ የተፈበረኩ የጥላቻ ትርክቶች በትግሬውና በኦሮሞው ወጣት አእምሮ ውስጥ ካለውድ በግዱ ሲጫን ባዥቷል፡፡ የቅጥየለሹ የጥላቻ ስብከት በየትግሬና ኦሮሞው ጆሮ ሲያቃጭል ቆይቶ በመጨረሻው አማራ ከእንስሳትም ባነሰ እንዲታይና የዱሮ ዐፅሙና የአሁን አስሬኑ ሳይቀር በእሳት እንዲቃጠል እየተደረገ የአእምሮ ህሙማን ዘረኞች ጮቤ መርገጫ ትዕይንት ሆኗል፡፡ ይህ የሚጠቁመው ታዲያ አማራ መሞቱ ብቻ ሳይሆን ሞቶም ሬሣውን በማንገላታት የደስታ ምንጭ ማድረግን ጭምር ነው፡፡ በዚያ ላይ ወንድ ከሴት ሳይሉ መድፈር፣ ሀብት ንብረቱን መቀማትና ማቃጠል፣ ቤት ንብረቱን ማፍረስ ወይ መውረስ፣ የአማራነት መታወቂያ የያዘን እያፈሱ ካለምግብና ካለህክምና ከዚያም በዘለለ እየደበደቡና እያሰቃዩ እሥር ቤቶችን መሙላት፣ አዲስ አበባን እንዳይረግጣት መከልከል፣ ህክምና እንዳያገኝ መንገዶችን መዝጋት፣ እህልና ሸቀጦችን ማሳጣትና በርሀብ መፍጀት፣ ከትምህርትና ከሥልጣኔ በረከቶች ማገድ፣ ተላላፊ የአባለዘርና የኢ-አባለዘር በሽታዎችን ማዛመትና የአማራን ዘር ማንዘር መጨረስ፣ ደስታውን መቀማት … ይህ ሁሉ ከሃይማኖትም ከሰብኣዊነትም ከሀገር ልጅነትም፣ ከኅሊናም፣ ከባህልና ወግም ያፈነገጠ ዕኩይ ድርጊት ሁሉ የሚፈጸመው ታዲያ በመንግሥታዊ መመርያ ተደግፎ ነው፡፡ አማራን መግደል ያሾማል፤ ያሸልማል፡፡ አማራን መጥላትና ማዋረድ በ“ፌዴራል” ደረጃ ያሾማል፤ ያሸልማል፡፡ እውነቱ ይሄው ነው፡፡
አንድ ኦሮሞ ዶክተር ከሽመልስ አብዲሣ ኮርጆ የተናገረውን እናስታውስ፡-
“አማራ ከ20 እና 30 ሚሊዮን አይበልጥም፡፡ ይህን ቁጥር ወደ 20 ሽህና ሁለት ሽህ አውርደን ህዳጣን በማድረግ ባርያ እናደርገዋለን፡፡ እንደሱርማና አሪ ጎሣ ምንም ተፅዕኖ ወደማይኖረው የminority ዝቅተኛ ደረጃ በማውረድ ፀጥ ረጭ አድርገን እንገዛዋለን፡፡ ” (በትክክል ባልጠቅስ ይቅርታ፡፡)
አማራ ግን የተዞረበት አይታወቅም – በፀጥታው ጸንቷል፡፡ እየደረሰበት ያለውን ግፍና መከራ የተለማመደው ይመስላል፤ የዕብዶቹን ጭካኔም ማመን የፈቀደ አይመስልም፡፡ ትንሽ ሰው ትልቅን ሰው ከሚያሸንፍበት አንዱ ዘዴ ለነገሮች ክብደት ሰጥቶ ያለማየት ጣጣ ነው – አንድን የፈጠጠ እውነት ማመን ያለመቻል ሥነ ልቦናዊ ተግዳሮት አማራን ሳይጠናወተው አልቀረም – በፈረንጅኛው disbelief ይሉታል፡፡ እየተፈጸመበት ያለው ዕልቂት ያልገባው አብዛኛው አማራ ከያለበት እየተለቀመ ሲገደልና ሲፈናቀል በዝምታው ረግቷል፤ የመታረጃ ተራው እስኪደርስ ከገዳዮቹ ጋር አሼሼ ገዳሜ ባዩ አማራም እንደዚሁ በሚያስገርም ሁኔታ ብዙ ነው፡፡ ምን እስኪሆን እንደሚጠብቅም አንድዬ ይወቀው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ ለአማራ ነፃነት ብለው በረሃ የወረዱት ራሣቸው የነካቸው ሳይታወቅ እርስ በርስ እየተፈጃጁ የነፃነት ትግሉ ላይ ቀዝቃዛ ውኃ እየከለሱበት ሲታይ የዚህ ሕዝብ አበሣ እንዳላለቀ መረዳት አይከብድም፤ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ይባላልና አማራ ጠላቶቹ እስኪታዘቡትና የአማራን ተፈጥሯዊ ማንነትና ምንነት እስኪታዘቡ ድረስ እየሣቁ እየተሣለቁበት በዚህ መልክ ራሱን በራሱ እየበላ ከቀጠለ የነጻነት ጊዜ ባይቀርም መዘግየቱ ግን የሚጠበቅ ነው፡፡ በ”በሬው ሳይገዛ ሌባው በረት ሞላ” ዓይነት የሥልጣንና የዝና ሽሚያ የተለከፉ ብዙ የፋኖ አመራሮች በሚያደርጉት የውስጥ ፍትጊያና መጨራረስ ስንት ጀግና አዋጊዎችና አመራሮች ወደማይቀረው ተሸኙ – ሁሉም መሄዱ ለማይቀረው፡፡ ያሳዝናል፡፡ በሥጋዊ ፍላጎቶች የተተበተበ ሰው በመሠረቱ ለነፃነት ትግል ብሎ ከቤቱ ሊወጣ አይገባም፡፡ ነፃነት ብዙ መስዋዕትነትን ትጠይቃለለች – አንዱ ብኅትውና ነው – በአብርሃም ማስሎኣዊ አገላለጽ self-actualization ላይ መድረስና ስለሌሎች ሕይወትን ቤዛ ማድረግ፡፡ በዕውቀትና በጥበብ ያልዳበረ ለሌሎች መሞትን የባሕርይ ገንዘቡ ያላደረገ የነፃነት ታጋይ ሠፈሩን ለቅቆ ባይሄድ ይሻለዋል፡፡ ይህ ስምና ዝና የሚሉት ጣጣ ትልቁን ዳቦ ሊጥ ያደርጋል፡፡ እንደአገኘሁና ተመስገን ከመሆን አድነኝ ብለን መጸለይ በሚገባን ሰዓት ለሆዳችን ብለን – ማንም እንሁን ማን – ከአማራ ገዳዮች ጋር መቆም ኃጢኣትም ወንጀልም ቅሌትም ነው፡፡ እነተመስገን ማይማን አጋሰሶች ስለሆኑ ብዙም ላይፈረድባቸው ይችላል፤ ለነፃነት ትግል በረሃ ወጥቶ ለሥጋ ፍላጎቶች መንበርከክ ግን ከነውርም ነውርና እጅግ አፀያፊ ተግባር ነው፡፡ ሀገር ስትኖረን ለሚደረስበት ነገር አሁን መገዳደሉ ትርጉም የለውም፡፡ መነሻችን በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት የለም የሚለው ነውና ወደዚያ ጎራ ብለን ጅምራችንን እንጨርስ፡፡
ኢትዮጵያና ኬንያ ቢዋጉ ድምበር ዘለል ጦርነት ነው፡፡ የኮሎምቢያ መንግሥትና ፋርክ [FARC] ቢዋጉ የእርስ በርስ ጦርነት ነው፡፡ የስሪላንካ መንግሥትና የታሚል ታይገር አማፂ ቡድን ቢዋጉ የእርስ በርስ ጦርነት ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች ሲዋጉ ግድ ሆኖባቸው ከሁለቱም ወገን ሰው ይሞትባቸዋል – ጦርነት ነውና፡፡ ነገር ግን አንደኛው በሌላኛው ሬሣ አይጫወትም፤ አይዝናናበትምም፡፡ አንዱ ለአንዱ ያለው ጥላቻም ገደብ አለው – ለዚያውም ጥላቻ እኛ በምናውቀው ሁኔታ ካላቸው፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው የአንዱ ጎራ ገዳይ በሌላኛው ጎራ ሟች አስከሬን አጠገብ ቁጭ ብሎ ሊያለቅስና ሊያዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በዓላማ ጉዳይ ወንድሙን እንደገደለ ይረዳልና፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ በርስ በርስ ጦርነት ተገናኙ እንጂ ወንድማማቾች መሆናቸውን ሁለቱም ያውቃሉ፡፡ በዚያ ላይ ሁለቱም ሰዎች ናቸው፡፡ ሲያስቀኑ!!
የኛ ግን ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደሞከርኩት በገዳዮች አእምሮ ውስጥ በተቀበቀበ ሰው ሠራሽ የጥላቻ መርግ ምክንያት ገድሎት እንኳን መሞቱን አያምንም ወይም ሊያምን አይፈልግም፡፡ በዚያም ሳቢያ ገዳዩ ወደ አውሬነት ይለወጥና ሬሣውን በእሳት ያጋያል ወይም እየጎተተና እየሰቀለ ይጫወትበታል – ሊያውም በመንጋ ሆኖ፡፡ የምርኮ አያያዝን የተመለከትን እንደሆነ ይህም አስደንጋጭና በየትም ዓለም ያልታዬ ነው፡፡ ምን አለፋን – ኦሮሙማነት በሰይጣን እጆች የተሠራ ፀረ አማራ የሆነ የሲዖል ካርበን ኮፒ ነው፡፡ እንዲያውም ከኦሮሙማ ይልቅ ሲዖል ሳይሻል አይቀርም፡፡
ዋናው መነሻየ ኢትዮጵያ ውስጥ ስም የለሽ ኦሮሙማዊ የአማራ ፍጂት እንጂ የእርስ በርስ ጦርነት እንደሌለ ማስረዳት ነው፡፡ የእርስ በርስ ጦርነት አለ ካልን በአ.ፋ.ህ.ድ እና በአ.ፋ.ብ.ኃ፣ በአራት ኪሎ ሸኔና በኦነግ ሸኔ(የነአቢይ የጫካ ሸኔን አይመለከትም)፣ በነባሩ ሕወሓትና በአዲሱ ሕወሓት መካከል ቢሆን ያስኬዳል፡፡ ሸኔ፣ ሸኔን ቢገድል መቼስ እየቆራረጠ ሥጋውን ሊያስበላ የሚችል ጥላቻ በሁለቱ መካከል አለ ብለን ማመን ይቸግረናል፡፡ በሁለት ጎራ ላይ የቆሙ ሁለት ትግሬዎች – የፈለጉትን ያህል ቢዋጉና ቢገዳደሉ – አንዳቸው የሌላኛቸውን አስከሬን በመኪና እየጎተተ አይጫወትበትም፡፡ አንዳቸው ባንዳቸው ላይ የስብዕናን ክብር የሚያጎድል ተግባር አይፈጽምም፤ እያዘነ ይገድለዋል፤ እየራራም ይቀብረዋል፡፡ ኦሮሙማ ግን የትም ዓለም በሌለ ጭካኔ አማሮችን ይጨፈጭፋል፡፡ በሌላ አቅጣጫ ለምሣሌ ፋኖዎች መከላከያን ሲማርኩ ልክ እንደነሱው በማየት ሲያበሏቸውና ሲያጠጧቸው እናያለን፤ ይህ የሰውነት ደረጃ ልኬትን ያሳያል፡፡ በእጅህ የገባ ጠላትም ይሁን የጦር ምርኮ እጁ ከተያዘበት ዕለት ጀምሮ ምንም ዓይነት ሰብኣዊ ከብር ሊነካበት አይገባም፡፡ የኛ ሀገር ፖለቲከኞችና የእሥር ቤት አስተዳደሮች እኮ ሰው ለመሆን ራሱ ብዙ ንጥረ ነገር ይጎድላቸዋል፡፡
በመሠረቱና እንደእውነቱ ሬሣ የማንም ይሁን የማን ክቡር ነው፡፡ አስከሬን ሰው ነበረ እንጂ ሰው አይደለም፡፡ ሰው ሆኖ ተፈጥሮ እንዴት የሞተን ሰው በክብር ከመቅበር ይልቅ በእሳት እያንጨረጨረ መጫወቻ ያደርጋል? ከየት ያመጡት ፋሽን ይሆን? ኤዲያ! ምነው ዝም እንዳልኩ ብቀር ኖሮ፡፡ የዚህች አገር ገመና የሰውን ልጅ አለመፈጠር የሚያስመኝና ፈጣሪ ራሱ ሰውን በመፍጠሩ መጸጸቱን እንድናስታውስ የሚያደርግ እጅግ ሰቅጣጭ ክስተት ነው፡፡