
እስረኛው ሕይወቱ ያለፈው በህክምና እጦት ምክንያት መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ለሮሐ ሚዲያ ገልፀዋል።
የተባሉ የ63 ዓመት አዛውንት ከባህርዳር ወንድማቸውን ለመጠየቅ አዲስ አበባ እንደገቡ ‘ከፋኖ ታጣቂዎች ተልዕኮ ተቀበለህ መጥተሀል’ በሚል በፌደራል ፖሊስ ተጠርጥረው ለአራት ወራት ያህል በእስር ላይ መቆየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ጨምረው ተናግረዋል።
አቶ አባይነህ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ፥ በምርመራ በቆዩበት ወቅት በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ችሎት ቀርበው የተናገሩ ቢሆንም በቂ ሕክምና ሳያገኙ ቆይተዋል ሲሉ የገለፁት ቤተሰቦቻቸው ጉዳቱ በጊዜ ሂደት አመርቅዞ ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል ብለዋል።
በማረሚያ ቤት ውስጥ ሕይወታቸው ያለፈው አቶ አባይነህ ‘ህመም እየተሰማኝ ነው ወደ ሕክምና ውሰዱኝ’ ቢሉም አጃቢ የለም በሚል ሕክምና ሳያገኙ መዋላቸውን ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ባልደረባ ለሚዲያችን ተናግረዋል።
አቶ አባይነህ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ የሽብር ወንጀል ችሎት በአራባ ሽህ ብር ዋስ እንዲፈቱ የበየነ ቢሆንም ፌደራል ፖሊስ በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ ሽብር ለመፍጠር ሲያሴሩ አግኝቻቸዋለሁ በሚል ሌላ ክስ ከፍቶ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ አድርጓቸዋል ብለዋል ቤተሰቦቻቸው።
ይሄው ፍርድ ቤት በሁለተኛውም ክስ በሠላሳ ሺህ ብር ዋስ ውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ቢበይንም ሳይለቀቁ መቆየታቸውን እና በዚህ መኃል በምርመራ ወቅት በደረሰባቸው ደብደባ ምክንያት እና በህክምና እጦት በማረሚያ ቤት ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ገለፀዋል።
በአቶ አባይነህ አማሟት ምክንያት የተቆጡ የአማራ ተወላጅ እስረኞች ከጥበቃ አባላት ጋር ግጭት መፍጠራቸውን ነው ሚዲያችን ያረጋገጠችው።
ግጭቱ የተፈጠረው በቂሊንጦ ዞን አራት ተብሎ በሚጠራው የእስረኞች ማቆያ ሲሆን የማረሚያ ቤቱን ስም አጥፍታችኋል በሚል ኢንስፔክተር ኢብራሂም የተባሉ የማረሚያ ቤቱ የእስረኞች አስተዳደር በአማራ እስረኞች ላይ መዛታቸውን ነው ያገኘነው መረጃ
————————–
For the Record
zehabesha 5555