ማይክሮሶፍት በኢትዮጵያ ያለውን የትምህርት ስርዓት ለማዘመን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስራ ጀመረ

Microsoft collaborates with the Ethiopian Ministry of Education to help digitize the education sector..አዲስ አበባ ሰኔ 10 ፣ 2014 – ማይክሮሶፍት ከኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የትምህርት ሴክተሩን ስኬታማ ዲጂታል ሽግግር የሚደግፍ የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደር የመረጃ ስርዓትን ተግባራዊ አደረገ።

የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ዘርፉ ያለውን ደረጃ አቅም በማሳደግ ውጤታማ፣ጥራት ያለው እና እኩል የትምህርትና ስልጠና ስርዓቶችን ተግባራዊነት የማረጋገጥ ተልዕኮ እንዳለው ይታወቃል። በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ስኬታማነት ለማረጋገጥ በዋናነት ግብአት የሆነውን የተሟላ መረጃ አስፈላጊነት በመገንዘብ የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር  ሀገር አቀፍ የትምህርት መረጃ ትንታኔዎችን ለማስተዋወቅ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ከፍተኛ የትምህርት ስልጠና ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም በተግባር ባልተሟላበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ሰጪዎች ትክክለኛ አና አስፈላጊ መረጃን ባለማግኘታቸው ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ አሰቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሩዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመተግበር ላይ የነበሩ ስልቶችን ተፅእኖ እና ውጤታማነታቸዉን ለመመዘን አዳጋች ያረገዋል፡፡ የትምህርት ትራንስፎርሜሽኑ ሂደት ስኬታማነት የመረጃ እና ግንዛቤ ግብዓቶችን በእጅጉ አስፈላጊ የሆኑበት ወቅት ላይ መሆናችንን ያሳያል፡፡

በትምህርት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መርሃግብራችን መሰረት ማይክሮሶፍት የትምህርት ስርዓትን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማደረስ ብሎም ከተለመደው የማይለዋወጥ መረጀን እንደ ግብዓት ከመጠቀም  ወደ የተቀናጀ ወቅታዊ መረጃ እና የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት አገልግሎቶችን እና ልምዶችን በሚደገፉ የመፍትሄ አማራጮች እንዲያንቀሳቅሱ እያበረታታ ነው።

በማይክሮሶፍት አዡር፣ ፓወር ቢአይ እና ኦፊስ365 የተሰራው ኢድሊኢጎ፣ የቴክኖሎጂ አቅርቦት በትምህርት ስርዓት ወስጥ የላቀ ትንተና እና ውሳኔ አሰጣጥን ዕውን ለማድረግ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅርበት በመተባበር ተተግብሯል። ስኬታማ የፕሮጀክት አፈፃፀምን ለማረጋገጥ ብሎም ቀጣይነት ያለው የማሻሻያ የስራ ፍሰት እንዲኖር የሚያግዙ መሪ እና የፕሮጀክት አስተዳደር ቦርድ ስልቶች አንዲካተቱም ተደርጓል፡፡

ኤች.ኢ.ቲ.ኤም.አይ.ኤስ የሚኒስቴሩን መረጃ የመሰብሰብ፣ የማስተዳደር፣ ሪፖርት የማድረግ እና የመተንተን ችሎታዎችን ያጠናክራል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለውን የመረጃ አሰባሰብ እና ትንተና ሂደት እንዲቆጣጠር የሚያስችል ጠንካራ የቴክኖሎጂ መድረክ ያቀርባል። ይህም የቴክኖሎጂ መድረክ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ጀምሮ እስከ ኮሌጅ ወይም የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ድረስ ባሉ በርካታ ባለድርሻ አካላት ዘንድ አገልግሎት  መስጠት ይችላል።

የአቅም ግንባታና ሥልጠና ከጅምሩ በማካተት ከ50 በላይ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ 380 የግል ዩኒቨርሲቲዎች እና 1,800 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማትን ተደራሽ ያደረገ ሲሆን፤ ስኬታማነቱን ላማረጋገጥ በማሰብ እና አሉታዊ ተጵዕኖ ለመቀነስ ትግበራው በየደረጃው እንዲቀርብ ተደርጓል።

“የትምህርት ሚኒስቴር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ልማት የሚያፋጥን ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያስችል የትምህርትና የሥልጠና ሥርዓቶችን በዘላቂነት የመገንባት ራዕይ ያለዉ ሲሆን ፤ ይህ አሰራር በትምህርት ዘርፍ ያለንን ዲጂታል ስትራቴጂ እንድንከተል ያስችለናል ሲሉ የአይሲቲ እና ዲጂታል ትምህርት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘላለም አሰፋ ተናግረዋል።

“ማይክሮሶፍት በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ መሪዎችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ውስብስብነት ያለምንም ችግር እንዲዳስሱ ለመርዳት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። ግባችን ከመንግስት እና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር፣ የመረጃ ትንታኔዎችን በመጠቀም የሚቻለውን ለመስራት እና የተማሪን ስኬታማነት ለማረጋገጥ ነው፡፡ ሂደቱ  ቀልጣፋ፣ ምላሽ ሰጪ እና ዘላቂ ሂደቶችን እና የገብዓት ድልድል ለመፍጠር ያግዛል” በማለት በማይክሮሶፍት የመማሪያ ፓስፖርት እና ኢ.ኤም.አይ.ኤስ. ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሉዊዝ ማክኬት ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደር መረጃ ሥርዓትን በመዘርጋት የዕቅድ፣ የውሳኔ አሰጣጥ፣ ክትትልና የሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግምገማን እያሻሻለ ይገኛል።

 

ስለ ማይክሮሶፍት

ማይክሮሶፍት (Nasdaq “MSFT” @microsoft) ለአስተውሎት ክላውድ ወቅት የዲጂታል ለውጥን እየተገበረ ይገኛል፡፡ ተልእኮውም በአለማችን ላይ ያለ እያንዳንዱ ሰው እና እያንዳንዱ ድርጅት የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ እባክዎን የማይክሮሶፍት መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ የዜና ማእከል ይጎብኙ ።

ስለ ኢድሊጎ

የማይክሮሶፍት የቴክኖሎጂ አቅርቦቶች አጋር EDLIGO GmbH (የቀድሞው Education4sight)፣ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተካነ ኩባንያ ነው። የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ በመጠቀም ደንበኞቻቸውን በክህሎት አስተዳደር እና የአስተዳደር ትምህርት  ውስጥ ትክክለኛ ውሳኔዎችን እንዲያደርጉ ሲሰራ የቆየ  ኩባንያ ነው። በኤርላንገን የተመሰረተ እና የጀርመን በፈጠራ ስም ካፈሩት አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ በሆነው ፍሬድሪክ-አሌክሳንደር ዩኒቨርሲቲ የወጣው ኢድሊኢጎ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ግንባር ቀደም ለመሆን ሁሌም የሚሰራ ኩባንያ ነው። ኢድሊኢጎ ደንበኞቻችን የእኛን መድረክ በተሳካ ሁኔታ ከአስር በሚበልጡ አገሮች በመጠቀም፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት እና ከአስር በላይ የፈጠራ ባለቤትነት ማረጋገጫዎች ባለቤት ነው፡፡


Abele tesfaye

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

rtttttt
Previous Story

ውሻ ሆይ! ይቅር በለኝ! – በላይነህ አባተ

rt66665
Next Story

የስብሀት ነጋ ወንድም በሜልቦርን ነዋሪ የሆነው አቤሴሎም ነጋ ሲያጭበረብር ኖሮ ኖሮ በመጨረሻም የህግ አገር በመሆኑ በሌብነት እና በማጭበርበር ወንጀል ተፈረደበት

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop