ከህሊና ፈረደ
ታዛቢው እንደ አትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኝነቱ ፣ ውጭ ሃገረ በተለይ የእንግሊዝ ሃገር ነዋሪ እንደመሆኑ እና ከላይ በርዕሱ የተጠቀሱት ሰብአዊ ጥሰቶች ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቀኖና እና ቃለ-አዋዲ ውጭ በአማራ ምህመናን እና ካህናት ላይ እየደደረሰ ያለውን መገፋት ፣ ግፍ እና መገለል በመታዘብ እና ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ድምጽ ለመሆን በማሰብ ያስተላለፈው መልዕክት መሆኑን ያስገነዝባል።
እንዲሁም ለመላው አማኝ ምህመናን እና ካህናት “ ኋላ ከመታመም አስቀድሞ መጠንቀቅ” አንዲሉ በአሁኑ ሰዓት በአንዳንድ ቤተ-አምነቶች ፅንፍ የለቀቀ አካሄድ እየተከናወነ ስለሆነ ይህን ኢ-ሃይማኖታዊ እና ከእምነት የራቀ አካሄድ አንዲያወግዙት አና እንዲያስቆሙት በማሰብ የተከተበ መልዕክት መሆኑን ለአንባቢው እንገልፃለን ።
በሃይማኖት ሽፋን ሃገር ቤት ያለውን ሥረዓት ትራስ አድርጎ ፣ የሥርዓቱ ጋሻ ጃግሬ እና ተልዕኮ ፈፃሚ በመሆን ምእመኑን እና ካህናትን ማሸማቅቅ ፣ ከስራ ማገድ እና የእምነት ነፃነታቸውን መገደብ አግባብ ካለመሆኑ ባሻገር ልዑል እግዚአብሔር የማይወደው “የፀረ እምነት” ገቢር መሆኑን ልንገልፅ እንወዳለን።
በአሁኑ ጊዜ በሃገረ ኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በሚከተለው የተጎላደፈ ፣ ውጥንቅጡ የወጣ እና ተረኝነትን መሠረት ባደረገ የፖለቲካ መዘወር እና አካሄድ በሃገር ቤት ያሉ የተለያዩ ተቋማት ነገር አለሙ ሁሉ “እግር ተወርች” ሆኖባቸው የቆመ ህንፃ ታቅፈው ከወዲያ ወዲህ “ንፋስ አንደሚያወዛውዘው ዛፍ” አየተወላገድ እና ግራ ገብቷቸው ይገኛሉ።
እፍረት ያጣው እና “ሕዝብን ከመጤፍ ያልቆጠረው” መንግሥት የተቋማት አመራሮች ፣ አስተዳዳሪዎች አና መሪዎች ከአንድ ብሄር ዘንግ በወጡ ፣ በፈለቁ እና በተመለመሉ ምሰለኔዎች ፣ የሰርዓቱ ጥቅም ተጋሪዎች እና አጨብጫቢዎች አንዲዘወሩ እያደረገ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ውሎ አደሯል።
የሚያሳዝነው የአመራር ብቃት ፣ ለሕዝብ በሃቅ አገልጋይ መሆን ፣ እውቀት ፣ ሚዛናዊነት እና ግብረገባዊነት በምድረ ኢትዮጵያ የቀደምት ዘመን ትዝታ እና አሻራ አየሆነ መምጣቱ በግልፅ እየታየና ተቋማዊ መሠረት ያለው እና አካሄድ ከሆነ ውሎ አድሯል።
ከዚህ ባሻገር ኢትዮጵያዊ ቀለም ያለው የአስተዳደር ሰብጥር ፣ የብሄር ተዋፅኦ (የሚደገፍ ባይሆንም) እና በየተቋሙ ይታይ የነበረው ኢትዮጵያዊ ዘንግን ያገናዘበ የስራ አመራር ምደባ የማይታሰብ አየሆነ ከመምጣቱ ባሻገር “የቀደም የአባቶቻችን ትብዕል ፣ ጥበብ ፣ ሰልታዊ የአመራር ሰልት እና ዘየ” አፈር ደሜ በልቶ አንድ ብሄር የገነነባት እና የነገሠባት ሃገረ ኢትዮጵያ እያየን መምጣታችን ሃገር እንደ ሃገር የገባችበትን ምጥ ፣ ጣጣ ፣ መከራ አና ፈተና ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
እንግዲህ ይህ ማለት ባንኩንም ፣ ታንኩንም (መከላከያው) ፣ መላ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተቋማቱን ከአንድ ብሄር ማለትም ከኦሮሞ ብልፅግና በወጡ ታማኝ ምስለኔዎች አንዲመራ እና እንዲሰተዳደር አያደረጉ መሆኑ ለማንም ሚሰጥር አይደለም ።
የቅርቦቹ በኢትዮጵያ የተሰየሙ መንግሥት ተብየዎች ግዙፍ ፈተና ሁኖባቸው የነበረው ታላቋን ፣ ዓለም ዓቀፋዊ እና አህዳዊ የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የነሱ ተጋላቢ ፣ ተለጣፊ ፣ ተሽከርካሪ ማድረግ አለመቻላቸው እና “ክብር ይግባቸውና “ሰማዕት ለሆኑ የቤተክርስቲያን አባቶች እና መሪዎች” ቅድስት ቤተክርስቲያን አረማዊ በሆኑ አመራሮች እዳትመራ ጥርሳቸውን ነክሰው በመታገል ከእንደዚህ አይነቱ አዘቅት አና ጣልቃገብነት ጠብቀዋት ኑረው ነበር ።
አሁን አሁን ግን “የእሳት ልጅ አመድ እንዲሉ” ከቤተ-እምነቷ በወጡ ካህናት ቁንፅል እውቀት ፣ የተዛነፈ ህሳቦት ፣ መፈሳዊነት ማነስ እና አመለካከት እንዲሁም የፖለቲካውን ላዕላይ ሥልጣነ ምዕውሩን (መንበሩን) በጨበጡ እና ዘዋሪ በሆኑ መናፍቃን የተዛነፈ አመለካከት ፣ መር የለቀቀ አካሄድ እና የአንድ ብሔር አቀንቃኝነት ልክፍት “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአማራ ሕዝብ መሰባሰቢያ እና ደጅ መጥኛ” ናት በሚል መሠረተ ቢስ ክስ ፣ ህሳቤ እና ውዥንብር አየከሰሷት ይገኛሉ።
ከዚያም አልፎ አዲስ አበባ ላይ ከትሞ ያለው ገዠው ፖርቲ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እንደ አሻው በእጅ አዙር ለማሽከርከር ፣ የፖለቲካው ፕሮፖጋንዳ መንዧ አና ከተቻለም የምታገኘው ገቢ ተጋሪ ይሆን ዘንድ መረቡን ከዘረጋ ወሎ ያደረ ከመሆኑ ባሻገር ይሀን ሰይጣናዊ እና መናፍቃዊ ህልሙን የቻለውን ያህል እርቀት ሂዶ ተግባራዊ እንደሚያደርገው ሳይታለም የተፈታ እና ጥርጥር የሌለው መሆኑን “ሳታመሃኝ ብላኝ” እንዲሉ “ይህ ሁሉ መላላጥ” ለምን እንደሆነ ከገባን ውሎ አድሯል እንላለን።
የኦሮሙማው መንግሰት ያሴረው የነበረው ይህ ስር የሰደደ ፣ የተጠና ደባ ፣ ተንኮሳ ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የመቆጣጠር መሰሬ አካሄድ ፣ ጣልቃ ገብነት እና ሽረባ የተሳካ በሚመስል መልኩ በስልት እና በረቀቀ መልኩ አየተሄደበት ሲሆን ዛሬ ዛሬ በሃገር አቀፍ ደረጃ ብቻ ሰይሆን “የሃገሩን ሰርዶ በሃገሩ በሬ” እንዲሉ ሃገር ቤት እያከናወኑት እንዳለው ሁሉ በሌሎች ዓለማት የተቋቋሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ቤተክርስቲያናትን በኦሮሞ ተወላጅ እና በሰርዓቱ የጥቅም ተጋሪ ካህናት በእጅ አዙር አድትወድቅ ፣ እድትሰተዳደር እና እንድትመራ ሴራው እንደተጀመረ እና የተነኮሉ መህለቅ አደተዘረጋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምህመናን አና ካህናት ከወዲሁ ልታውቁት ይገባል እንላለን።
ይህን የግንዛቤ ማስጨበጫ መሠረት ሃሳብ ተመርኩዞ “ከአፈርኩ አይመልሰኝ” እንዲሉ በአማራ ተወላጅ ካህናትን ምንም አይነት ዕፀፅ እና የተክሀኖ ግድፈት ሳይኖርባቸው በማናለብኝነት “ ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ደጅ አሳደረች” አንዲሉ ከሰሞኑ ከቤተክርስቲያኒቱ ፣ ቀኖና እና ቃለ አዋዴ ውጭ “ሳይንካካ ተቦካ” እንዲሉ በተለይ ነባር ሆነው ከተመሠረቱት ቤተክርስቲያናት እጃቸውን ማሰገባት ሲያቅታቸው አዳዲስ በተቋቋሙ ቤተክርስቲያናት አካባቢ ሃገር ቤት ያለውን የሴራ ተልእኮ ሰጪ አካላትን ለማስደሰት እና የታማኝነታቸውን ግብረ መልስ ለማሳየት ሲባል በሀገረ እንግሊዝ – ለንደን መካነ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን (United kingdom-London) ልብሰ ተክህኖ ለብሰው ለቅዳሴ የተዘጋጁን ካህን ምህመናኑ በምልአት ለአምልኮት በተገኙበት ልብሰተ ተክሀኖን አስወልቆ ከመግፈፍ ጀምሮ ፣ ደበዳቤ በመፃፍ በድፍረት በማሸማቀቅ ከአገልግሎትና እንዳግዷቸውና ከቤተክርስቲያኗ እንዳባረሯቸው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፣ በተለይ በታላቋ በሪታንያ (እንግሊዝ) የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምህመናን ፣ ካህናት እና ቤተ-እምነቶች በሙሉ ሊያውቁት ይገባል እንላለን።
እንግዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ቀኖና ፣ ሕገ ደንብ እና ቃለ አዋዲ ባልጠበቀ እና ባላገናዘበ መልኩ በግብር ይወጣ ፣ በማናለብኝነት እና ተጠያቂነትን ገሸሽ በማድረግ በለንደን መካነ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ይህ ጥዮፍ ድርጊት ተፈፀመ የሚለውን በመረጃ ፣ በማስረጃ እና የደብዳቤውን ግልባጭ አያይዘን በመለጠፍ አቤቱታችንን ሕዝብ አውቆ የህሊና ፍርድ እዲሰጥ እና ከሃሳዊ መሲያን ጥንቃቄ ያደረግ ዘንድ አሰረግጠን አናሳስባለን።
የሚገርመው ፣ አሰፈሪው እና አሳፋሪው ድርጊት አምላካችን መዳሃኒታችን እየሱስ ክርስቶሰ እዳስተማረን እና የአምላኳን ህያው ቃል ተቀብላ አና በውሰጧ አሰርፃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንደምታስተምረው ፍቅርን ፣ መቻቻልን ፣ ይቅርታን ፣ መከባበርን ፣ መታረቅን እና መረዳዳትን ስትሰብክ እና ተግባራዊ እያደረገች ዘልቃለች።
ይህን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያን ከትውልድ ትውልድ በቅብብሎሽ ተከትላ የምትመራበትን መንፈሳዊ እና መሠረታዊ መርህ ፣ እሴት እና ትብዕል መሠረት በማድረግ የሚከተሉት ጥረቶች ተከናውነው የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደሪ ገብረ መላሸም አደሚከተለው ቀርቧል:
- በታላቅዋ ብሪታንያ -ሎንደን ከሚገኙ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች መካከል ካህናትን በማወጣጣት የካህኑ እግድ እዲነሳ እና እርቅ ይወርድ ዘንድ ቢሞከርም አስተዳዳሪው ሁለት ጊዜ እሽታቸውን በመግለፅ በቀጠሮው እኒህ አባት አለመገኘታቸው፣
- በዚህ የሽምግልና ወጣ ውረድ መካከል የደብሯ አስተዳዳሪ ለለበጣ ይሁን ጌዜ ለማራዘም የቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና እና የቃለ ዓዋዲው ሕግ በመጣሱ ቅር የተሰኙትና ጉዳዩንም በሽምግልና እንዲፈታ ከጠየቁት የደብሩ የጉባኤ መምህር ከሆኑት አባት እግር ላይ በመውደቅ የካህኑን እግድ አንደሚያነሱ እና ካህኑ ወደ አገልግሎት አንደሚለሱ አንደሚያደርጉ ቃል-ገብተው ይህን አለማድረጋቸው ቃለ-አባይ የሚያደርጋቸው ከመሆኑ ባሻገር የቤተከርስቲያኗ ሕገ-ደንብ እና ቀኖና ይህ መሰሉን አካሄድ እደማይፈቅድ ፣
- የቤተክርስቲያኗ መምህር ይህን ሁሉ እርቀት በመጓዝ ዕርቅ ለመፍጠር እና የካህኑ አግባብ ያለሆነው እግድ አዲነሳ ቢጥሩም ምላሽ ባለማግኘታቸው በግል ለቤተክርስቲያኗ የሰበካ ጉባኤው አስተዳደር ደብዳቤ በመፃፍ ቢጠይቁም በመታበይ ይሁን ፣ በማን አለብኝነት እና “ምን ይመጣብኛል” በሚል ህሳቦት ወይም በጀርባ ያሉትን “አይዞህ ባዮች” ተማምነው እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ ለጥያቄው ሁሉ “ጀሮ ዳባ ልበስ” ብለው ምላሽ አልሰጡም፣
- በዚህም ምክንያት የደብሯ መምህር ሕገ ቤተክርስቲያንን ከማይጠብቁና ከሚያፈርሱ ሕገወጥ ጋር አላገለግልም ብለው ራሳቸውን ከሚወዷትና እጅግ ከደከሙላት ከመካነ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እራሳቸውን አግልለዋል።
ማጠቃለያ
እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምህመናን አና ካህናት መካከል ክፍፍል መፈጠር ፈር የተቀደደው እና የጀመረው በታላቋ በሪታንያ- እንግሊዝ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ይህ የክፍፍል አባዜ ምከንያቱ ምን ይሆን ለሚለው ምላሹ :
በምህመኑ እና ካህናት መካከል በፖለቲካ ፖርቲዎች ደጋፊነት መቧደን ፣ መለያየት እና በብሄር ተከፋፍሎ መጠዛጠዝ፣
ቤተክርስቲያንን የግል እና የተወሱኑ በድኖች ግላዊ ሃብት ለማድረግ አና ለመቆጣጠር በሚደረግ ፍትጊያ እንዲሁም ከላይ እደተገለፀው በኢትዮጵያ ሰልጣን ላይ ላለው መንግስት ቤተክርስቲያናት ተዘዋሪ እንዲሆኑ እና ስር አንዲወድቁ በሚደረግ ከቀኖና እና ከቃለ-አዋዲው ውጭ በሚከወን አቡህ እና ቀና ያልሆነ እንቅስቃሴ ነው።
ይህ ከቃለ- አዋዲው ፣ ከቀኖና ፣ ከቤተክርስቲያን ጉባኤ ሕግጋት እና ውስጠ ደንብ ውጭ “በለንደን መካነ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን – በታላቋ ብሪታንያ” “አስተዳዳሪዎች እና የጥቅም ተጋሪዎች” የተፈፀመውን የግብር ይውጣ ፣ መነፈሳዊውን እና ዓለማዊውን ሕግጋትን ሳይቀር ጥሶ የተፈፀመ ድርጊት የደብሯ ምህመናን ፣ ካህናት ፣ መላው ለንደን የሚገኙት ቤተክርስቲያናት እና የቤተክርስቲያኗ ተቆርቋሪ የሆኑ ሁሉ “ሳይቃጠል በቅጠል” እነዲሉ አዲቃወሙት እና አዲያወግዙት አናሳስባለን ፣ አናስታውቃለን።
አያይዘንም የመፍቴሄ ሃሳባችን በቅን ልቦና እደሚከተለው እናሰፍራለን :
- ከቤተክርስቲያኗ የታገድት ካህና እግዳቸው ተነስቶ ከይቅርታ ጋር ወደ አገልግሎታቸው አንዲ መለሱ ፣
- ይህን ሕጋዊ ያልሆነ ድርጊት የፈፀሙት የደብሯ አሰተዳዳሪ ፣ ተባባሪ ካህናት እና የሰበካ ጉባኤ አባላት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ሕግጋት እና ደንብ መሰረት እዲጠየቁ እና አስፈላጊው እርምጃ አንዲወሰድባቸው ፣
- ይህ ከባድ እፀፅ ሲከወን እጁን አጣጥፎ የተቀመጠው ፣ የበይ ተመልካች የሆነው እና በመላ ምህመኑ ደምፅ ያልተሰየመው የሰበካ ጉባኤ “ከደሙ ንፁህ” ሰላልሆነ ሰልጣኑን አስረከቦ አውቀት በተላበሱ ፣ ሙያው ባላቸው ፣ ታመኝ ፣ ለህምነታቸው ቀናይ በሆኑ አና ምራቃቸውን በዋጡ ካህናት እና ምህመናን እዲተኩ አንጠይቃለን።
በመጨረሻም “በለንደን መካነ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ደብር” የተከወነው ይህ ፀረ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፣ መናፍቃዊ ፣ ከቀኖና እና ከቃለ-አዋዲው ውጭ የሆነ ሕገ ወጥ ደርጊት በእነጭጩ አና በአፍላው ካልተቀጨ ነገ ከነገ ወዲያ በተላቋ -ብሪታንያ- እንግሊዝ ባሉ ሌሎች ቤተክርስትያኖች ፣ በሃገር ቤት እና በሌላ ዓለማት ባሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ቤተክሪስቲያኖች ተሰፋፍቶ እና እግር ሰዶ ካህናት እንደሚሳደድ ፣ በኢምንት ምክንያት ወይም ያለ ምክንያት እደሚባረሩ ጥርጥር የሌለው ሲሆን በልምድም ያየነው ነው ።
ካህናት እና መህመናን መብታቸው እና የእምነት መሰረታቸው አየተገፈፈ እና እየተሸራረፈ ከሄደ በተለይ ወጣቶች የመናፍቃንን ቤተ-እምነቶች በር እነዳያንኳኩ እንሰጋለን።
ከህሊና ፈረደ
ከእንግሊዝ – ለንደን