ፀዳሉ ደሴ ለአገዛዙ እጅ መስጠቱን በተመለከተ የፃፍኩትን ተከትሎ አንዳንዶች በተለይም አፋህዶች “ውሸት ነው” በሚል ምላሽ ሰጥተውኛል:: በፎቶ በቪዲዮ ሲያዩ እውነታውን ሲያውቁ ምን ሊሰማቸው እንደሚችል አላውቅም::
ሻለቃ ፀዳሉ ደሴ ዝም ብሎ በራሱ ለብልፅግና እጅ አይሰጥም:: ሌሎች አፋህድ ውስጥ ያሉም አንድ በአንድ እጅ እንዲሰጡ ለማድረግ በአፋህድ የፖለቲካ አመራር በኩል ትልቅ ስራ እየተሰራ ነው::
ይህ የፀዳሉ ደሴ ውሳኔ : የአፋህድ የፖለቲካ አመራር እውቅና ሊኖረው የሚችል ቢሆንም ወታደራዊ አዛዦችን እነ ሻለቃ ደረጄ በላይን በጣም እንዳስፈረ ነው የደረሰኝ መረጃ የሚጠቁመው::
ብልፅግናዎች ለጊዜው ትልቅ አቀባበል ቢያደርጉለትም አትጠራጥሩ: ፀዳሉ ደሴ ሚሊሺያ መድበውለት: ፊት አዝማች አድርገውት ፋኖዎችን እንዲወጋ አስታጥቀው ያሰማሩታል:: እምቢ ካለ ደግሞ ዘብጥያ ያወርዱታል::
ለርሱ ይብስበታል እንጂ ሜዳ ላይ ያለው ሁኔታ እርሱ እጅ በመስጠቱ አይለወጥም:: ላለፉት 6 ወራት ሰውዬው በአፋህድ ውስጥ ሆኖ ሲሰራ የነበረው ሌሎች ፋኖዎች ላይ መተኮስ ነበር:: እንደውም አሁን በይፋ ብልፅግና ነኝ ማለቱ ጥሩ ነው::
በነገራችን ላይ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙኸባም ወደ ብልፅግና ሊገቡ እንደሚችሉ አንዳንድ ፍንጮች ደርሰውኛል::
ኮሎኔሉ አፋህድ ወይንም ሞት በሚል: ከ95% በመቶ በላይ የወሎ ፋኖዎችን ወደ ጎን አድርገው: ራሳቸውን አግለው : ዳዎንት የምትባል ወረዳ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ነበር:: አሁን እዚያ አቅራቢያ በሽሽት ነው ያሉት::
ወደ ደቡብ ጎንደር እንዳይሻገሩ : በዚያ የክፍያለው ደሴን መሞት : የፀዳሉ ደሴን ለብልፅግና እጅ መስጠት ተክትሎ : የአፋህዱ የአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ተዳክሟል::
ኮሎኔሉ ከነምሬ ወዳጆና ሻለቃ ድርሳን ጋር በመነጋገር ወደ አማራ ፋኖ በወሎ ቤተ አማራ መግባታቸው ለርሳቸው በጣም የተሻለ አማራጭ ነበር:: ግን ለዚያ አማራጭ በጣም ዳተኛ ናቸው::
ኮሎኔሉ ያንን ማድረግ ካልቻሉ ግን: አገዛዙ በማንኛውም ጊዜ ጥቂት ሃይል ልኮ በቀላሉ ኮልኔል ታደሰ እሸቴ ላይ ያደረገውን በኮሎኔል ፋንታሁን ላይ ሊያደርግ ይችላል:: ህይወታቸው ትልቅ ወታደራዊ አደጋ ላይ ነው ያለው::
ይህንን ኮሎኔሉ ወታደራዊ ሳይንስ የሚያውቁ እንደመሆናቸው ይረዳሉ ብዬ አስባለሁ::
ሌሎች የወሎ ፋኖዎችን መቀላቀል ካልፈለጉ: ወደ ጎንደር ከዳውንት መሻገር ካልቻሉ: ተከበው በአገዛዙ እንደ ኮሎኔል ታደስ ከሚሞቱ: እንደ ፀዳሉ ደሴ እጅ ለብልፅግና ሊሰጡ ይችላሉ:ገበ