በ አምሳል ወረታ
1. መግቢያ
ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ፣ በተለይም ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ ባሉት ተከታታይ ሰባት ዓመታት፣ የአማራ ሕዝብ ስልታዊ ጥቃቶች፣ከክልሉ መሪዎች ጀምሮ ከፍተኛ እልቂት፣ መፈናቀል እና የፖለቲካ መገለል ደርሶበታል። ከዚህም በተጨማሪ፤ አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ ያወጀውን ጦርነት ተከትሎ በሚፈፀሙ የድሮን ጥቃቶች፣ የአገዛዙ ሰራዊት በሚፈፅማቸው ጥቃቶች፣ እንዲሁም በመሠረተ ልማቶች ላይ በሚፈፀሙ ውድመቶች ምክንያት የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለው መጠነ ሰፊት ጥቃት በመባባስ ላይ ይገኛል። በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጡት እነዚህ ሁሉ የህልውና አደጋዎች ቢኖሩም፣ በታሪካቸው በፖለቲካዊ እና በወታደራዊ ትግላቸው ጠንካራ አንድነት ማጎልበት ከቻሉት የትግሬ እና የኦሮሞ ህዝቦች አንፃር ሲታይ፤ የአማራ ህዝብ አንድነትን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ችግር ሲገጥመው ይስተዋላል።
ይህ ጽሑፍ የአማራውን የመከፋፈል መንስኤዎች፣ ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት እና በኋላ በአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀሙትን ማንነት ተኮር እልቂቶች እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ይመረምራል፣ እንዲሁም በኦሮሙማ መራሹ የብልፅግና ስርዓት ላይ እየተደረገ ባለው የህልውና ትግል ዙሪያ የአንድነት እና የተጋድሎ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፎችን በዝርዝር ያቀርባል። 2. አገዛዙ በአማራ ፋኖ እና በአማራ ህዝብ ላይ ያወጀው ጦርነት የአማራ ህዝብ ዘርፈ-ብዙ ጥቃቶች እየደረሱበት ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ መንግስት የአማራን ስቃይ እውቅና ከመስጠት ይልቅ አማራው እየደረሰበት ካለው ጥቃት ራሱን መከላከል የማይችል ህዝብ እንዲሆን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥት በአማራ ላይ የሚፈጸሙትን ግፍ ችላ እንዳለው ሁሉ የአማራን የህልውና ትግል ለመንግስት ስጋት አድርጎ ይመለከተዋል።
- በፈረንጆቹ ሐሴ 2023 ዐቢይ አህመድ በአማራ ክልል ላይ ሙሉ ወታደራዊ ዘመቻ በይፋ
ከፍቷል።
- ህጻናትን፣ ሴቶችን እና አረጋውያንን ጨምሮ የአማራ ንፁሃንን ዒላማ ያደረጉ የድሮን
ድብደባዎች፣ የከባድ መሳሪያ ጥቃቶች እና የጅምላ እስር ተፈፅመዋል።
- ትምህርት ቤቶችን፣ ሆስፒታሎችን እና የእርሻ መሬቶችን ጨምሮ ወሳኝ መሰረተ ልማቶች
እንዲወድሙ ተደርጓል።
መንግስት በፋኖ እና የአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን ጦርነት ምክንያታዊ ለማድረግ “አክራሪዎች” እና “ሽብርተኞች” ብሎ በመፈረጅ አማሮችን ትጥቅ ለማስፈታት እና ለቀጣይ እልቂት በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ እንዲሆኑ አልሞ ተንቀሳቅሷል። በአማራ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ መሪዎች ላይ የተፈፀመው የጅምላ እስር አሁን ያለው የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግስት አማራነትን ከተጋረጠበት የህልውና አደጋ ከመጠበቅ ይልቅ በስጋትነት እንደሚመለከተው ግልፅ ማሳያ ነው።
3. የተጋድሎ ውርስ፡ ፋኖ እና የአማራ ማንነት
ፋኖበኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አዲስ ኃይል አይደለም። ፋኖነት በአማራ ባህል ውስጥ የረዥም ጊዜ ታሪክ ያለው ባህላዊ የራስ መከላከል እና የተጋድሎ እንቅስቃሴ ነው። ታሪክ እንደሚነግረን በ1888 ዓመተ-ምህረት ከጣሊያኖች ጋር ከተደረገው የዓድዋ ጦርነት እስከ 1930ዎቹ የፋሽስት ወረራ ድረስ
የፋኖ አርበኞች ኢትዮጵያን ከውጭ ወራሪዎች በመከላከል ረገድ ቁልፍ የሚባል ሚና ተጫውተዋል። እንዲያም ሆኖ፤ ዛሬ ላይ ያለው የፋኖ ተጋድሎ፤ የአማራን ሕዝብ ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት የሚፈልጉ ውስጣዊ ኃይሎችን ለመፋለም ጦር መሳሪያ ያነሳ ሃይል በመሆኑ ከቀደሙት የፋኖነት እንቅስቃሴዎች የተለየ ያደርገዋል። 3.1. የፋኖ መነሳት እና ለህልውና የሚደረገው ትግል የመንግስት ጥበቃ በሌለበት እና በማንነት ላይ ያነጣጠረ ስርዓት-ወለድ ጥቃቶች እየተፈፀሙ ባለበት ሁኔታ፣ የአማራ ህዝብ ህልውናውን ለማስጠበቅ በንቃት መታገል አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል። የፋኖ አነሳስ በህይወት ለመኖር የሚደረግ ትግል እንጅ በሌሎች ላይ የተቃጣ የጠብ አጫሪነት እንቅስቃሴ አይደለም። ሰዎችህይወታቸው ከፍተኛ አደጋ ላይ ሲወድቅ፣ ቤታቸው ሲፈርስ፣ ልጆቻቸው ሲገደሉ፣ እና ድምፃቸው ሲታፈን፤ ወይ የሚደርስባቸውን መጠነ ሰፊ ጥቃት አሜን ብለው ለመገዛት ወይም ህልውናቸውን ለማስጠበቅ ተደራጅተው መታገልን ለመምረጥ ይገደዳሉ።
የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ራስን በመከላከል ላይብቻ የተገደበ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያን በጥላቻና በዘር ከከፋፈለው የፖለቲካ ስርዓት ማላቀቅንም ያለመ ትግል ነው። የፋኖ ትግል የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ እየደረሰበት ያለውን መገለል በጉልህ የሚያሳይ ነው። ተጋድሏቸውም የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን አስገዳጅ ነባራዊ ሁኔታ ነው።
3.2. የአማራ ትግል፡ ለህልውና እና ለፍትህ የሚደረግ ህዝባዊ ተጋድሎ
እየተደረገባለው ህዝባዊ ተጋድሎ፤ የትኛውም ቡድን፣ ግለሰብ፣ ወይም መሪ የአማራ ህዝብ ለህልውና የሚያደርገውን ትግል ብቸኛ ባለቤት ነኝ ብሎ ሊጠይቅ አይችልም። ይህንን ትግል በብቸኝነት ያመጣው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ወይምቡድን የለም። ትግሉ ህዝባዊነትን የተላበሰ፣ እንደ ህዝብ በፅናት መቆም የተቻለበት፣ እንደ ህዝብ መስዋዕትነት የተከፈለበት እና ህልውናውን ለማስከበር የሚደረግ ፅኑ ተጋድሎ ነው። የአማራ ህዝብ ትግል ህልውናን ለማስከበር የሚደረግ ትግል እንጅ እንደ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ብቻ ሊታይ የሚገባው ትግል አይደለም። አማራ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ቢኖር፣ ደህንነቱን እስኪያረጋግጥ፣ በማንነቱ ምክንያት ለጥቃት የማይጋለጥህዝብ እስከሚሆን ድረስ፣ ከሚመጣው እልቂት፣ መፈናቀል እና መጥፋት ስጋት ነፃ እስኪሆን ድረስ እያደረገ ካለው ህዝባዊ ትግል ውጭ ሌላ ዋስትና የለውም።
4. በአማራ ትግል ውስጥ የቀጠሉ አለመግባባቶች፡ ምክንያቶቻቸው፣ የሚያስከትሏቸዉ አሉታዊ ውጤቶች እና ለህልውና ትግሉ የሚያስፈልጉ ስልታዊ መፍትሄዎች
ባለፉት ከሃምሳ ዓመታት በላይ፣ በተለይም ደግሞ ባለፉት ሰባት ዓመታት፣ የአማራ ሕዝብ ስልታዊ ጥቃት፣ እልቂት፣ መፈናቀል እና የፖለቲካ መገለል ገጥሞታል። ይህ ሁኔታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አገዛዝ እጅግ ተባብሶ በመላው የአማራ ክልል በድሮን ጥቃቶች፣ በወታደራዊ ዘመቻዎች እና ወሳኝ መሰረተ ልማቶች ወድመዋል። የአማራ ህዝብ ለብዙ አሥርተ ዓመታትጥቃት ሲደርስበት የቆየ ህዝብ ቢሆንም፣ ለስርዓታዊ ጥቃት ምላሽ በመስጠት ፋንታ በፖለቲካ የተከፋፈለ እና ያልተደራጀ ሆኖ ይቷዋል። በአንፃሩ የትግራይ እና የኦሮሞ ህዝቦች ጠንካራ ውስጣዊ አንድነትን አሳይተዋል፣ አሉብን የሚሏቸውን ስጋቶች ለመመከት ውጤታማ በሆነ መንገድ መንቀሳቀስ ችለዋል። አማራ የገጠሙትን የልዩነት ምክንያቶች ለመተንተን፤ ሥር የሰደዱ ምክንያቶችን፣ አሉታዊ ውጤቶቹን መመርመር እና ከኦሮሙማ መራሹ ብልጽግና ፓርቲ ጋር ለሚደረገው ተጋድሎ ዘለቄታዊ አንድነትን ማምጣት የሚያስችል ስልታዊ ማዕቀፍ ማቅረብን ያካትታል። 4.1. በአማራ ትግል የሚታዩ የልዩነት ምክንያቶች
ሀ. የፖለቲካ እና የርዕዮተ ዓለም ክፍፍል ውርሶች
አማራን እንዳይግባባ ካደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ፖለቲካዊ ክፍፍል አንዱ ነው። በህወሓት (ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) ስር ጠንካራ ፖለቲካዊ አንድነትን መገንባት ከቻሉት ትግሬዎች እና እንደ ኦነግ (ኦሮሞ ነጻነት ግንባር) እና የዐቢይ አህመድ ኦሮሙማ ፕሮጀክት ያሉ ጠንካራ የብሔርተኝነት እንቅስቃሴዎችን መገንባት ከቻለው የኦሮሞ ህዝብ አንፃር ሲታይ፤ የአማራ ህዝብ ወጥ እና ዘላቂ የሆነ የፖለቲካ ድርጅት ማቆም ሲሳነው ተመልክተናል። ለዚህ ችግር መንስዔ የሆኑት ቁልፍ ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታል፦
- የሚጣረሱ የፖለቲካ ውግንናዎች፦ የአማራ ክልልን የፖለቲካ ከባቢ ስንመለከት፤ በፌደራሊስቶች፣ በአንድነት አቀንቃኞች እና የአሁኑን መንግስት በሚደግፉ ወገኖች መካከል
የተከፋፈለ የፖለቲካ ምህዳርን ያሳያል።
- ጠንካራና የተማከለ አመራር አለመኖር፦እንደ ህወሓት ወይም ኦነግ ጠንካራ ተዋረድ ያለው አመራር ከማስጠበቅ በተቃራኒ እንደ ፋኖ ያሉ የአማራ ሃይሎች ያልተማከለ እና አብዛኛውንጊዜ ባልተቀናጀ መዋቅር ውስጥ ይሰራሉ።
- የመንግስት ሰርጎ ገብነት እና ትግልን ጠላፊዎች መኖር፦ የመንግሥት ሃይሎች፤ በዋናነት በህወሓት እና በኦሮሙማ ስምሪት የሚሰጣቸው አካላት፣ የአማራ ትግል መሪዎችን በመደለል እና የትግሉን መሠረት በማዳከም በአማራ የፖለቲካ ውስጥ አለመግባባቶች እንዲፈጠሩ በተጠና ሁኔታ ሲሰር ቆይተዋል።
ለ. የጎሳ ፌደራሊዝም ወጥመድ እና የክልላዊ ቁጥጥር አለመኖር
የኢትዮጵያ የዘር ፌደራሊዝም ሥርዓት በብሔሮች መካከል የተለያዩ ክፍፍሎችን እየዘረጋ የአስተዳደር ሥልጣንን ለንዑስ ብሔርተኛ ቡድኖች ይሰጣል። ጠንካራ ማዕከላዊ የንዑስ ብሔርተኝነት-ግዛቶች ከሆኑት የኦሮሚያ እና የትግራይ ክልሎች በተቃራኒ አማራ በራሱ የክልል አስተዳደር ላይ በወርድ እና ቁመቱ ልክ አስተዳደራዊ ቁጥጥር የለውም።
- ወጥነት ያለው የክልል አስተዳደር እጦት፦ ትግራይ እና ኦሮሚያ ጠንካራ የሆነ ብሔር ተኮር አስተዳደሮች ሲኖሯቸው፣ የአማራ ክልል አስተዳደር ግን ደካማ እና በውጫዊ ሁኔታዎች ተፅዕኖ ይደረግበታል።
- የአማራ ህዝብ ተበታትኖ መኖሩ፦በሚተዳደሩበት ክልል አንድ ላይ መኖር ከቻሉት ሌሎች ብሔሮች በተቃራኒ፤ በሚሊዮን የሚቆጠረው የአማራ ህዝብ እንደ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ደቡብ ክልሎች ውስጥ አናሳ እና ለጥቃት ተጋላጭ ሆነው እንዲኖሩ የተደረጉበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በዚህም አማራው እንደ ህዝብ ሰፊና የጋራ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳይችል
እክል ፈጥሮበታል።
ሐ. ስነ-ልቦናዊ እና ባህላዊ ምክንያቶች
የአማራ ህዝብ ከብሔር ማንነት ይልቅ ይልቅ ኢትዮጵያዊ አድርጎ ሲመለከት ኖሯል። ራስን በሀገራዊ ብሔራዊ ማንነት መግለጫ ክቡር ቢሆንም፤ የንዑስ ብሔርተኝነት ዕሳቤ በነገሰበት የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ አማራን ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን አድርጎታል።
✔ በብሔር ማንነት መሰባሰብን መጠየፍ፦ የንዑስ ብሔርተኝነት ንቅናቄን በግልጽ ከሚያራምዱት ትግራዮች እና ኦሮሞዎች በተቃራኒ ብዙ አማሮች የኢትዮጵያን አንድነት ይቃረናል ብለው በመፍራት በብሔር ማንነታቸው ለመደራጀት ያመነታሉ።
✔ በጋራ ከመታገል ይልቅ ግለኝነትን ማስቀደም፦ ብዙውን ጊዜ አማራ በራስ
ለመተማመን ከፍተኛ ዋጋ የመስጠት ባህል አለው። ይህ የግለኝነት ልማድ ብዙውን ጊዜ ጠንካራ አንድነት ያላቸው አማራዊ እንቅስቃሴዎችን ለመመስረት ፈቃደኛ እንዳይሆኑ አድርጓል።
5. የአማራው አለመግባባት ያስከተለቻው አሉታዊ ውጤቶች
በአማራ ህዝብ ላይ ያላቋረጡ ጥቃቶች ሲፈፀሙ ቢኖሩም የአማራ ህዝብ ተከፋፍሎ ቆይቷል። ምክንያቶቹ የሚከተሉትን ጉዳዮች ያካትታሉ፦
ሀ. የፖለቲካ እና የአመራር መበታተን
- የአማራ ፖለቲካ እንደ የተማከለ ፖለቲካዊ ውቅር ካላቸው ህወሓት እና ኦነግ በተቃራኒ እርስ በርስ በሚጋጩ ርዕዮተ ዓለማዊ ዕሳቤዎች እና በተለያዩ አንጃዎች የተከፋፈለ እንዲሆን አድርጓል።
- የመንግስት የመሪዎች ተባባሪነት ተከታታይ መንግስታት ጠንካራ እና አንድ የሆነ ተቃውሞ እንዳይፈጠር በአማራ ትግል መሪዎች ውስጥ ሰርገው እንዲገቡ አስችሏል።
ለ. በጎሳ ፌደራሊዝም እና በተጠና መልኩ ማዳከም
- የጎሳ ፌደራሊዝም አወቃቀር እና ሕገ መንግስቱ ሌሎች ብሔሮች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በመስጠትና ጠንካራ የፖለቲካ አደረጃጀት እንዲኖራቸው ሲያደርግ አማራን ግን በራሱ ክልል ሳይቀር ሙሉ አስተዳደራዊ ቁጥጥር እንዳይኖረው አድርጓል።
- ከአማራ ክልል ውጭ (በኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወዘተ) የሚኖሩ አማራዎች ምንም አይነት የፖለቲካ ወይም ወታደራዊ ጥበቃ የላቸውም።
ሐ. ባህላዊ እና ስነ ልቦናዊ እንቅፋቶች
- የሀገራዊ ማንነት የብሔር ማንነት ውዝግቦች፦ብዙ አማሮች እራሳቸውን በመጀመሪያ ኢትዮጵያውያን አድርገው በመመልከታቸው ምክንያት አማራ ልክ እንደ ኦሮሞ እና ትግሬ በማንነቱ ተጠናክሮ ለመታገል እክል ገጥሞታል።
- ከመጠን ያለፈ ግለሰባዊነት፦ በጋራ መታገልን ከሚያስቀድሙ ሌሎች ብሔሮች በተቃራኒ አማራ ብዙውን ጊዜ በግል ህልውና ላይ የሚያተኩር ማህበረሰብ በመሆኑ የጋራ የትግል ንቅናቄዎችን ለመፍጠር ተቸግሯል።