መነሻውን ጅቡቲ መዳረሻውን ሞጆ አደርጎ ወታደራዊ መሳሪያዎቸን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ባቡር ሱማሌ ክልል ኤረር አካባቢ የተቃጠለ ሲሆን በዚህ ቃጠሎ ኮንታክት ዋየር፣ ሚሴንጀር ዋየር ሙሉ ለሙሉ ወድሟል፣ ፍርጎው ሙሉ ለሙሉ እየወደመ ሲሆን፣ ሀዲዱ በመቅለጥ ላይ ላይ እንዳለ ለኢትዮ 251 ሚዲያ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ምንጮች አክለውም እሳቱን አሁን በከፍተኛ ሁኔታ እየነደደ እንደሆነ ገልጸው የሚፈነዳ ነገር ይሰማል ብለዋል፡፡ የተቃጠለው ኮንቲነር ከወታደራዊ መሳሪያዎች በተጨማሪ ምንነቱ ያልታወቀ ተቀጣጣይ ነገር ይዞ ሲጓዝ እንደነበር የውስጥ የመረጃ ምንጮች ለኢትዮ 251 ሚዲያ አክለው ገልጸዋል።
ኢትዮ 251 ሚዲያ