tefera mamo
ብሥራት ደረሠ (አዲስ አበባ)
በሰላምታ ልጀምር፡፡ እንደምን ሰነበታችሁ አንባቢያን፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ደግሞ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንደኛው ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመጋቢት 27 በሰላም አደረሣችሁ፡፡ የፊታችን ሚያዝያ 12 ቀን 2017ዓ.ም የሚከበረው የጌታ ትንሣኤ የኢትዮጵያንም ትንሣኤ ደርበን እንድናከብር የአምላክ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ ለርሱ የማይቻል ነገር የለምና ከልብ ከጸለይን ከገባንበት የመከራ አዘቅት ለማውጣት አባታችን ኅያው እግዚአብሔር አፍታ አይፈጅበትም፡፡
ወደተፌ ከመሄዴ በፊት አንዳንድ ንዴቶቼን ላስቀድም፡፡ አቢይንና ኢብራሂም ትራኦሬን ሳስብ ራስህን እነቅ እነቅ የሚል ስሜት መላ አካሌን ይወረኛል፡፡ እውነቴን ነው፡፡ በኢትዮጵያዊነቴም ሽምቅቅ ብዬ አፍራለሁ፡፡ 130 ሚሊዮን ሕዝብ አምጦ የወለደው አቢይ አህመድ በሰባት ዓመታት የሠራንን ጉድና የቡርኪና ፋሶው መሪ ትራኦሬ በሁለት ዓመታት ለሀገሩ የሠራው የእውነተኛ ብልጽግና ትሩፋት ሲነጻጸር ኢትዮጵያውያን በቁጭትና በንዴት ብናብድ ቡርኪናዎች ደግሞ በደስታ ሰክረው በሃሤት ባሕር ቢዋኙ የፈጣሪን ግለልጽ አድልዖ ከመታዘብ በዘለለ ምንም ማለት አይቻልም፡፡ የ37 ዓመቱ ትራኦሬ ሕዝቤ ቤትአልባ አይሆንም ብሎ ቤት እየሠራ ለሌላቸው በሰልፍ ሲያድል የ50 ዓመቱ ጎልማሣ አቢይ አህመድ ዘር እየመረጠ በየቀኑ ቤታቸውን በልማት ስም በማፍረስ ሚሊዮኖችን ያፈናቅላል፡፡ ትራኦሬ የስሚንቶን ዋጋ 50% ቀንሶ ሀገሩን ግንባታ በግንባታ ሲያደርግና የእህል ምርትን እያሣደገ ርሀብን ታሪክ ለማድረግ ሲጥር የኛው ዲያቢሎስ ለራሱ የ1.5 ትሪሊዮን ቤተ መንግሥት በመገንባትና በብዙ ቢሊዮን ብር የሚገመት የግል አውሮፕላን በመግዛት ይዝናናል፤ ይህንንም የሚያደርገው በቀን አንዴ ቁራሽ እንጀራ መቅመስ ካቃተው ምሥኪን ሠራተኛና ወዛደር በግብር፣ በቀረጥና አግባብነት ከለሌው የተለያዬ ቅጣት በሚሰበሰብ ገንዘብ ነው፡፡ በዚያ ላይ ለጦርነት የሚያወጣው ወጪ ማለትም ለጦር መሣሪያ፣ ለወታደር ደሞዝ፣ በሃያና ሠላሣ ሽህ ለሚገመቱ የግል ጠባቂ ኮማንዶዎቹ ደሞዝ፣ ለድሮንና ተዋጊ ጀቶች ግዢ፣ ለስለላና ክትትል፣ ለሎቢስቶች፣ ለሚዲያ ሠራዊት የሚወጣው ወዘተ. ሲታይ በዚህ ሰውዬ ምክንያት የሀገሪቱ ልማት ቀጥ ብሎ እንደቆመና ኢትዮጵያ ለምን ያህል ዓመታት ወደድንጋይ ዘመን እንደተሳበች መገመት አይከብድም፡፡ እኔ በግሌ የቋንቋ ችግር እንዳለብኝ የምረዳው ይህን በሰው አምሣል የተፈጠረ በላዔሰብ ለመግለጽ ቃል ሲያጥረኝ ነው፡፡ ኦሮምኛን ጨምሮ ከሰባት ሺህ በላይ የሚገመቱት የዓለማችን ቋንቋዎች አቢይን በትክክል መግለጽ የሚችል ቃል የላቸውም፡፡ ዛፍ ቢተከል ለምንገድላቸው ሰዎች አስከሬን ጥላ ይሆናቸዋል የሚል ፌዘኛ ሳዲስት እና ታማሚ እናቷን ለመመገብ ጥናቷንና ትምህርቷን ትታ መንገድ ላይ ለውዝ ስትሸጥ ያገኛትን የ8 ዓመት ሕጻን መኪናው ውስጥ አስገብቶ በሥርዓት አነጋግሮ ወደቤተ መንግሥቱ በመውሰድና ካቢኔውን በመሰበሰብ ለዚያ ዓይነቱ ሀገራዊ ችግር ዘላቂ መፍትሔ የሚያፈላልግ ቡርኪናዊ መሪ እኩል የሀገር መሪዎች ሲባሉ በትራኦሬ እንደመቀለድ ነው የሚሰማኝ፡፡
ይሄ የሰይጣን ልጅ መነሻየን አሳተኝና ወደ ዋናው ጉዳይ እንዳልገባ አዘገየኝ፡፡ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ ጥሩ ሥራ መሥራት ጀምሯል፡፡ በረሃ ከወረደ በኋላ ድምጹ ጠፍቶብኝ በበኩሌ ተቸግሬ ነበር፡፡ አሁን ግን በሱ ምህኛት ብዙ እንቶፈንቶዎች ሲንጫጩ ሰማሁ-አየሁና ሥራ መጀመሩ ገባኝ፡፡ ኢትዮጵያ መቼም የምትገርም ሀገር ከሆነች ቆየች፡፡ ባስቀመጡት የሚገኘው ሰው ቁጥር ዜሮን ሊነካ ተቃርቧል፡፡ የት ይደርሣል የተባለው ጥጃ ሁሉ ሉካንዳ ደጅ ሄዶ ሲግጥ ለመታየት አንድ ግፋ ቢል ሁለት የምግብ ሰዓት ቢፈጅበት ነው፡፡ እንዴት የመሠለው ሣተና ኢትዮጵያዊ ስለኢትዮጵያዊነት በትንታግ ምላሱ ሲምበለበል ታየውና ትንሽዬ ርሀብ ጎብኘት ስታደርገው ወይም ያቺ ለራሱ ሊያደርጋት ሌት ተቀን የሚቃዥባት ሥልጣን ልትርቀው እንደቃጣት ሲያስብ 360 ዲግሪ ይገለበጥና ወርቁን ድንጋይ ነው ብሎ ዕርፍ ይልልሃል፡፡ ይሉኝታና ሀፍረት ምናምን ትዝ አይሉትም፡፡ በዚህ የመበስበስ ሂደት ያጣናቸውን ቤታቸው ይቁጠራቸው፡፡ እኔ አሁንና እዚህ ብርሃኑ፣ ኤርምያስ፣ አጌና፣ አፍራሳ፣ ቶላ፣ ታላቁ፣ ታናሹ እያልኩ የሰው ስም አልጠራም – ነውርም ነው፡፡ ሥራቸውን በመጠኑ መጥቀስ ግን መብቴ ነው፡፡
ተፌ ምን አለ? “እስካሁን እንደታማነው ከወያኔም ሆነ ከሌላ ጋር አብረን አልሠራንም፡፡ ግን እንደዬሁኔታው አብረን ለመተጋገዝ ጥረት እናደርግ ይሆናል” የሚል ዓይነት አስተያየት ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡ በመሠረቱና እንደውነቱ ከሆነ አማራን ነፃ ለማውጣትም ይሁን ሌላ ዓላማ ይዞ እየታገለ ያለ ኃይል ከማን ጋር መተባበር እንዳለበት የሚያውቅ ራሱ ብቻ ነው፡፡ የሌላው ማሽቃበጥ ለሌላ ግላዊ ተልእኮና ፍላጎት እንጂ ለትግሉ ስኬት በማሰብ አይደለም፡፡ ሕወሓት ፀረ አማራ ነው፡፡ አብዛኛው ትግሬ ሕወሓት ነው፡፡ በመሆኑም ባለፉት ጥቂት የማይባሉ አሠርት ዓመታት በተሠሩ ስህተቶች ምክንያት በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያልተፈለገ አሉታዊ ክስተት መፈጠሩ እውነት ቢሆንም አሁን ግን ሁለቱንም የሚያጠፋ ኦሮሙማ የተባለ ጭራቅ ስለመጣ መተባበራቸው የምርጫ ጉዳይ ሣይሆን ግዴታ ነው፡፡ እንደእስካሁኑ በጠላትነት እየተያዩ የሚጃጃሉ ከሆነ ለመጥፋት ጥቂት ሣምንታት ብቻ ይቀራቸዋል፡፡ አቢይ ቀላል ሰው አይደለም፡፡ ከጎኑ የተሠለፈው እልፍ አእላፍ ዓለም አቀፍ የአጋንንት መንጋ ነው፡፡ አቢይ ከልጅነቱ ጀምሮ የተዘጋጀው አማራንና ኦርቶዶክስን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ከተሠለፈው ኃይል ጋር ሆኖ ምናባዊ የህልም ዓለም ቅዠቱን እውን ለማድረግ ነው፡፡ ለዚያ ቅዠቱ ደግሞ አማራንና ትግሬን ብቻ አይደለም እወክለዋለሁ የሚለውን ኦሮሞንና ቤተሰቡን ጭምር ለላከው ሣጥናኤል ይገብራል፡፡
እኔ አሁን ምኞቴ ብችል ትግራይ ሄጄ በወያኔ የጠፉ ወንድም እህቶቼን ወደቀደመው የጋራ መንገድ መመለስ ነው፡፡ ወልቃይትና ራያ የሚባል ነገር ቧልት ነው- እዬዬም ሲደላ ነውና፡፡ እነዚህ አካባቢዎች እንኳንስ አማራና ትግሬ የኬንያው ኪኩዩና የሦርያው አላዊ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ የእግዜር የእጅ ሥራዎች ናቸው፡፡ ዛሬ ማታ ወይ ነገ ጧት የሚሞት ሰው በማይሞት መሬት መገዳደል ከጅልነትም ባለፈ ዕብደት ነው፡፡ ለማንኛውም በመጀመሪያ አማራና ትግሬ ኅልውናቸውን ያረጋግጡ፡፡ ኦሮሙማም ብልጥ ሆኖ እነዚህን ሰሜነኞች ሲያፋጃቸው ሞራል አጣሁ እንጂ ልስቅም ይዳዳኛል፡፡ ሲገርሙ! ምን አዙሮባቸው ይሆን ይሄ የሰይጣን ልጅ?
ጄኔራል ተፈራ ቶሎ በል፡፡ ዘግይተሃል፡፡ ሰሜንን አስተባብር፡፡ የሚንጫጫውን ተወው፡፡ታዬኝ ተፌ ወያኔ ወይም ዳግማይ ይበሉት ሣልሳይ ብአዴን
ሲሆን፡፡ የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር አሉ? ማናት ያቺ ደሞ – አህያይቱ – “አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ” ብላለች የአያ ጅቦ የተንኮል አመጣጥ ቢገርማት፡፡
አንዱ ጫጫቲያም አንድ ቦታ እንዲህ አለላችሁ፤
ሰሞኑን የጀነራል ተፈራ ማሞ የፓለቲካ DNA ምርመራ ውጤት ብአዴን መሆኑን ሲሰሙ ብዙ ሰዎች በድንጋጤ ደርቀው ቀርተዋል። እስከሁን ድንጋጤው ያልለቀቃቸው ….
ተመልከቱልኝ እንግዲህ ይህን መሠል character.assassination. የአባቴ አምላክ አንተኑ አድርቆ ያስቀርህ አይባል ነገር ክርስቶስ “የሚሰድቧችሁን መርቁ” ብሎ ሳይቸግረው ማገጃ አጥር አስቀመጠብን፡፡ ብቻ ያኛው ወገን ተቅበጥብጧል፡፡ ደግሞኮ አማራ ነኝ ይላል፡፡ ይሄ የሥልጣን ፍቅርና የከርስ ነገር ገና ብዙ ያሣየናል፡፡ ወንዶች ግን ጆሯችሁን በጥጥ ድፈኑና ሥራችሁን ብቻ ሥሩ፡፡ ሥራችሁ ይናገር፡፡ የአማራ ትግል ያሸንፋል፡፡ በግለሰቦች ማምለክና ተክለ ሰውነት ግንባታ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናልና ይቅር፡፡ መልካም የሣምንት ዕረፍት፡፡ ብዙ የምለው ነበረኝ ግን ይቅር ግዴለም፡፡