የደምቢ ዶሎውን እገታ በተመለከተ ብዙ ነገር እየተባለ ቢሆንም የወንጀሉን ዓላማ በመግለጥ ወንጀለኛው ማን እንደነበር የሚያጋልጥ ጽሑፍ እስካሁን አላየንም። (የማንበብ ትእግስት የሌላችሁ የእገታውን እኩይ ምክንያት ወደሚያትተው ወደ ክፍል ሁለት ንባብ እንድትሄዱ ትጠቆማላችሁ)
የእነዚህን ልጆች እገታ እንደተከታተለ፣ እገታቸውን በአደባባይ ሰልፎች እንዳጋለጠ፣ ተደጋጋሚ ጽሑፍና ግጥሞችን ለመታሰቢያቸው እንደጻፈ አንድ ሰው፣ የእገታው ባለቤት ማን ይመስልሃል? ብለው ወዳጆቼ ለሚጠይቁኝ ጥያቄ ያለኝን ምላሽ ነው የማካፍላችሁ። ለባለሙያዎችና ተመራማሪዎች መነሻ ሃሳብ ይሆናቸዋል በሚል የተጻፈ ነው።
ብርቱካን የተባለችው በኢቢኤስ የቀረበች ወጣት ለጽሑፍ መነሻ ትሁን እንጂ ልጂቷ በደንቢ ዶሎ በመጀመሪያው ዙር ከታገቱት 17 ልጆች ወይም ሁለት አመት ቆይቶ በሁለተኛ ዙር ከታገቱት 10 ልጆች ወይም በሌላ ቦታ ከታገቱት እልፍ ሴቶች መካከል ትሁን አትሁን ሳይሆን ቁም ነገሩ የዚህ የደምቢ ዶሎ እገታ ወንጀል መነሳትን አስታከን ስለ ደምቢ ዶሎ የአማራ ተማሪዎች እገታ እንድንወያይ ምክንያት ስለሆነችን ነው።
የደምቢ ዶሎን እገታ ስንከታተል መረጃዎች ሁሉ ተሰብስበው አቢይ አህመድ ቢሮ እንደተቆለፈባቸው እናውቃለን። ስለ እገታዎቹ ሁነኛ መረጃ ያለውም ንጉሡ ጥላሁን ዘንድ እንደነበረም ይሄንንም መረጃ ለአቢይ እንዳስተላለፈ እናውቃለን። እገታውን ካቀነባብረው ኃይል በተጨማሪ ለማለት ነው።
እገታው ጭካኔ የተሞላበትም ቢሆን ከተለመደና ተራ የዘረፋ ወንጀል ከሆነው የሸኔ የገንዘብ አምጡ እገታ መለየቱን ማንም የሚያስተውለው ነው። ሸኔ የፖለቲካ እገታ አይፈጽምም ለማለት አይደለም።
እገታው ፖለቲካዊ ዐላማ የነበረው ነበር። ሰሞኑን እገታውን ኮሬ ነጌኛ ነው ያካሄደው፣ በፊት ደግሞ ኦነግ ነው፣ ከዚያ በኋላ ደግሞ የነአቢይ ሸኔ ነው፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የነጃዋር ሸኔ ነው የሚሉ መላ ምቶች ተሰምተዋል። ሸኔ አማራን ከኦሮሞ ክልል የሚያጸዳ ማሽን እንደመሆኑ የአማራ የኮሌጅ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ክልል ተነቅለው እንዲወጡ የሽብር ተግባር መፈጸሙ ተጠባቂ ነው። ከደምቢ ዶሎዎቹ ታጋቾች ሌሎች በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተማሪዎች ከየሄዱበት ኮሌጆች ጠፍተው ወደ ቤተሰብ እንዲመለሱ የተደረገበትን የቅድመ ኮቪድ ሽብር ማን ይረሳል? ዛሬ በብርቱካን ምክንያት ጉዳዩ አደባባይ ስለወጣ እንጂ በመቶዎች በሚቆጠሩ የጸበል ቦታዎች የሚንከራተቱት እነዚያን አእላፍ ልጆች ቤት ይቁጠራቸው። እኔ እንኳን የማውቃቸው የቤተሰብ አባላት አሉ፣ እስከዛሬም ጸበል ለጸበል የሚደክሙ።
በዚያን ወቅት ትልቁ የፖለቲካ ዓላማ ምን ነበር? ይህንን ወንጀል ለመፈጸም በእንግሊዝኛ ሞቲቭ፣ ኦፖርቹኒቲ፣ እና ዌፐን (ሚንስ) እንደሚባለው መግደያ ምክንያት (ተነሳሽነት)፣ የመግደል እድልና የመግደያ መሣሪያው የነበረው ማን ነበር ብለን እንመራመር። የአቢይ፣ የሽሜ፣ የጃዋር፣ የጃል መሮ ሸኔዎች ሁሉም ይህን ሁሉ ያሟላሉ። ይሁንና የነአቢይን ሸኔ ከተመለከትን በዚያን ጊዜ እነ አቢይ ገና ለምርጫ ዝግጅት የሚያደርጉበት ዘመን ስለነበረ የመግደያ ምክንያቱን እጅግ ደካማ ያደርገዋል። በወንጀል ምርመራ ኤክስፐርትነት ሳያስፈልገን ነጥቦችን በማገጣጠም የወንጀሉን ፈጻሚ እናገኘዋለን። ወንጀርሉ አማራን አፍኖ ገንዘብ ከሚጠየቅበት የሸኔ የተለመደ የእገታ ወንጀል የተለየ ስለነበረ ብቻም አይደለም።
በዚያን ወቅት የልጆቹ አጋቾች ከቤተሰብ ሲደወል ያቀርቡት የነበረውን ጥያቄ ብንመለከት ጥያቄያቸው የአማራ ክልል ሕዝብ በነቂስ በአቢይ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲወጣ ይደረግ የሚል ነበር። የቢቢሲና የዘሐበሻን የወቅቱ ዘገባዎች ይመለከቷል። ይህ የወንጀሉን ምክንያት እንድናውቅ ይረዳናል። አቢይ የአማራ ክልል ሕዝብ በተቃውሞ ቢሰለፍበት በኦሮሚያ መጠነኛ የማይባል ድጋፍ እንደሚያገኝ ይታወቃል። ቢሆንም ለዚህ ተጨማሪ ድጋፍ ሲል በአማራ ክልል የነበረውን ከፍተኛ ተቀባይነት ዜሮ በሚያስገባው መልኩ ይሄዳል ተብሎ አይታመንም። ለጃል መሮው ሸኔ ወይም ኦነጦ ደግሞ ይህ የአማራ ክልል ተቃውሞ ለፖለቲካው ይጠቅመዋል ተብሎም አይታሰብም።
ታድያ ለማን ነው የደምቢ ዶሎ እገታ በተፈጸመበት በዚያ ወቃት ‘አቢይ አህመድን እና አማራን ማለያየት’ ትልቅ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ የነበረው? ብለን እንጠይቅ።
እስካሁን የመግደያ ምክንያት፣ እድልና መሣሪያ ከነበራቸው ወንጀለኞች የስም ተራ ያልጠቀስነው ሕወሃትን ነው። ሕወሃት እነዚህ የወንጀሉ 3 ዐበይት መመርመሪያ መለኪያዎችን ታሟላ ነበር ወይ? መልሱ አዎ ነው። ሕወሃት በኦሮሞ ክልል፣ በወለጋ በተለይ በደምቢ ዶሎ በሸኔም ውስጥ ሆነ በኮሌጅና በኅብረተሰቡ ሰፊ ኃይል እንዳላት ይታወቃል። በ77 ድርቅ ጊዜ በወለጋ ከሰፈሩ የትግራይ ልጆች እጅግ ብዙ የሕወሃት አባላት ሸኔን መቀላቀላቸው ይታወቃል። በሰላይነት የሚሠሩም በዚያው በኦሮሞ መካከል ተወልደው ያደጉ ሺዎች እንዳሏት ይታወቃል። ከትግሬ ነገድ ውጭም ብዙ የኦሮሞ ተላላኪዎች የነበሯትና ያላት ድርጅት ናት። መሣሪያውም ሆነ እድሉ ነበራት። ከላይ ካሉት ሌሎች ወንጀለኞች ሕወሃትን ለየት የሚያደርጋት ግን የወንጀል ምክንያቱ ነው።
ወቅቱ ምን ነበር?
ሕወሃትና አቢይ አህመድ ለእርስ በእርስ ጦርነት ሰፊ ዝግጅት የሚያደርጉበት ወቅት ነበር። ሕወሃት ደግሞ ከምሥረታዋ የሚታወቅ ባሕርይ አላት። ወደ ፍጥጫ ስትገባ ግዙፉ የቅድመ ዝግጅት አካል አድርጋ የምትጠቀመው ጠላቷን ከሕዝብ የመነጠልን ስትራቴጂ ነው። ሕወሃት ማንንም ከሕዝብ የመነጠል ሥራ አስቀድማ ሳትሰራ ጦርነት ገጥማ አታውቅም። አንድ ግለሰብ እንኳን ቢሆን። የስኬቷ አንዱም ምስጤር ይኸው ነበር (ከአቢይ አህመድ በስተቀር በሕወሃት ረጅምና በስኬት የደመቀ የትግል ጉዞ ድል ያደረጋት አልነበረም። ጀብሃን፣ ትነግን፣ ኢዲዮን፣ ኢሕአፓን፣ ደርግን፣ ሻዕቢያን ደምስሳለች)። ጠላትን ከሕዝብ መነጠል አስቀድማ በትጋት የምትሠራው የቅድመ ጦርነት ዝጅግቷ ግዙፍ አካል ነው። አቢይ አህመድን ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ከነበረው ከአማራ ክልል ሕዝብ የሚነጥለው ዘመቻ ሳታካሂድ ወደ ጦርነት ልትገባ አትችልም።
ለዚህም ነው በእገታው ታሪካዊ ሰዐት ላይ ቆመን ወንጀሉን ለመፈጸም ትልቁ የወንጀል ምክንያት የነበራት ሕወሃት ነበረች ለማለት የምንችለው። እስኪ ደግሞ ወደ መረጃው እንሂድ።
ልጆቹ በተደጋጋሚ ወደ ቤተሰብ የመደወል እድል ባገኙ ጊዜ ይሉ የነበሩት “በክልሉ ጸረ መንግሥት ሰልፍ እንዲወጣ አድርጉልን” ነበር። እርግጥም በአማራ ክልል እስከመንደርና ቀበሌ ድረስ ክልል አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ተወጥቷል። ከጦርነቱ ጥቂት ጊዜያት በፊት። (ሰልፉና ጦርነቱ በዚያው በፈረንጆች 2020 እንደነበር ልብ ይሏል።) ድብልቅልቅ ላለው የተቃውሞ ሰልፍ አንዱና ዋናው መግፍኤም ይኸው እገታ ነበር።
ነገሩ በቡዳ ቤት ሰላቢ ገባ ሆነና አቢይ አህመድም የጦርነት ዝግጅትና ከበባውን ባጠናቀቀ ወቅት የነሱን ስትራቴጂ በላያቸው ገልብጦ ባደራጀው ሸኔ በኩል አማሮችን በወለጋ አርዶና ጨፍጭፎ በሸኔና በሕወሃት በማላከክ በፓርላማ አስለቅሶ ፕሮፓጋንዳውን ቀልብሶ የተሳካ ዘመቻ አከናውኖባቸዋል።
አሁን ጥያቄው መሆን ያለበት አቢይ አህመድ ማስረጃዎቹን ሁሉ ከሰበሰበ በኋላ ለምን ደበቃቸው? የሚለው ነው። ማስረጃው ሕወሃትን የሚጎዳ ከሆነ ለምን አውጥቶ እነሱን ለማጥቂያ አልተጠቀመውም? የሚለው ጥያቄ ማለት ነው። የዚህን ትክክለኛ መልስ ለማግኘት ያስቸግራል። እንደኔ ጊዜው ገና ስለሆነ ይመስለኛል። አንዳንድ ነጥቦችን ስናገጣጥም አቢይ አህመድ በኦሮሚያ የሚደረገውን የአማሮች ጭፍጨፋ (የእስካሁኑን ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት ሊፈጽሙ የተዘጋጁትን ከአሥርና ሃያ ሚልዮን በላይ አማራና ኦርቶዶክስ የሚጨፈጭፉበትን ማለቴ ነው) በነዚህ በኦሮሚያ ተወላጅ ትግሬዎችና በኦርቶዶክስ ኦሮሞዎች ላይ የማላከክ ትልቅ ዝግጅት ያለው ይመስለኛል። ከምሥጢራዊ የኦህዴድ/ኦነጋውያን ስብሰባ የወጡ የድምጽ ቅጂዎች በኦሮሚያ ተወላጅ ተጋሩ የሸኔ አባላት ላይ የታቀደውን ይፋ ማድረጋቸውን እናስታውስ። የአብይን ጄኖሳይዳዊ ትልም ይበልጥ ለማብራራት አቢይ የሚከተለው ፍኖተ ካርታ የፖል ካጋሜን ሩዋንዳዊ መንገድ ነው። የጄኖሳይዱ ዋና አስፈጻሚ የባእዳን ተላላኪ የሆነው ካጋሜ ጄኖሳይዱን ካስፈጸመ በኋላ እንደ አቢይ አይነት የእርቅ ምናምንቴ ኮሚሽን አቋቁሞ በወንጀሉ ተጠያቂ ሳይሆን ለሰላሣ አመታት በሥልጣን የዘለቀበትን መንገድ ማለቴ ነው።
አቢይ እነ ሽመልስ አብዲሳ፣ አዳነች አቤቤና ሌሎች መሠረተ ሸዋ ኦርቶዶክስ ኦሮሞዎችን በዚህ በአማራ ጄኖሳይድ ተጠያቂ አድርጎ ለእርድም፣ ለፍርድም ወይም ለኮሚሽናዊ ይቅርታም እነሱን ጭዳ ካደረገ በኋላ ያዘጋጀውን የወሃቢ መስመር ወደፊት በማምጣት ሙሉ ቁጥጥር ለማድረግ እንደተዘጋጀ ከበቂ በላይ ፍንጮች አሉ። ለዚህም ያለ ጊዜው ፈንድተው የነበሩ የነአንጋሳ ኢብራሂምን በሽመልስ ካቢኔ ላይ የተደረጉ ንግግሮች፣ ዛሬ በምክትልነት የቢሮ ኃላፊነት ቦታዎችን የያዙ የነገ ተተኪዎችን ማንነት በመፈተሽና የብልጽግና የክልል ቢሮዎችን ሙሉ በሙሉ እነ ማን እንደተቆጣጠሩ በማየት ሥዕሉን ለማግኘት ይቻላል። በዐቢይ አህመድ ፕሮጄክት ውስጥ ንቁ ተሳታፊዎቹ እነ አህመዲን ጀበል ሲሆኑ ዴዴብ ተሳታፊዎቹ ደግሞ እነ ለማ መገርሳ፣ እነ ሽመልስ አብዲሳ፣ እነ አዳነች አቤቤ፣ እነ መረራ ጉዲና፣ እነ በቀለ ገርባ፣ እነ አዲሱ አረጋ፣ እነ ታከለ ኡማ ናቸው። እነዚህ የራሳቸውን ማኅበረሰብ ያስከበቡ፣ ያስወረሩ፣ ያስደፈሩ፣ ያስዘረፉ ጅሎች በአቢይ ፍኖተ ካርታ መሠረት ኤክስፓየሪ ዴታቸው ሩቅ አይደለም። ዋና ተፈላጊነታቸው አማራውን በተመለከተ በወንጀል ጓንቲነት እና ቱለማን በተመለከተ ደግሞ ከብቦ ለማድቀቅ ብቻ ነው።
በክፍል ሁለት እንገኛኝ።
በክፍል ሦስት የአጋቹን ማንነት በወንጀሉ ምክንያት መነሻነት መርምረን ጆሮን ጭው የሚያደርገውን እዚህ ያልተጠቀሰ የወንጀል ዓላማ እንገልጣለን።
በቸር ይግጠመን