ከባዱ የፋኖ “ዘመቻ አንድነት” ውጊያ/ ፋኖ በጎንደርና ባሕርዳር ከተማ ዙሪያ/የኤርትራ ክስና የጀኔራል ምግበ ጉዳይ March 23, 2025 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ከባዱ የፋኖ “ዘመቻ አንድነት” ውጊያ/ ፋኖ በጎንደርና ባሕርዳር ከተማ ዙሪያ/የኤርትራ ክስና የጀኔራል ምግበ ጉዳይ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email 2 Comments ሌባ ስርቆት ከመሄድ በፊት ለጌዪርጊስ ይሳላል ይላሉ አበው። የወያኔና የሻቢያ ጥምረት እኔም ጉንድሽ አንተም ጉንድሽ ለመባባል እንጂ ለህዝባቸው አንዳችም የሚቀይረው ነገር የለም። በቅርቡ ወሬ ቀማሚውና ወያኔ አፍቃሪው “የሴራ እርካብ የደም መንበር” ጸሃፊ የወያኔውን የባህል ጄኔራል ምግበን ቃለ መጠየቅ ብጤ አድርጎለት ነበር። ሸፍጠኛው የወያኔ ወታደር በአነጋገርም ባመላለስም ከጠያቂው ልቆ በመስማቴ ተደንቄአለሁ። ይህም ሆኖ አልፎ አልፎ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያሾልክ ነበር። ለምሳሌ ሃገረ ትግራይ ስንሆን፤ የትግራይን ህዝብ ነጻ ስናወጣ በማለት እየተናገረ ጋዜጠኛው ላቀረበለት አንድና ሁለት ቀጥተኛ ጥያቄም ይለፈኝ ብሎታል። መወስለትን ተክነውበታል። አቶ ጌታቸው ረዳ ነፍሴ አውጭኝ በማለት የሾማቸውን ሰዎች ለወያኔ እስራትና ግርፋት አጋልጦ ወደ አዲስ አበባ ከኮበለለ በህዋላ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ መቀሌ እመለሳለሁ ካለን እንሆ ሶስተኛ ሳምንቱን ያዘ። እነዚህ ሙቶች ለሃገርም ለትግራይ ህዝብም እንደማይጠቅሙ ገና ከጅምራቸው ግልጽ ቢሆንም አሁንም የእነርሱ ደጋፊዎችና ፍርፋሪ ለቃሚዎች በዚህም በዚያም አለን ይላሉ። ይህ ሁሉ ግን ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው። ፓለቲካ የቀትር ጥላ ነው። ከጊዜ ጋር የሚሰወር። አሁን በእውነት ፋኖና ወያኔ አንድ ላይ በመሆን ተዋግተው ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም ያመጣሉ? የሚሉሽን ብትሰሚ ገቢያም ባልወጣሽ ነው ነገርየው። ሲጀመር የወያኔው ደም አፍሳሽ ምግበ የፋኖ አመራር ውስጥ የሚገባበት አንድም መንገድ የለም። ወሬው የፈጠራ ያው አሞራውን ጅግራ ነው ብለው ለመብላት ያሰራጩት የፓለቲካ ስልት ነው። ትላንት የአማራን ህዝብና የአፋርን ህዝብ ያበራየ ደም አፍሳሽ ምን ያህል ልቡ ቢለወጥ ነው ከፋኖ ጋር ሆኖ ለዚያውም በአመራር ላይ የሚዋጋው? የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር እንዲሉ ነው ጉዳዪ። በሌላ መልኩ ግን ወያኔ ከሻቢያ ጋር ማበሩ ምንም እማኝ የሚያስፈልገው ነገር አይደለም። ለዚህ ነው ወያኔ ማለት እስስት ነው የምንለው። በአንድ በኩል የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ መሬትን ተቆጣጥረው እንዴት የፊደራል መንግስቱ ዝም ይላል ይላሉ። በሌላ በኩል ከሻቢያ ጋር ቂጥ ገጥመው ራሳቸውን ለጦርነት ያዘጋጃሉ። ሲጀመር ማን ሆነና ነው “የኤርትራን መገንጠልና ሃገር መሆን እወቁልኝ” እያለ በተመድና በአውሮፓ ከተሞች ሲዋትት የነበረው? ቆርሶ እንካችሁ ያለውን ምድርና ሃገር አሁን ወረረኝ ያዘብኝ እያሉ መዘላበድ የራስን ስልጣን ለማሰንበት የሚደረግ የፓለቲካ እቃ እቃ ጫዋታ ነው። ባጭሩ የብልጽግናው መንግስትና ሻቢያ/ወያኔ መፋለጣቸው አይቀሬ ነው። ያለ ባሩድ ሽታ መኖር አይችሉምና። ይህም በመሆኑ ውጊያው ትግራይ ውስጥ እንዳይሆን ሁሉም ነገር በአማራና በአፋር ክልል ላይ ተቆልሎ የሚገኘው። ይሄ ሁሉ የፓለቲካ ስህተት ብልጽግናን ዞሮ እንደሚገዳደረው ገና የስሜን ጦርን ወያኔ መትቶ ብልጽግና መቀሌ ከገባ በህዋላ ሙትና ቁስለኛውን ትቶ ከወጣ በህዋላ ነው። የፕሪቶሪያ ስምምነት/የናይሮቢ የውል ስምምነትና ማሻሻያ ሃስብ ሁሉ ለወያኔ የጊዜ መግዣ እንጂ ጭራሽ ትጥቅ እንደማይፈቱ የምናውቃቸው እናውቅ ነበር። ተፈታ ተብሎ ወደ 100ሺ ብር ለአንድ የወያኔ ታጣቂ ለማቋቋሚያ እየተሰጠ ብልጽግና ተረከብኩ ያለውም መሳሪያ የዛገና የሻገተ ወያኔ ከማህል ሃገር ጭኖ መቀሌ አምጥቶ አቧራ ሲጠጣ የነበረ የማይሰራ የመሳሪያ ክምር ነው። ዲዲአርም እንዳይሳካ ብዙ ጫና በጦርነት ፈላጊዎቹ የወያኔ ደም አፍሳሾች በኩል እንደነበረ የአዲስ አበባ መንግስት ያውቃል። ወያኔን ለምኖ ተለማምጦ ወደ ሰላም ማምጣት አይቻልም። ግን ብልጽግና ጠቡ ከአማራ ህዝብ ጋር እንጂ ከወያኔ ጋር አይደለም። ስንቶች አማሮች ናቸው ምንም ባላረጉት ታፍነው ጨለማ ቤት ውስጥ ያሉት? የገደሉት፤ የዘረፉት፤ ሃገርና ምድርን የሚያሸብሩት የወያኔ አለቆች ግን በሸራተን መግለጫ ይሰጣሉ፤ መቀሌ ላይ ናና ግጠመን ይላሉ። ግን እድሜ ለሻቢያና ወያኔ እንዲሁም ለጠባብ ብሄርተኞቹ የኦሮሞ ፓለቲከኞች የችግራቸው ምንጭ ሁሉ የአማራ ህዝብ ነው እያሉ ህዝባቸውን በውሸት ትርክት ስለጋቱ ውጊያው ከአማራ ህዝብና አጎራባች ክልሎች ጋር ይሆናል። ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ! ስናሳዝን። በማጠቃለያው ፋኖ፤ ብልጽግና፤ ወያኔና ሻቢያ፤ እንዲሁም አውቶቡስ እያስቆመ ዘር እየመረጠ የሚያፍነው እኩዪ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ነኝ የሚሉት ድኩማኖች ሁሉ ድርሻቸው አንድ ነው። እየገደሉ መሞት፤ እየሞቱ መኖር፤ እያስለቀሱ መሳቅ፤ እየሳቁ ማልቀስ። ህባችን በማሸበርና መከራ ውስጥ በመክተት የሚመጣ አንድም ነጻነት የለም። ግን ለውጭ አተራማሾችና ለሃገር ስልጣን ናፋቂዎች ጉዳይ ማስፈጸሚያ ለመሆን የተንጣለለ መስክ ናቸው። ጦርነት በሰው ልጆች ላይ የመከራ ዝናብ አዝናቢ ነው። ዛሬ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ብልሃት አንድ ሆነውም ሆነ በተናጠል የሚፋለሙና ለመፋለምም በዝግጅት ላይ ያሉ ሁሉ ቆም ብለው መንገዳቸውን እንዲፈትሹ እንመክራለን። ዋ እበላ ሲሉ መበላትም አለ። የተሻለ እናመጣለን ሲባልም ጽልመትና ድቅድቅ ጨለማ ከአሁኑ የከፋም ሊመጣ ይችላል። ያለፈ ታሪካችን የሚያስተምረን “ትሻልን ትቼ ትብስን” ነውና። ተው እናንተ ጠበንጃ አምላኪዎች። አደብ ግዙ። በቃኝ! Reply you all are tgrie puppets ,you post this kind nonsense to make money and to make your atm friends happy , but we all know that who is zemene is ,,,, he is uncoliffied 4th grader basterd and traitor ,just like his grand father king teklehimanot ,the one who sold himself for 40 thousand liray for italians ,,,,history repeat itself Reply Leave a Reply to Tesfa Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story ሰበር መግለጫ. አርበኛ ዘመነ ካሴ ይድረስ ለአብይ አህመድና ለዳንኤል ክብረት. Next Story ቀኒቷ ደረሰች! ደረሰች! ደረሰች!
ሌባ ስርቆት ከመሄድ በፊት ለጌዪርጊስ ይሳላል ይላሉ አበው። የወያኔና የሻቢያ ጥምረት እኔም ጉንድሽ አንተም ጉንድሽ ለመባባል እንጂ ለህዝባቸው አንዳችም የሚቀይረው ነገር የለም። በቅርቡ ወሬ ቀማሚውና ወያኔ አፍቃሪው “የሴራ እርካብ የደም መንበር” ጸሃፊ የወያኔውን የባህል ጄኔራል ምግበን ቃለ መጠየቅ ብጤ አድርጎለት ነበር። ሸፍጠኛው የወያኔ ወታደር በአነጋገርም ባመላለስም ከጠያቂው ልቆ በመስማቴ ተደንቄአለሁ። ይህም ሆኖ አልፎ አልፎ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያሾልክ ነበር። ለምሳሌ ሃገረ ትግራይ ስንሆን፤ የትግራይን ህዝብ ነጻ ስናወጣ በማለት እየተናገረ ጋዜጠኛው ላቀረበለት አንድና ሁለት ቀጥተኛ ጥያቄም ይለፈኝ ብሎታል። መወስለትን ተክነውበታል። አቶ ጌታቸው ረዳ ነፍሴ አውጭኝ በማለት የሾማቸውን ሰዎች ለወያኔ እስራትና ግርፋት አጋልጦ ወደ አዲስ አበባ ከኮበለለ በህዋላ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ መቀሌ እመለሳለሁ ካለን እንሆ ሶስተኛ ሳምንቱን ያዘ። እነዚህ ሙቶች ለሃገርም ለትግራይ ህዝብም እንደማይጠቅሙ ገና ከጅምራቸው ግልጽ ቢሆንም አሁንም የእነርሱ ደጋፊዎችና ፍርፋሪ ለቃሚዎች በዚህም በዚያም አለን ይላሉ። ይህ ሁሉ ግን ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው። ፓለቲካ የቀትር ጥላ ነው። ከጊዜ ጋር የሚሰወር። አሁን በእውነት ፋኖና ወያኔ አንድ ላይ በመሆን ተዋግተው ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም ያመጣሉ? የሚሉሽን ብትሰሚ ገቢያም ባልወጣሽ ነው ነገርየው። ሲጀመር የወያኔው ደም አፍሳሽ ምግበ የፋኖ አመራር ውስጥ የሚገባበት አንድም መንገድ የለም። ወሬው የፈጠራ ያው አሞራውን ጅግራ ነው ብለው ለመብላት ያሰራጩት የፓለቲካ ስልት ነው። ትላንት የአማራን ህዝብና የአፋርን ህዝብ ያበራየ ደም አፍሳሽ ምን ያህል ልቡ ቢለወጥ ነው ከፋኖ ጋር ሆኖ ለዚያውም በአመራር ላይ የሚዋጋው? የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር እንዲሉ ነው ጉዳዪ። በሌላ መልኩ ግን ወያኔ ከሻቢያ ጋር ማበሩ ምንም እማኝ የሚያስፈልገው ነገር አይደለም። ለዚህ ነው ወያኔ ማለት እስስት ነው የምንለው። በአንድ በኩል የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ መሬትን ተቆጣጥረው እንዴት የፊደራል መንግስቱ ዝም ይላል ይላሉ። በሌላ በኩል ከሻቢያ ጋር ቂጥ ገጥመው ራሳቸውን ለጦርነት ያዘጋጃሉ። ሲጀመር ማን ሆነና ነው “የኤርትራን መገንጠልና ሃገር መሆን እወቁልኝ” እያለ በተመድና በአውሮፓ ከተሞች ሲዋትት የነበረው? ቆርሶ እንካችሁ ያለውን ምድርና ሃገር አሁን ወረረኝ ያዘብኝ እያሉ መዘላበድ የራስን ስልጣን ለማሰንበት የሚደረግ የፓለቲካ እቃ እቃ ጫዋታ ነው። ባጭሩ የብልጽግናው መንግስትና ሻቢያ/ወያኔ መፋለጣቸው አይቀሬ ነው። ያለ ባሩድ ሽታ መኖር አይችሉምና። ይህም በመሆኑ ውጊያው ትግራይ ውስጥ እንዳይሆን ሁሉም ነገር በአማራና በአፋር ክልል ላይ ተቆልሎ የሚገኘው። ይሄ ሁሉ የፓለቲካ ስህተት ብልጽግናን ዞሮ እንደሚገዳደረው ገና የስሜን ጦርን ወያኔ መትቶ ብልጽግና መቀሌ ከገባ በህዋላ ሙትና ቁስለኛውን ትቶ ከወጣ በህዋላ ነው። የፕሪቶሪያ ስምምነት/የናይሮቢ የውል ስምምነትና ማሻሻያ ሃስብ ሁሉ ለወያኔ የጊዜ መግዣ እንጂ ጭራሽ ትጥቅ እንደማይፈቱ የምናውቃቸው እናውቅ ነበር። ተፈታ ተብሎ ወደ 100ሺ ብር ለአንድ የወያኔ ታጣቂ ለማቋቋሚያ እየተሰጠ ብልጽግና ተረከብኩ ያለውም መሳሪያ የዛገና የሻገተ ወያኔ ከማህል ሃገር ጭኖ መቀሌ አምጥቶ አቧራ ሲጠጣ የነበረ የማይሰራ የመሳሪያ ክምር ነው። ዲዲአርም እንዳይሳካ ብዙ ጫና በጦርነት ፈላጊዎቹ የወያኔ ደም አፍሳሾች በኩል እንደነበረ የአዲስ አበባ መንግስት ያውቃል። ወያኔን ለምኖ ተለማምጦ ወደ ሰላም ማምጣት አይቻልም። ግን ብልጽግና ጠቡ ከአማራ ህዝብ ጋር እንጂ ከወያኔ ጋር አይደለም። ስንቶች አማሮች ናቸው ምንም ባላረጉት ታፍነው ጨለማ ቤት ውስጥ ያሉት? የገደሉት፤ የዘረፉት፤ ሃገርና ምድርን የሚያሸብሩት የወያኔ አለቆች ግን በሸራተን መግለጫ ይሰጣሉ፤ መቀሌ ላይ ናና ግጠመን ይላሉ። ግን እድሜ ለሻቢያና ወያኔ እንዲሁም ለጠባብ ብሄርተኞቹ የኦሮሞ ፓለቲከኞች የችግራቸው ምንጭ ሁሉ የአማራ ህዝብ ነው እያሉ ህዝባቸውን በውሸት ትርክት ስለጋቱ ውጊያው ከአማራ ህዝብና አጎራባች ክልሎች ጋር ይሆናል። ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ! ስናሳዝን። በማጠቃለያው ፋኖ፤ ብልጽግና፤ ወያኔና ሻቢያ፤ እንዲሁም አውቶቡስ እያስቆመ ዘር እየመረጠ የሚያፍነው እኩዪ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ነኝ የሚሉት ድኩማኖች ሁሉ ድርሻቸው አንድ ነው። እየገደሉ መሞት፤ እየሞቱ መኖር፤ እያስለቀሱ መሳቅ፤ እየሳቁ ማልቀስ። ህባችን በማሸበርና መከራ ውስጥ በመክተት የሚመጣ አንድም ነጻነት የለም። ግን ለውጭ አተራማሾችና ለሃገር ስልጣን ናፋቂዎች ጉዳይ ማስፈጸሚያ ለመሆን የተንጣለለ መስክ ናቸው። ጦርነት በሰው ልጆች ላይ የመከራ ዝናብ አዝናቢ ነው። ዛሬ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ብልሃት አንድ ሆነውም ሆነ በተናጠል የሚፋለሙና ለመፋለምም በዝግጅት ላይ ያሉ ሁሉ ቆም ብለው መንገዳቸውን እንዲፈትሹ እንመክራለን። ዋ እበላ ሲሉ መበላትም አለ። የተሻለ እናመጣለን ሲባልም ጽልመትና ድቅድቅ ጨለማ ከአሁኑ የከፋም ሊመጣ ይችላል። ያለፈ ታሪካችን የሚያስተምረን “ትሻልን ትቼ ትብስን” ነውና። ተው እናንተ ጠበንጃ አምላኪዎች። አደብ ግዙ። በቃኝ! Reply
you all are tgrie puppets ,you post this kind nonsense to make money and to make your atm friends happy , but we all know that who is zemene is ,,,, he is uncoliffied 4th grader basterd and traitor ,just like his grand father king teklehimanot ,the one who sold himself for 40 thousand liray for italians ,,,,history repeat itself Reply