አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025

አበበ ፈለቀ

475097409 10226263633363714 778916154386615081 nበዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት ውስጥ ወድቀዋል። የተለያዩ የኢትዮጵያ የንግድ ተቋማት፣ ሬስቶራንቶች፣ ገበያወች ውስጥ የሚሰሩትም በፍርሃት በመዋጣቸው ከቤት አለመውጣትን መርጠዋል።

በዚህ መነሻነት፣ ጉዳዩ ያስጨነቃችሁ አሜሪካ የምትኖሩ የማህበረሰባችን አባላት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ፣ የልዩ ፕሬዝዳንታዊ (Executive Order) ትዕዛዙንና አፈጻጸሙን አገላብጬና የህግ ባለሞያወችን አናግሬ ያገኘሁትን መረጃ ባጭሩ እነሆ።

የዚህ ዘመቻ ዋና ኢላማወች፦

  •  በአሜሪካ ስርዓት ውስጥ ያልተመዘገቡ (Undocumented)፣ በህጋዊ መንገድ ለመቆየት የሚያበቃ መረጃና ፍቃድ የሌላቸው፣ በየትኛውም የስደተኝነት ወይም የጥገኝነት ማመልከቻ ሂደት ውስጥ የሌሉ፣
  • የጥገኝነት ማመልከቻቸው በሁሉም የማመልከት ሂደቶችና ደረጃወች ላይ ውድቅ ተደርጎ በስደተኞች ፍርድ ቤት ሃገር እንዲለቁ (Removal Order) የታዘዙ
  • በየትኛውም የጥገኝነት ማመልከቻ ሂደት ውስጥ ያሉ፣ እንዲሁም የስራ፣ የትምህርትም ሆነ የጉብኝት ቪዛ ያላቸው ቢሆኑም በወንጀል የተከሰሱ፣ የተፈረደባቸው፣ የተጠረጠሩ ወይም የወንጀል ታሪክ ያላቸው ከሆነ ለዚህ የአፈሳ ተዕዛዝ የተጋለጡ ናቸው።

ይሄ ዘመቻ የማይመለከታቸው፦

  •  ህጋዊ ነዋሪወች፤ የመኖርያ ፈቃድ (Green Card) ያላቸው ሰወች ከሃገር የሚያስባርር ወንጀል እስካልፈጸሙ ድረስ
  • ቀኑ ያላለፈ ቪዛ ያላቸው፤ የተማሪ፣ የስራ፣ የጉብኝት ቪዛ ያላቸው እና በቪዛው ላይ ያለውን የመቆያ ጊዜና ደንብ/ ግዴታ ያከበሩ
  • ጥገኝነት (Asylum) ያመለከቱ ጉዳያቸው በየትኛውም ደረጃም ላይ ቢሆን በሂደት ላይ ያለ፣ የስራ ፈቃድ ያላቸው እና ምንም አይነት የወንጀል ታሪክ የሌላቸው
    ይሄ ጉዳይ የሚመለከታቸው ሰወች ማደረግ ያለባቸው፦
  • የስደተኛ ጉዳይ አስፈጻሚ ሃይሎች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልያዙ በስተቀር የቤታችሁን በር ያለመክፈት መብት አላችሁ
  • በቁጥጥር ስር ቢውሉም ለማንኛውም ጥያቄ መልስ አለመስጠት እና ጠበቃ የመጠየቅ መብት አላችሁ
  •  ከቦት ቦት ሲንቀሳቀሱ መታወቂያ እና የህጋዊነት መኖርያ ፈቃድ ወይም የማመልከቻ ደረሰኝና ማስረጃወች መያዝ
  • ለክፉም ለደጉም የአደጋ ጊዜ እቅድ ማውጣት፣ የአስፈላጊ የቤተሰብ ተጠሪወችንና የህግ ባለሞያወችን ስልክ መያዝ
  •  በማመልከቻ ሂደት ላይ ያላችሁ ከጠበቆቻችሁ ጋ መማከር፣ ማመለከቻችሁ ያለበትን ደረጃ በሚገባ ማወቅ፣ የፍርድ ቤት አልያም የቃለመጠይቅ ቀጠሮወችን አለማሳለፍ
  •  የወንጀል ክስ ወይም ታሪክ ካለ የህግ ድጋፍ መፈለግ
  •  ከመጨነቅ ይልቅ ተረጋግቶ ህጋዊ መሰረት ካላቸው እና ከታመኑ ምንጮች ብቻ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃወችን ማግኘት
    ይሄ መረጃ ግንዛቤን ለማስፋት የቀረበ እንጂ የህግ ባለሞያን ምክር የሚተካ አለመሆኑን ከወዲሁ መግለጽ እወዳለሁ። መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄወች ሁሉም ሰው እንዳለበት ሁኔታ የሚወሰኑና የሚለያዩ ስለሆኑ ራስን መጠበቅ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ በቂ መረጃ ላይ መመርኮዝ እና፣ ሁል ጊዜም ቢሆን ህጋዊ ድጋፍን ማግኘት አስፈላጊና ጠቃሚ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡

የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
Go toTop