የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ በአንጀት ሕመም ትላንት የቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ በዚያው ዕለት ከሆስፒታል ወደ ማረሚያ ቤት መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገልጸዋል፡፡
ታካሚዎቹ በሆስፒታሉ ቆይተው ክትትል እንዲደረግላቸው እንዳልተፈቀደላቸው የገለጹት ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ፣ በመሆኑም ደም ከፈሰሳቸው በአስቸኳይ እንዲያመጧቸው ለማረሚያ ቤት ደብዳቤ ተጽፎ መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው መኮንን በበኩላቸው፣ በቀጠሮ እንዲመጡ እንጂ እዚያው ሆነው እንዲታከሙ ከሆስፒታል የደረሰን ጥያቄ የለም ብለዋል፡፡