November 29, 2024
1 min read

የሰብዓዊ ቀውስ በአማራ ክልል 6.1 ሚሊዮን ዜጎች የምግብ ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው

60429196 1004በጦርነቱ ምክንያት 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ህጻናት ከትምህርት ውጪ እንደሆኑ ተገልጿል

የሰብዓዊ ቀውስ በአማራ ክልል

የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ አደራጃለሁ የሚል ውሳኔ ካስተላለፈበት ሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ መካከል ጦረነት በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የአማራ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉባኤ ከሰሞኑ በክልሉ ባለው የሰብዓዊ ቀውስ ዙሪያ ያለመ መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡

የክልል እና የፌደራል ተቋማትን ጨምሮ በርካታ ሀገር በቀል እና ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በተካፈሉበት በዚህ መድረክ ላይ በአማራ ክልል ያሉ የሰብዓዊ ቀውስ ሪፖርቶች ቀርበዋል፡፡

ከነዚህም መካከል አሁን ላይ 6 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ያፈልጋቸዋል የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ያህሉ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው ተብሏል፡፡

እንዲሁም 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ህጻናት በጦርነቱ ምክንያት ከትምህርት ውጪ ሆነዋል የተባለ ሲሆን አራት ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ደግሞ የጤና አገልግሎት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡

መረጃ- አል-ዐይን

258 112333 whatsapp image 2024 11 28 at 16.57.07 dfb69542

1 Comment

  1. ያኔም ሆነ አሁን ሰብአዊ ቀውሱን ተርቦ ባስተማረን ህዝብ ላይ የምናደርሰው እኛ አውቀናል መጥቀናል የምንል ጊዜ ከፈጠረው የብሄር ሰካራሞች ጋር በማበር ነው። ለመሆኑ በአማራ ክልል ላለው የማያባራ መከራ ተጠያቂው ማን ነው? በእኔ እምነት መንግስትና ተፋላሚ ሃይሎች ሁለቱም የመከራ አዝናቢዎችና ተጠያቂ ናቸው ባይ ነኝ። መረጃ – መንግስት ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ሥራ ካልጀመራችሁ ቁጭ ብላችሁ ደሞወዝ የለም በማለቱ ወደ ማስተማሪያ ቦታ የሄድትን ፋኖ ተብዬው አፍኖ እያንዳንዳቸውን ወደ 100 ሺህ ብር ካልከፈላችሁ አለቅም ብሎ አግቶ ይዞአል። ይህ ዝም ብሎ ስም ለማጥፋት የሚነዛ ወሬ ሳይሆን የታጋች ቤተሰቦች በጭንቀት በየደብሩ ነጠላ ዘርግተው ለማስፈቻ ገንዘብ እየለመኑ እንደሆነና የታጋች መምህራን ድምጽ ሰሚ አጥቶ በየስርቻው በፋኖ ሃይሎች ታጉረው ይገኛሉ። ሁለት – ፋኖ ከተማ ያዝኩ ይህን አደረኩ እያለ የሚያናፍሰው ወሬ መለካት ያለበት በግድም ሆነ በውድ ለቆ ከወጣ በህዋላም ሆነ እነርሱ በገቡ ሰአት የሚዘረፈው የሚገደለው፤ የሚጋየው የህዝብ ንብረት በእነዚህ ሁለት ተፋላሚ ሃይሎች መቆራቆስ ነው። አንተ ብልጽግና ነህ አንቺ ፋኖ ነሽ እያሉ የሰውን ሰቆቃ ሰማይ ላይ ያደረሱት እነዚህ እኩይ ሃይሎች ወይ ተዋጥቶ አልተዋጣላቸው ዝም ብለው የህዝቡን የገመና ጊዜ እያራዘሙት ይገኛሉ።
    ረሃቡ፤ በሽታው፤ የትምህርት ተቋማት መዘጋት፤ የግል አገልግሎቶችና ፍጆታ አቅራቢዎች መመናመንና መክሰም ከዚህ የአማራን ህዝብ ነጻ አውጣለሁ በማለት ልክ እንደ ኦነግ በብሄሩ የሰከረው የፋኖ ትርምስ ከመንግስት ሃሎች ጋር ሲገታገት ያመጣው ጣጣና መከራ ነው።
    ፋኖ ለአማራ ህዝብ የቆመ ሃይል ሳይሆን አማራን ከብልጽግና ጋር በጋራ የሚመነጥር የዛሬን እንጂ የወደፊቱን የማያይ የጭፍኖች ስብስብ ነው። መምህራንን የሚገድል፤ መኪና አስቁሞ የሚዘርፍ፤ ዘር ቆጥሮ የደም ብድር መለስኩ የሚል የህዝብ ሃይል ነው ሊባል አይችልም። በዚህ ላይ በመካከላቸው ያለው አለመግባባትና መከፋፈል ስለፋቸውን ፉርሽ ያደርገዋል። በመሰረቱ በፋኖና በኦነግ መካከል ምንም ልዪነት የለም። አለ ከተባለ ኦነግ አገርህ አይደለም እያለ አማራን ቤት ዘግቶ ማቃጠሉ ነው። አይ ጊዜ መቼ ይሆን የሃበሻ ፓለቲካ የራስን እንዘጥ እንዘጥ ብቻ ሳይሆን የአለም የፓለቲካ ንፋስንና የሃገርንና የህዝብን ጥቅም የሚያስቀድመው?
    ፋኖ የሰዎች እንባ የማይገደው፤ ሞትን የተቃመሰ፤ ሰላምን የገፈተረ፤ የሽፍቶችና አንዳንድ ለአማራ መብት የቆሙ መስሏቸው አስበውም ይሁን ሳያስቡት አብረው የተሰለፉ የክፉዎች ስብስብ ነው። ለአማራ ህዝብ ቆሜአለሁ እያሉ የአማራን ህዝብ ለመከራና ለስቃይ መዳረግ የትግል ስልት አይደለም። 6 ሚሊዪን የሚሆን የአማራ ህዝብ እርዳታ መፈለጉ ዓሊ የማይባል እውነት ነው። ግን እኮ እርዳታውም ቢገኝ በላተኛውና ዘራፊው ብዙ ነው። ከ10% እንኳን ለተረጂው አይደርስም። የእርዳታ እጅ የዘረጉ ሰዎችን የሚያፍን፤ የሚገድል የጨካኞች ጥርቅም ሊፈታው የሚችለው አንድ ሃይል ብቻ ነው። እሳት! ሞት! ሌላው ሁሉ ተሞከሮ አልሆነም። እብድን እብድ እየመከረው ሰው በሃገሩ እንደ አውሬ ታድኖ የሚገደልበት ዘመን ላይ እንገኛለን። ሞት ለሁሉም አይቀሬ ነው። በስመ ነጻነት በሰዎች ላይ የሚደርሰው በደል ግን የሞት ሞት ነው።
    ስለሆነም የዚህ ሁሉ ገመና ተጠያቂው በቅድሚያ መንግስት ነው። ያኔ ሲጨንቀው ኑ ድረሱልኝ በማለት ማርካችሁ ታጠቁ እንዳላለ ስልጣኑን ሲያደላድል ትጥቅ ፍቱ ማለቱ የፓለቲካውን የለየለት የገበጣ ጫዋታ ያሳያል። ለነገሩ የፍትህ ስርዓቱን አሻሻልን ወዘተ እያለ ፍርድ ቤት የፈታውን በር ላይ አፍኖ የሚወስድ መንግስት ማን ሊዳኘው ይችላል? ይህስ አሰራር ከአለፈው የመንግስት አሰራር በምን ይለያል? አሁን ማን ይሙት አቶ ታዬ ደንደአ መታሰር ይገባዋል? ጠ/ሚሩና አስራራቸውን መወረፍ ዘብጥያ ያስወርዳል? ግን ፍትህ በሃበሻ ምድር ሞታ ከተቀበረች ቆይቷል። ለዚህ ነው የፋኖና መሰሎቹ የትጥቅ ትግል ጊዜን ያልተመረኮዘ፤ የቅርብ ወይም የሩቅ እቅድ የሌለው ባጭሩ ልክ እንደተለመደው የሰው ቁጥር ቅነሳ ጦርነት የሚያደርገው። ፍሬ ቢስና ከንቱ! ለህዝቡ የሚቆረቆር የፓለቲካ ጥያቄውን ግልጽ አድርጎ ተመካክሮ፤ ተደራድሮ፤ ዋስትና ተቀብሎና ሰቶ በሰላም ለመኖር ከእንግዲህ በቃ ማለት የሚችል ነው። በዚህ የጦር ግንባር እከሌን ሸኘን፤ በዚያ ያን ከተማ ያዝን፤ እዚህ ጋ ይህን አደረግን እያሉ ማወናበድ የፓለቲካ የመኖሪያ ብልሃት እንጂ ለተራበውና ለተጠማው ህዝባችን ከምሲን አያመጣለትም። ለዚህ ሁሉ የመከራ ዶፍ መፍትሄው እርቅና ድርድር ነው። ከዚያ ውጭ ከላይ እንዳልኩት ሁሉ በወረፋ መገዳደል እንጂ አንድም ፍሬ አይገኝም። ኦ ሰላም በስምሽ ስንት ግፍ ተሰራ – ያለፈው ላይበቃ ዛሬም? አታድርስ ነው። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop