ሲል የጮኸ ክርስቶስ ስቀል ባርባንን ፍታ፣
ለአብዮት አመዴ የደለቀው “ሙሴ መጣ”፣
ፀፀት እንደ ሰለሊት ፈርፍሮት ንስሃ ያልገባ፣
ራሱን ታጠፋው ይሁዳም ያነሰ ቀውላላ፣
በእድፋም እጁ ዛሬም ቦለቲካ የሚያቦካ!
ምሁር ነኝ ባይ ፈሪሳዊ ዛሬም አላ!
ጭራቅ ሲመጣ ሙሴ እያለ የደሰኮረ ዲግሪ ጫኝ መንጋ!
በሱስ ስብከት ወላጅ እናቱን ጦቢያን ያስበላ፣
ሶቅራጥስን መርዝ አጠጡ እንዳለው የታሪክ ትቢያ፣
ሳይመራመር ምሁር ነኝ ባይ ምድር አጣቧላ!
ጲላጦስ እንኳ እንጁን ታጥቦ ሲያቅማማ!
ክርስቶስን “ስቀለው ስቀለው” ሲል ያስተጋባ፣
እስጢፋኖስን የቀጠቀጠው በድንጋይ ዱላ፣
በዝቶና ፋፍቶ ምድርን ዓለምን ሞልቷላ!
ጅብ ግራ እግሩን እየዋጠው በፍርሃት እሚተኛ፣
ቀኙን ለማትረፍ ዝምበል የሚል ዘልዛላ፣
ግድብ ሞልቶ ሲፈስ ያድራል በበራራ!
ጭራቅ እያረደ ህጻን ሴትን አሩግ ሲበላ፣
እርስ በርሱ የሚናከስ ተባብሮ በመግጠም ፋንታ፣
በጎጥ ካሳማ ተወጥሮ የገጠመ ገመድ ጉተታ፣
የምሁር መንጋ ኩበት በየመንደሩ ተከምሯላ!
ኮርማ ቆብ ደፍቶ ጳጳስ ነኝ ብሎ ሲመጣ፣
መጀመርያ ፍሬ አፍርጠህ ሰንጋ ሁን በማለት ፋንታ፣
ይፍቱኝ እያለ እጁን የሚስም የምዕመን ጎጋ ፣
የቤተክስያን አጥር ግቢ ደጀ ሰላም አጣቧላ!
አወይ መንጋ! መንጋ! መንጋ!
በላይነህ አባተ ([email protected])
ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ ሰባት ዓ.ም.