November 4, 2024
24 mins read

እንኳንስ ለዓመታት ለወራትስ ቢሆን አገር (ህዝብ) በእንዲህ አይነት ግለሰብ ሥር መውደቅ ነበረበት?

6724a00985f5400272263635November 3, 2024

ጠገናው ጎሹ

የዚህ እጅግ ፈታኝ ጥያቄያዊ  ርዕሰ ጉዳዬ መነሻና ማጠንጠኛ የህወሃት/ኢህአዴግን መርዛማ የፖለቲካ  አስተሳሰብና አካሄድ እየተጋተ ያደገውና በፍፁም ታማኝነት ሲከድር (በሰው ሥጋ ለባሽ መሳሪያነት ሲያገለግል) ለጎልማሳነት እድሜ የበቃው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየ መከረኛው ህዝብ በህወሃት ላይ ከነበረው ብርቱ ጥላቻ የተነሳ እና ግን በእጅጉ የተሳሳተና ግልብ በሆነ ተስፈኝነት ምክንያት “የዘመኑ ሙሴ” በሚል ያደረገለትን አቀባበል ተጠቅሞ ያንኑ ያደገበትንና የጎለመሰበትን እኩይ የጎሳ ደምና አጥንት ስሌት ፖለቲካ እጅግ ለመግለፅ በሚያስቸግር አሰቃቂ የተረኝነት አገዛዝ ሥልት ማስኬድ ከጀመረ ይኸው ከስድስት ዓመታት በላይ  ቢሆነውም አሁንም ቆም ብሎ ለማየትና ለመረዳት የሚያስችል እንጥፍጣፊ ህሊናዊ ቅንነት ይኖረዋል በሚል ተጨማሪ ባዶ ተስፈኝነት ራሱንን ያታለለውና በማታለል ላይ የሚገኘው ወገን ቁጥሩ ቀላል አይደለምና በእጅጉ ሊያሳስበን ይገባል የሚል ነው።

በሌላ አገላለፅ እንጥፍጣፊ ህሊናዊ  ቅንነትን መጠበቅ የሚቻለው ከመጀመሪያውም (ከአነሳሱም) በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በጎ የሆነ ህሊናዊ ማንነት፣ ምንነትና እንዴት ከነበረው ሰብአዊ ፍጡር መሆን ሲገባው የህሊና እና የሞራል እኩይነቱን ከየምንባቡ በቃረማቸው ጥራዝ ነጠቅ ቃላት/አባባሎች/ተረትና ምሳሌዎች እና ባሰለጠነው ቀጣፊ አንደበቱ ከማስተጋባት እንደማያልፍ ለመገንዘብ፣ ለመፀፀትና ተገቢውን የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ባለመቻል ከስድስት ዓመታት በላይ የቆየንበትና አሁንም  እንደ ማህበረሰብ (እንደ ህዝብ)  ተዘፍቀን የምንገኝበት ክፉ አባዜ/አዙሪት ነፃነት ወይም ሞት ለሚል ተጋድሎ ካላነሳሳን ከማሰቢያ አእምሮና ከማከናወኛ አካል ጋር በፈጣሪ አምሳል ተፈጠርን ማለታችን እንዴት የተሟላ ትርጉም ይኖረዋል? ነው እጅግ ፈታኙ ጥያቄ ።

አዎ! በእውነት ስለ እውነት ከተነጋገርን እጅግ የመዘግየታችን ውድቀት ያስከፈለን ግዙፍና መሪር ዋጋ መሪር ትምህርት ሆኖን ከእንግዴህ ግን  እንደ አብይ አህመድ አይነቱን ፍፁም የለየለት ሸፍጠኛ፣ ሴረኛ የፖለቲካ ደንቆሮ፣ የሥነ ልቦና እና የሥነ ምግባር ደሃ የሃሰት (የውሸት) አምራችና አከፋፋይ የሃይማኖታዊ እምነት ነጋዴ፣ በግፍ ለሚያስገድላቸውና የቁም ሰቆቃ ሰለባዎች ለሚያደረጋቸው አያሌ ንፁሃን ወገኖች ተሳስቶት እንኳ እንደ አገር መሪ ሃዘኑን የማይገልፅና ለሆነው ሁሉ ይቅርታ የማይል እጅግ ጨካኝ/አረመኔ እንዲያውም በተቃራኒው ለርካሽ ፖለቲካው መሸፈኛነት በየመንገዱ ተከልኳቸውና አስተከልኳቸው የሚላቸውን ችግኞች አድገው “ለሞቱት ጥላ ይሆናሉ” በሚል የሚያሾፍ ፣ በረሃብ አለንጋ ለሚገረፉት (የቁም ሞት ሰለባዎች ለሆኑት) ዜጎች ደግሞ “ሙዝ በዳቦና ቅጠል በጨው ቀቅላችሁ ብሉ” እያለ የሚሳለቅ እና በአጠቃላይ የፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን እጅግ አስከፊ የሆነ የሰብእና ቀውስ ወይም ዝቅጠት የተጠናወተውን ግለሰብ እና የሚመራውን (የሚዘውረውን) እጅግ ጭራቃዊ የጎሳ ደምና አጥንት ስሌት ሥርዓተ ፖለቲካና ሥርዓተ መንግሥት አምርሮ ከመታገል ውጭ ሌላ አማራጭ ፈፅሞ የለም።

ይህ ካልሆነ እጅግ አስከፊና አደገኛ የሆነውን የፖለቲካና የሰብእና ቀውሱን/ ዝቅጠቱን ወደ ሥልጣነ መንበሩ ከወጣ ብዙም ሳይቆይ በግልፅና በቀጥታ ያሳየን ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየ  ወደ ሁለተኛው “የተመርጫለሁና ይህን የሚገዳደር ቢኖር ወዮለት” የሚል አዋጅ እስኪያውጅ ድረስ  የመጠበቅ ጉዳይ ይሆንና አገር (stateማለት የህዝብ፣ የልዑላዊ መልከአ ምድር እና ህግ የሚያወጣ ፣ የሚያስፈፅምና የሚተረጉም መንግሥት በአንድ ላይ የሚፈጥሩት ግዙፍና ጥልቅ ነገር መሆኑ ይቀርና አገር ማለት በመንግሥትነት ስም የሚጠሩ ባለጌና ጨካኝ ቡድኖች እንደፈለጉ የሚያደርጉት መሬትና የሰዎች ስብስብ ይሆናል። ለሩብ ምእተ ዓመት ከመጣንበት ህወሃት መራሽ ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት ለመማርና የሚበጀንን ሥርዓት እውን ለማድረግ ባለመቻላችን ከስድስት ዓመታት ወዲህ የምንገኝበት ለመግለፅ የሚያስቸግር ሁኔታ የሚነግረን ይህንኑ ግዙፍና መሪር እውነታ ነውና ከምር ሊያሳስበን ይገባል።

እናም ለሩብ ምዕተ ዓመት በበላይነት የቆየውንና አሁን ለምንገኝበት ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት ምክንያት የሆነውን ሥርዓተ ፖለቲካ የተከሉትን እኩያን የህወሃት ገዥ ቡድኖችን መርዘኛ አስተሳሰብ ሲጋት ያደገው እና ከስድስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ የዚህኑ ሥርዓተ አገዛዝ ሁለንተናዊ ባህሪና አስተሳሰብ  ኦሮሙማ የተሰኘውን ለማንምና ለምንም ፈፅሞ የማይበጅ የፖለቲካ ትርክትና እምነት በመከረኛው የኦሮሞ ህዝብ ስም እጅግ አስከፊ በሆነ እና ለትውልደ ትውልድ በሚተርፍ ሁኔታ ያስቀጠለውን  አብይ አህመድንና ካምፓኒውን (ጠርናፊ ገዥ ቡድኑን) የሰበብና የትንታኔ ድሪቶ እየደረቱ ከዚህ በላይ እንዲቀጥል መፍቀድ ከመከራና ከውርደት ጋር የመለማመድ ክፉ ደዌ ( አባዜ) ካልሆነ ፈፅሞ ሌላ ሊሆን አይችልም!

ከአያሌ ዓመታት በኋላም እንዴት እንዲህ ያደርጋል/ያደርጋሉ? ምን አይነት ጨካኝነት ነው?  እንዴት እንደ አገር መሪነት አያስብም/አያስቡም? መቼ ነው ጤናማ ልብ (ህሊና) የሚገዛው/የሚገዙት? እየገደሉንና እያጋደሉን አይደለም ወይ? አገር እያሳጡን አይደለም ወይ? የሃይማኖት ተቋማትን ከሰላምና ከምህረት አውድነት ወደ የጦርነት ዒላማነትና የመከራ መናኸሪያነት እየለወጡብን አይደለም ወይ?  ፈጣሪያችንን ምን ብናስቀይመው ነው? እግዚአብሔር ልብ እንዲሰጣቸው ወይም እንዲገስፃቸው ከመፀለይ ውጭ ሌላ ምን ያዋጣናል (ምን እናደርጋለን)? ወዘተ የሚል እና ከረቂቅ የማሰቢያ አእምሮና ብቁ የማከናወኛ አካል ጋር የመፈጠርን ትልቅና ቅዱስ ዓላማ በእጅጉ የሚያጎሳቁልና ፈፅሞ ስሜት የማይሰጥ እሮሮና ጩኸት ከመስማት የበሳ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊና መንፈሳዊ ዝቅጠት ፈፅሞ የለም።

በዚህ አይነት ዘመን ጠገብና እጅግ አሳፋሪ ሁለንተናዊ ውድቀታችን ምክንያት ነው የብልግና እና የጭካኔ ሥርዓትን በበላይነት የሚዘውሩት አብይ አህመድና ጓደኞቹ እና  በሰው ሥጋ ለባሽነት የሚጠቀሙባቸው አማራ ነን ባይ አጋሰሶች ስብሰባና ጉባኤ በሚሉትና በየአጋጣሚው በሚያዘጋጁት የፕሮፓጋንዳ መድረክ  በፖለቲካ ወለድ የመከራና የውርደት ሰለባነታችን ላይ ህሊናን በሚፈታተን ሁኔታ  እየተሳለቁብን የቀጠሉት ።

ይህ እጅግ ግዙፍና አስከፊ የፖለቲካና የሞራል  ማንነታቸው ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ደግሞ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ ሽፋን የሚሰጡ ግለሰቦችን በታማኝነት የማሰማራትና የማሰራት እኩይ ዘመቻቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል።  ለዚህ ደግሞ  የምሁርነትን (የመማርን) እውነተኛ ትርጉም በማርከስ (በእጅጉ በማጎሳቆል) በቀጥታ የአብይ አህመድና የካምፓኒው (የገዥ ቡድኑ) አጃቢ አሻንጉሎቶችና የትውልድ ማፈሪያዎች የሆኑ ግለሰቦችን ፍለጋ ሩቅ መሄድ ወይም ብዙ መድከም አላስፈለጋቸውም።

ትምህርትንና የትምህርት ሥርዓትን የብልፅግና እኩይ የፖለቲካ ጨዋታ መጫዎቻ በማድረግ ትውልድን እየገደለና እያስገደለ  ያለውን ብርሃኑ ነጋን (በነገራችን ላይ መምህራን ራሳቸውን መመገብ ተስኗቸቸው የእነ አብይንና አዳነች አቤቤን የምፅዋት ቁራሽ ከምሥጋና ጋር ተቀብለው ለመመገብ በተገደዱበት መሪር ሁኔታ ውስጥ ፕሮፌሰር ተብየውና የትምህርት ሚኒስተር የሆነው ብርሃኑ ነጋ በሚዲያ ላይ ብቅ ብሎ የብልፅግና ሥጋ ለባሽ አጋሰስነቱን ትንሽ ሳያቅማማ በአድናቆት የሚነግረን። ታዲያ ከዚህ የከፋ ትውልድ ገዳይነትና አስገዳይነት አለ እንዴ?) ፣  ሲጀመርም ብዙ ርቀት እንደማይሄድ ግልፅ የነበረውን አብን ተብየ ለብልፅግና ሴራ ገፀ በረከትነት በማቅረብ “የተከበሩ ሚኒስትርነትን” የተሸለመውን የሰው አጋሰስ በለጠ ሞላን  ባህር ማዶ በቆየበት ረጅም ዘመን  በዲስኩሩም ሆነ በፃፈው መፅጽሐፍ ስል ነፃነትና ፍትህ እጦት ሲተርክልን የነበረውንና የእነ አብይን “የለውጥ ድል” በመቀላቀል የህይወቱን የመጨረሻ ምእራፍ ያበላሸውንና የትውልድ መጥፎ ምሳሌ የሆነውን  አረጋዊ በርሄን፣ የብልፅግና (የአዳነች አቤቤ) መጫወቻ ካርድ እና አስተምረዋለሁ ለሚለው ወጣት ትውልድ መሸማቀቂያ  የሆነውን  ሲሳይ መንግሥቴን  ከ1997 ዓ:ም ጀምሮ እጅግ ሥር በሰደደና ትውልድ ገዳይ በሆነ የአድርባይነት ደዌ ተለካፊነት የሚታወቀውንና አሁን ደግሞ የቢጤዎቹ የእነ ብርሃኑ ነጋ የፖለቲካ ቡድን አባልነት አርማን ለጥፎ የአዳነች/የብልፅግና ምቹ አጋሰስ የሆነውን ግርማ ሰይፉን  የተማረውንና ያነበበውን የፍልስፍና ትምህርት እነ አብይ አህመድን ለማሞገስ እና በሌላ በኩል ግን የነፃነትና የፍትህ ፈላጊና ታጋይ ወገኖችን ለማጣጣልና ለማብጠልጠል የሚጠቀመውንና ለሚያስተምራቸው ወጣቶች ብቻ ሳይሆን ለመላው ወጣት ትውልድ እጅግ አሳፋሪ ምሳሌ የሆነውን ዳኛቸው አሰፋን ፣ ከየቦታውና ከየቤተ መፃህፍቱ እየቃረመ ያነበበውንና ያነበነበውን እና ይህንኑ ለማስተጋባት ያሰለጠነውን አደገኛ አንደበቱን ሥር የሰደደ የአድርባይነት ሰብእናውን ለማርካት ሲል አገርን ምድረ ሲኦል ያደረገውን የቤተ መንግሥት ፖለቲካ በመቀላቀል የመከራና የውርደት ዶፍ አማካሪነቱን እንደ የአርበኝነትና የፅድቅ ሥራ ቁጠሩልኝ ባዩን ዲያቆንና ሙዓዘ ጥበባት ተብየ ዳንኤል ክብረትን፣ በጋዜጠኝነቱ እውነትን በመዘገቡ ለእሥር ተዳርጎ ዋጋ እንደ ከፈለ እና ያንን የእሥር ቤት ጊዜውን “የቃሊቲው መንግሥት” የሚል መፅሐፍ በመፃፍ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና ለዴሞክራሲያዊት አገር እውን መሆን ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳደረገ ሲተርክልን እንዳልነበረ በቅጡ የማሰቢያ ጊዜ እንኳ ሳይወስድ እንደ ጠላሁት ታገልኩት ከሚለው የህወሃት ፖለቲካ ወለድ ወንጀል ጋር ሲነፃፀር እንኳንስ ለማመን ለማሰብም በሚከብድ ሁኔታ አገርን ምድረ ሲኦል እያደረገ ያለውንና በመከረኛው የኦሮሞ ስም የሚቆምረውን ተረኛ የሮሙማ/ብልፅግና ገዥ ቡድን ተቀላቅሎ በመከረኛው ህዝብ ላይ የሚሳለቀውን ሲሳይ አጌናን ተራቀቅንበት ይሉለት የነበሩትን ምሁርነት አገርን እንዳልነበረ ላደረጉ/በማድረግ ላይ ለሚገኙ የጎሳ ደምና አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞች/ገዥ ቡድኖች አሳልፈው በመስጠት የመማርንና የመመራመርን እውነተኛ ትርጉም (education is the means to fight against catastrophe/ the means to shape and reshape oneself with all-round personality) ያጎሳቆሉትንና  ለትውልድ  መልካም አርአያዎች ሳይሆኑ በሞት የተለዩትን እንድርያስ እሸቴን እና በየነ ጴጥሮስን  ፣ ወዘተ መጥቀስ  ይቻላል።

የመጨረሻዎቹን ሁለት ምሁራን መጥቀሴን በተመለከተ ከቤተሰብነት ወይም ከወዳጅነት ወይም ከየዋህነት ወይም ከአጉል ተለምዶ ወይም ከማይጨበጥ መንፈሳዊ ፍርሃት የተነሳ “እንኳንስ ምሁራንን ማነኛውንም የሞተን ሰው ማሄስ ነውር ነው” የሚል ወገን እንደሚኖር በሚገባ እረዳለሁ ። ለዚህ የሚኖረኝ አጭር መልስ ትክክል የማይሆነው የሞተንና ራሱን መከላከል የማይችልን ሰው እውነት ባልሆነ ነገር  ወይም ከግል ጥላቻ በመነሳት መተቸት ነው እንጅ ፀሐይ ከሞቀው እና ከአገር ጉዳይ ጋር በተያያዘ የግለሰቡን/ችን ፖለቲካዊና ሞራላዊ  ምንነትና ማንነት  ማሄስ ከትክክልም ትክክል ነው፤  እንደዚያ ካልሆነማ ታሪክና ከታሪክ መማር የሚባል ነገር ፈፅሞ አይኖርም ነበር የሚል ነው  ። “አይ ምንም ቢሆን … “ የሚል ካለም  የሚኖረኝ ምላሽ በህይወት ኖርንም አልኖርን ስለ ድክመቶቻችን መናገርና መነጋገር ነውር ወይም የኩነኔ መንገድ ከሆነ እሰየው ይሁን ( If you think so, so be it) የሚል ነው።

ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየውን ምናልባት የቅንነትና የፀፀት እንጥፍጣፊ ህሊና ይኖረው ይሆናል በሚል እጅግ በወረደና አሳፋሪ በሆነ ተስፈኝነት ይጠባበቅ ለነበረና ለሚጠባበቅ የዋህ ወይም ወላዋይ ወይም አድርባይ ወይም እናቴን ያገባት ሁሉ አባቴ ነው ባይ ሁሉ አስተማሪነት ያለው እና በቃኝ/በቃን ብሎ ለነፃነትና ለፍትህ ተጋድሎ የሚያስነሳ የብልፅግና የፖለቲካ ተውኔትን እየመረረንም ቢሆን አይተናል፤አድምጠናልም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ከፓርላማ ተብየው በፊት እኩይ የጎሳ ደምና አጥንት ስሌት ፖለቲካን የሥራ እድል  ምንጭና የሙስና ቢዝነስ ማሳለጫ ያደረገውን የካድሬ ሠራዊቱን ሰብስቦ  አዲስ ባይሆንም በእጅጉ አስከፊ እየሆነ የቀጠለውን የሴራኛነት፣ የሸፈጠኝነት፣ የፍፁም ሃሰተኛነት ፣ የቅዠተኛነት ፣ የጨካኝነት፣ እና በአጠቃላይ የትውልድ ገዳይነት ዲስኩሩን ከየቦታው በቃረመውና በሚቃርመው ተረትና ምሳሌ እያጀበ እጅግ መርዘኛ በሆነ ሁኔታ የደሰኮረውን ርካሽ የፖለቲካ ዲስኩርም ታዝበናል።

ቀጥሎ ያመራው ደግሞ የደንቆሮ  አሻንጉሊቶቹ (ካድሬዎቹ)  እና  በተቀዋሚነት ስም ፋይዳ አልባ  የልክልኩን ነገሩትና በጥያቄ አፋጠጡት “  ዲስኩር የሚደሰኩሩ (የሚያላዝኑ) ተቀዋሚ  ተብየ ፖለቲከኞች  ወደ ታደሙበት የስብሰባ አዳራሽ ነበር።

በዚህ መድረክ ላይ ያደረገው እጅግ የበከተና የከረፋ ዲስኩርና ያሳየው ንቀት (ትእቢት) እንደ አዲስ ነገር አስገራሚና አሳዛኝ ባይሆንም መሬት  ላይ  ግልፅና  ግዙፍ ሆኖ  የሚታየውንና  የሚዳሰሰውን  እጅግ  መሪር  እውነታ  ገልብጦና  ገለባብጦ  ሊያስነብበንና  ሊያሳምነን  የሄደበት  ድፍረትና  ርቀት  ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቃን አሰኝቶ  ህልውና፣ ነፃነት፣ ፍትህ ፣ እኩልነት፣ ሰላምና የጋራ እድገት እውን የሚሆንበትን  ሥርዓት በሁለገብ ተጋድሎ  አምጠን እንወልድ ዘንድ ካላነሳሳን መቸውም ቢሆን ከውድቀትና ከመከራ አዙሪት ለመውጣት የምንችል አይመስለኝም።

ይህንን የምለው ያልተባለ ወይም ያልተነገረ ልዩ የመፍትሄ ሃሳብ ለማቅረብ ሳይሆን ዘመን ጠገቡና ከሰብአዊና ከዜግነት መብት ባለቤትነት በታች ያወረደንን እና የዓለም ከንፈር መምጠጫና መሳለቂያ ያደረገንን የእኩያን ገዥ ቡድኖች ሥርዓተ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ የታሪክ መማሪያነት መቃብር አውርደን በህዝብ፣ ከህዝብና ለህዝብ የሆነ ሥርዓተ ፖለቲካንና ሥርዓተ መንግሥት እውን ለማድረግ እስካልቻል ድረስ እንኳንስ ለዓመታት ለወራትም አገርን (ህዝብን) ያህል ነገር ፈፅሞ መምራትና ማስተዳደር የሌለባቸው ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛ፣ እና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች ሰለባዎች ሆነን እንቀጥላለንና ነገ ሳይሆን ዛሬውኑ በቃ እንበል የሚለውን ሃያል መልእክት ለማጠናከር ነው።

እናም ልብ ያለው ልብ ይበል!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/ ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
Go toTop