ማንኛውም የፓርላማ ጥያቄ ከ15 ቀን በፊት ጥያቄ እንደሚገባ ይታወቃል፣ እናም ዛሬ የአብኑ ተወካይ አቶ አበባው የጠየቀው ጥያቄ ከ15 ቀን በፊት የገባ ነው። ስለሆነም ደላላው አብይ አህመድ መልሱን ለራሱ እንዲመች አድርጎ መመለሱ ሳይታለም የተፍታ ሀቅ ነው።
በዛሬው ዕለት በፓርላማ በህዝብ ፊት የቀጠፋቸው ቅጥፈቶች:-
1. “የቀበሌ ማዳበሪያ እየሰጠን ነው” የሚለው ነጭ ውሸትን ብንመለከት ከ90% በላይ ገጠር በፋኖ ስር በሆነበት ክልል በቀበሌ ማዳበሪያ አድያለሁ ማለቱ ትልቅ ውሸት ከመሆኑ በላይ እንደ ሰከላና ግሽ አባይ ባሉ ከተሞች በቆየባቸው ወራት የአርሶደር ቤት ማዳበሪያ እየፈለገ የገደላቸው አርሶ አደሮች ማስታወስ ብቻ ይሄ ትልቅ ቅጥፍት መሆኑን መረዳት ይቻላል።
2. “በክልሉ ኢንዱስትሪያላዝድ አድርገናል” ይላል እውነታውን ስንመረምረው
• ኮምቦልቻ ኢንዱስቲሊያል ፓርክ ስራ የጀመረው በ2017 እኤአ
• ደብረብርሃን ኢንዱስትሪያል ፓርክ ስራ የጀመረው በ2019 እኤአ
• ቡሬ ኢንዱስቲሪያል ስራ የጀመረው በ2015-16 እኤአ ሲሆን እንደ ጎርጎራ እና ሃይቅ ባሉ ሆቴሎች አርሶ አደሮች ያለበቂ ካሳ መፍናቀላቸው ሳያንስ በተለይ በጎርጎራ ለዚሁ ትግል መቀጣጠል ዋና ምክንያት የሆነ ነው። የጎርጎራው በገዳም ውስጥ በሬዎችን ለማረድ ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ እና ሆዳም ካድሬዎችን ሆድ ለመሙላት ከባህልና ሃይማኖታዊ ውጪ በሆነ መልኩ እርድ ለማድረግ ሲል የተቃወሙ የገዳሙን መነኮሳትን እና የከተማውን ወጣቶች በቁጥር 22 የሚሆኑ በጭካኔ መጨፍጨፉ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
3. “ክልሉን ከሌሎች ክልሎች በተሻለ ጠቅመናል፣ አልምተናል” የሚለው ትልቅ ውሸት ደግሞ ባለፈው አንድ አመት ብቻ እንኳን በአማራ ክልል ብቻ አንድም አዲስ የህክምና ነክ የንግድ ፍቃድ ተከልክሏል፣ የግል አስመጪዎች ወደ ክልሉ ምንም አይነት መድሐኒት እንዳያስገቡ የከለከለ አገዛዝ ስለልማት ማውራት አይችልም፣ ሞራልም የለውም።
እዚሁ ላይ ለካድሬው መልስ ሰጥቼ ማለፍ እፈልጋለሁ። ፋኖ የስኳር በሽተኞች ስብስብ አይደለም፣ እንደውም የአይበገሬዎቹ እሳት የላሰ የወጣቶች ስብስብ ነው እና ወደ ባህርዳር የስኳር መድሐኒት ላይ እቀባ መደረጉ የሚጎዳው ህዝቡን እንደሆነ ማስታወስ እፈልጋለሁ።
በመጨረሻም ከመለስ ጀምሮ በአማራ ክልል የድልድይ ፓለቲካ አለመቅረቱ ይገርማል፣ የአባይ ድልድይ ለ27 አመታት ህዝብን ያደነቆረ ፕሮፓጋንዳ፣ አሁንም በአማራ ህዝብ ላይ እንደማይሰራ መረዳት ያስፍልጋል።
ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር