September 3, 2024
32 mins read

የአብይ ኮሬ ነገኛ በ ዘማታሪስ ሰርክል መነጽር

GWQTwUEXIAEI4mP

አብይ አህመድ ጠ/ሚ ከመሆናቸው በፊት ወታደር የነበሩና በኢንሳ (INSA) የመረጃደህንነት አስተዳደር ዳሪክተር ሆነው ያገለገሉ ናቸው፡፡ በዚህ የስራ ዘመናቸው ውስጥ እሳቸው እንደነገሩንና የውጭ ሃገር ጋዜጠኞች እሳቸውን ቃለ መጠይቅ አድርገው እንደቀረቡት ፤ የ ዘ ኒዎረከሩ ጆን ሊ አንደርሶን ( Jon Lee Anderson) ሰላይና ደብል ኤጀንት እንደነበሩ ተነግሮናል፡፡ ለኦነግ፣ ግንቦት 7 እና ለሲ.አይ.ኤ. መረጃ ያቀብሉ እንደነበር በተደጋጋሚ በማስረጃ በተረጋገጠ ሁኖታ ዜናውን ያደረሱን እሳቸው እራሳቸው ጠ/ሚሩ ናቸው፡፡

ታዲያ በእርካብና መንበር መጽሐፋቸው አንዴ እነደ ኒኮሎ ማካቬሌ ሌላ ግዜ ደግሞ እንደ ሙሴ ሆነው እራሳቸውን የገለጡት ጠ/ሚ ስልጣንን ለመንጠቅ በሚያሰፈስፉበት ወቅት የስለላ መጽሓፎችን አዘውትረው ማንበብ ይወዱ ነበር አሉ፡፡ እዚህ ላይ ደግሞ የደራሲ ሮበርት ሉድለም የስለላ መጽሓፎችን አግኝተው አገላብጠዋቸዋል፡፡ ይህ ደራሲ፣ ዘ ማታሪስ ሰርክል(The Matarese Circle) በሚለው ልብ አንጠልጣይ፣ በገቢር የተሞላ ጀብደኛ ድርሰቱ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ስለነበረው የምእራብና ምስራቁ አለም ፖለቲካ ስለላ ጽፏል፡

በ2ኛው የአለም ጡርነት ግዜ የጀርመን ናዚዝም፣ የጣሊያን ፋሺዝምና የጃፓን ሚሊተሪዝም በአውሮፓና እሲያ በኪያሄዱት ጦርነት ብዙ ህዝብ አልቋል፡፡ በዚያን ግዜ በሚከተሉት ርዕዮት አለመም ሆነ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ላይ ባላቸው ፍልሰፍናቸው የተለያየ አመለካከት ያላቸው አሜሪካና እንግሊዝ ከሶቪየት ህብረት ጋር አጋርንት ፈጥረው በጋራ ናዚ ጀርመንን ተዋጉ፤ ድሉም ለነሱ ሆነ፡፡

2ኛው የአለም ጦርነት ካበቃ ቦኋላ ቀዝቃዛው ጦርነት በካፒታሊሰቶቹ አሜሪካና ምእራብ አውሮፓ ሃገራትና በኮሚኒስቶቹ በሶቪየት ህብረት በሚመሩት ምስራቅ አውሮፓ ሃገራት መካከል ይካሄድ ጀመር፡፡ የአሜሪካው ስለላ ድርጅተ ሲ.ኤይ.ኤ.ና በሶቪየት ህብረቱ የስለላ ድርጅት ኬ.ጂ.ቢ መካከል ትግሉ፤ግድያውና አፈናው ቀጠለ፡፡ በዚህ ወቅትም ለሁለት ወገን የሚሰሩ ደብል ኤጀንት ሰላዮች ተልእኮ ለመፈጸም ይንቀሳቀሱ ነበር፡፡

መች የቱን ከአንደኛው የአለም ጦርነት በፊት አድርጎ የቀዝቃዛው አለም ጦርነት ወቅትን የሚተርከው የሮበርት መጽሐፍ ሁለቱ ወንኛ ገፀ ባህሪያት የሲ.ኤይ.ኤው ሰላይ ኤጀንት በራንዶነ ስኮፊልደና የኬ.ጂ.ቢ.ው ሰላይ ኤጀንት ቫሲሊ ታሌንኮቭ ሲሆኑ ሁለቱም በሚሰሩበት ድርጅት አንቱ የተባሉ ናቸው፡፡

ስኮፊልድ በምስራቅ አውሮፓ ኮሚኒስት ሃገሪች ውስጥ የነበሩ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችና ሳይንትስቶችን በአጠቃላይ ተጽኖ ፈጣሪ ሰዎችን ከእየ ሃገራቸው እያስከዳ ወደ ምዕራቡ አለም የሚያፈልስ ድርጅት ውስጥ አውሮፓ  ተቀምጦ ይሰራ ነበር፡፡ ይህን ተልኮ ለማክሸፍ በኬ.ጂ.ቢ. በኩል ታሌንኮቭ ተልእኮ ተሰጥቶት ይነቀሳቀስ ጀመር፡፡

ሁለቱ ደግሞ ለግድያ የሚፈላለጉ ጠላቶች ነበሩ፡፡ ለዚህ ምክነያቱ ደግሞ በስራው ሂደት ውስጥ ታሌንኮቭ የስኮፊልድን ሚስት ግድያ አቀነባብሮ ያሰፈፀመ መሆኑና ለዚህ በቀልም ሰኮፊልድ የታሌንኮቨ ወንድምን መግደሉ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ. 1978 ዓ.ም. የመከላክያው ዋና ጸሐፊ፣የብሔራዊ ደህንት ካውንስልና የአሜሪካ ፕሬዚደንት የጦር አማካሪ የሆኑት ጆይንት ቺፍስ ኦፍ ሰታፍ ጀነራል አንቶኒ ብላክበርን የገና ዋዜማ ላይ ኒወርክ ውስጥ  ተገድለው ተገኙ፡፡ ከጥቂት ግዜ በኋላ ደግም የሶቪየት ህብረት ኒውኩላር ሳይንቲስት ዲሚትሪ ዩሪ ዩሬቪች በአደን የግዜ ማሳለፊያ ላይ እንዳለ ተገደለ፡፡

ታሌንኮቭ ከአለቆቹ ዘ ማታሪስ ሰርክል የሚባሉ አለማቀፍ ቅጥረ ነፍሰ ገዳዮች በአለም ላይ ተጽኖ ፈጣሪ ሰዎችን እየገደሉ መሆኑን ተነግሮት ስኮፊለድን እንዲያገኘውና እነሱን ለማስቆም ወደ አሜሪካ ተላከ፡፡ ሁለቱ ባላንጣዎች ከብዙ መገዳደር በኋላ ተገኛኝተው በጋራ ከሚሰነዘርባቸው ጥቃት ለማምለጥ መተባበር ጀመሩ፡፡ ምክነያቱ ደግሞ ዘማታሪስ ሰርክል በሁለቱም ላይ እርምጃ መውስደ በመጀመሩ ነው፡፡

ሁለቱም በቅንጅት ስለ ዘማታሪስ ሰርክል አመሰራረትና አላማ ማጥናት ይጀምራሉ፡፡ እ.ኤ.አ. 1911 ዓ.ም. ጉላም ዲ ማታሪስ የተባለ የመሬት ከበርቴና ታላቅ የንግድ ሰው የተለያዩ አለም አቀፍ ነጋዴዎችን ከአምስት ሃገራት ከአሜሪካ፣ ሶቬይት ህብረት፣ሰፔይን፣ጣሊያንና ግሬት ብሪትን ሰብስቦ በጉብታ ላይ በሚገኘው ቪላው ውስጥ የመጀመሪውን ማታሪስ ጉባኤ ይመሰርታል፡፡

ከዚያም ጉባኤው እንዳበቃ አራቱ ተሰብሳቢዎች ለስራቸው የሚያስፈልጋቸውን እቅድና ገንዘብ ይዘው ቦታውን ለቀው ከሄዱ በኋላ ሚስጥር እንዳይወጣ በቪላው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ጉላም ዲ ማታሪስን ጨምሮ ይገደላሉ፡፡ ግድያውን የተካሄደው ደግሞ የወደፊቱ የማታሪስ ሰርክል መሪ የሚሆነው እረኛው ልጅ ተብሎ በሚጠራው (The Shepered Boy) ነው፡፡ ይህ ልጅ ከእድሜው በላይ የበሰለና በግዜው ክርሰቲያን ት/ቤት ተማሪ የነበረ ነው፣ ልዩ ተሰጦ የነበረውም (Child prodigy) ነበር፡፡

ዘማታሪስ ሰርክል ጎልምሶ ከ2ኛው የአለም ጦርነት በኋላ በአለም አቀፍ ደረጃ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችን የሚያሰማራና የሚገድል የማፍያ ቡድን ሆነ፡፡ የአለምን ኢኮኖሚና ፖለቲካ ለመቆጣጠር በግዜው በሽብረተኛነት የተፈረጁትን የፍልስጤሙን ፒ.ኤል.ኦ፣ የጀረመኑን ባድር ሚነሆፍ ና የጣሊያኑን ሬድ ብረጌድ በገንዘብ ይደግፍ ጀመር፡፡

የድርጅቱ ፍልስፍና የሃገራት ህልው መሆን አላስፈላጊና በሃብት ላይ የተመሰረተ አሌ የሚለው  ተቆጣጣሪ የሌለው ፖለቲካዊ ኃይል ለወደፊቱ ገዢ ሆኖ መውጣት አለበት ብሎ የሚያምን ነው፡፡ ድርጅቱ ፈላጭ ቆራጭ አመራር አብዛኛውን መሐበረስበን የበተች ተገዥ በሚያደርግና የጣሊያኑን ኮርፖሬት ፋሺዝምና በዳርዊንዝም ንድፈ ሃሳብ ጠንካራው ደካማውን መግዛት አለብት የሚል መዋጥና መደቆስ ላይ የተመረኮዘ አቅጣጫ አስቀምጦ ነው የሚጓዘው፡፡

ታሌንኮቭና ሰኮፊልድ ይህን ድርጅት ለማጋለጥ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ የግድያ ሙከራና የስም ማጥፋት ዘመቻ ተደርጎባቸዋል፡፡ ሁለቱም በየመንግሰታቸው ባንዳ ከሃዲ ተብለዋል፡፡ ዘ ማታሪስ ሰርክል እራሱን አንሰራፍቶ በአሜሪካም ሆነ በምስራቅና ምእራብ አውሮፓ ሃገራት ረጃጅም እጆቹን አስገብቶ የፖለቲካ፣  ደህንነት፣ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ተቋመትን፣ሚዲያዎችን… ተቆጣጥሮ የሻውን ሲያደርግ በዚህ ልብ ወለድ ውስጥ ተጽፎ ይነበባል፡፡ እንዲህ አይነት ያሉ እኩይና መሰሪ ድረጅቶችን ለማጋለጥና ለማሸነፍ ባላንጣዎች ልዩነታቸውን ትተው መተባበር እንደሚሰፈልጋቸው ድርሰቱ በታሪክ ፍሰቱ ውስጥ ይገልጻል፡፡

በመጽሐፉ ውስጥ የዚህን ቅጥረ ገዳያ ድርጅት ምርመራ ምክነያት የሆኑት የጆይንት ቺፍ ሰታፉ ጀነራልና የሶቪየት ህብረቱ የኒኩላር ፊዚስቱ ግድያ እንደሆነ ሁሉ የአብይ አህመድን አስተዳደር ስንመረምር፣ እሳቸው ወደ ስልጣን በመጡ ጥቂት ግዝያት ውስጥ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠ/ኢታማዡር ሹም ሰአረ መኮንን፣ የህዳሴው ግድብ ዋና ስራ አሰኪያጅ ኢነጂነር ስመኝው በቀለ፣ የአማራ ክልል ፕሬዚደንት ዶ/ር አምባቸው መኮንንና ከፍተና ባለስልጣናት፣የአማራ ክልል ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ጀነራል አሰምነው ጽጌ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሺነር የነበሩትአበረ አዳሙ… ግድያዎች በእሳቸው መሪነት ተፈጽመዋል፡፡

ዘ ማታሪስ ሰርክል በየሃገራቱና ስለላ ተቋማት ውስጥ ራሱን አስርጾ እንደሚያሰገባ ሁሉ ጠ/ሚ አብይም፣ አብረሃም ተክሉ ለማ በተባለ ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ፣ የአሜሪካን መከላከያ ምስጢር እያዘረፉ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡ ከዚህ በላይም እሳቸው ስልጣን ከመያዛቸው በፊት ለኦነግ፣ግነቦት ሰባትና ሲ.አይ.ኤ. ሲሰልሉም እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

እራሳቸውንም ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት መሪዎች ጋር በማቀናጀት የአማራን መሬት፣መተማ ላይ ለሱዳን አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ የጋምቤላን መሬት ለደቡብ ሱዳን በማሰወረርም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሞክረዋል፡፡

የ ማታሪሱ ሰርክል እነ ፒ.ል.ኦ፣ ሬድ ብርጌድን ይደግፍ እንደነበር ሁሉ እሳቸውም ኦነግ ሸኔን፣ አማር ክልል ውስጥ በፋኖ ስም የሚገድሉ ዘራፊዎችን አስርጸው አስገብተዋል፣ ከፍተኛ ብር በመመደብ ትግራይ ውስጥ ሌላ ዙር እልቂት ለመፈጸም እየተዘጋጁ ነው፡፡ አብይ የገንዘብ ምንጩ ምንድን ነው ካልን ከየክልሉ የሚዘርፈው መአድንና የአማራ መሬት ሽያጭ ነው፡፡

አብይ እራሳቸው ሶስተኛና አራተኛ ክፍል ተማሪ ሆነው ከአስተማሪዎቻቸውጋር ተቃቅፈው እንደሚሄድና ከእሳቸው የበለጡ ክፍል ተማሪዎችን ፈተና እንደሚያርሙ ነግረውን ነበር፡፡ እሳቸው አንደኛ ደረጃ ተማሪ በነበሩበት ግዜ እኔ አዲስ አበባ ዩንቨርስቴ ተማሪ ነበረኩ፡፡ ከዚያም የሂሳብ አስተማሪ ሆኜ እ.ኢ.አ. ከ1985ዓ.ም. አስከ 1988 ዓ.ም. ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ከደቡብ ኦሞ፣ጂንካ እስከ ሲዳማ ክልል አገልግያለሁ፡

አሳቸው እንዳሉት የአራተኛ ክፍል ተማሪዎችን ወይም የበላዮቻቸውን ክፍል ተማሪዎቹን ፈተና የሚያርም ተማሪ ከነበሩ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ከእኔ ተለምዶ ሁለት አይነት  ፈተናን ለተማሪዎቻቸው የሚሳርሙ መምህራን ነበሩ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ወልጌና ሃለፊነት የማይሰማቸው መምህራን ናቸው፡፡ ሁለተኞቹ ደግሞ ገብያ የሚወጣላቸው፣ ሲያዙት አቤት ሲለኩት ወዴት የሚል ታማኝ ተማሪ ካላቸው ሲደክማቸው አግዘን ይሉታል፡፡ የአብይ መምህራን የትኞቹ እንደሆኑ እግዜር ይወቀው፡፡ ሁለቱም ግን የጥሩ መምህራን ተምሳሌት አይደሉም፡፡

የአራተኛም፣ የአምስተኛም …እስከ ሰባተኛ ክፍል ድረስ ያሉት ተማሪዎችን ፈተና ማረም ከእድሜ በላይ የመብሰልና ልዩ ተስጦ ያለው ልጅ አያደርግም፡፡ የ ማታሪሱ ሰርክል እረኛውን ልጅ አብይ  ለመምሰል ቢሞክሩም እሱን ፈጽሞ  አይመስሉም፡፡ የተፈጥሮ ልዩ ስጦታ ያለውና ከእድሜው በላያ የበሰለ ልጅ  (child prodigy)   ማለት ወረቀት ተቀዶለት የምታየው ፊደል ይህ ካልሆነ ኤክስ አድረጋ ያ ከሆነ ደግሞ ራይት አድረግ የሚባል አይነት አይደለምና፡፡

የ ማታሪስ ሰርክል አባላት ፋሺዝምን መመሪያቸው ሲያደርጉ የኮሬ ነገኛ አባል ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ደግሞ ለመሰሎቻቸው ሰለ ኦሮሙማ ርዕዬት አለም ሲሳረዱ በድብቅ ተቀርጾ በወጣው መረጃ ላይ እንደሚሰማው፣ የነአብይ ኦሮሙማ ስብስብ እንደ ፋሺዝም ሁሉ በቡድና ዘር የበላይነት ላይ የተመሰረተና  ቋንቋን በማናገር፣ የኢኮኖሚ የበላይነትን በማሰፈን ቀጥሎም ኢሬቻን ከቀይ ባህረ እስከ ኤደነን ባህረ ሰላጤ በማስከበር በኦሮሞ ስም ቡድናቸውን መንገስ የሚፈልጌ ስብስቦች ናቸው፡፡ ይህን ለማስፈጸምም “አሳምን ወይም አደናግር” መመሪያቸው ይጠቀማሉ፡፡

እናንተ መጽሐፉን አንብባቸሁ የኔን ሃሳብ ውድቅ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ እኔም አንድ ሃሳብ ላጋራችሁና ነገሬን ልቋጭ፡፡ ነገሩ በሰሞኑ የፓሪስ ኦሎምፒክ ኮሚቴ መሪዎች አደረጉት ስለተባለው ውይይት ነው፡፡ ይኸውም የዶ/ር አሸብርንና የኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ፓሪስ በሚገኝ የኢትዮጳውያን ሬሰቶራንት ያደረጉት ፌሽታ ውስጥ በደምጽ ተቀረጸ የተባለውን መረጃን ይመለከታል፡፡

ጉምቱ የኦሮሚያ ባለስልጣን ስም እየተጠቀሰ፣ አትሌት ገዛህኝን በስናይፐር ይጠበጠባል ሲባል የሚሰማበት፣ በአመራር ደረጃ ማጭበርበር ሲካሄድ ሃላፊዎቹ የሚሰተፉበትን ማጭበርበር የሚያጋልጥ ሆኖ የተቀናበረው ማስረጃ የሚያሰደምም ነው፡፡ ለኦሎምፒክ ኮሚቴው ዝቅጠት መረጃ ሆኖ የቀረበውን በድምጽ ቅንብር ብቻ ሆኖ ስላገኘንው ደግሞ ታማኒነቱን የቀነሰ ነው የሚሆነው፡፡

ያህ ሁሉ ሴራ ነውን? የስለላው ቡድን የቀናበረውና ተፈላጊ ሰዎችን ለመምታትና ለማስፈራራተ ተከውኖ ይሆንን? እኒህ የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ስናነሳ በስዩም ተሸመ በኩል ሾልኮ ወጣ የተባለው መረጃ ሌላ ይዘት ኖሮት እናገኘዋለን፡፡ በተቀረጸው ድምጽ ውስጥ ስማቸው የሚጠቀሱት በድምጽ በንግግሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች አሉ፡፡

ሌተናነተ ኮሮኔል  ደራርቱ ቱሉ (አትሌት፣ወታደር)  ገዛህኝ አበራ(አትሌት፣ የፌድራሉ መንግስት ከትግራይ ክልል ጋር ባደረገው ጦረነት የተሳተፈ)፣ ኃይሌ ገ/ስላሴ( አትሌት፣ሻለቃና የተሳካለት ነጋዴ)፣ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊርጊስ (ሩሲያ የተማሩና ከራሺያ ማፊያ ጋር በጦር መሳሪያ ንግድ ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚታሙ)፣ የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዚደንት  ኦቦ አውሉአብዲ…ኒህ ናቸው ሰሞች ነው እንግዲህ ማስረጃው ሚጠቅሳቸው፡፡

ወታደሮቹንና ባለስልጣናቱን ነጥዬ ማሳየት የፈለግኩት ይህ ነገር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጋር የተገናኘ ይሆን ይሆን እንዴ የሚለውን ጥያቄ ለማመላከት ነው፡፡ መጀመሪያ ግን ስዩም ተሸመ ማን ነው? ስዩም ተሸመ እራሱን እንደ አክቲቪስት የሚቆጥር ቢሆንም በዚያ ረገድ አንዳንድ ስራ  ቢሰራም ፐሮፓገነዲስት ነው፡፡ ለዚህ ደግም በፌድራል መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል በተደረገው ጦርነት የኢትዮጵያ ጦር ወደ መቀሌ በፍጹም በልተጠጋበት ወቅት ፐላኔት ሆቴል ላይ የኢትዬጵያ ኮማነዶ ወረደ እያለ ይዘግብ ነበር፡፡ ጠ/ሚ መቀሌ ያሉት ዱቄት ሆነው ተበትነዋል ባሉ ግዜ ደግሞ፣ እሱ  በዩቲብ ቻናል ላይ ብቅ ብሎ እስከዛሬ ድረስ ፐላኔት ሆቴል ተያዘ ብለን ስንዋሽ የነበረው ለድሉ ስንል ነው ብሎ በአደባባይ ፐሮፓጋንዲስት መሆኑን ያረጋገጠ ሰው ነው፡፡

አሁን አሁን ደግሞ ስለ ኤርትራም ይሁን ስለ ምንም ጉዳይ የአብይ አህመድን አቋም አስቀድሞ በአክቲቪዝም ስም  የሚንጸባርቅ የጠ/ሚሩ ቅድመ ጥላ አፈቀላጤ ሆኗል፡፡ እናም ይህንን የኦሎምፒክ ኮሚቴ ቅሌት የተባለውን በድምጽ የተቀረጸ ማስረጃ ይዞ ወጣ፡፡ ጥያቄው አብይ በዚህ በወጣው የኦሎመፒክ ኮሚቴ ግርግር ምን ሊያሰተላልፉ የፈለጉት ምልእክት አለ ነው?

ፍልቅልቂቷ ደራርቱ ጭዳ የሆነች ይመስለኛል፡፡ ወጣት ሳለሁ ኤርትራ ዘምቶ የመጣ ወታደር እኛ ሰፈር ነበረ፡፡ ወሬው ሁሉ ወታደራዊ ቋንቋ ነበረው፡፡ ልጅቷን ከወደደና እየተጠጋት ከሆነ፣ ሃሳቡን እንዲህ ሲል ይገልጻል፤ ልጅቱ በዙ23 ቀለበት ውስጥ ገብታለች፡፡ ልጂቱ ደግሞ በፍቅሬ ነሆለለች ላመለት፤ በአውቶማቲክ ተኩስ ረመረምኴት ይል ነበር፡፡ ታዲ ደራረቱ ገዛህኝ ሰልፍ ሊያስወጣብሽ ነው ስትባል ዘመኑ የስናፐር ነው በዚያ ይጠበጠባታል ብትል፣ የመልስ ምት በሰፖርት ሚዲያ ይሰጠዋል ተብሎ ለመተርጎም እድሉ ሰፊ ነው፡፡

ስለ ዶ/ር አሸቢር ብዙ አላውቅም ግን ኢትዮጵያ ሳለሁ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት የመሆን ፍላጎት እንደነበራቸው ሰምቼለሁ፡፡ ያን ግዜ ግን ኮታው ለኦሮሞ ብቻ የሆነ በመሆኑ ከንቱ ልፋት ሆኖ ቀረ እንጂ፡፡  ጠላቶቻቸው ከወያኔ ጋር ተለጣፊ ነበሩ ሲሉ ይከሷቸዋል፡፡ ማን ያልነበረ አለ? ድፍን ኦህዲድ/ ብልጽግና ጠ/ሚ አብይን ጨምሮ የወያኔ ተለጣፊና ገዳይ አልነበሩም እንዴ? ዳንኤል ክብረትስ በሄደበት ሁሉ የአዜብ መስፍን አሞጋሽና ቋሚ ደጋፊዬ እሷ ናት ይል እንዳልነበር ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ ወያኔን ከሰው ሃሰብ አዕምሮ አውጥተን እንሰርዘው ሲል አያፍርም፡፡ እድሜ ይስጠው እንጂ ነገ ምን እንደሚል ተጠባቂ ነው፡፡

ዘመኑ “ማየትና መስማት ማመን ነው” የምንልበት ዘመን አይደለም፡፡አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሁሉንም የሰሜት ህዋሳቶቻችንን የነጠቀበት ግዜ ነው፡፡ አንድ ፈረንጅና አንድ ጥቁር ሴት ወሲብ ሲፈጽሙ የሚያሳይ ቪዲዮ ቢደርሳችሁ የ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስራ ሊሆን ስለሚችል እለፉት፡፡ በተፈለገው አንግል የሰውን አንገት ቆርጦ ጠያፉ ነገር ላይ በመቀጠል ሊከናወን ከድምጽ ቅንብርም ጋር ሊቀርብ ይቻላል፡፡ይህ በየሰፈሩ ያሉ ልጆች እንደሚሰሩት ሳይሆን በኤክስፐርቶች ደረጃ ሰለሚሰራው ነው የምነግራችሁ፡፡

አሁን ስለነ ደራርቱ ስለወጣው የተቀረጸ ድምጽ ላውጋ፡፡ በአስከሪብቶ የሚቀረጽ ድምጽ አለ፡፡ አሁን  ተቀረጸ የተባለው ድምጽ እየተዟዟረ እንደሆነ ወይንም ከአንድ አቅጣጫ እንደተቀረጸ መለየት ያስፈልጋል፡፡ ቀረጸ የተባለውም ሰው ሳያውቀው ሞባይሉ ላይ ድምጽን የሚቀዳ አፕ ተጭኖበት ሊሆን ይችላል፡፡ ወይንም ከብዙ ሞባይሎች የተቀዳ ድምጽ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቀናብሮ ወጥቶ ሊሆን ይችላል፡፡

ያም ብቻ አይደለም ሰዎቹ ያንን ሁሉ ንግግር ያደርጉ የነበሩት ሞቅ ብሏቸው ስለነበር የልተናገሩትን ሁሉ በእነሱ ድምጽ መቀጠል ይቻላል፡፡ ደራርቱ ከአትሌት ኃይሌ ጋር ችግር እንደሌለባት በእናታችሁ እሱን ተዉት ስትል ትደመጣለች፡፡ የሆኖ ሆኖ ስዩም ተሾመ ያወጣውን የድምጽ ቅጂ ስፒች አናሊስቶች ጋር ወስዶ ማስመርመር ነው የሚያስፈልገው፡፡ ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ አይደል የሚለው ተረቱ፡፡ ሰዎቹ በጠረጴዛ ዙሪያ የነበራቸውን አቀማመጥ ማወቅ ከተቻለ ከየት አቅጣጫ እንደተቀዳ ማወቅ ይቻላል፡፡

ከድምጽ ጥራቱ ጋር ተያይዞም በኪስ ውስጥ ከተቀመጥ ሞባይል ወይንስ ጠረጵዛ ላይ ከተለጠፍ ወይም ግድግዳ አካባቢ ከተቀመጡ ግድግዳ ላይ ከተለጠፈ መቅጃ፣ ይህ እንግዲህ አስቀድመው ሪዘረቬሽን ሲይዙ ከሬሰቶራንቱ ባለቤቶች እውቅና ውጭ የሚደረግ ነው፣ ነገሩ ከየት አቅጣጫና እንዴት ተሰራ የሚለውንም መልስ ይሰጣል፡፡ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አንዱ ችግር ድምጽ ውስጥ ያለን ሰሜት (Voice emotion detection)  ላይ አጠቃሎ ማየት (Bias) አለው::  ሆኖም ግን በእውነተኛ ሳቅ የታጀቡ ንግሮች፣ የሰዎቹ የነግግር ሁኔታ፣ ማን ነው አቅጣጫ ሰጪ ጥያቄና ሃሳብ የሚቀርበው? ንግግሩ በማን ነው የሚዘወረው? የሚለውን ስንመለከት ደራረቱ ካለ ቦተዋ የተገኘች ሰሊጥ ሆና ትገኛለች፡፡

ይህንን ዩንቨርሰቲዎች ውስጥ በወሰድኴቸው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስም ይሁን ሌሎች ኮረሶች በለኝ መጠነኛ እውቀት ቢያንስ ቢያንስ ለራሴ አረጋግጫለሁ፡፡ ሌላው በድምጽቅጂው  ውስጥ ስማቸው የተጠቀሰው የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚደንት አወሎ አብዲን የሚመለከት ነው፡፡

እኚህ ሰው ሮይተርስ ባወጣው የአብይ ማታሪስ ሰርክል – ኮሬ ነገኛ አስወጋጅ፣መቺ፣ገዳይና ጠላፊ ቡድን ውስጥ ስማቸው የተጠቀሰ ነው፡፡ ዘ ማታሪስ ሰረክል የስፔኑን አለም አቀፍ ነጋዴ በመግደል ስራውን ፈረንሳይና ጣሊያን ድንበር ኮርሲካ ውስጥ በማሰወገድ  እንደጀመረ፤ ኮሬ ነገኛ እነደ ድመት ልጆቹን ለመብላት እያኮበከበስ ቢሆን?

ስለ ዶ/ር አሸቢር አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ለእኚህ ሰው ከቴውደሮስ ጸጋዬ ጋር ኢንተርቪው እንዲያደርጉ ማን ነው ፍቃድ የሰጣቸው? ቴዲ የሚያምንበት አላማ ለእራሱ እንደተጠበቀ ሆኖ እንደ አያቶቻችን እምነት ልበ ብርሃን የሚባል ሰው ነው፡፡ አንድ ጥያቄ ከአድማጭ ተመልካች ተጠየቀና ዶ/ር አሸቢር ፖለቲካ ነው አልመልስም አሉ፡፡ አገኛቸው መሰል፣ አብይ ለምን አልናገርም አሉ ብሎ ሲያፋጥጣቸው ያሳዩት ፊት ኤጭ እሱ ምን አባቱ አይነት ንባብ ይነበብበታል፡፡ ይህ ደግሞ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ጄኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ አበባ ውስጥ የተደበደበው እኮ አብይ በጦነቱ ውስጥ ከፐሮፓጋንዳ በስተቀር ምንም አስተዋጾ አልነበረውም በማለቱ ነው፡፡

የወጣው የድምጽ ማስረጃ የሚያሰገርም ነው፡፡ ነገሩ ሆነና በአንድ ወንጭፍ ሶስት ወፍ ሴትየዋም ተገኘች፡፡ የአበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም እንዲሉ፣ ከዞህ በኋላ ወላ ጀነራል ነሽ ሚኒሰትር …በአርግድ አርበርብዱ ድምጽ ሳይሆን በቪዲዮ ምስል ይገዛሉ፡፡ ነገሩ እንደዚያ ነውና፣ የሁላችሁም ማስረጃ በእጃችን አለ ነው ውስጠ ዘው፡፡ ጀዋርም አዚያ ሰፍር ዝር ብሎ ነበር አሉ፡፡ ወቼ ጉድ?!

“ሁለቱን ማግኘት ካልቻልክ ከምትወደድ ይልቅ ብትፈራ ይሻላል!” ኒኮሎ ማካቬሌ

“ብዙዎች አንተ መስለህ የቀረብከውን ነው የሚያዩት ጥቂቶች ግን አውነተኛ ማንነትህን ይረዳሉ!” ኒኮሎ ማካቬሌ

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫነኩቨር ካናዳ

GWYe8ssXEAI7Bg5

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/ ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
Go toTop