July 29, 2024
24 mins read

በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት!!! ጥቁር ገበያ አበደ!!! ብር በጆንያ ብሪቱ አበደች!!!

ሚሊዮን ዘአማኑኤል  (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

birr

A FREE-FLOATING EXCHANGE RATE SYSTEM

የገቢ ንግድ (ኢንፖርት) በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት ሲዘረጋ

  • የነዳጂ ዋጋ 5.6  ቢሊዮን ዶላር የነበረ ወጪ ወደ 11.2 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ይጨምራል፡፡
  • የማዳበሪያ ዋጋ 1.2 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ወጪ ወደ 2.4 ቢሊዮን ዶላር ይመነደጋል፡፡
  • ምግብ ነክ ምርቶች 2 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ወጪ ወደ 4 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያስከፍላል፡፡
  • መድኃኒት ምርቶች 196 ሚሊዮን  ዶላር የነበረ ወጪ ወደ 392 ሚሊዮን  ዶላር ከፍ ይላል
  • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስቀመጥከው 100 ሚሊዮን ብር  በዶላር ሲመነዘር ፣በብሔራዊ ባንክ አንድ ዶላር 57.77 ብር ሲሰላ 1,731,002  አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሠላሳ አንድ ዶላር የነበረህ ሲሆን በጥቁር ገበያ 120 ብር ሲሰላ 833,333 ስምንት መቶ ሠላሣ ሦስት ሽህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሦስት ዶላር አሁን ያለህ ሂሳብ ይሆናል፡፡  897,669 (ስምንት መቶ ዘጠና ሰባት ሽህ ስድስት መቶ ሰልሳ ዘጠኝ) ዶላር ተዘርፍሃል ማለት ነው፡፡
  • የኢትጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ  ከመንግስታዊ የልማት ኢንተርፕራይዞች ዋጋ 38 ቢሊዮን ብር የተተመነ ዋጋ የነበረው ሲሆን በአሁኑ የጥቁር ገበያ ዋጋ 316,666,666 ሚሊዮን ዶላር ዋጋቸው ይወርዳል ማለት ነው፡፡

የዓለም ባንክና የዓለም ዓቀፍ ገንዘብ ተቆም (አይኤምኤፍ)  የኢትዩጵያን ብር የገንዘብ ምንዛሪ ተመን እንዲያስተካክል በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት ማለትም (A FREE-FLOATING EXCHANGE RATE SYSTEM) የገንዘብ የመግዛት አቅም በጥቁር ገበያ ዋጋ እንዲወሰን ሲያሳስብ ፖሊሲያቸው በተለይ የብልጽግና መንግስት ዘመን ለሃገሪቱ ምንም የፈየደው ነገር እንደሌለ፣ የሃገሪቱን የማይክሮና የማክሮ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሁኔታዎች እንደማይሻሻል ችግሩንም እንደማይፈታ እንዲያውም እንደሚያባብሰው ይታመናል፡፡ በሃገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ  በሃገሪቱ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የምርትና ሸቀጦች  የፍላጎትና የአቅርቦት ኃይል በማዛባት የሃገሪቱ የብር መግዛት አቅም እየወደቀ እንዲሄድ በማድረግ በሸቀጣ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ግሸበት ከመቼውም ግዜ በላይ ይከሰታል፡፡ በነጻ ገበያ በጥቁር ገበያ ዋጋ መተመን ማለት ፀረ እድገትና ፀረ ምርት ነው፡፡ ምክንያቱም ሃገሪቱ ከውጭ የምታስገባቸው የነዳጅ ፍጆታ፣ የካፒታል ጉድስ እቃዎችና እንደስትሪ እቃዎች ብሎም ስንዴ፣ የበቆሎና የዘይት የመሣሰሉት  የምርትና ሸቀጦች  ዋጋ በጣም ስለሚጨምሩ የዋጋ ግሸበቱ ወደ ሁለት አሃዝ ማሻቀቡ ግድ ላል፡፡

በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት ስረ መሠረቱ ሃገሪቱ ያለባትን የውጭ እዳ እንዴት ለመክፈል ትችላለች ተብሎ በዓለም ባንክና የዓለም ዓቀፍ ገንዘብ ተቆም (አይኤምኤፍ) የሚመቻች ግዜያዊ መፍትሄ እንጂ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ የፈየደው አንዳችም ነገር የለም፡፡ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት ማለት በዓለም አቀፍ ንግድ ፍላጎት የውጭ ምንዛሪ ተመኑ በጥቁር ገበያ አንዴ ከፈ ወይም  አንዴ ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ (A floating currency is allowed to rise or fall depending on global demand.) በዓለም ባንክና የዓለም ዓቀፍ ገንዘብ ተቆም (አይኤምኤፍ)የብልጽግና መንግሥት አንገት ጥምዘዛ የተነሳ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት እንዲተገብሩ ታዞል፡፡ በዚህም መሠረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  የውጭ ምንዛሪ ይፋዊ መገበያያ ተመን፣ከጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ ኢ-ይፋዊ መገበያያ ተመን ጋር እኩል እንዲሆን ተወስኖል፡፡  ይህም ማለት በብሔራዊ ባንክ የአንድ ዶላር ተመን 58 ብር ሲሆን፣ በጥቁር ገበያ ደግሞ አንድ ዶላር 120 ብር ይመነዘራል ማለት ነው፡፡ ሰለዚህ የብሔራዊ ባንክና የጥቁር ገበያ  የውጭ ምንዛሪ ይፋዊ መገበያያ ተመን ከዚህ በኃላ 120 ብር ይሆናል ማለት ነው፡፡

Higher demand means higher value, while lower demand means lower value. Using a floating currency can be considered a fiscal benefit when the economy is strong and fiscal policy is sound. But, if market sentiment towards the government and its monetary policy is weakened, it could lead to a devaluation of its currency

ይህ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በገበያው አማካኝነት እንዲበየን የማድረግ ሂደት መሆኑን መግለጫው ያስረዳል። ይህንን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ የሚያስገኘው ፋይዳን ሲዘረዝርም ፣ ”  በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመንን ማረጋገጥ በአቅርቦት እና በፍላጎት መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ መዛባት ለማስተካከል የሚረዳ ፣ የገቢ እና የወጪ ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ዋጋ ከገበያ እውነታዎች ጋር እንዲጣጣም የሚያስችል እና በክፍያ ሚዛን ላይ ያለውን አለመመጣጠንም ለማስተካከል ይረዳል” ብሏል።

በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት መዘርጋት ማለት፡-

{1} የኢትዮጵያን ብር የገንዘብ ምንዛሪ ተመን በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት በመከተል

ምክንያት በሃገሪቱ ገበያ የምርትና ሸቀጣሸቀጦች ዋጋ ግሸበት ይባባሳል፡፡

{2} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት የብር ምንዛሪ ተመን አንዴ ከፍ ወይም ዝቅ  በማድረግ ተለዋዋጭና እርግጠኛ ያለመሆን ጥርጣሬ በሃገሪቱ ያሰፍናል፡፡ በአመዛኙ የብር ቅነሳው ተስፋ መቁረጥ ያስከትላል፤ እናም ቀጣይ ተለዋዋጭ ጭማሪ በውጭ ምንዛሪ ተመን ያመጣል፡፡ የሃገር ውስጥ ምርትና ሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ አለመረጋጋት ያስከትላል ብሎም በሃገሪቱ አጠቃላይ ምርት ይቀንሳል፡፡

{3} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣የኢትዮጵያን ብር የገንዘብ ምንዛሪ ተመን  አንዴ ከፍ ወይም ዝቅ በማድረጉ ምክንያት የሃገሪቱ ኢንፖርት/ገቢ ንግድ የሸማቾች ፍጆታ ሸቀጣሸቀጦች ዋጋ ይጨምራል፡፡ ኢትዮጵያ በገቢ ንግድ ምርትና ሸቀጣ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ላይ የምትተማመን ሃገር በመሆኖ በተለይም ከውጭ አገር በሚመጡ ምርቶች በተለይ በምግብ ምርቶች ስንዴ፤ስኳር፣ዘይት ወዘተ ዋጋ በእጥፍ በላይ ይጨምራል ማለትም  በብሔራዊ ባንክ የአንድ ዶላር ተመን 58 ብር ሲሆን፣ በጥቁር ገበያ ደግሞ አንድ ዶላር 120 ብር ይመነዘራል ማለት ነው፡፡ ሰለዚህ የብሔራዊ ባንክና የጥቁር ገበያ  የውጭ ምንዛሪ ይፋዊ መገበያያ ተመን ከዚህ በኃላ 120 ብር ስለሚሆን  ህዝቡ በኑሮ ውድነትና በዋጋ ግሸበት ይሰቃያል፡፡

{4} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ የሃገር ውስጥ ሃብትና ንብረት መሬት ጭምር ይረክሳል፣የኢትዮጵያን ብር/የገንዘብ ምንዛሪ ተመን ጥቁር ገበያ አንዴ ከፍ ወይም አንዴ ዝቅ  በማድረጉ ምክንያት የሃገሪቱ የተፈጥሮ ሃብትና ንብረት የውጭ ምንዛሪ ባከማቹ ዩኤስ ዶላርና ፓውንድ ወዘተ ባላቸው ባለሃብቶች እጅ ይነጠቃል፣ይወድቃል፡፡ የዓለም ዓቀፍ የንግድ ካንፓኒዎች በሃገሪቱ ውስጥ የመሬት ወረራ ያደርጋሉ፡፡

{5} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ መንግስት ግልፅነት የሌለው፣ የብር/የገንዘብ ምንዛሪ ተመን በጥቁር ገበያ አንዴ መጨመርና አልያም መቀነስ ምክንያት በህዝቡ ላይ የኑሮ ውድነት ይከሰታል በዚህም ህዝቡ በመንግስት ላይ እምነት ያጣል፡፡

{6} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ በሃገሪቱ የሚወጣና የሚገባ ገንዘብ ልዩነት balance of payments (BoP) አይስተዋልም ወይም አይታይም፡፡ የዚህም ምክንያቱ በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ የብር ምንዛሪ ተመን በጥቁር ገበያ አንዴ ከፍ ወይም ዝቅ ማለቱ ለብዙ አመታት መቀጠሉ አይቀሬ ነው፡፡ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ ውጤታማ እንዲሆን፤የምርት አቅርቦት መጨመርና የምርት ፍላጎት ማደግ ያስፈልጋል፡፡ የምርት ፍላጎት ከፍና ዝቅ ማለት የኢትዩጵያ የውጭ ንግድ ምርቶች በሃገር ውስጥ የምርት ፍላጎት መተካት ይኖርበታል፡፡ የሃገሪቱ ኢንፖርት/የገቢ ንግድ በሦስትና አራት እጥፍ ከኤክስፖርት/የውጭ ንግድን ይበልጣል፡፡ ይህም የሚጠቁመን ነገር ቢኖር፤ የሃገሪቱ አጠቃላይ ብሄራዊ ምርቶች አነስተኛ በመሆናቸው የምርት አቅርቦት እጥረት ከምርት ፍላጎት ጋር ማጣጣም አይቻላቸውም፡፡ በአጭር ግዜ ውስጥ የምርት አቅርቦት መጨመር አይቻልም ሰለዚህም በሃገሪቱ የሚወጣና የሚገባ ገንዘብ ልዩነት ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ ይሄዳል፡፡

{7} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ የኢትዮጵያን ብር የገንዘብ ምንዛሪ ተመን ከፍና ዝቅ ማለት በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ጎጂ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡ የብር ምንዛሪ ተመን በጥቁር ገበያ አንዴ ከፍ አሊያም ዝቅ  ማለት ጠንካራ የውጭ ምንዛሪ ተመን ያላቸው ሃገራትን ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል ማለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሃገሪቱ የገቢ ንግድ አንድ ዕቃ ለመግዛት ከበፊቱ የበለጠ ብዙ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ መክፈል ይጠበቅባታል፡፡ ሰለዚህም የዓለም ዓቀፍ የንግድ እንቅስቃሴችን የየገቢ ንግድ ከውጭ ንግድ ከፍተኛ በመሆኑ ምክንያት የንግድ ሚዛኑ ከፍና ዝቅ ያለ ነው፡፡ የኢትዩጵያ የውጭ ንግድ መሠረቱ የግብርና ምርቶች በመሆናቸው በዓለም ዓቀፍ ንግድ ላይ ዋጋቸው መለዋወጥ ይታይበታል፡፡ በሌላ በኩልም፤ የኢትዩጵያ የገቢ ንግድ መሠረቱ የካፒታል ጉድስ ምርቶች፣ ያላለቁ የካፒታል ጉድስ ምርቶችና ግብአቶች  ወዘተ በውድ የውጭ ምንዛሪ ተገዝተው በመግባታቸው ምክንያት በሃገር ውስጥ የሚመረቱ አጠቃላይ ብሄራዊ ምርቶች የማምረቻ ወጭ ይጨምራል፡፡ ማለትም የነዳጅ፣ የኬሚካል፣ የማዳበሪያ፣ የተለያ ማሽነሪዎች፣ ፋብሪካዎች፣ መኪኖች፣ መለዋወጫ እቃዎች ዋጋ መናር ምክንያት  የማምረቻ ወጭ ይጨምራል፤ ከዛም የምርቱ ዋጋ  ይጨምራል፡፡

 

{8} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ የኢትዩጵያን ብር የገንዘብ ምንዛሪ ተመን ከዓለም አቀፍ ንግድ ፍላጎት ጥቁር ገበያ አንዴ መጨመርና አንዴ መቀነስ ሃገሪቱን የዕውን ሃብት ይቀንሳል ማለትም ዋጋ ግሽበቱ ሃገሪቱን ሃብትና ንብረት እየዋጠ ይሰለቅጣል ብሎም የኑሮ ውድነቱን ያባብሳለው፡፡ የግል ባላሃብቶችና ካንፓኒዎች ከውጭ ንብረትና እቃዎች በውጭ ምንዛሪ በብድር ያስገቡ፤ የብር ምንዛሪ ተመን በጥቁር ገበያ መወሰን  እርምጃ ለእዳና ኪሳራ ይዳርጋቸዋል፡፡ እዳቸው ይጨምራል እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ዩኤስ ዶለር ዋጋ የመግዛት አቅም ከፍተኛ ይሆናል፡፡

{9} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ የኢትዮጵያን ብር የገንዘብ ምንዛሪ ተመን መጨመርና የመቀነስ ምክንያት በሃገር ቤት የባንክ አካውንት ደብተር ከፍተው የቁጠባ ሂሳብ በማስቀመጣቸው ምክንያት ገንዘባቸውን ተዘርፈዋል ለምን ቢባል ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ጠቃሚ ያልሆነ ወይም ዋጋ የሌለው የወለድ ተመን የተነሳ ነው፡፡ በአንጻሩም ዘረፋው በዚህ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን የሃገሪቱ አንጡራ ሃብትና ንብረት በመቀነሱ ጭምር የሃብታችን ደረጃ ዝቅ ማለቱ ግድ ይላል፡፡ በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ የገንዘብ ምንዛሪ ተመን በጥቁርገበያ መሆን ምክንያት መንግስት የባንክ የቁጠባ ሂሳብ አስቀማጩ ግለሰብ ካስቀመጡት ገንዘብ መንግስት ሃብታቸውንና ገንዘባቸውን  ዘርፎቸዋል ማለት ነው፡፡

 

  • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቁጠባ ሂሳብ ያስቀመጥከው 100 ሚሊዮን ብር  በዶላር ሲመነዘር ፣በብሔራዊ ባንክ አንድ ዶላር 57.77 ብር ሲሰላ 1,731,002  (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሠላሳ አንድ) ዶላር የነበረህ ሲሆን በጥቁር ገበያ 120 ብር ሲሰላ 833,333 (ስምንት መቶ ሠላሣ ሦስት ሽህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሦስት) ዶላር አሁን ያለህ ሂሳብ ይሆናል፡፡  897,669 (ስምንት መቶ ዘጠና ሰባት ሽህ ስድስት መቶ ሰልሳ ዘጠኝ) ዶላር ተዘርፍሃል ማለት ነው፡፡
  • በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣የብሩ የመግዛት አቅም በመውደቁ የተነሳ ትላንት፤ አምስት ሊትር ዘይት በ1000 ብር ይገዛ ከነበረ፤ ዛሬ 2000 ብር ይገዛል ስለዚህ ትላንት ያስቀመጠው 1000 ብር፤ ከዛሬ 10 ብር ጋር እኩል ሆኖል እንደማለት ነው፡፡) በዚህ ምክንያት መንግስት ሃብታቸውንና ገንዘባቸውን  ዘርፎቸዋል ማለት ነው፡፡

{10} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ በሌላው ዓለም እንደሆነው ሁሉ፤ የኢትዩጵያ የብር ምንዛሪ ተመን በጥቁር ገበያ ሲወሰን  አስቀድመው የሰሙ፣ የጠረጠሩና ያወቁ ሁሉ ያላቸውን ብር ወደ ዉጭ ሃገር ምንዛሪ ዩኤስ ዶለር፣ ፓውንድ ወዘተ በመቀየር መንግስት የብር ምንዛሪ ተመን በጥቁር ገበያ ዋጋ ሲወስን  በናፍቆት ይጠባበቃሉ፡፡ ለምሳሌ  በኢትዩጵያ የጥቁር ገበያ አንደ ዩኤስ ዶለር 120 ብር ሲሰላ  ከበፊቱ ተመን ወደ ዩኤስ ዶለር የቀየሩ ነጋዴዎች ከምንዛሪው ለውጥ በኃላ ያላቸው ብር ከእጥፍ በላይ እንደሆነላቸው  ማስላት ቀላል ነው፡፡

{11} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ የኢትዩጵያ የብር ምንዛሪ ተመን ከጥቁር ገበያ ጋር እኩል መሆን እርምጃ ሃገር ውስጥ አጠቃላይ ብሄራዊ ምርት በተለይም የኢንደስትሪና የማንፋክቸሪንግ ምርት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ባለመሆናቸው ከገንዘብ ቅነሳው ጥቅም ተጋሪዎች አይሆኑም፡፡ በዚህም የሃገሪቱ ከውጭ የምታስገባውን ኢንፖርት/የገቢ ንግድ የመተካት ሚና ለመጫወት እድገታቸው አይፈቅድላቸውም፡፡

{12} በኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት፣ የብር ምንዛሪ ተመን በጥቁር ገበያ ሲሰላ  እውነተኛ ገቢን ይቀንሳል ብሎም አጠቃላይ የምርት ፍላጎትን ይቀንሳል፡፡ በዚህም ምክንያት የሃገሪቱ አመታዊ አጠቃላይ ብሄራዊ ምርት (GDP)ና መንግስት የሚሰበስበው የገቢ ታክስ ይቀንሳል፡፡ በዚህም ምክንያት መንግስት የሚያከናውናቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች የመንገድ፣ የባቡር፣ የኤርፖርት  መሰረተ-ልማት ዝርጋታ ግብንባታቸው ይጨምራል፡፡ መንግስት የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ለማስቀጠል ፣ብዙ ገንዘብ እንዲያትም ይገደዳል እናም የዋጋ ግሽበት በሃገሪቱ ይከሰታል፡፡ መንግስት ከውጭ ሃገራት የተበደረውን እዳ ለመክፈል ዓቅም ያጥረዋል፣ እንዲሁም ሌላ አበዳሪ ማግኘት ይሳነዋል፡፡ በአጠቃላይ የብር ምንዛሪ ተመን ቅነሳ መዘዙ ቁልቁለት የመውረድና የቂሎች ጨዋታ ነው የሚሉት፡፡

ሌላኛው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተብሎ የተጠቀሰው በቅርቡ በብሔራዊ ባንክ ይፋ የተደረገውና ወደ ትግረበራ የገባው በወለድ ተመን ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ሥርዓት ነው። በቀመጠል የተጠቀሰው ቁልፍ ማሻሻያ የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያ ሲሆን ፣ የዚህም ዋና ዋና ትኩረቶች የመንግሥት ገቢን ማሳደግ፤ የመንግሥት ወጪንና የድጎማ ሥርዓትን ውጤታማ ማድረግ፣ በጡረታ ፈንድ ሥርዓቶች ላይ መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን መተግበር፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማና ተወዳዳሪ ማድረግ እና የመንግሥት ብድር አስተዳደር ውጤታማና ዘላቂ እንዲሆን ማረጋገጥ መሆናቸውን መግለጫው ያመለክታል።

 

ምንጭ

Source:-Zenawi and the devaluation of the birr:A layman’s guide

Seid Hassan:2010-09-30, Issue 498, http://pambazuka.org/en/category/features/67399

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop