July 11, 2024
24 mins read

ንጉስ ዳዊት የተናዘዘበትንና ንስሀ የጠየቀበትን የእረኛውን ዋሽንት እንስማ!

በላይነህ አባተ ([email protected])

አባቶች የሚባሉት በጎቻቸውን ለተኩላ አስረክበው በየከተማው አድፍጠዋል፡፡ ባለማተቡ የጦቢያ የበግ እረኛ ግን በክረምት ገሳውን፣ በበጋም ጥቢቆውን እየለበሰ በየወንዙ ዳር፣ በየመስኩና በየገደላገደሉ በጎቹን ከተኩላና ከቀበሮ ጠንክሮ እየጠበቀ ከስድስት ሺህ ዘመናት በላይ ያስቆጠረውን ቅዱስ የእረኝነት ሥራውን ቀጥሏል፡፡  በየኢትዮጵያን ቅድመ ኦሪት፣ ኦሪትና ድኅረ ኦሪት ዘመናት ለመፈተሽ ላልሞከረ እረኛ ያልሰለጠነና ያልተማረ የበግ ጠባቂ ይመስለዋል፡፡ ሳይቸግር ጨው ብድር እንደሚባለው የራሱን መንፈሳዊና ባህላዊ ሐብት በሚገባ ሳያውቅ ተሌሎች ዘንድ እንደ ወተት ዝንብ ዘሎ ለተንጠቦለቀና ለባከነ አገር በቀል ዜጋም የጦቢያ እረኛ ዋሽንት ተራ የሸምበቆ ጉማጅ መስሎ ሊታየው ይችላል፡፡ የጦቢያ እረኛና የዋሽንቱ ቁርኝት ግን መለኮታዊ መሰረት እንዳለው ልብ ይሏል፡፡

Washint

እረኛ፡- እረኛ ጠባቂ ነው፡፡ እረኛ በጎቹን ተኩላ ወይም ቀበሮ እንዳይነጥቅ ተግቶ የሚጠብቅ ሥርዓት ያለውና ማተብ ያሰረ ባለሙያ ነው፡፡ እረኛ ኃላፊነት የሚሰማው፣ የነጣ የጠዳ ህሊና ያለው፣ በጎቹን ቀበሮ ከሚነጥቃቸው እርሱ ቢጠፋ የሚመርጥ ጠባቂ ነው፡፡ ቅዱሱ መጽሐፍ ዮሐ ፲፡፲፩ ላይ “ቸር ጠባቂ ነኝ! ቸር ጠባቂ ስለቦጎቹ ነፍሱን ይሰጣል፡፡ ጠባቂ ያይደለ በጎቹም ገንዘቡ ያይደሉ ምንደኛ ግን ተኩላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፡፡ይላል፡፡ አዎ እረኛ በጎቹን ለተኩላ ወይም ለቀበሮ ትቶ ተሚሄድ የክረምት ዶፍ ቢወርድበት፣ የበጋ ቃጠሎ ቢያጋየው ይመርጣል፡፡ የሉቃስ ወንጌል ፲፭፡ ፬-፭ “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን  በርሃ ትቶ የጠፋውን እስክሚያገኘው ድርስ ሊፈልገው የማይሄድ ማነው?” በሚለው መሰረት እረኛ ተበጎቹ አንዷ ወንዝ ተሻግራ ብትሄድና ወንዙ ቢሞላ የጠፋችዋን በግ ፍለጋ ጢም ያለውን ወንዝ ሰንጥቆ ተሻግሮ ይሄዳል፡፡ እረኛ ግልግል በቀበሮ አስበልቶ ተሚገባ ሞትን ይመርጣል፡፡ እረኛ የበጎቹን ነፍስ ተነጣቂ ቀበሮ ይጠብቅ ዘንድ አደራው ክእግዜአብሔር የተሰጠውን ያህል ይሰማዋል፡፡ እረኛ በጎቹን ከነጣቂ ቀበሮ ሊጠብቅ እንዲችል ብልሃቱና ጥንካሬውን ይሰጠው ዘንድ የምድርና የሰማይን ጌታ ዋሽንቱን እያንቆረቆረ ይለምናል፡፡

የጦቢያ እረኛ የብሉይ ኪዳኑን እረኛ የዳዊትን ግብር ወርሷል፡፡ ኦሪቱ ሕዝቄል ፴፬፡፳፫ ላይ “… በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ፣ እርሱም ያሰማራቸዋል እርሱም ባሪያዬ ዳዊት ነው፣ እረኛም ይሆናቸዋል፡፡” ይላል፡፡ የጦቢያ እረኛ የእግዜር ባርያ ነው፡፡ የጦቢያ እረኛ በጎቹን በተኩላ ላለማስበላት ቃል ኪዳንን በልቡ ያተመና ማተብን በአንገቱ ያሰረ ነው፡፡ እንደ ጦቢያ የበግ እረኛ ሁሉ የኢትዮጵያ መነኩሳት፣ ቀሳውስት፣ ጳጳሳትና ፓትሪያሪኮችም የመንፈስ በጎቻቸውን እንዲጠብቁ መለኮታዊ አደራና ግዴታ አለባቸው፡፡ የዮሐንስ ውንጌል ፲፡፭ ላይ “እርሱም በጎቹን በስማቸው ይጠራቸዋል፤ አውጥቶም ያሰማራቸዋል፡፡ ሁሉንም አውጥቶ ባሰማራቸው ጊዜ በፊት በፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ይከተሉታል፤ ቃሉን ያውቃሉና፡፡

በዚህም መሰረት ጥንታውያን የመንፈስ አባቶቻችን በክፉ ዘመን ግዜ ተበጎቻቸው ኋላ ሳይሆን ፊትለፊት እየሄዱ የእረኝነት ኃላፊነታቸውን በሚገባ ተወጥተዋል፡፡ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን የኦቶማን ኢምፓዬር የእጅ አዙር ወረራ ወቅት በጎቻቸውን ላለማስበላት ሲሉ ተበጎቻቸው ፊትለፊት ሄደው ታርድዋል፤ በእሳት ጋይተዋል፡፡ በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን በአድዋው ጦርነት ወቅት ታቦታቸውን ይዘው ተበጎቻቸው ፊት ለፊት ተሰልፈው ተኩላን ተፋልመዋል፡፡ በአምስቱ ዘመን ጊዜም እነ ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስና ሚካኤል ተበጎቻቸው ፊትለፊት ተሰልፈው በተኩላዎች ተበልተዋል፡፡ የደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኩሳት በጎቻቸውን በተኩላ አናስነካም ሲሉ በመደዳ ተረሽነዋል፡፡ ክቡር መላከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ በርሃ ገብተው ተዋጊ በጎቻቸውን እያደራጁ በጎቻቸውን ሊፈጅ የመጣን ተኩላ ተፋልመዋል፡፡ አቡነ ቴዎፍሎስም በሬቢስ በሽታ በተለከፉ አገር በቀል ተኩላዎች ተነድፈው አልፈዋል፡፡

የዛሬዎቹን ጳጳሳትና ፓትሪያሪኮች ግን እንደ ጥላሁን ገሰሰ ሆድ ይፍጀው ብለን እንዳናልፍ  እንኳ ትዝብቱን ተማተብ ማሰሪያ አንገታችን በላይ ጢቅ ስላደረጉት ቡልቅ ቡልቅ እያለ ይፈሳል፡ ፡ የዘመኑ ጳጳሳትና ፓትርያሪክ የመነኮሱትና ተመንበር  የተጎለቱት ለበግ እረኝነት እንዳልሆነ ሐዋርያው ያዕቆብ “በሥራ ያልተፈነ እምነት የሞተ ነው!” የሚለው ሥራቸው ይመሰክራል፡፡ የዚህ ዘመን ጳጳሳትና ፓትርያሪክ በትጋት በመጠበቅ ላይ ያሉት በግ ፈጅቶ የማይጠግበውን ተኩላ እንጅ በጎችን እንዳልሆነ እንኳንስ እግዜአብሔር ሕዝብም ከሰላሳ ዓመታት በላይ በአንክሮ ተመልክቷል፡፡ እነዚህ ጳጳሳትና ፓትሪያርክ የእረኛው ዳዊት ወንጭፍ የጎልያድን ተኩላዎች፣ የእነ አቡነ ጴጥሮስ፣ አቡነ ሚክኤል፣ የእነ መላከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬና ሌሎችም ቅዱሳን እረኞች ግዘታና ፀሎት በተለያዬ ጊዜ የወረሩን ተኩላዎች ሸኮና ሲሰነክል እንደኖረ ለማስታወስ ለግመዋል፡፡ በሮም ጠቦቱ ተኩላ አጤ ኔሮ አንገታቸውን ያስቀነጠሳቸውን ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ፣ በኢትዮጵያ ኮርማው ተኩላ ፋሽሽቱ ሞሶሎኒ በባሩድ ያስረሸናቸውን ቅዱሳን መነኩሳትና ጳጳሳት ስማቸውን ብቻ ዘርፈው ግብራቸውንና ሰማእትነታቸውን ረስተዋል፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም  በጎቻቸውን ለተኩላ አሳልፈው ላለመስጠት ተበጎቻቸው ፊትለፊት ተገኝተው ሰማእት የሆኑትን አቡነ ጴጥሮስና ሚካኤልን ተተኩላ ተሻርከው ህይወታቸውን ለማዳን ባለመጣራቸው “ቂሎች!” እያሉ ይሳለቁባቸዋል፡፡

የዘመኑ ፓትርያሪክና ጳጳሳት በሰላም ጊዜ ያማረ ካባቸውን ደርበው፣ የተዋበ ቆባቸውን ቦጅረውና መስቀላቸውን አንዠርገው ተበጎች ፊት ለፊት ይገኙና የበግ እረኛ ይመስላሉ፡፡ ክፉ የተኩላ ቀን ሲመጣ ተበጎች ጀርባ ይሰለፉና በጎችን ፊትለፊት አሰልፈው በተኩላዎች ያስፈጃሉ፡፡ በጎች ተኩላ ሲያሳድዳቸውና ተቤተክርትያን ደጀ ሰላም ሲገቡ ገፍትረው አስወጥተው ከተኩላ አፍ ይከታሉ፡፡ በጎች በተኩላ ማለቅ መሯቸው ተኩላን ሊዥልጡ ግር ብለው ሲወጡ ተኩላን ለማዳን የበግ መንጋውን አታለው ወደ ጉረኖ ያስገባሉ፡፡ በጎች ተመልሰው ወደ ጉረኖ ሲገቡ እነሱ በጓሮ በር ሄደው ከተኩላዎች ጋር ዱለት እየዛቁ ይዶልታሉ፡፡ ተሚያስፈራሯቸው ባለወንበር ተኩላዎች ትእዛዝ እየተቀበሉ ግልገል  ተኩላዎችን የበግ ቆዳ አልብሰው፣ ቆብና ካባ ደፍተው፣ እረኛ አስመስለው ወደ መንጋው በግ ይለቃሉ፡፡ የበግ ቆዳ ለብሰው የተቀላቀሉት ተኩላዎች መንጋውን በግ በድምጡና በልሳኑ ከፋፍለው እርስ በርስ ያፋጃሉ፡፡ ይህም ሆኖ ተስፋ ያልቆረጠው የበግ መንጋ ላቱን እየቆረጠ አስራት ሲያገባ ጳጳሳትና ፓትርያሪኮች ከተኩላዎች ጋር አንጨርጭረው እየጠበሱ ይውጣሉ፡፡

ከእንዲህ ዓይነት ኃጥያትና እርኩስ ታሪክ የጠዳው ባለዋሽንቱ የጦቢያ የበግ እረኛ ግን ዳዊቱን በብቱ አንግቶ፣ ዋሽንቱን እያንቆረቆረ የተለመደ የድስት ሺ ዘመን ቅዱስ የበግ እረኝነት ሥራውን በመፈጠም ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ባለዋሽንቱ የጦቢያ በግ እረኛ እንደ ቅዱስ ዳዊት ከእረኛዎች ሁሉ ይለያል! ይለያል! ይለያል!

ዋሽንት፡-የዳዊትና የጦቢያ እረኛ ዋሽንት እንደ ጣት አጥቅ ካለው የሸንበቆ ተክል የሚሰራ ነው፡፡ ዋሽንት እረኛ በአጥቁ ለክቶ፣ ቀዳዳዎችን በእሳት ወይም በስለት በስቶ የሚያመርተው የእምነት፣ የእውቀትና የሰሜት እስተንፋስ ማስተላለፊያ በረከት ያለው ፍኖተ-ልሳን ነው፡፡ ዋሽንት በአፍንጫና በአፍ የገባ አየር በደም ተዘዋውሮ ከራስ ጠጉር እስክ እግር ጥፍር ያለውን ሰውነታችንን አዳርሶ ደስታን፣ ሕመምን፣ ሐዘንን፣ ትካዜን፣ ትዝብትን፣ ጭንቀትን፣ እፎይታን ወዘተርፈ ተሽክሞ ሲመለስ የሚንቆረቆርበት የልባዊ ስሜት እስተንፋስ ማስወጫ ነው፡፡ ዋሽንት እረኛው ዳዊት እንባውን እንደ ጅረት እያፈሰሰ ኃጥያቱን ለመለኮት የተናዘዘበት፣ ምድር በሰላም በፍትህ እንድትሞላ፣ እንደ ጎልያዱ ያሉ አረመኔዎች እንዲንበረከኩ አምላኩን የተለማመነበት ቅዱስ መሳሪያ ነው፡፡

እረኛና ዋሽንት፡- እረኛና ዋሽንት ተገናኝተው የእረኛ ጣቶች የዋሽንትን ዓይኖች ክፍት ክድን ሲያደርጓቸው ወፎች በምንቃራቸው በዝማሬ፣ ወንዞች በፏፏቴቸው በውዳሴ፣ ጋራና ሸንተረሩ በገድል ማሚቶ ቅዳሴ ያጅባሉ፡፡ በጎች አርስ በርሳቸው ተቃቅፈው፣ የቀንድ ክበቶች ተመስክ ጋድም ብለው፣ የጋማ ከበቶች ጆሯቸውን ቀስረው በተመስጦ ያዳምጣሉ፡፡ ተክሎች ቅጠሎቻቸውን ዘረጋግተው፣ መስኮች እንደ ስጋጃ ለጥ በለው የዋሽንትን እስተንፋስ ይምጋሉ፡፡

እረኛና ዋሽንት ሲገናኙ የመለኮት በሮች ይከፈታሉ፤ የተፈጥሮ ሚስጥሮች ይገለጣሉ፡፡ ይኸንን ለማመን መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ መኖርን፣ የዋሽንትን ጣእመ ዜማ እያዳመጡ ማደግንና ከተቻለም ራሱን እረኛውን መሆንን ይጠይቃል፡፡ እረኛ በጥዋት ሲነሳ መጀመርያ በዋሽንቱ ጸሎት ያደርሳል፡፡ ሌሊቱን ያነጋው እግዚአብሔር ቀኑን እንዲባርከው በዋሽንቱ ይጠይቃል፡፡ ሰፈሩ፣ መንደሩ፣ አድባሩ፣ አገሩና ዓለም ሰላም እንዲውሉ ዋሽንቱን እያንቆረቆረ ይለማመናል፡፡ ለሰው ልጅ እንጀራ፣ ለሚጠብቃቸው በጎች የለመለመ መስክ፣ ለአእዋፍ ጥራጥሬ፣ ለእጸዋትም ካፊያውንና ዝናቡን እንዲያወርድላቸው ይለማመናል፡፡ የሰውን ልጅ ተጎልያድ ጭካኔ፣ በጎችን ተቀበሮና ተተኩላ፣ ከብቶችን ታፋ ተሚዘንችር ጅብ እንዲጠብቃቸው እንደ እረኛው ዳዊት ይማጠናል፡፡

እረኛ በጎቹን እንደ ውቂያኖስ ተተንጣለለው ሜዳ አስማርቶ “ቡርፍ ቡርፍ” እያደረጉ ሳሩን ሲግጡለትና ሆዳቸው ሞላ ሲል ደስ ይለዋል፤ አንጀቱ ይርሳል፡፡ የዮሐንስ ወንጌል ፲፡፭  “እርሱም በጎቹን በስማቸው ይጠራቸዋል፤ አውጥቶም ያሰማራቸዋል፡፡” ባለው መሰረት  እረኛ ዋሽንቱን እያንቆረቆረ “ቦቄ፣ ቀንዶ፣ ለምለም!” ብሎ በጎቹን በስማቸው እየጠራ ያወድሳቸዋል፡፡ ጠቦት የሚያደርሱለትን እናት በጎች፣ ወተት የሚያጠጡትን ላሞችና አርሰው የሚያበሉትን በሬዎች እጅግ አርጎ ያመሰግናል፡፡ እረኛ በቀን ውሎው በተመስጦ በስሜት ህዋሳቱ ተፈጥሮን እየቃኘ ስለ መስኩ፣  ሸንተረሩ፣ ጋራው፤ ተራራው፣ ስለ ባህሩ፣ ስለ ሐይቁ፣ ስለወንዙና ጅረቱ ከዋሽንቱ ጋር ያዜማል፡፡ የጦቢያ እረኛ ዋሽንቱን እያንቆረቆረ እንደ አየር ወለድ ተላይ ዘሎ ሲፈጠፈጥ ጥቅጥቅ ጉም የመስለ የእሳት ጪስ የሚተፋውን ዓባይን በዘፍጥረት ወንዝነቱና በአገር ሐብትነቱ “ዓባይ! ዓባይ! የአገር ሲሳይ” እያለ ያሞካሸዋል፡፡ ኮብልሎ ተአገር በውጣቱ ደሞ “ዓባይ ማደርያ የሌለው ግንድ ይዞ ይዞራል” እያለ ይወቅሰዋል፡፡

የጦቢያ እረኛ ሲመሽ ተሚተኛበት ቆጥ ተሳፍሮ የዋሽንት ዜማ እያንቆረቆረ ውሎውንና ሲታዘባት የዋላትን ዓለም ይዳስሳል፡፡ በቀን ውሎው የሰራው ስህተት ታለም እንደ ዳዊት ዘምሮ ንስሀ ይገባል፡፡ የማህበረሰቡንም ውሎ ፈትሾ የሰውን ከንቱነት፣ ኢፍትሐዊነት፣ ክህደት፣ ሌብነት፣ አጭበርባሪነት፣ ስግብግብነት፣ አድርባይነትን፣ አስመሳይነትና ሆዳምነት የሚገልጡ ሰምና ወርቅ ስንኞች ይደረድርና ዋሽንቱን አንቆርቁሪው ይላታል፡፡ እረኛ በዋሽንቱ ጀግናን “ከቶ ሰው አይፈራም ከክርስቶስ በቀር” እያለ ያሞካሻል፤ ጡርቂን “ፈሪ ለእናቱ ያገለግላል ምጣዱ ሲጣድ ሊጥ ያቀብላል” እያለ ይሳለቅበታል፡፡ እረኛ በዋሽንቱ አለልክ ያበጠ አንደሚፈርጥ፣ ጎልያድ በአበራሮ እንደሚወድቅ ይተነብያል፡፡

የጦቢያ እረኛ አገሩ አማን ገበያው ጥጋብ እንዲሆን በዋሽንቱ ይለማመናል፡፡ ለጠገበ ጥጋቡን እንዲያበርድለት፣ ለተራበና ለተጠማ ራሀቡን ጥማቱን እንዲቆርጥለት ይማጠናል፡፡ ለታመመ ምህረቱን እንዲያውርድለት፣ ለሞተ ኃጥያቱ እንዲፋቅለትም ይጸልያል፡፡

የጦቢያ እረኛ የቅዱስ ዳዊትን ዋሽንትና ዳዊት ተረክቦ እንደ ቅዱስ ዳዊት የመለኮትን ፈቃድ በመፈጠም ላይ ይገኛል፡፡ እኛ ግን በመዝሙረ ዳዊትና በዋሽንት ሳይሆን በዓለም ወጥመድ ተጠልፈናል፡፡ ከመዝሙረ ዳዊትና ከዋሽንት ስለራቅንም ዓይናችንን በጨው የታጠብን ቀጣፊዎች፣ ቀማኛዎች፣ ሌባዎች፣ አስመሳዮች፣ እድርባዮች፤ ከሀዲዎች፣ ሆዳሞችና ለሰው ልጅ ነፍስ ደንታ የሌለን አረመኔዎች ሆነናል፡፡ የበግ ለምድ ለብሰን ፓትርያሪክ፣ ጳጳስና መነኩሴ ነን የምንል ሳይቀር ውሏችን ከተኩላ ጋር ሆኗል፡፡ የምንሰማው የዳዊትንና የጦቢያ እረኛን ዋሽንት ሳይሆን የገዥ ተኩላዎችን ጩኸትና ድንፋታ ሆኗል፡፡ የምንፈጥመውም የመለኮትን ትእዛዝ ሳይሆን እልፍ አእላፍ በጎች የፍጁትን የጎልያድ ተኩላዎችን ቀጭኝ ትእዛዝ ሆኗል፡፡

መንፈሳችን በጤና ተኝቶ እንዲያድር፣ ሥጋችን እንደ አበደ አውሬ መቅበዝበዙን ትቶ ሰከን ብሎ እንዲውል፣ መንደር፣ አገርና ዓለም ሰላም እንዲሆኑ መጀመርያ እንደ ቅዱስ ዳዊትና የጦቢያ እረኛ ሰቅሰቅ ብለን አልቅሰን ንስሀ ልንገባ ይገባል፡፡ ለዚህች አጭር የምድር ቆይታ ስንል የተዘፈቅንባቸውን የጭካኔ፣ የቅጥፈት፣ የስግብግብነት፣ የክፋት፣ የሆዳምነት፣ የአድርባይነት፣ የአስመሳይነት፣ የስርቆትንና አረመኔነት ባህሪዎች በንስሀ እንዶድና አመድ አጥበን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ በተለይ ለእረኝነት የተቀባን አባቶች እንደ ዳዊትና የጦቢያ እረኛ በጎቻችንን በትጋት ልንጠብቅ ይገባል፡፡ በሰላም ጊዜ እረኛ መስለን ፊትለፊት ታይተን ነጣቂ ተኩላ ሲመጣ ተኋላ ተደብቀን በጎችን አስነጥቀን በጓዳ በር ከተኩላ ጋር የበጎቻችንን ምላስና ስንበር ጠብሰን መብላቱን ማቆም ይኖርብናል፡፡ ይኸንን ኃጥያትና ያልተባረከ ታሪክ ለመፋቅ ደሞ መዝሙረ ዳዊትን ከልብና ተአንጀት እንዳይፋቅ አርጎ ተማተምና የእረኛን ዋሽት አዘውትሮ በጥሞና ከመስማት ይጀምራል፡፡ ኃጥያታችን እንዲያስተሰርይ፣ በመንፈሳችን እርጋታ እንዲሰፍን፣ በመንደሩ፣ በአገሩና በዓለም ሰላም እንዲንሰራራ ንጉስ ዳዊት የተናዘዘበትንና ንስሀ የጠየቀበትን የእረኛውን ዋሽንት አዘውትረን እንስማ! አመሰግናለሁ፡፡

 

ሐምሌ ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

 

የእረኛው ዋሽንት በአሸናፊ ከበደ  Ashenafi Kebede: The Shepherd Flutist Ethiopian Symphony (youtube.com)

ፍቅር እስከ መቃብር በዋሽንት፡-ፍቅር እስከ መቃብር ትረካ መግቢያ / Fikir eske mekabir tireka megbya / washint (youtube.com)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop