ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ንጉሴ – የአማራ ፋኖን የተቀላቀሉ ሁለተኛው ጀነራል ሆነዋል

July 5, 2024
449790756 122113477346354019 689840974864997621 nሰበር ዜና!
በርካታ ኮሎኔሎች ወደ ፋኖ የገቡ ሲሆን በቅርቡ ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ፋኖን ተቀላቅለዋል።
ሌሎች በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር የሚገኙ የአማራ ጀነራሎች፣ የወታደራዊ ባለማዕረግ መሪዎች ትግሉን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል።
አያሌ የአማራ ተወላጅ የዩኒቨርስቲ ምሑራን፣ ሐኪሞች፣ መሃንዲሶች፣ ወጣቶች ከአማራ አርሶአደር ጎን ተሰልፈው የሕልውና ትግሉን እያደረጉ ይገኛሉ።
ምክንያቱም ትግሉ ማዕረግ ፣ እድሜ ፣ ሙያ፣ ፆታ፣ ኃይማኖት ፣ የቦታ ርቀት የማይወስነው አማራን የመታደግ የሕልውና ትግል ነው

Addisu Derebe

https://youtu.be/ISPM1cpTXQU?si=2kRzM_TY7hEaqW3U

2 Comments

  1. አማራ ከዚህ ስርአት ጥርግ ብለህ ወጥተህ ፋኖን ተቀላቀል ኢዜማ የሚባል አንካሳ ድርጅት ወደ ክልል ዝር ቢል አይቀጡ ቅጣት ቅጣው።

  2. ጥቂቶች ጮቤ በሚረግጡባት የሃበሻ ምድር የመከራ ዶፍ ያልነካው ድሮም ሆነ አሁን የለም። የሚያሳዝነው አሁን ፋኖን ተቀላቀሉ የሚባሉት ጄኔራሎች የጡረታ መብታቸውን አስከብረውና ተከብረው ቀሪ ዘመናቸውን በሰላም የሚኖሩበት የጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመሆናቸው ፊታቸው ይመሰክራል። ይህ አይነቱ ፍስሃ ግን በሃበሻ ምድር የለም። ሁሌ እንዘጥ እንዘጥ። ሁሌ በለው በላትና በላቸው ነው። ስነልቦናችን የተወቀረው በመጠራጠር፤ ያልሆነ ነገርን አግኖ በማውራት፤ የሌላውን በጎ ሥራ ጥላሸት በመቀባትና በሸፍጥ ነው። ይህን ነገር አሊ የሚሉ ሁሉ ገና ያልተገለጠላቸው ወይንም አይተው እንዳላዪ ሰምተው እንዳልሰሙ በመሆን በደንበር ገተር የሚራመዱ ብቻ ናቸው። እስከ አሁን ያለፍንበት መንገድ የሚያሳየው ግን ይህኑ የመጠላለፍ ስልትና የመከራ ዶፍ ነው።
    ያኔ ድሮ ገና ሰው ሰው ሲሸት በምስራቅም ሆነ በሌሎች ግንባሮች እናት ሃገራቸውን አገልግለው በጡረታና በሃኪም ትዕዛዝ ከሰራዊቱ የተሰናበቱትን ደርግ በጨነቀው ጊዜ እናት ሃገር ትፈልጋቹሃለች በማለት አጋፎ ወስዶ ለሻቢያና ለወያኔ እሳት ነው የማገዳቸው። በ 17 ዓመት የደም ጎርፍ ያተረፈ ቢኖር ሻቢያና ወያኔ የሃገር አለቆች መሆናቸው ብቻ ነው። እነርሱም ከባለፈው የከፋና የከረፋ በመሆን እንሆ ዛሬም ያንኑ ህዝብ በማመሳቀል ላይ ይገኛሉ። ነጻነት ወይም ባርነት ምረጡ ያለው ሻቢያ ዛሬ ላይ ቁጭ ብሎ የ 30 ዓመቱን ትግል ላሰላሰለው አስመርሮ ምናኔ ያስገባል። ለነገሩ ህዝቡ እየሸሸ ነው። ምን ያድርግ። ለዚህ ነው የብሄር ነጻነት የግል ጥቅም የማሳደጃ ብልሃት እንጂ ህዝብን ነጻ የማውጫ ዘዴ አይደለም ያልነው። የወያኔው ነገር ከሻቢያው ግኝት ቢከፋ እንጂ የተሻለ ነገር እንደሌለው ሥፍራው ያሉ በየጊዜው ይነግሩናል። ግን መናገር፤ መጻፍ፤ መሰብሰብ በማይፈቀድበት በሻቢያና በወያኔ ግዛት ሰው በጅምላ እንደተነዳ ኖርኩ ብሎ ያልፋል። መጥኔ! የብልጽግናው ጉዳይም ከሻቢያና ከወያኔ ተግባር የተሻለ አይደለም። አዋሽ አርባ የታሰሩትን ሂዱና እዪ!
    ይህ የፋኖና የኦነግ ሸኔ ሩጫም ሰው አስጨራሽ፤ ቤት አፍራሽ ውሎ አድሮም እንደ ልጆች ጫወታ ያደረ እንጀራ ቁርስርስ ጫወታ ፍርስርስ እንደሚሆን ያለፈ ታሪካችን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ከብልጽግናው መንግስት ጋር ነገር እየከረረ፤ የውጭ ሃይሎች እጅ እየተወሸቀበት፤ በዚህም በዚያም የተበታተነው ፋኖ ነኝ ባይ ሁሉ መንገድ እየዘጋ፤ ተማሪዎች እንዳይማሩ እያደረገ ፋኖ የአማራን ህዝብ ኦነግ/ሸኔ የኦሮሞን ህዝብ እንደ ገና ዳቦ እሳት መሃል ላይ አስገብተው እያከሰሉት ይገኛሉ። ብሄርተኞች በሽተኞች ናቸው። የሚያዪት የዛሬን ቅዥታቸው የቀንና የማታ ነው። ቅዥት ራዕይም ህልምም አይደለም። ባጭሩ የጄኔራሎቹም ሆነ የሌሎች ፋኖን መቀላቀል እልል የሚያሰኝ ነገር አይደለም። የጊዜውን መጨለም የሚያሳይ እንጂ። ሌላው የሃገሪቱ ክፍል እየለማ/ሰው እየተማረ አማራ በሚኖርባቸው ክፍላተ ሃገራት መከራ መዝነቡ አያስፎክርም። በየድህረ ገጽ የሚለጠፈውንና የሚባለውን ሳይሆን በብልጽግና እና በፋኖ ፊልሚያ ህዝቡ እየደረሰበት ያለውን ግፍ ሥፍራው ሂዶ ማየትና መረዳት አስፈላጊ ይሆናል። ሰቆቃን ሌላ ሰቆቃ እየተካው ይኸው ዛሬም ልክ እንደ በፊቱ የብልጽግና ደጋፊ ነህ ብሎ መግደል፤ ፋኖን አስጠግተሃል፤ አብልተሃል ብሎ ማንገላታትና በብቀላ መንፈስ መረሽን የተለመደ ሆኗል። መቆሚያው መቼ ነው? መቼ ነው በክብ ጠረጴዛ ላይ በሃሳብ ፍልሚያ ለላቀው ሃሳብ ተሸንፈን በሰላም የምንኖረው? ለእኔ አይታየኝም። ልብ እንበል በምድሪቱ የቤት እንስሳትና የድር አራዊቶች ሳይቀሩ ሰላም አጥተዋል። መቼ ነው ሰው በሰላም ሰርቶ ውሎ ወደ ቤቱ የሚገባው? ያ ጊዜ ይመጣ ይሆን? አላውቅም። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

191731
Previous Story

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በጥይት ተመቶ ተገደሉ | “ሊከዱን ቀን እየጠበቁ ነው” ጄ/ል አበባው |“ስራችን አስከሬን ማንሳት ብቻ ሆኗል” | በመጨረሻ ከፋኖዎች ጋር እንጨባበጣለን፣ ”ሁሉም እስረኞች ሊፈቱ ነው፣ ሁለት መኪና ተማሪ ታገተ፣ አስቸጋሪ የተባለው ሽፍታ ተገደለ

191749
Next Story

“ልጆቼ ተከተሉኝ” – ጄ/ሉ ለመላው አማራ ጥሪ አቀረቡ | አሜሪካ ስለ ፋኖ በዝግ መከረች | የጠቅላዩ ንግግር መዘዝ አመጣ….|

Go toTop