የሽግግር ፍኖተ ካርታ – በገለታው ዘለቀ

June 21, 2024

2 Comments

  1. ወንድም ገለታው፦
    ሰገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ አባባልህ በጣም ይስማማኛል። ስለሆነም፣ (1) የጎሣዎች ም/ቤት ውክልና እኩል መሆኑ ደግ። ግን እንዴት ነው ተመርጠው የሚመጡት ? እንደ ፌደሬሽን ም/ቤት አባላት ከሆነ ንትርክ ይመጣል። (2) በሕገ መንግሥት ዓላማ ላይ ስምምነት ማስፈለጉ ትክክል ነው። ግን የዛሬው ሕገ መንግሥት፣ ከምእራፍ 3 ውጭ፣ ሌላው እንኳን ባለሙያ የመንደር ሽማግሌም ያየው አይመስልም። የዛሬው ትርምስ መሠረቱ እሱ ነው። ታዲያ ረቂቅ ሕገ መንግሥት ብታቀርብልን የሁላችንም ተሳትፎ ያሻሽለዋል። መቼ ነው የምታቅርብልን ? (3) እኔ የአርሶ አደር ልጅ ነኝ። የተወለድሁትም ሸዋ አይደለም። ስለሆነም ከነገሥታቱ ጋር ዝምድና የለኝም። ግን አንተ ያመጣኸው ንጉሠ ነገሥት በሕገ መንግሥታችን ውስጥ ያለምንም ሥልጣን የማስገባቱ ጉዳይ እጅግ ጠቃሚ ነው። የንገሥታቱ ዝርያ ከሀዲያ፣ ከጉራጌ፣ ከትግሬ፣ ከኦሮሞና ከአማራም፣ ምናልባትም ከሌሎችም ብሔሮችም ይመዘዛል። ስለሆነም፣ ሰፊ ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው ስለሆነና ቅርስ በመሆኑ ከስደት ቢመለስ ለአገራችንም ጠቃሚ ነው። የሚነግሠው ግን ሙሉ ጤና፣ ብስለትና ማስተዋል፣ ኢትዮጵያዊ ባሕሪም እንዲኖረው ግዴታ መኖር አለበት ። በተጨማሪ፣ ፕሬዚደንት ከመምረጥ ንጉሠ ነገሥቱ፣ እንደ ጃፓንና እንግሊዝ፣ የክብር የሀገር መሪ ሊሆኑ ይችላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠንካራ ባለሙያ ከሆነ፣ ለዚያውም በዲሞክራሲያዊ መድበለ ፓርቲ ሥርዓት የአሸናፊ ፓርቲ መሪ ስለሚሆን፣ የፖለቲካ ዓለቃም አያስፈልገውም።

    ዛሬ በሕገ መንግሥታችን በአስከፊ ሁኔታ የጎደለው ሹማምንቱ ቀይ መስመር ሲያልፉ የማሰናበት ሥልጣን፣ እንዴትና በማን እንደሚወሰን የተደነገገበት አንቀጽ የለም። ሌሎችም ብዙ ጉድለቶች በየምዕራፉ አሉ። እንግሊዝና አሜሪካ ድንጋጌ ስላላቸው፣ ሪቻርድ ኒክሰንን በአሜሪካ፣ ቦሪስ ጆንሰንንና ሊዝ ትራስን በእንግሊዝ ከሥልጣን ሲባረሩ አይተናል.። የእኛ ሕገ መንግሥት ድንጋጌ ስለሌለ “ንጉሥ አይከሰስ፣ ሰማይ አይታረስ።” ተክቶታል። የሕገ መንግሥቱ ዓላማም ኢትዮጵያን ለማሳደግ ሳይሆን በቡድን ለመግዛትና ለመጠቀም እንጂ አገር ለማስተዳደር አይደለም። ስለዚህ፣ መቼ ነው ረቂቅ ሕገ መንግሥት የምታቀርብልን ? የ1986 ዓ.ም. የነማንዴላ ሕገ መንግሥት ግሩም ነው። እስካሁን ሥራየ ብሎ ያረቀቀ ሰው ወይም ቡድን አልመጣም።

    ካለው ትርምስ በሽግግር መንግሥት እንውጣ ቢባል፣ ሙሉ ሽግግሩ እንዴት ይሁን ? እምቢልታ መንደርደሪያ አዘጋጅቷል። ተገናኝታችሁ እሱንም ጉዳይ ብታዩት ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Efrem Madebo 1
Previous Story

ኢትዮጵያን እናድን !

821
Next Story

ፋኖ በለው – ደጉ በላይ ብርጌድ አዲስ ሙዚቃ – ሽለላ እና ቀረርቶ

Go toTop