ኣንድ የፋኖ ድርጅት ወይንስ ኣንድ የፋኖ መሪ? ኣንድ መሆን ለምን ኣቃታን ዘመነ ካሴ?

June 21, 2024
Fano
ኣንድ የፋኖ ድርጅት ወይንስ ኣንድ የፋኖ መሪ?
ኣንድ መሆን ለምን ኣቃታን ዘመነ ካሴ?

ፋኖ ታምራዊ እድገት ኣሳይቷል:: ግዙፍ  ድርጅት በኣራቱም የኣማራ ክፍለ ሀገራት ፈጥሯል::  ነገር ግን ኣራቱ ኣንድ ለመሆን ጊዜ ወሰደ:: የህዝቡንም መሰዋትነት ጨመረ::  ኣማራ ጠሉ መንግስት ግልፅ የሆነ የዘር ፍጅት እየፈፀመ ነው:: ፋኖን መመክት ሲያቅተው ፋኖ ሲያጠቃው መደዳውን የኣማራን ህዝብ መጨፍጨፍ ቋሚ ኣካሄድ ኣድርጎታል:: ይህ ኣካሄድ በኣስቸኯይ መቆም ኣለበት::

ፍኖ ኣንድ መሪ መምረጥ የበለጠ ያስቸገረው ይመስላል::  ኣንድ መሪ ቢመርጥም ለምን ጎጃም ለምን ወሎ ለምን ሽዋ ለምን ከጎንደር በሚል ኣኩራፊ ሊበዛ ይችላል:: ኣኩራፊዎች ደግሞ ትግሉን ሊጎትቱት ይችላሉ::
ስለዚህ ፋኖ ኣንድ መሪ ሳይሆን ኣንድ ድርጅት ነው የሚያስፈልገው:: የቡድን ኣመራር ማለት ነው::  ኣራቱ ክፍላተ ሀገራት በጋራ ለመስራት  ምንም ችግር የለም:: ስለዚህ ቀጥሎ መምጣት ያለበት በመጀመሪያ የስራ ዘርፎችን መለየት ማለትም የጦር መሪ ምክትል መሪ ህዝብ ግንኙነት ምክትል ፀሐፊ የውጭ ጉዳይ ስትራቴጂስት የፖለቲካ ሃላፊ  ሎጂስቲክ ወዘተ በማለት የስራ ዘርፎችን ማውጣት::ለምሳሌ ኣስራ ስድት የስራ ዘርፎች ካሉ ከኣራቱ ክላፋተ ሀገራት ኣራት ኣራት ፋኖዎች በመምረጥ ኣስራ ስድት የስራ ዘርፎች ላይ መመደብ:: መሪ የሚባል ሳይኖር በቡድን መምራት::
ለምሳሌ ኣብይ የሚባል ጠቅላይ ሚንስቴር ባይኖር ኢትዮጵያ ይህንን ያህል እልቂት ኣይደርስባትም ነበር::  ሰራዊቱን መካላከያ ሚንስቴር ቢመራው ግብርናውን ግብርና ሚንስቴር ጤናውን ጤና ሚንስተር  ወዘተ ሆኖ በቡድን ቢመሩ ኣምባ ገነን ኣብይ ኣይኖርም ነበር:: ስለዚህ ኣንድ መሪ የሚለውን ኣጥፎቶ ፋኖ ኣንድ ድርጅት የሚለው ላይ ቢያተኩር ጥሩ ነው  ምን ትላላችሁ?

1 Comment

  1. አንተ ነህ አንዱ እዩኝ እዩኝ ባይ ትሁት ሁን እኔ ብለህ መግለጫ አትስጥ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

191411
Previous Story

“ፕሬዘዳንት እንደምሆን አብይ ቃል ገብቶልኛል” ዛዲግ | ጀ/ል አበባውን አፉን ያዘጉት ጥያቄዎች ህዝቡ በቃኝ ብሏል | ዐቢይ አደገኛ ዛቻ “ገና የጭካኔያችንን ጥግ ትመለከታላችሁ”||ጎንደር ልጇን ከፍ አድርጋ አክብራዋለች

Efrem Madebo 1
Next Story

ኢትዮጵያን እናድን !

Go toTop