የወልቃይት ባለቤትን ይፋ የሚያደርገው ሰነድ | ትግራዋይ| የህልውና ዘመቻ| 15 ዓመት የጠበቃቸውን ክፍለ ጦርለምን ወጉት

June 7, 2024

 

1 Comment

  1. እኔን የሚገርመኝ ዘመነ የተባለው የኢንተርኔት አገልግሎት የቆሻሻ ክምር አስተናጋጅ መሆኑ ነው። ምንም ያለሆነን ነገር ሆነ ብሎ ማውራትና ማስወራት የማደናገሪያ ስልት የሆነበት ይህ በአስረሽ ሚችው የተወናበደው ዓለማችን እውኑን ከሌላው ለመለየት ከተሳነው ሰንብቷል። ግራም ነፈሰ ቀኝ ወደ ሃበሻው የፓለቲካ እሰጣ ገባ ስንመለስ ደግሞ ውሃን ቢወቅጡት እንቦጭ አይነት ነው። እንዲህ ያለ የውስልትና ዘመን ይመጣል ብሎ የገመተ ነብይም ሆነ ባህታዊ በምድራችን የለም።
    የብልጽግናና የፋኖ ፍልሚያ የሚጎዳው የአማራን ህዝብ ብሎም ሃገሪቱን ነው። የሚያስተርፈው ደግሞ እንደሚነገረን ነጻነትን ሳይሆን ባርነትና መከራን ነው። ገና የፋኖና የብልጽግና ጦርነቱ ሳይፈነዳ በፊት አንድ ከረጅም ጊዜ በህዋላ ወደ ሃገር ቤት የተመለሰ ሰው ሃገሩን እንዴት አገኘኸው ስለው ” ምድሪቱ ሥር ዓት አልባ ሆናለች” ነበር ያለው። አሁን መንገድ የሚዘጋው፤ ትምህርት ቤት እንዳትማሩ የሚለው፤ የህክምና ተቋማትንና ሌሎች የመንግስት የህዝብ መገልገያዎችን የሚዘርፈው ይኸው ነጻ እናወጣሃለን የሚለው የፋኖ ስብስብ ነው። ይህ በምድር ላይ ያለ እውነት እንጂ ከሚያልፍ ወንዝ የተቀዳ ወሬ አይደለም። መኪና አስቆሞ መዝረፍ፤ ቀረጥ መቀበል፤ ሌላም ሌላ ጉዳይ ሁሉ የሚከናወነው በአማራው ክልል ህዝብን ነጻ እናወጣለን እያሉ በሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ነው። አዎን አውቃለህ በእኛ ስም የሚነግድ ናቸው እንዲህ የሚያደርጉት ይሉናል። እሱ የወሬ ማላበሻ እንጂ እውነትነት የለውም።
    ከተማ ያዝን፤ ይህን ያህል ማረክን ያን ያህል እምሽክ አረግን ሲሉን ልክ እንደ ወያኔ አንድም ሰው እንደሞተባቸው አያወሩም። ይህ በእነርሱ አጠራር በየክፍለሃገሩ በፋኖ ስም የሚንቀሳቀሰው ሃይል ሰውን መግደልና ማስገደል – ለምሳሌ በቅርብ ቀን የብልጽግና የመንግስት አመራር በመሆኗ ብቻ የልጆች እናትና ነፍሰ ጡር ሴት መግደል ጀግንነት አይደለም። ባጭሩ በዚህም በዚያም የሚገደለው የአማራው ህብረተሰብ ነው። ሰውን በመግደል ፍትህን ማስፈን አይቻልም። ያ ቢሆን ኑሮ ደርግና ወያኔ ምድሪቱን ምድረ ገነት ባደረጓት ነበር። ስንቶች እረገፉ እንበለ ፍርድ! በዚህ ፍልሚያ የሚያስፎክር ያዙኝ ልቀቁኝ የሚያሰኝ አንድም የጀግንነት ባህሪ የለም። አሁን እንሆ ይህን እየጻፍኩ በተደወለልኝ ስልክ መሰረት ወያኔ ተከዜን ተሻግሮ ወረራ እንደ ጀመረ ነው። ይህ ነው እንግዲህ በሶስት አቅጣጫ ህዝብ እያስጨረሱ መዳረሻችን 4 ኪሎ ነው እያሉ መደንፋት ዋጋ ቢስ የሚያደርገው። ፓለቲካ ውስብስብ ነው። አንድ ጋ የታስረና በእጅ የገባ ሲመስል ሌላው ጋ እንደ ተልባ ስፍር መንገድ ያበጃል። ያፈተልካል! ለዚህ ነው በተደጋጋሚ የፋኖ ጉዳይ አልተዋጠልኝም በህዋላ ህዝብን ያስጨርሳሉ እል የነበረው። አሁን ብልጽግናና ወያኔ ተሻርከው ፋኖን ለማጥፋትና ወያኔ የእኔ ነው የሚለውን ምድር ለመረከብ የጀመረው ዘመቻ እንደሆነ ማን ማወቅ ይችላል? ፓለቲካ በጊዜአዊ ጥቅም የተጣበቁ ሃሎችን ይፈጥራል። ሲጀመር አንድ የፓለቲካ ድርጅት የተጠቃለለ አመራር ከሌለው ዋጋ ይብሉን። ፋኖ በየስፍራው የሚያቅራራ እንጂ ወጥ የሆነ አመራር የለውም። አንድ ስለ ሰላም ሲያወራ ሌላው አፍራሽ ጉዳይ ይደነፋል። ሁሉም በያለበት የመሰለውን እንደ መሳፍንት ዘመን እየዘረፈና እያፈረሰ መንገድ እየዘጋና ሲልለት እየከፈተ የምንዋጋው ለህዝብና ለሃገር ነው ቢል ማን የሚሰማ አለ? የሃገሪቱ ችግር ሁሉን ነገር በጠበንጃ አፈሙዝ ብቻ ለመፍታት የተደረጉና የሚደረጉ መሆናቸው ነው። ጦርነት የኋላ ቀርነት ምልክት ነው። ዋ ይህን ህዝብ ከበፊቱ ለከፋ ሰቆቃ አጋልጣችሁ የት ልትገቡ ይሆን?
    የብልጽግናው መንግስት ለወያኔ ተጎንብሶ እንኳን ቢሰግድለት በጭራሽ ልባቸው የማይለወጥ ሽንኮች በመሆናቸው ለጦርነትና ለተንኮል ቀዳሚ የላቸውም። ግራ የገባው መንግስት አንዴ ትጥቅ ፍቱ ሌላ ጊዜ እንደ ፓርቲ እንዲመዘገቡ ፈቀድን ቢልም ወያኔ ባሩድ እያሸተተ መኖር ልምድ ነው። ብቀላ ብቀላን እየወለደው እንኳን ትጥቅ ሊፈታ በወሎ፤ በጎንደርና በአፋር አሁን በቅርብ ቀናት ዛሬን ሳይጨምር የፈጸማቸው ወንጀሎች ያልተገታ ጦረኝነቱን ያሳያል። ይህን ትራፊ ቡድን ከትግራይ መሬት ጠራርጎ በማስወጣት ለትግራይ ህዝብና ለምድሪቱ ሰላምን ለማስፈን ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባ ነበር። ግን አሜሪካ ተፈርታ፤ አረቦች ተደምረው በሚያሰሙት ጭኸትና ጫጫታ ይኸው ወያኔ ለ 4 ኛ ጊዜ ወረራ ጀምሯል። አምናለሁ ከእኛ ያፈነገጠ ነው ገለ መሌ እንደሚሉ እነ ጌታቸው። ይህ 100% ውሽት ነው ከወያኔ አመራር አፈንግጦ አንድም ሰው አንድ ቀን እንዲኖር አይፈቀድለትም። ይህ በጥናት በዘዴ የተጀመረ ጦርነት ነው። ማቆሚያውን ጀማሪዎቹና በየብሄሩ ጡሩንባ የሚነፋውና ብልጽግና መንገድ ይፈልጉ። እኔን የሰለቸኝ ታሰረ፤ ሞተ፤ ተፈናቀለ፤ ተሰደደ፤ ጦርነት ተከፈተ፤ ቤት ተቃጠለ፤ ተዘረፈ የሚሉ የሙት ወሬዎች ናቸው። ስለሆነም ነገርን በስማ በለው በውጭና በውስጥ ሆኖ እንደ ገደል ማሚቶ ከማስተጋባት ይልቅ የእውን ጋዜጠኛ በስፍራው በመገኘትና ተንኳሽና ተከላካይን ለይቶ ህዝብን በማናገር በህቡ ዕ እውነቱን ማወቅ ግድ ይላል። እውነቱ አሁን ላይ የአማራ ክልል የሚባለው ክፍል ላይ እሳት እየነደደ ይገኛል። ይህም ትምህርት ቤቶችን፤ ኮሌጆችን፤ የህክምና ተቋሞችን፤ የንግድ ልውውጦችን፤ አርሰው የሚበሉ ገበሬዎችን ሁሉ ያመሳቀለ ህዝቡን ወደ ድንጋይ ዘመን የሚለውጥ የፋኖና የብልጽግና ግብግብ አሁን ደግሞ የወያኔ ወረራ ታክሎበት መከራው መጠነ ሰፊ ሆኗል። መቼ ነው ህዝባችን ሰው በመሆኑ ብቻ ተከብሮ ብሄሩ ተረስቶ በፈለገው የሃገሪቱ ምድር እንደ ልቡ ሰርቶ በሰላም የሚኖረው? አይ ሃገር አይ በህዝብ ስም ንግድ፤ የኦሮሞ ነጻ አውጪ፤ የፋኖ ታጋይ፤ ሃርነት ትግራይ፤ ሃርነት ኤርትራ የገልቱዎች ልፋት። ትሻልን ትቼ ትብስን .. አይጣል ነው። ከዚህ በህዋላ የሚሆነውን ቆይተን እንይ…. ለዛሬው ግን ያው የሰቆቃ ወሬ ነው። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

GPdsLIPaYAAkf23
Previous Story

“አንድም አማራ እንዳይቀር” ሽመልስ – 1 ሚሊዮን ወጣቶች አፈሳ በይፋ ተጀመረ/ | የአማራ ፋኖ በጎንደር ከፍተኛ ድል ተቀዳጄ | ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ እንኳን ለቤትዎ አበቃዎት!

Loneliness
Next Story

ብቼኝነት ሞት ነው !Loneliness is Death! Eenzaamheid is dood!

Go toTop