ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም እንደገባ አስካሁን በደም ይዋኛል ፡፡
ያች ግም ሞት ሀያ ለኢትዮጵያም ሆነ ለኢትዮጵያዉያን በግም ሞትነት ከዚያ አስካሁን ስተዘከር ለኢህአዴግ ግን ዕንደ ዕድል ሆኖ ድል እና ልደት ዕየሆነ በአገር ሀብት እና ነብረት በደመቀ ሁኔታ ሲታሰብ ኖሯል፡፡
ዛሬ ዛሬ ግን በተለይም ከቀድሞዉ ኢህአዴግ ሊቀ መንበር ሞት በኋላ ጀምሮ ለወጪ እንጂ ለመጪ ተብሎ ሲከበር አልታየም እንዲያዉም ይከበር አዩከበር የሚል ጠፍቶ ሳይከበር እንደከበር ሆኖ የዕረፍት ቀን ሆኖ ይገኛል ፡፡
ርግጥ ግም ሞት ሀያ ለኢትዮጵያዉያንም ሆነ ለአገሪቷ በታሪካቸዉ ገጥሟቸዉ የማያዉቅ የታሪክ እና የትዉልድ ስብራት እና ጠበሳ ሆኖ ከጀመረበት አንስቶ በህዝቦች መካከል ጥላቻ እና ፍርኃት ፣ አገሪቷል ያለ ባህር በር በማስቀረት ከብሄራዊ አንድነት እና ከታላቅነት ማማ የወረዱበት ነበር ፡፡
በዓሉ የኢትዮጵያም ሆነ የህዝቧ ሳይሆን በዘመናት የህዝብ ተጋድሎ በጊዜ እና ታሪክ አጋጣሚ በህልሙም ያላሰበዉን የስልጣን ባለቤት ለሆነዉ ኢህአዴግ ዉልደት እና ትንሳዔ መሆኑ ለሶስት አሰርተ ዓመታት ህዝብ እና መንህስት አጋም እና ቁልቋል ሆነ ስለመቆየታቸዉ በኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በምጣኔ ሀብት እና በህዝቦች መስተጋብር ላይ ከፍተኛ ጥልመት እና ሞት ይዘዉ የተከሰቱት ከግም ሞት 20 ቀን 1983 በኋላ የመጡት የሽግግር መንግስት እና ሕገ- ኢህአዴግ ነበሩ ናቸዉ ፡፡
ዛሬም ድረስ በአገራችን ህዝቦች መካከል በይ እና ተመልካች ፣ ወዳጂ እና ጠላት በሚል ጎራ በፖለቲካ ፣ በታሪክ ፣ በምጣኔ ሀብት ፣ በባህል፣ በማንነት ልዩነቶች የተነሳ ቅራኔ የተዘራዉ ከዚያ ጀምሮ ነዉ ፡፡
ለዚህም ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ በማንነት ፣ በፖለቲካ አመለካከት እና ኢትዮጵያዊነት ምክነያት የሚደርሱ ኢሰባዊ ፣ ኢ-ሀጋዊ ፣ ኢ-ፍትሀዊ በደሎት ከስደት አስከ ዉርደት ፣ ከማጥላላት አስከ ሞት መቀጣላቸዉ መንስዔዉ ግም ሞት እና ፍሬዉ ስለሆነ ይህ ግም ሞት ለኢትዮጵያ እና ህዝቦች ያስገኘዉ ጥልመት እና ሞት መሆኑ እንደ ከዚህ ቀደም ግንቦት 20 ቀን የጥልመት እና ሞት ሆኖ ይተሰባል ፡፡
ምን አልባትም ለብዙዎች ዕልቂት እና በዓለም ታሪክ የባህር በር እና ታሪክ አልባ እንድትሆን በተካደች አገር መታሰቢ የሚሆን እንደሚሰራ እንገምታለን፡፡
በመጨረሻም ግም ሞት ሀያ እና ፍሬዎቹ ያስከተሉትን መከራ በምድራችን እንዳይደገም የኢትዮጵያ ህዝብ በፅናት እና በአንድነት ሊቆም እና ሊቋቋም ይገባል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ብሄራዊ እና ዓለማቀፋዊ ማህበረሰብ አቀፍ ፣ ግብረሠናይ ፣ ዕርቅ / ፍትህ፣ ሽግግር…ወዘተ የሚሉ እና የአገር እና የህዝብ ጉዳይ ያሳስበናል የሚሉ ዕዉነተኛ ሠላም ፣ ዕርቅ እና መግባባት እንዲኖር ለአመታት አሁን ለምንገኝበት አጣብቂኝ መንሰዔ የሚባሉትን እና የጉዳዩ ባለቤት መስጠት ላይ ቅድሚያ መስጠት እና ይህንም ለህዝብ እና ለዓለም ማሳየት መሆን አለበት ፡፡
የችግሩን መንስዔ ሳይነኩ ስለ ችግሩ ማዉራት ችግር ከማወሳሰብ ዉጭ ችግር አይፈታም ፡፡
ማላጂ
አንድነት ኃይል ነዉ !