የፋኖ አደረጃጀቶች አንጻራዊ ወሳኝነትና የእስክንድር ነጋ ወሳኝ ሚና

ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ የተነሳው  በእስክንድር ነጋ ላይ ግልጽ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ በመዛት ስለነበር፣ ያ ማራ ሕዝብ ደግሞ ጭራቅ አሕመድን  ጨርቅ በማድረግ ቅኔያዊ ፍትሕ  (poetic justice) ሊሰጠው የሚገባው  በእስክንድር ነጋ መሪነት ነው።   

________________________________________

ያማራ ፋኖ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የቤታማራና የሸዋ ፋኖ እየተባለ በክፍለሀገር ደረጃ በጥቂት ቡድኖች ተሰባስቧል።  የሚቀጥለው እርምጃ ደግሞ እነዚህን ክፍለሀገራዊ የፋኖ ስብስቦች በማዋሃድ አንድ አድርጎ ባንድ አመራር መምራት ነው።  እነዚህን ክፍለሀገራዊ የፋኖ ስብስቦች አንድ ማድረግ ግን በስልጣን ሽኩቻ፣ በራስ ወዳድነትና በሌሎች የተለያዩ ምክኒያቶች ጊዜ ሊወስድ ይችላል፣ እንደሚወስድም በግልጽ እየታየ ነው።  ያማራ ሕዝብ ደግሞ በኦነግና በወያኔ ጥምረት እንዲሁም በምዕራባውያን ሙሉ እገዛ በከፍተኛ መጠን እየተጨፈጨፈ ስለሆነ፣ እነዚህ ክፍለሀገራዊ ፋኖወች ጊዜ ወስደው በመዋሃድ አንድ እስከሚሆኑ ድረስ የመጠበቅ ዕድል የለውም።  ስለዚህም የፋኖ ክፍለሀገራዊ አደረጃጀቶች ጊዜ ወስደው በመዋሃድ አንድ እስከሚሆኑ ድርስ ያማራ ሕዝብ ተጨፍጨፎ እንዳያልቅ ፣ ከነዚህ ክፍለሀገራዊ የፋኖ አደረጃጀቶች ውስጥ ወሳኝ የሆኑትን መለየትና በነሱ ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል።

ከፋኖ ክፍለሀገራዊ አደረጃጀቶች ውስጥ የበለጠ ትኩረት ሊደረግባችው የሚገባቸው የበለጠ ወሳኝ የሆኑት የትኞቹ ናቸው የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ደግሞ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መዳረሻው ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያስፈልጋል።  ይህ ጥያቄ ደግሞ ያማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል መስቀለኛ መንገድ ላይ ያቆመ የወቅቱ ወሳኝ ጥያቄ ነው።

ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መነሻው አማራ መድረሻውም አማራ ነው ማለት፣ የትግሉ አላማ አማራ ክልል የሚባለውን ወያኔ ሠራሽ ክልል በመቆጣጠር በቂ ኃይል ገንብቶ በቀረው የጦቢያ ክፍል ላይ ከጭራቅ አሕመድ ጋር መደራደር ማለት ነው። ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መነሻው አማራ መድረሻው ጦቢያ ነው ማለት ደግሞ፣ ጭራቅ አሕመድን በመገርሰስ ኦነጋዊ መንግስቱን ካፈራረሱ በኋላ በፍርስራሹ ላይ ጦቢያን ጦቢያ ለማድረግ ያንበሳውን ሚና የተጫወተው፣ በጦቢያዊነቱ የማይደራደረው፣ በቁጥር ደግሞ ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝብ ድምር በሚሊዮኖች የሚበልጠው ትልቁ ያማራ ሕዝብ በቁጥሩ መጠን ሚና የሚጫወትባትን፣ በተገቢው ደረጃ አማራ አማራ የምትሸትን፣ ሕብረብሔራዊት ጦቢያን እንዳዲስ መገንባት ማለት ነው።

ያማራ ሕልውና ትግል መነሻው አማራ መድረሻውም አማራ ከሆነ፣ ትግሉ አማራ ክልል የሚባለውን ወያኔ ሠራሽ ክልል በመቆጣጠር የሚጠናቀቅ አጭር ተጓዥ ትግል ነው።  በዚህ አጭር ተጓዥ ትግል ላይ ወሳኙን ሚና የሚጫወቱት ፋኖወች የጎንደርና የጎጃም ፋኖወች ሲሆኑ፣ የቤታማራና የሸዋ ፋኖወች ዋና ሚና ለጎንደርና ለጎጃም ፋኖወች ደጀን መሆን ነው።  ስለዚህም መነሻውንም መድረሻውንም አማራ ያደረገ ያማራ ሕልውና ትግል የበለጥ ትኩረቱን ማድረግ ያለበት በጎንደርና በጎጃም ፋኖወች ላይ ነው።

በሌላ በኩል ያማራ ሕልውና ትግል መነሻው አማራ መድረሻው ጦቢያ  ከሆነ፣ የትግሉ የመጀመርያ ዓላማ የጭራቅ አሕመድን ጭራቃዊ መንግስት ማስወገድ ሲሆን፣ የትግሉ ሁለተኛ ዓላማ ደግሞ ወያኔና ኦነግ በጎጠኝነት ያፈራረሷትን ጦቢያን በጎጠኝነትአልባ ሕገመንግስት ላይ መገንባት ነው።  ስለዚህም መነሻው አማራ መድረሻው ጦቢያ የሆነ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ረዥም ተጓዥ ትግል ነው።  የዚህን ረዥም ተጓዥ ትግል የመጀመርያ ዓላማ በማሳካት ላይ (ማለትም ጭራቅ አሕመድን በማስወገድ ላይ) ወሳኙን ሚና የሚጫወቱት ፋኖወች የቤታማራና የሸዋ ፋኖወች ሲሆኑ፣ የጎንደርና የጎጃም ፋኖወች ዋና ሚና ለቤታማራና ለሸዋ ፋኖወች ደጀን መሆን ነው።  ስለዚህም መነሻውን አማራ መድረሻውን ጦቢያ ያደረገ ያማራ ሕልውና ትግል የበለጠ ትኩረቱን ማድረግ ያለበት በቤታማራና በሸዋ ፋኖወች ላይ ነው።

ባጭሩ ለመናገር ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መነሻው አማራ መድረሻውም አማራ ነው ማለት አማራ ክልልን በመቆጣጠር በቂ ኃይል ገንብቶ ከጭራቅ አሕመድ ጋር መደራደር ማለት ሲሆን፣ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መነሻው አማራ መድረሻው ጦቢያ ነው ማለት ደግሞ ካማራ ክልል በመነሳት አራት ኪሎን ተቆጣጥሮ የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት ማፈራረስ ማለት ነው።

ስለዚህም ለጭራቅ አሕመድ ስልጣን ይበልጥ የሚያሰጉት የቤታማራና የሸዋ ፋኖወች እንጅ የጎንደርና የጎጃም ፋኖወች አይደሉም ።  ለምሳሌ ያህል የጎንደርና የጎጃም ፋኖወች እስካሁን ከፈጸሟቸው ጅብዱወች ውስጥ ጥቆቶቹን እንኳን የቤታማራና የሸዋ ፋኖወች ፈጽመዋቸው ቢሆን ኖሮ፣ ጭራቅ አሕመድ ከወራት በፊት ጨርቅ ሁኖ፣ ሙቶ፣ ተቀብሮ ነበር።  ጭራቅ አሕመድ ከሞላ ጎደል ሙሉ ኃይሉን በቤታማራና በሸዋ ፋኖወች ላይ ያሰማራውም በዚሁ ምክኒያት ነው።

የጎንደርና የጎጃም ፋኖወች ከቤታማራና ከሸዋ ፋኖወች የበለጠ ጠንካራ መሆናችውን ራሱ ጭራቅ አሕመድ አጥብቆ ይፈልጋል።  የሚፈልገው ደግሞ በሁለት ምክኒያቶች ነው።  የመጀመርያው ምክኒያት ለስልጣኑ እጅግም የማያሰጉት የጎንደርና የጎጃም ፋኖወች ለስልጣኑ አደገኛ ከሆኑት ከቤታማራና ከሸዋ ፋኖወች የበለጠ ተጠናክረው፣ አመራሮቻቸው የበለጥ ጎልተው እንዲታዩና ያማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል መምራት ያለብን እኛ ነን ብለው እንዲያስቡና አልፎ ተርፎም በቤታማራና በሸዋ ፋኖወች ላይ እንዲታበዩ ስለሚፈልግ ነው።  ሁለተኛው ምክኒያቱ ደግሞ የጎንደርና የጎጃም ፋኖወች እስከተወሰነ ደረጃ ተጠናክረው ከተማወችን እየተቆጣጠሩና እየለቀቁ ውሃ ቀዳ ውሃ መልስ መጫወታቸው ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ መልካም አጋጣሚ ስለሚፈጥርለት ነው።

መነሻው አማራ መድረሻውም አማራ የሆነ ትግል፣ የመጨረሻ ግቡ ከጭራቅ አሕመድ ጋር መደራደር ነው ።  ጭራቅ አሕመድ ግን የሚደራደረው ለመደራደር ብሎ ሳይሆን በድርድር ሰበብ ጊዜ ለመግዛት ሲል ብቻ የሆነ፣ አታላይነት በሳልነት የሚመስለው ማይም፣ ንግግሩና ምግባሩ እንጦጦና የረር የሆኑ ቀጣፊ ነው፣  ጭራቅ አሕመድ አሊ የኦነጉ ኦቦ፣  አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ እንዲሉ።  ባጭሩ ለመናገር፣ ጭራቅ አሕመድ ማለት ሲያቃጡበት የሚጥመለመል ሲዞሩለት የሚናደፍ ዐሲል ዕባብ ማለት ነው።  ስለዚህም ከጭራቅ አሕመድ ጋር መደራደር ማለት አመችውን ጊዜ ጠብቆ የሚነድፍን ዐሲል እባብ በኪስ መያዝ ማለት ነው።  ለዚህ ደግሞ ከጭራቅ አሕመድ ጋር እንደራደራለን ብለው በጭራቅ አሕመድ ከተነደፉት ከተዋሕዶ አባቶች የበለጠ ማስረጃ የለም።

የተዋሕዶ አባቶች በተዋሕዶ ሕልውናዋ ላይ የመጣውን ሳጥናኤሉን ጭራቅ አሕመድን ለመቆራርጥ፣ መዕምኖቻቸውን በነቂስ አነሳስተው፣ ሰይፋቸውን ካፎቱ አውጥተው በጭራቁ ላይ አቃጡበት፡፡  ጭራቅ አሕመድ ደግሞ በተዋሕዶ ሰይፍ ሊቆራርጥ መሆኑን አውቆ፣ በፍርሃት እየራደ ተዋሕዶ አባቶች እግር ሥር ወድቆ ጫማቸውን በምላሱ እየላስ በእንባው ያርስ ጀመር።  የተዋሕዶ አባቶች ደግሞ ያገር መሪ ቀርቶ ተራ ግለሰብ ያደርገዋል ተብሎ በማይታሰበው በጭራቁ ያልተለመደ ድርጊት ከመገረም አልፈው በመደመም ከወደቀበት ሊያነሱት ጎንበስ ብለው እጃቸውን ዘረጉለት።  ጭራቁ ግን የተወሕዶ አባቶች እሱን ለማንሳት የዘረጉለትን እጅ ስቦ መሬት ላይ በግንባራቸው ፈጠፈጣቸው።  እነሱ ከግራቸው ሊያነሱት ሲሞከሩ እሱ እግሩ ሥር ጣላቸው።  እግሩ ሥር ከጣላቸው በኋላ ደግሞ እግራቸው ሥር እንዲወድቅ በማድረጋቸው የያዘባቸውን ከፍተኛ ቂም በከፍተኛ ደረጃ ተወጣባቸው፣ አለቅጥ አዋረዳችው።  አንዳንዶቹን ደግሞ አገራቸው እንዳይገቡ ካገራቸው አየር ወደብ (air port) ላይ ከሕዝባቸው መኻል እያከላፈተ አንገታቸውን አስደፈቶ መለሳቸው።

አቶ ዳንኤል ክብረት እየሱስን ባይኔ በብረቱ አየሁት ያለው፣ ጭራቅ አሕምድ የተዋሕዶ አባቶችን እግር በምላሱ እየላስ በእንባው ሲያብስ አይቶ ነው።  አቶ ዳንኤል ያላወቀው ይልቁንም ደግሞ አውቆ እንዳላወቀ የሆነው ግን የጭራቅ አሕመድ ዓላማና የእየሱስ ዓላማ ሐራምባና ቆቦ (ፍፁም ተቃራኒ) መሆናቸውን ነው፣ ዱባና ቅል እየቅል እንዲሉ።  እየሱስ የሐዋርያወቹ እግር ያጠበው ትሕትናን ሊያስተምራቸው ሲሆን፣ ጭራቅ አሕመድ ተዋሕዶ አባቶች እግር ሥር የወደቀው ግን ሊያነሱት እጃቸውን ሲዘረጉለት፣ የዘረጉለትን እጆች ስቦ በግንባራቸው ለመፈጥፈጥ ነው።

ስለዚህም መነሻየን አማራ መድረሻየንም አማራ አድርጌ፣ አማራ ክልልን በመቆጣጠር ተጠናክሬ ከጭራቅ አሕመድ ጋር እደራደራለሁ ማለት ራስን በጭራቅ አሕመድ ለማስበላት ማዘጋጀት ማለት ነው።  ወያኔ ትግራይ ላይ ተጠናክሬ ከጭራቅ አሕመድ ጋር እደራደራለሁ ሲል በጭራቅ አሕመድ እንደተበላው፣ መነሻውን አማራ መድረሻውን አማራ ያደረገ ትግልም የመጨረሻ እጣው በጭራቅ አሕመድ መበላት ነው።  ባጭሩ ለመናገር መነሻውን አማራ መድረሻውንም አማራ ያደረገ የፋኖ ትግል ራሱ ሙቶ አማራንም ይዞ የሚሞት ይዞ ሟች ትግል ነው።

ጭራቅ አሕመድ ስልጣን ላይ የሚቆይባት እያንዳንዷ ቀን ያማራን ሕዝብ ግብአተ መሬት የምታቃርብ የተረገመች ቀን ናት ።  ጭራቅ አሕመድ ያማሮችን ማሕፀን ዘርከቷል ወይም ደግሞ እንዲዘረከት አድርጓል፣ ሽሉን ደግሞ በልቷል ወይም ደግሞ አስበልቷል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ያማራ ሕፃናትን ጎጆ ውስጥ ዘግቶ በሰደድ እሳት አንጨርጭሯል ወይም ደግሞ እንዲንጨረጭሩ አድርጓል፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማሮችን የፊጥኝ አስሮ ባደባባይ ረሽኗል ወይም ደግሞ አስረሽኗል፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማሮችን ባደባባይ ዘቅዝቆ ሰቅሏል ወይም ደግሞ አሰቅሏል፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማሮችን አጋድሞ አርዷል ወይም ደግሞ አሳርዷል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ያማሮቸን ቆዳ በቁማችው ገፏል ወይም ደግሞ አስገፍፏል፡፡   ጭራቅ አሕመድ ያማሮቸን ሬሳ በሞተር ሳይክል ገትቷል ወይም ደግሞ አስገትቷል፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማሮችን በግሬደር ቀብሯል ወይም ደግሞ አስቀብሯል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ካማራ አስከሬን በተቆረጡ እጆችና እግሮች ሆያ ሆየ ጨፍሯል ወይም ደግሞ አስጨፍሯል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ላማራ ተቆርቋሪ አመራሮችን ያለ ርህራሄ ርፍርፏል ወይም ደግሞ አስረፍርፏል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ያማራ ከተሞችን አቃጥሎ አውድሟል ወይም ደግሞ አስወድሟል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ያማራ ባለሃብቶችን ሐብትና ንብረት ዘርፏል ወይም ደግሞ አስዘርፏል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ባንድም በሌላም መንገድ በሚሊዮኖች ቀንሷል ወይም ደግሞ አስቀንሷል፡፡

ስለዚህም፣ ያማራ ሕዝብ ሕልውና ይጠበቅ ዘንድ የመጀመርያው አጣዳፊ እርምጃ ጭራቅ አሕመድን አስፈላጊ በሆነ በማናቸውም መንገድ (by any means necessary) ማስወገድ ነው።  ጭራቅ አሕመድን በፍጥነት ማስወገድ የሚቻለው ደግሞ መነሻየ አማራ መድረሻየ ጦቢያ ብሎ በመታገል፣ በዚህ ትግል ላይ ወሳኝ ሚና በሚጫወቱት በቤታማራና  በሸዋ ፋኖወች ላይ የበለጥ ትኩረት በማድረግ ነው።  መነሻው አማራ መድረሻው ጦቢያ የሆነን ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ለመምራት ደግሞ ባሁኑ ጊዜ ካርበኛ እስክንድር ነጋ የተሻለ አማራጭ የለም

አርበኛ እስክንድር ነጋ አብዛኛው የጦቢያ ሕዝብ በሙሉ ልብ የሚያምነው፣ የእውነተኛነትየርተኧኛነት (ቀጥተኛነት)፣ የፍትኸኛነትየጽናትና ያይበገሬነት ተምሳሌት ነው።  የእስክንድርን ታማኝነት፣ ሰብዓዊነትና ጨዋነት እጅጉን የሚያጎላው ደግሞ ከኦሮሙማው መሪ ከጭራቅ አሕመድ ቀጣፊነት፣ አጭበርባሪነት፣ ቀላማጅነት፣ ባለጌነት፣ ነውረኛነት፣ ጋጠወጥነት፣ መሠሪነት፣ አውሬነትና አረመኔነት (ባጠቃላይ ደግሞ አጸያፊ ሰብእና) አንጻር ሲታይ ነው።  ስለዚህም በእስክንድር ነጋ የሚመራ፣ መነሻየ አማራ መድረሻየ ጦቢያ ብሎ የተነሳ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል አማራ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንን በዙርያው በማሰበሰብ የትግሉን ሜዳ አማራ ክልልን ብቻ ሳይሆን መላዋን ጦቢያን የሚያጠቃልል ሰፊ ሜዳ አድርጎ ፣ በመላዋ ጦቢያ ላይ በሰፊው የተሰራጩትን እልፍ አእላፍ አማሮች በስፋት አሳትፎ፣ የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት መግቢያ መውጫ በማሳጣት ውድቀቱን በከፍተኛ ፍጥነት እንደሚያቃርበው ሳይታለም የተፈታ ነው።

እነ ኦቦ ዮናስ ብሩን የመሰሉ የጭራቅ አሕመድ ቀንደኛ ደጋፊወች የቀሩትን ሁሉንም ፋኖወች እያሞገሱ በፋኖ በእስክንድር ነጋ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈቱትም፣ ሌሎቹን ፋኖወች ወደዋቸው ሳይሆን ዋና ስጋታቸው ፋኖ እስክንድር ነጋ መሆኑን በደንብ ስለሚያውቁ ነው።

ፋኖወች ዘመነ ካሴ፣ ምሬ ወዳጆ፣ መሳፍንት ሰይፉና መሰሎቻችው ጭራቅ አሕመድን ለማስወገድ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፣ እየተጫወቱም ነው።  መላውን የጦቢያን ሕዝብ ቀርቶ መላውን ያማራን ሕዝብ በዙርያቸው ለማሰባሰብ ግን አይችሉም ባይባልም እንኳን በጣም ያዳግታቸዋል፣ የእስክንድርን ያህል አይቀልላቸውም።  በተጨማሪ ደግሞ ፋኖወች ዘመነ ካሴ፣ ምሬ ወዳጆ፣ መሳፍንት ሰይፉና መሰሎቻቸው ጎበዝ ወታደሮች ቢሆኑም፣ የፖለቲካ ብስለታቸውና የእይታ አድማሳቸው ግን እንደ ፋኖ እስክንድር ነጋ የሰፋ አይደለም።  ጭራቅ አሕመድ ደግሞ የተዋጣለት አታላይ ከመሆኑም በላይ በማታለል በተካኑ ምዕራባውያን አማካሪወች የሚመከር ነው።  ስለዚህም ፋኖወች ዘመነ ካሴ፣ ምሬ ወዳጆ፣ መሳፍንት ተስፉና መሰሎቻቸው የጭራቅ አሕመድን የረቀቀ ሸርና ደባ የመገንዘብ ችሎታቸው እጅግም ነው።  ለዚህ ማስረጃ ደግሞ ፋኖ ዘመነ ካሴ ለእስር የበቃው፣ መቸም መታመን የሌለበትን ጭራቅ አሕመድን አምኖ ከጭራቅ አሕመድ ጋር ለመሸማገል ቀርቦ ጭራቅ አሕመድ ስለካደው መሆኑን መጥቀስ ብቻ በቂ ነው።  አንዴ ለመሸማገል የሞከረ ደግሞ ሁለቴም፣ ሶስቴም ለመድገምና ለመደጋገም፣ ለመሠለስና ለመሠላለስ አይመለስም፣ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይለቅምና።

ምዕራባውያን ያማራን ሕዝብ የሚጠሉት አማራ በመሆኑ እንጅ፣ ያማራ ሕዝብ ምንም ቢያደርግ ከጎኑ እንደማይቆሙ ያሜሪቃ ባንዲራ የተለጠፈበትን ጥብቆ (T-shirt) ለብሶ ያሜሪቃን ድጋፍ ለማግኘት ለሚሞክረው ለፋኖ ዘመነ ካሴና ለመሰሎቹ  አልታያቸውም። ጥቂት የትግሬ ሴቶች ተደፈሩ ከሚል በመረጃ ካልተረጋገጥ አሉባልታ (unconformed report) ተነስተው ኡኡታውን ሲያቀልጡት የነበሩት ምዕራባውያን፣ ባማራ ሕዝብ ላይ በቪዲዮ የተደገፈ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ሲፈጸም ሰምተው እንዳልሰሙ፣ አይተው እንዳላዩ የሆኑት ያማራን ሕዝብ መጨፍጨፍ በቀጥታና በተዛዋሪ የሚደግፉ በመሆናቸው መሆኑን ለፋኖ ዘመነ ካሴና ለመሰሎቹ አሁንም ድረስ አልተገለጠላቸውም።  ለዚህ ደግሞ ያሜሪቃ መንግስት አመራሮች በተለይም ደግሞ የጦቢያ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከታቸው ሚካኤል መዶሻ (Mike Hammer) እና አለቃው አንቶኒ ብሊንከን (Antony Blinken) በየጊዜው ከሚያወጧቸው ፀራማራ መግለጫወች ውስጥ እንዱን ብቻ መጠቀስ በቂ ነው።

 

We … urge the Government of Ethiopia to withdraw Amhara regional forces from the Tigray region and ensure that effective control of western Tigray is returned to the Transitional Government of Tigray.”  (Press Statement, Anthony J. Blinken, May 15, 2021)

“ያማራ ክልል ኃይሎቹን ከምዕራብ ትግራይ እንዲያስወጣና፣ ምዕራብ ትግራይን ለትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት እንዲመልስ የኢትዮጵያን መንግሥት አጥብቀን እንጠይቃለን” (ዕለታዊ መግለጫ፣ አንቶኒ ብሊንክን፣ ግንቦት 7፣ 2013 ዓ.ም) 

 

ፋኖወች ዘመነ ካሴ፣ ምሬ ወዳጆ፣ መሳፍንት ተስፉና መሰሎቻቸው የምዕራባውያን (በተለይም ደግሞ የንግሊዝና ያሜሪቃ) ዋና ዓላማ ቢቻል ያማራን ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት፣ ባይቻል ደግሞ ቁጥሩን በጭፍጨፋ፣ በርሐብና በበሽታ በማመናመን፣ ብዛቱ ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝብ ብዛት እጅጉን ያነሰ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚጫወተው ሚና ኢምንት የሆነ  አናሳ ብሔረሰብ (minority)  ማድረግ መሆኑ አይታያቸውም።  ስለማይታያቸው ደግሞ የሕዝብን ትግል በመቀልበስ አቻ የሌላቸው መሠሪወቹ አሜሪቃኖች እነዚህን ፋኖወች በተለያዩ መንገዶች በማሳመን ጉያቸው ውስጥ አስገብተው፣ ካማራ ሕዝብ ጥቅም ይልቅ ያሜሪቃን ጥቅም የሚያስቀድሙ፣ ያሜርቃ ጉዳይ አስፈጻሚ  እንዲሆኑ የማድረጋቸው  ዕድል ከፍተኛ ነው።  እነዚህን ፋኖወች ላሜሪቃ ጉዳይ አስፈጻሚነት እያዘጋጁ ያሉት ደግሞ የነዚህ ፋኖወች የውጭ አገር አፈቀላጤወች ነን የሚሉ፣ ከነ አንቶኒ ብሊንከን (Antony Blinken) እና ሚካኤል መዶሻ (Mike Hammer) ጋር በየጊዜው እየተገናኙ የሚዶልቱ፣  ባማራ ሕዝብ ደም የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት ያሰፈሰፉ የስልጣን ጥመኞች ናቸው።

ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ምዕራባውያን ሙሉ ድጋፍ በሚያደርጉለት በጭራቅ አሕመድ ቁርጥምጥም ተደረጎ ከመበላት የሚድነው፣  እንደ ወርቅ  በእሳት ተፈትኖ በወጣው፣  ከእምነቱና ካቋሙ   ዝንፍ እንደማይል  በተግባር ባሳየው፣ በስልጣን፣ በጥቅም  ወይም በሌላ በማናቸውም  መደለያ ሊደለል በማይችለው፣  የምዕራባውያን  ጉዳይ  አስፈጻሚ ይሆናል ተብሎ በማይጠረጠረው በቁርጥ ቀን ልጁ ባርበኛው እስክንድር ነጋ መሪነት መነሻየ አማራ መድረሻየ ጦቢያ ብሎ ሲታግል ብቻ ነው።

 ሙሉ ጥንካሬው አውሬነቱ ብቻ የሆነው፣ ጨለማን ተላብሶ ተከላካይ አልባ ሰላማዊ ሰወችን ከማረድና ከማወራርድ በስተቀር በታሪኩ አንድም ጊዜ እንኳን ፊት ለፊት ተዋግቶም ሆነ ድል አድርጎ የማያውቀው፣ የጦቢያን የመንግስት መዋቅር ሙሉ በሙሉ ባይቆጣጠርና የምዕራባውያን ሙሉ ድጋፍ ባይኖረው ኖሮ የሸዋ ፋኖ ብቻ ደምጥማጡን ሊያጠፋው የሚችለው ሙትቻው ኦነግ፣ ኢትዮጵያን በኦሮሙማ መልክ እሰራታለሁ እያለ ሲፎክርና ሲደነፋ፣ ኢትዮጵያን በደምና ባጥንቱ የገነባትንና ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች ጠብቆ ያቆያትን፣ በጀግንነቱ ወደር የሌለውን፣ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረውን፣ ጎጠኝነትን የሚጸየፈውን፣ የሕዝብ ቁጥሩ የኦሮሞ ስም ስለተለጠፈበት ብቻ ኦሮሞ ነው የሚባለውን የሞጋሴና የጉዲፈቼ ድምር በብዙ ሚሊዮኖች የሚበልጠውን፣ ትልቁን የአማራን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉት ደግሞ፣ ኢትዮጵያ በሚገባት ደረጃ አማራ፣ አማራ የምትሸት አማራዊ ትሆናለች ከማለት ይልቅ ያማራን ሕዝብ ከኦሮሙማ በማሳነስ መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ ሲሉ ከማየት የበለጠ አሳፋሪ ነገር የለም።  

በመጨረሻም ምክር ቢጤ ለክቡር ውድ ወንድሜ ላርበኛ እስክንድር ነጋ።  መነሻችንም መድረሻችንም አማራ የሚለው የፋኖ ክፍል የውጭ አገር አፈቀላጤ የሆነው፣ አንተን እስክንድርን ዝቅ አድርጎ ዘመነ ካሴን ከፍ ለማድረግ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አርበኛ ዘመነ ካሴ እያለ የሚጽፈው፣ የትናንቱ የመለስ ዜናዊ ቅጥረኛ የዛሬው የሚካኤል መዶሻ (Mike Hammer) ሤረኛ አቶ ግርማ ሳ ባንተ በእስክንድር ነጋ ላይ ጦርነት እንደሚያስከፍትብህ በግልጽ ዝቶብሃል።  የዛተብህ ደግሞ መነሻችን አማራ መድረሻችን ጦቢያ የሚለውን ትልቅ መፈክር ትተህ መነሻችንም መድረሻችንም አማራ በሚለው ትንሽ መፈክር በመካተት በዘመነ ካሴ ሥር ካልሆንክ ወዮልህ በማለት ነው።  ወዮልህ ያለህ ደግሞ ፀር ሕዝብና ፀረ ፋኖ ተደርገህ እንደምትቆጠር ማወቅ አለብህ ብሎ በመጻፍ ነው።  ወያኔወችን አቦይ፣ ኦነጎችን ኦቦ እያለ በመሽቆጥቆጥ የሚጠራው አድርባዩ አቶ ግርማ ካሳ አንተን እስክንድር ነጋን ፀር ሕዝብና ፀረ ፋኖ ለማለት መድፈሩ ብቻ፣ አንተን ለመቀበር የማይፈነቅለው ዲንጋ፣ የማቆፍረው ጉድጓድ እንደሌለ በግልጽ ይነግርሃል።

ስለዚህም የትናንቱ የወያኔ አቃጣፊ የዛሬው የፋኖ አቃፊ አቶ ግርማ ካሳ መነሻችንም መድረሻችንም አማራ የሚሉትን ፋኖወች ባንተ በእስክንድር ነጋ ላይ አነሳስቶ በዛቻው መሠረት ከጀርባህ እንዲወጉህ ሊያደርግ እንደሚችል መጠርጠር አለብህ።  ያ ባይሳካለት ደግሞ መነሻውም መድረሻውም ገንዘብ በሆነው በመረጃ ቲቪ አማካኝነት  ለጭራቅ አሕመድ መረጃ ሽጦ ሊያስገድልህ እንደሚችል መጠርጠር አለበህ።  በጥርጣሬህ መሠረት ደግሞ መውሰድ ያለብህን ጥንቃቄወች ሁሉ መውሰድ አለብህ፣ ያልጠረጠረ ተመነጠረ፣ የጠረጠረ ቤቱን አጠረ ነውና።

የስልጣን አራራ (ጥም) ሌላው ቀርቶ ከራስ አብራክ የወጣን የራስ ልጅን እንደሚያስገድል ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪከ በደንብ ስለምታውቅ፣ እነ አቶ ግርማ ካሳና መሰሎቻችውአንተን እስክንደር ነጋን በሰላሳ ጠገራ ሽጠው ለወያኔና ለኦነግ አሳልፈው ከሰጡ በኋላ አማራን እንወክላለን ብለው ከወያኔና ከኦነግ ጋር ባሜሪቃ አደሪዳሪነት  ለመደራደር  ቆርጠው ቢነሱ  ሊገርምህ አይገባም።  ካልደፈረሰ እንደማይጠራ፣ ሲደርስ እንደሚያዳርስ አትርሳ።  ያመንካቸው  ሁሉ እየካዱህ  በየመንገዱ ሲንጠባጠቡ ስታይ  የብሩህ  ቀንን መቃረብ  እያበሰሩህ  መሆኑን አወቅ፣  ሊነጋ ሲል ይበልጥ ይጨልማልና  (the darkest hour is just before dawn)።

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

5 Comments

 1. Excellent! You’ve done the right thing at this very crucial moment. Very truly , these paid agents who ‘ve disguised themselves as an Amhara have engaged in a relentless anti- FANo patriot Eskindir Nega campaign. All of them are indded hotch-potches of ADP/Beaden, OLF/ODP, EZEMA, TPLF etc. Their conspiracy against the Amhara people is doom to failure. What they have done to AAPO and its persident Prof. Asrat Woldeyes will never ever happen again with FANO survival struggle at this moment. FANO prevails, Down with Abiy Ahemed’s OLF Oromuma savage regime in Bantustan apartheid Ethiopia.

 2. Excellent! You’ve done the right thing at this very crucial moment. Very truly , these paid agents who ‘ve disguised themselves as an Amhara have engaged in a relentless anti- FANo patriot Eskindir Nega campaign. All of them are indeed hotch-potches of ADP/Beaden, OLF/ODP, EZEMA, TPLF etc. Their conspiracy against the Amhara people is doom to failure. What they have done to AAPO and its persident Prof. Asrat Woldeyes will never ever happen again with FANO survival struggle at this moment. FANO prevails!
  Down with Abiy Ahemed’s OLF Oromuma savage regime in Bantustan apartheid Ethiopia.

 3. መስፍን አረጋ ያልከው ሁሉ በአመዛኙ እውነት ቢሆንም በዚህን ጊዜ እንዲህ የከረረ ትችት ማንንም ሊጠቅም አይችልም ይልቁንስ ፋኖ ስህተቱን አጥርቶ የሚጓዝበትን ማመላከት እንጅ ይሄ ይሻላል ያ ይሻላል የሚለው ማንንም አይበጅም በእርግጥም ለአቅመ ማሰብ ያልደረሰ ወጣት ካልሆነ በስተቀር ትግሬዎች ይህችን አገር ከተቆጣጠሩ በኋላ የእስክንድርን ጀግንነት፤አገር ወዳድነትና ሌሎችን ኳሊቲዎችን የማያውቅ ይኖራል ብዬ አልገምትም ችግሩ ግምቦት 7 የተባለው ነቀርሳ እስክንድርን ተጠምጥሞ ቀለቡን ከዚሁ ሊያሰፍር ነው የሚሉ ያለፈውን የግምቦት 7 ተንኮል የተገነዘቡ ያንገፈግፋቸው ወገኖች በመጯጯሃቸው የማይገባቸውን ስም ሊያሰጣቸው ባልተገባ ነበር። እነ ምሬ ወዳጆን የመሰሉ ቁጥቦች እነ ማርሸትንና ዶር ያሲን መሰለኝ ኮለኔል ሙሃባን ሌሎችንም እኩል ማክበር ያስፈልግ ነበር እኛ 3ጊዜ መብላት መብት ባደረግንበት ሁኔታ የሚንገኝ ዛሬ ይሙቱ ነገ የማያውቁትን ወንድሞች ተገቢውን ክብር መስጠት ያስፈልጋል ያለበለዚያ አቶ ዳን ኤል ክብርትስ ሆኑ ብርሃኑ ነጋ ግርማ ሰይፉስ ከዚህ በላይ ምን አጠፉ። ለማንኛውም ብእርህ አንድነት የሚያመጣ እንጅ እንዲህ በእጅጉ ከርሮ የቀረባ ባይሆን መልካም ነው።

  • Murad, I agree with your assessment of the article. Yes, Eskinder is one of a kind but without Fano leaders and Fanos themselves he can’t do anything by himself. So, let them on the ground brain storm and form the Political body of Fano and divide power by themselves.

 4. Mesfin, at this moment, the main issue is Abiy Ahmad, and the priority should be removing him and his cronies (those in the Amhara, Tigray, and Oromo regions and others who prioritize their personal gain over governance.) This is a crucial opportunity to unite and achieve this goal. Mesfin, I believe you were a unifier, not a divider and continue that way.
  If I were you, I wouldn’t write anything against any Fano leaders who are fighting against the manipulative boy king.
  Abiy has lost the support of the international community and even his own supporters are ashamed of him.
  He remains in power not due to his own strength, but because the opposition is weak and lacks a coordinated strategy.
  To the leaders of Gonder, Gojam, Wello, and Shewa Fano: What are you waiting for? Unite and coordinate with Tigray, Oromo, and other ethnic leaders to bring democracy to Ethiopia! Facilitate the unification and seize this golden opportunity. It is achievable!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

ryryry
Previous Story

ፋኖ አዲስ አበባ ገባ ሁለተኛ ጥቃት ተፈፀመ | ጎንደር ህዝቡ ገንፍሎ ወጣ | በባህርዳር ውጊያ ተጀመረ ባለስልጣን ተገደለ | ኮረኔል ደመቀ ላይ የግድያ ሙከራ

20
Next Story

የጎንደሩ ፍልሚያ በ20 አከባቢዎች እየተካሄደ ነው | የጎንደሩ ከባድ የከበባ ውጊያ | ዘመቻ ግንቦትና ወልቃይት

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop