May 10, 2024
23 mins read

የኦሮሞ ብልፅግና እና የህውሃት ያልተቀደሰ ጋብቻ

Abiy and Debre

የኦሮሞ ብልፅግና እና የህውሃት     ያልተቀደሰ ጋብቻ።

 

“የማይዘልቁ ፍቅረኞች በየወንዙ ይማማላሉ” እንዲሉ እነ ኦነግ ብልፅግና እና ህወሃት እንጣመር እና አጋር ፓርቲ እንሁን በሚል የጫጉላ ሽር-ሽር ላይ እንደ ሆኑ እየሰማን ነበር። እንግዲህ ያዝልቅላችሁ ከማለት ውጭ ምን ማለት ይቻላል።

 

የሚያሳዝነው ግን የአንድ ሚልዮን የትግራይ ወጣት ነፍስ “የደም ካሳ” ሳይከፈል በህውሃት አዛውንት ባለስልጣኖች የስልጣን ጥም መመንዘሩ ነው። የትግራይም ሕዝብ እንደ ሕዝብ ይህን አካሄድ ካልተቃወመ ከባድ ችግር በሕዝቡ የመንፈስ እና የሰውነት ማንነት ላይ እንዳለ የሚያሳይ ይሆናል ።

 

በተለይ የትግራይ ዲያስፖራዎች እና እንደ ኤርምያስ ለገሰ ያሉ ተቀጣሪዎቻቸው ሰሞኑን እየለፈለፉት ያለው ከእውነት የራቀ ዲስኩር የትግራይን ሕዝብ በእውነት የሚጠቅም ከሆነ የምናየው ከመሆኑ ባሻገር መላው የትግራይ ሕዝብ ፣ በዲያስፖራ ያሉ ትግራዊ የሰብሃዊ እና የማህበራዊ አንቂዎች ትክክለኛውን የታሪክ ፣ የቱፊት እና የማንነት  ጠርዝ ይዘው እንዲጓዙ እንመክራለን። ነግሮቹ “ ከድጡ ወደ ማጡ” እንዳይሆንባቸው ከወዲሁ እኛ አማሮች ምክራችንን ጀባ እንላለን።

 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ከዚህ የቁጩ ስምምነት ጀርባ አጂሪት ህወሃት “ትላንት ብልፅግና ወይም አጋር ፓርቲ የሚባል ጉዳይ አታንሱብኝ ብላ ወደ ደደቢት ካመራች ፣ ጦር ከመዘዘች ፣ የትግራይን ሕዝብ እና መሪዎቿን ካስበላች በኋላ ምን ፈልጋ ይሆን ከብልፅግና ጋር የአጋር ፖርቲ ስምምነት የማድረግ ዳርዳርታ ያሰበችው?” የሚለውን ጥያቄ በጊዜ ሂደት ጉንጉን ሴራውን እና ዓላማውን የምናየው ይሆናል።

 

እንደሚታወቀው የኦሮሞ ብልፅግና እና የህወሃት ቡድኖች በዘር ፣ በነገድ ፣ በታሪክ ፣ በጆግራፊያዊ አቀማመጥ ፣ በባህል ፣በቋንቋ ፣ በቱፉት ፣ በማንነት ወ.ዘ.ተ. የሚገናኙ ሕዝቦች አይደሉም።

 

እነዚህ ብሔሮች ላለፉት 30 ዓመታት በረቀቀ እና በሴራ ኢትዮጵያን ፣ የኦርቶዶክስ እና የእስልምናን ሃይማኖት መርሆዎችን (Pillars) በመፈነቃቅል ፣ በማሽመድመድ ፣ በመበጣጠስ  ፣ ሕዝብን ከሕዝብ እያጋጩ ፣ ቤተ-ክርስቲያናትን እና የእስልምና ተቋማትን እያቃጠሉ ፣ ካህናትን እና የእስልምና አባቶችን እያሳደዱ ፣ እያፈኑና እየገደሉ ዘልቀዋል። ይህን የሚያደርጉት ደግሞ የጋራ የስልጣን ጥማቸውን ለማመቻቸት ፣ ለማስቀጠል እና ሃገረ ኢትዮጵያን በጋራ ለመዝረፍ ነው።

 

እነዚህን ቡድኖች በቅርብ ለሚያውቃቸው፣ ምርምር ላካሄደ እና የሴራቸውን ውስጠ ወይራ ቀመራቸውን ለተረዳ ይህን ለምን ለማድረግ ተነሳሱ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ በጣም ቀላል ነው።

 

አንደኛው እና ዋነኛው በ1885 እና በ1935 ኢትዮጵያ የጣሊያንን ፋሽሽታዊ ወራሪ ኃይል አዋርዳ እና አፈርድሜ አብልታ ስትመልስ ጣሊያኖች የትግራይን እና ከፊል የኤርትራ ባንዳዎችን ፀረ ኢትዮጵያዊ አቋም እንዲያራምድ ሲያደርጉ ፣ ጀርመኖች እና ምዕራባውያን ደግሞ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለመላው ጥቁር ሕዝብ ነፃነት መጎናፀፍ ምክንያት ስለሆነች ይህ ኩነት ዳግም እንዳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ ላይ የጥላቻ መንፈስ ያሳድር ዘንድ የእውሸት የትርክት መፅሃፎችን በመፃፍ እና “ኦነግ” የሚባል ፀረ ኢትዮጵያ ድርጅት በማቋቋም አገረ ኢትዮጵያን ለመበጣጠስ ነበር የጅማሮ እቅዳቸው።

 

ምዕራባውያን ተፃፃሪ ቡድኖችን በማቋቋም  ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ያደረጉት እንቅስቅሴ በአምላክም ረዳይነት ሆነ በሕዝቡ አሻፈርኝነት አልሳካ ሲላቸው “ኢትዮጵያን እንዳሰብነው ለመሰባባር ፣ ለመገነጣጠል እና ለመበጣጠስ ያልቻልነው አማራው ጠንካራ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ስላለው እና በሃገሩ ጉዳይ የማይደራደር በመሆኑ ነው” በማለት አጀንዳቸውን ቀይረው ህውሃት እና ኦሮሞ ብልፅግናን በገንዘብ ፣ በመሳሪያ እና በቁሳቁስ በመደገፍ እና በማደራጅት በአማራ ሕዝብ ላይ እንዲነሳሱ ፣ የአማራን አፅመ እርስቱን  በጋራ እንዲቀራመጡ እና የተፈጥሮ ሃብቱን በደቦ እንዲመዘብሩ ለእነዚህ ሃገር አጥፊ ቡድኖች የአይዟችሁ ባይነቱን እና ይሁንታቸውን በመስጠት አሁን ላሉበት ቅጥ ያጣ ፣ የሃገር አፍራሽነት ፣ የመገንጠል ፣ የሁሉ የኛ ነው እና አጉራ ዘለል ባህሪ እንዲላበሱ ትልቁን ሚና አሜሪካ እና ምዕራባዊያን ተጫውተዋል።

 

እነዚህ ጉግ-ማንጉግ ቡድኖች ሲመቻቸው ፣ ለጥቅማቸው እና ለዝርፊያ ሲያስቡ “ኢትዮጵያን” በስሱ እያቆለጳጰሱ ፣ ሳይመቻቸው ደግሞ “ኢትዮጵያ በቃችን” እያሉ እና እያደናበሩ ለዘመናት በአማራው ቸልተኝነት ፣ በምን ያመጣሉ ህሳቤ እና በበይ ተመልካችነት ያሻቸውን በማድረግ ለሃምሳ ሃመታት ዘልቀዋል።

 

እነዚህ እኩያን ቡድኖች ሃገር ኢትዮጵያን  ለመበጣጠስ ካላቸው ህሳቤ አልፈው ለምን አማራውን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ተነሳሱ የሚለውን ደግሞ በመጠኑ መዳሰሱ የግድ ስለሚል እስኪ ገረፍ ገረፍ እያደረግን እንዳስሰው።

 

የኦሮሞ ብልፅግና የራሱን ክልል የሚያተራምሰውን የኦሮሞ ሸኔ ትጥቅ ሳያስፈታ “ፋኖን ትጥቅ ላስፈታ ነው” በሚል እንደ አስራ አራተኛው ክፍለዘመን የግራኝ መሀመድ ወረራ በአማራ መልክአ ምድሮች የገባበት ጦርነት እንዳሰበው ካለመሆኑ ባሻገር ሰራዊቱም እንደ አሸን እየረገፈ ፣ ፋኖም ድል እየቀናው ይገኛል።

 

እንግዲህ የትግራይ ሕዝብ ሞት የማይገዳቸው ያፈጁ እና ያረጅ የህውሃት ባለሥልጣኖች ጎረቤታቸውን ፣ ቀላቢያቸውን ፣ የክፉ ቀን አለሁ የሚላቸውን ፣ ቀለብ የሚሰፍርላቸውን ፣ አስጠጊያቸውን ወ.ዘ.ተ. የአማራን ሕዝብ ከኦሮሞ ብልፅግና ጎን ሁነው ለመውጋት በመደራደር ላይ ከመሆናቸው ባሻገር የፋኖን የትግል እምርታ ለማጨናገፍ “ የቀቢፀ ተስፋ የውል ሰነድ ለመፈረም በመንደርድር ላይ ይገኛሉ ።

 

ህወሃት “የአማራን ሕዝብ ቋሚ ጠላቴ እና ሂሳብ አወራርዳለሁ” ብሎ ደደቢት በርሃ ከወረደ ማግስት ጀምሮ ይህን ህሳቤ የያዘና ብዙ ጊዜ ሞክሮ ያልተሳካለት ቢሆንም በዚህ ህሳቤው ከቀጠለ የአማራ ሕዝብ “በሶ ጨብጦ” የሚጠብቀው መስሎት ከሆነ የምናየው ይሆናል። ያም ሆነ ይህ “ በእንቅርት ላይ ጀሮ ገድፍ” እንዳይሆንበት እኛ የአማራ ሕዝቦች “ምከረው ምከረው ካልሆነ መከራ ይምከረው” እንዲሉ ለህውሃት ከወዲሁ የማስጠንቀቂያ ድወል በመላው የአማራ ሕዝብ ስም ፅኑ መልክታችንንን እናስተላልፋለን።

 

የኦሮሞ ብልፅግና እና ህወሃት የሚያመሳስላቸው እና የሚጋሩት ፅዩፍ ባህሪ አላቸው እሱም ተስፋፊነት ፣ ስግብግብነት እና “ሁሉ የኛ” ማለትም በነሱ አነጋገር “ ኬኞ እና ኩሉ አነ” በሚል ርኩስ አስተሳሰብ እና በግለኝነት አባዜ የተለከፉ ናቸው።

 

እነ ኦሮሞ ብልፅግና እና ህወሃት “አዲስአበባ ፣ ወልቃይት ፣ ራያ ፣ ደራ ወ.ዘ.ተ. “ የኛ ነው እያሉ ይዘባርቃሉ።

 

መጤ ሁሉ ያገኘውን ሁሉ “የኔ ነው” ካለ የኢትዮጵያ የዕርስት ባለቤት የሆነውን የአማራን አፅም እርስቶቹ  “የአንተ እይደለም ፣” ከተባለ እና ድፍረት በተሞላበት ህሳቤ ይህን ፅንፍ ህሳቤ ካራመዱ የሚሆነውን ሁሉ ወደፊት የምናየው ይሆናል።

 

ኦነግ ብልፅግና እና ህውሃት ሆን ብለው ይህን የሚያደርጉት በጋርዮሽ ፣ ተካፍለን እና አካፍለን በጋራ እንኑር የሚል ህሳቤ በአዕምሮአቸው ስላልተፈጠረ ፣ በድህነት እና በጠባብነት አስተሳሰብ አባዜ ስለተለከፉ እንዲሁም በጋራ ያፀደቁትን ፉርሽ ፣ መላ ሃገረ ኢትዮጵያን በይበልጥኑ የአማራን ሕዝብ የማይወክለውን ገንጣይ ፣ አስገንጣይ ህገ-መንግስታቸውን መሰረት በማድረግ ፣ በጉልበት እና በአጉራዘለልነት የአማራ አፅም እርስቶችን እነሱ በሳሉት ካርታ አጠቃለው የውጭ ሃገር መንግስታት አስጎባሻቸው በአሜሪካ ፣ በምዕራብውያን ሀገሮች አይዞህ ባይነታቸው ታክሎቡት በመገንጠል ሃገር ሆነው ለመኖር ስላሰቡ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል።

 

ህውሃትና የኦሮሞ ብልፅግና በለውጥ ተብየው የአምስት ዓመት ክራሞታቸው  የገቡበትን ፍትጊያ ፣ ጦር ያማዘዛቸው ጉዳይ ፣ አሻጥራቸውን እና እንደገና ከተገዳደሉ በኋላ ጥምረት የመፍጠር  “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚል የአነገቡት አካሄድ፣ሴረኛነታቸው ስግብግብነታቸውን ለማየት ብዙ እርቀት መሄድ አያስፈልግም።

 

የኦሮምያው ብልፅግና ቆዳውን ቀይሮ የትግራይን ሕዝብ “የደረሰብህ በደል ያንገፈግፋል ፣ አማራው አታሎናል፣ አማራ የጋራ የብሔር ጭቆና አድርሶብናል ፣ ወልቃይትና እራያ ያንተ ነውና የጋራ ጠላታችን አማራ ነው” እያለ እየወሸከተ ሃገርና ሕዝብን ለሌላ እልቂት እያንደረደረ ሲሆን “እባብ ለእባብ” እንዲሉ ህውሃትም ይህን የሸፍጥ አካሄድ ልቡ እያወቀ እየገፋበት ይገኛል።

 

በልምድ እንደታየው የሃገረ ኢትዮጵያ መሪዎች ወደ ውድቀት ሊያመሩ ሲሉ “ታስሮ እንደተፈታ ወይፈን” ይደነብራሉ ፣ ግራ ይገባቸዋል ፣ መስመራቸውን ይስታሉ፣ እውር ድንብሩን ይጓዛሉ፣ ዘላቂ ወዳጃቸውንና አጥፊያቸውን መለየት ይሳናቸዋል።

 

በኦሮሙማ የበላይነት የተዋቀረው ጅላንፎው የብልፅግና መንግስት “ ታሪካዊ የጋራ ጠላታችን አማራ ነው ፣ አማራን ደግሞ ማበርከክ የምንችለው ከውጭ ጎረቤት ሃገራት  የሚያገናኘውን የአማራን ለም መሬት ወልቃይትን እና ኩሩውን የራያን መሬት ወደ ትግራይ አጠቃለን በማካለል ብቻና ብቻ ነው” በሚል የከረፈፍ አካሄድ ከህወሃት ጋር ደም መቃባቱን ወደጎን ብሎ ተማምሎ የጋራ የጥፋት ጉዟቸውን ጀምረዋል።

 

ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የነበረውን የህወሃት አካሄድ ተከትለን አማራን ፀጥ አድርገን ፣ እረግጠንና አንገላተን በተለመደው መልኩ ካልገዛነው አማራ ይውጠናል  የሚለውን የደናቁርት ህሳቤ ህወሃት በለመደው አስማቱና ሽወዳው ለኦሮሙማው ብልፅግና ሹክ ብሎት “ጭዋታ ፍርስርስ ያደረ እንጀራ ቁርስርስ” ዓይነት የልጆች ጭዋታ”ና “የነተሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ” እንዲሉ ይህን በመርዝ የተለወሰ የደባና የተንኮል ውሳኔ ተከትለው ከተጓዙ እነ ብልፅግና “የፈንጅ ወረዳ”  እንደረገጡ ይቁጠሩት።

 

“አያ በሬ ሆይ ሳሩነን አይተህ ገደሉን ሳታይ” እንዲሉ የኦሮሞ ህዝብ ከሰላሳ ዓመት የህውሃት መወገር ፣ መታሰር ፣ መደፈር ፣ ስቃይና እንግልት እንዲላቀቅ “ የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው” ብሎ ከጎኑ የቆመውን ፣ በህግ ማስከበር የህልውና ጦርነት ወቅት ከቆላ ተምቤን ተነስቶ አዲስ አበባ ጫፍ አካባቢ ደርሶ ብልፅግናን ከስልጣኑ ሊያስፈነጥረው የነበረውን ህወሃትን መልሶ ወደ ሸጎሬው ቆላ ተንቤን የመለሰለትን  የአማራ ሕዝብ ክዶ “ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚል አጓጉል ህሳቤ  በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደረገው ደባና የጦርነት ጉሰማን የኦሮሞ ሕዝብ የበይ ተመልካች ሆኖ ካየ ለወደፊቱ ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለው መሆኑን ሊረዱት ይገባል።

 

የህውሃት የክህደት አካሄዱ በሃያ ሰባት ዓመታት የስልጣን ዘመኑ ያሳየው ፣ በአማራውም ሆነ በኦሮሞው ላይ የተገበረው በመሆኑ “የቆየ ይየው” እንዲሉ ለወደፊቱ ህወሃት እና ብልፅግና ሥልጣን ላይ ከሰነበቱ እርስ በርሳቸው እንደሚባሉ እና ጦር እንደሚማዘዙ”  እኛ የኢትዮጵያዊያንና የአማራ ሕዝቦች አስረግጠን እንናገራለን ፣ “የዛ ሰው ይበላችሁ” እንላለን። ህወሃት በ1983 ስልጣን በያዘ በሽግግር መንግስት ወቅት፣ በሕገ መንግስቱ ማርቀቅ እና ማፅደቅ ማግስት እንዴት አርጎ የእነ “ሌንጮ ለታን” የኦነግ ቡድን  ቁማር እደበላው እና እንደጨፈጨፈው ሊታወስ ይገባል።

 

ይህን ያልንበት ምክንያት “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ” እንዲሉ እነብልፅግና በአለበሌለ የጦር መሳሪያ ፣ በሚሲያል፣ በድሮን፣ ከአየር ላይ በሚወረወር ክላስተር ቦንብ ምድረ ትግራይን  አጋይተው እና ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የትግራይን  ሕዝብ ከጨፈጨፉ በኋላ “ወልቃይትና ራያን” በካሳ በመቸር ለመታረቅና እንደገና ጋብቻ ለመፈፀም መዳዳታቸው ከማሳቅ አልፎ ያንከተክታል።

 

እንደ ቀላል  የባልና ሚስት ተጣልቶ መታረቅ አይነት ጉዳይ ካደረጉት የሚጎዳውና ይበልጥ ዋጋ የሚከፍለው ኦሮሞ እና  የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ስለመሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው።

 

እንደ እስቆሮቱ ይሁዳ የአማራን ሕዝብ “የኦሮ- አማራ ጥምረት ብሉው ጉንጭ ስመውና በሕግ ማስከበሩ አድኑን” በለው የአማራን ሕዝብ ከተማፀኑና ስልጣናቸውን ካስጠበቁ በኋላ እነ ኦሮሞ ብልፅግና አማራን መካዳቸው ታሪክ የማይረሳው ጠባሳና የሚያስተዛዝብ አካሄድ እንደሆነ ሊገነዘቡት የግድ ይላቸዋል እንላለን።

 

ከዚህ ባሻገር ሊታወቅ የሚገባው “ቦ ጊዜ ለኩሉ” እንዲሉ አማራ ቢገደል ፣ ቢሰቃይ ፣ ቢፈናቀልና ቢንገላታ ለነፃነቱ መታገል ከአያት ቅድመ አያቶቹ የወረሰው ስለሆነ መስዋህትነት ሊይስከፍል ይችል እንደሆን እንጂ አሸናፊው ኢትዮጵያ ፣ ኢትዮጵያዊውና የሃገር ካሳማና መከታ የሆነው የአማራ ህዝብ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።

 

ወልቃይት ጠገዴ ፣ ጠለምትና ራያ  ከዕርስት ባለቤታቸው  አማራ ምድር ጋር ሆነው ለዘለዓለም እንደሚቀጥሉ የሚጠራጠርና የሚያቅማማ አማራ እንደሌለ ቁርጣችሁን እወቁ እንላችዋለን።

 

ይህን ሃቅና እውነታ እቀለብሳለሁ ብሎ የሆነ ቡድን ከመጣ ግን እንደ ታይዋኗ የቻይና አካል ፣ እንደ ካሽሚር ፣ እንደ ዮክሬን ፣ ፓሊስትያን ፣ ከርድሽ ና ሌሎችም የትግል አካሄዶች ፍልሚያው ይቀጥላል ።

 

የአባቶቻችንን የከለው አማራ ነገድ ምድርን  እንደ ቁራሽ እንጀራ እኛ አማሮች የትዕብታችንን መገኛና መቀበሪያ ምሬታችንን ለማንም አሳልፈን  አንሰጥም ፣ እርማችሁን አውጡ።

“አማራ ያቸንፋል”

“አዲስ አበባ ፣ ወልቃይት ፣ ራያ እና መተከል የአማራ ሕዝብ ቀይ መስመሮች ናቸው”

 

 

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop