ታሪክ ራሷን ደገመች ኢትዮጲያ በሌላ ግፈኛ መሪ መዳፍ ስር ወደቀች

በሃገራችን ኢትዮጲያ ከጥንት ከነገስታቱ ዘመን ጀምሮ  በጎ ታሪኮችም ክፉ ታሪኮችም  በመሪዎች ሲካሄዱ ኖረዋል:: ጸሃፍቱና መገናኝ ብዙሃን/ ሚዲያን የሚቆጣጠሩት  መሪዎች በመሆናቸው የመሪዎቹ ታሪክ ጸሃዩ ንጉስ ቆራጡ ፕሬዚዳንት ብልሁ አስተዋዩ ጠቅላይ ሚንስትር እየተባለላቸው ዛሬ ደርሰናል  ግፉም  እንዲሁ  ካንዱ መሪ ወደሌላው ታሪክ ተደገመች  ሆኖብናል::

በደርግ መንግስት  ቀይሽብር በተባለው ዘግናኝ  ጭፍጨፋ  ተጠያቂ የነበሩትን ለህግ የማቅረብ ሂደት ቀጥሎ አትሌት  ሻምበል ማሞ ወልዴ የኪነጥበብ ባለሙያ አስር አለቃ ተዘራ ሃይለሚካኤልና መሰሎቻቸው ሳይቀሩ ተይዘው ምርመራው ሲቀጥል ጥቆማው  ወደሁሉም የደርግ ሃላፊዎችና ባለስልጣናት ሲያመራ የዝግ ችሎቱን ያካሂዱ የነበሩት አፈንጉስ ተሾመ ቅጣው  ጉዳዩን በይደር እያቆዩ  ደርግ ተጠያቂዎቹን በሙሉ ማቅረብ  ያለመፈለጉን ሲረዱ ያንዳንዶቹም ምርመራ እንዳይካሄድ ሰሞኑን ዶ/ር  አብይ ባዘዙት መልክ ሲያግድ አፈንጉስ ተሾመ በጤና ምክንያት ብለው ከሃገር ተሰደው በዚያው ቀርተዋል::

አፈንጉስ ተሾመ በክፉ ቀን መሸሸግ እንደሚሻል “ክፉ ቀንና ቅምዝም ዱላን ዝቅ ብሎ ማሳለፍ ነው” በሚል ምሳሌያቸው የሚታወቁ ሲሆኑ  ትክክለኛው  የፍትህ መንበር ቅምዝሙን ሳይፈራ  ፍትህን የሚዳኝ መሆኑን በታሪክ በቅን ፍርዳቸው የተጋዙ የተገደሉ የተሰደዱ የሃገራችንም ሆነ የሌሎች ሃገሮች  ዳኞች ወርቃማ ምስክርነት ይገኛል:: በዚህ አጋጣሚ የወያኔን የካንጋሮ ችሎት ሳትፈራ  ወያኔ በግፍ ያሰራቸው የራሱን ባልደረቦች እነስዬ አብርሃን በነጻ ያሰናበተች ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳን ከወቅቱ የፖለቲካ ምልከታዋ  በማይገናኝ መልኩ ሙያዊ ብቃትዋን ላደንቅ እወዳለሁ::

የመቂው ጎልማሳ ባቲ ባልተለመደ ከኦነግ ፖለቲከኛንና ምሁራን በተለየ በመድረክ ውይይት ከሌሎች የኢትዮጲያ ፖለቲከኞች ጋር የሚወያይ ባለተስፋን ሰው ግድያ ዶ/ር አብይ ከፎከሩበት በፓርቲያቸው ላይ የሚነሳ አመጽን ከኢሃአፓ ጊዜ በበለጠ እጥፍ እንበቀላለን ያሉትን ለመጀመራቸው ማረጋገጫ  ሲሆን  የሚያሳዝነው ግን በዚህ መልኩ ለግል ስልጣን የሰዎችን ደም የሚያፈሱ መጨረሻቸው ለራሳቸውም ለልጆቻቸውም ሃፍረት መሆኑን  ምንም የተማረች ሃገሯን የትምትወድ ቢሆንም የደርጉ ጨፍጫፊ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ልጅ ዶክተር ትእግስትን በየሚዲያና በየመደረኩ የሚደርስባት ወከባ ማዋረድ ምስክር ነው:: የሌሎቹ አምባገነኖች ልጆች የስታሊን ልጅ እንዳደረገችውን ወላጅ አባትዋን ክዳ  ከሩሲያ ህዝብ ጎን በመቆም ለስደት የተዳረገችው ትገኛለች::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወያኔና የብልፅግና ጦር አበጋዞች የጦርነት ንግድና የ2.5 ቢሊዮን ዶላር የመሠረተ-ልማት ውድመት!!!

ስለዚህ ዶ/ር አብይ የሰው እድሜ ቢበዛ ሰባ ሰማንያ በሚለው ቅዱስ መጽሃፍ ግማሹን በሰላም ይፈጽሙ ዘንድ  የሰው ደም በፖለቲካ ሴራ  ፈስሶ እንዳይቀር  የሚቻልዎትን ያድርጉ በክፉ የዘር ፓለቲካ ወክለዋለሁ በሚሉት የኦሮሞ ክልል ጭምር የሚያልቀው ህዝባችን   ጉዳይ ግድ ብሎት ባፋጣኝ ስልጣኑንን የኔታ ፕሮፌሰር መስፍን  ለደርግ በሰጡት ምክር ለህዝብ ባላደራ በቶሎ ያስረክቡና ከምድራዊም ከዘላለምዋም ቁጣ ይተርፉ ዘንድ ምክሬን ለግሳለሁ:: የኤቤል ደም በከንቱ ፈስሶ እንዳልቀረ ሁሉ የወገኖቻቻን  ደምም  በከንቱ ፈስሶ እንደማይቀር መጽሃፉ/ ኪታቡ ታሪክም ባህላችንም ምስክር ነው

 

ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share