የትግሬ አዲስ አጀንዳ…

May 3, 2024

“…የፕሪቶሪያው ውል የተግባር መርሀ ግብር ላይ የራያንና የጠለምትን ጉዳይ እስከ ግንቦት 30/2016 ዓም የወልቃይት ጠገዴን ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓም ለመጨረስ ስምምነት ፈጽመን ወደ ሥራ ገብተናል። (ታደሰ ወረደ)

“…ይህ ዛሬ በድምፂ ወያነ የተለቀቀው ዜና የሳይበሩን ዓለም እንዲሞላው ተደርጓል። የትግሬና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ከብልፅግና የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ጋር በመሆን ስለ ሌላ ዙር ጦርነት ዝግጅት፣ ስለ ሌላ ዙር የይግሬና የዐማራ መከራ፣ ስለ ሌላ ዙር የጅምላ ብሔራዊ መርዶ ዝግጅት ጽፈዋል።

“…አገዛዙ ይሄ ክረምት እስኪያልፍለት ድረስ የዐማራው ትኩረት ትግራይ ብቻ እንድትሆን አቅዶ እየሠራ ነው ባይ ነኝ። ጦርነቱን በማጓተት ስትራቴጂ አድርጎ እየሠራ ነው። የትኩረት አቅጣጫን በማስቀየር በተለይ ይህችን ክረምት እንደምነም የፋኖን ትኩረት ወደ ራያና ወልቃይት በማዞር ለሚመጣው በጋ በድሮን እና በከባድ መሣሪያው ለመጠቀም ያስባል። ለማንኛውም ፋኖ ለሁለቱም ከወዲሁ መዘጋጀት ይኖርበታል ባይ ነኝ። በተለይ ትኩረቱን መንግሥት ላይ አድርጎ ለ4ኪሎ መዋጋት አለበት። ወያኔ እንደሆነች ዛሬ ብትገባ ነገ በዐማራው መነጠቋ አይቀርም። ኦሮሙማው አያዛልቃትም የሚሉ መተርጉማንም አሉ።

“…የብአዴንን ዝተት መግለጫ፣ የተመስገን ጥሩነህ ዛቻ፣ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሓላፊ ሚንስትር ለገሰ ቱሉን ቱሪናፋ ቀደዳ፣ ከመቀሌ ከመሴ፣ ከመቀሌ ደብረታቦር በሲሚንቶ ጫኝ መኪና ውስጥ መትረየስ፣ ቦንብ ለፋኖና ለሸኔ ሊላክ ሲል ተያዘ ወዘተ የሚለው የማደናገሪያ ዜና አይሠራም። ትግሬ ከኦሮሞ ጋር ሆኖ እየፎከረ ነው። በራያ ዘረፋው እንደተጧጧፈ እየተሰማ ነው። የጁላ ጦር የገበሬ ቤት በእሳት እየለኮሰ እያነደደ ነው ተብሏል። መፍትሄ ጨካኝ መሆን ብቻ ነው።

  • በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ…
  • እንመጣለን ነው የሚለው ትግሬው።

“…መከላከያ ሠራዊቱን አቁሞ ነው የሚያጠጣው። ዱርዬ የሚለው ዐማራን ነው የዐማራን ፋኖ። ህጻናት፣ ሴቶች፣ ባንዲራ ይዘን አይደለም የምንመጣው። ይዘን የምንመጣው ምን እንደሆነ በሁሉ ዘንድ ይታወቃል ነው የሚለው። አይደለም ዱርዬው የዐማራ ፋኖ መከላከያ ራሱ ያውቀናል ነው የሚለው።

“…አንዳንድ ምስኪን ዐማሮች በትግሬ ነፃ አውጪ በህወሓት ካድሬዎች ምላስ ሲደነዝዙ አያለሁ። ህወሓት በሕይወት እያለች አበደን ቃለ ለሰማይ ቃል ለምድር ዐማራና ትግሬ አይታረቁም። አይቀራረቡም።

“…ትግሬ ደም የፈሰሰበት ቦታ በበጋ አይዋጋም። ሰይጣኑ ክረምት ጠብቆ ወይ ዝናብ ጠብቆ ነው ለደም ግብር የሚገፋው፣ የሚነዳው። አሁን ክረምቱ መጥቷል። ትግሬም ቀሪ ሕዝቡን፣ ወጣቱን መገበር አለበት። ለዚያ ነው እንዲህ የሚሠራ የሚያደርገውን የሚያሳጣው።

“…በሱዳን ያለው የማይካድራው ጨፍጫፊ አራጅ ሳምሪ ቡድን ወደ ሁመራ፣ ወደ ወልቃይት ይንቀሳቀሳል። በሽሬ በኩልም የሚመጣ አለ። ወልቃይት የሚገባም አለ። መሳሪያ እስከ አፍንጫው ታጥቋል። ስዩም ተሾመ በግልፅ ተናግሯል። ቀለብም እንደጉድ በርዳታ መልክ ገብቷል። በጀትም በቢልዮን የሚቆጠር ብር ለህወሓት ከኦሮሙማው ተለግሷል። የሚቀረው በሰሜን ጎንደር፣ በወልቃይትና በሰሜን ወሎ ከዐማራ ጋር መፈሳፈስ ነው።

“…አሁንም ሌላ ዙር ሺ ቆማጣ፣ ሚልዮን አስከሬን፣ ውድመት፣ እሪታ፣ ኡኡታ፣ ቁቁታ ተዘጋጅቷል። አቢይ አሕመድ አያስጥልህም። የማትኖርበት ቤት አታምሽ። የትግሬንም የዐማራንም የመከራ ዘመን በኦሮሙማው ሴራ አታርዝም።

“…ዐማራ ዱርዬ የተባልከው ፋኖ አትራራ፣ እንደ እስራኤል ፍፁም አረመኔ ጨካኝ ቆራጥ መሆን ነው የሚጠበቅብህ። ዐማራና ትግሬ አንድ ሕዝብ ነው የሚለውን የሂዊ ሰበካ ለጊዜው ኢግኖር ግጨው።

 

• ሲያበሽቁ እኮ በማርያም… ዘመዴ

 


 

1 Comment

  1. በዘርና በቋንቋ የተሸነሸነችው ሃገራችን ኢትዮጵያ መከረዋ ብዙ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይን ተገላገልን እያለን ሌላ የባሰ መከራ አዝናቢ ሃይል ወረደብን። በዚህ ሁሉ የፓለቲካ ጋጋታ ዛሬም ትላንትም መከራውን የሚቆጥረው የአማራው ህብረተሰብ እንደሆነ እማኝ ማቆም አያስፈልግም። ልክ እንደትላንቱ አለዚያም ከዚያ በከፋ ሁኔታ ሰዎች በድብቅ እስር ቤቶች ይሰቃያሉ፤ አልፎ ተርፎም ይገደላሉ። የመደመሩ ስሌት ወደ መቀነስ ወርዶ ዛሬ ላይ በአማራውና በትግራዪ ህበረተሰብ ላይ ይህ ነው የማይባል የመከራ ዝናብ ሳያቋርጥ ይወርዳል። የሚያሳዝነው ግን እነዚህ ህብረተሰቦች ዛሬም በጦርነት ይፈላለጋሉ። ማን አትርፎ ማን ሊከስር እንደሆነ ቀን ያሳየናል! የትላንቱ ታሳሪ የዛሬ አሳሪና ገራፊ ነው። ዓለም ዘጠኝ ናት የሚሉት ዘመዶቼ ለዚህ ነው። አሁን ደግሞ ይባስ ተብሎ ወያኔ እንደገና ለዳግም ጦርነት መንደፋደፉ ወቸው ጉድ ያሰኛል። ለነገሩ የብልጽግናው መንግስትና ወያኔ አንድ የተስማሙበት ጉዳይ አለ አማራን እናዳክምና ያለውን እንከፋፈል ነገር። ግን ይህ እንኳን በሃበሻው ፓለቲካ ቀርቶ በሰከነው ዓለም ላይ የሚፈጸምም ውል ዘላቂነት የለውም። ወያኔና ብልጽግና ላይ ላዪን እንደ ካብ እባብ ለሰው ይታዪ እንጂ ውስጥ ውስጡን ለግድያ የሚፈላለጉ ሃይሎች ናቸው። ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽ ናቸውና ስራቸው የድርቡሽ ነው። በዚህ ላይ በየስፍራው ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው የስመ ብሄር ታጣቂና መከራ አዝናቢ ስንጨምርበት በእርግጥም ይች ሃገር ተረግማለች ያሰኛል። ለነገሩ የተማረ ይግደለኝ ብለን ይኸው ፊደል የቆጠረው ሁሉ ዶ/ር፣ ፕሮፌሰር፤ እንጅኒየር ወዘተ እያለ አለቃ ሆኖብን ሃበሳ ያሳየናል። አይጣል ነው።
    በረጅሙ የእድሜና የንጉስነት ዘመናቸው አጼ ሃይለስላሴ አንድም ቀን ከማን ብሄር እንደሆኑ ተናግረው ያውቁም። “ህይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ” በተሰኘውም መጽሃፋቸው ላይ ትውልዳቸው ከንጉስ ሰለሞን ከተገኘው ከቀዳማዊ ሚኒሊክ እንደሆኑ ብቻ ነው የሚጠቅሱት። ይኸው የዛሬዎቹ አረሆዎች ደግሞ አማራ፤ ትግሬ፤ ጉራጌ፤ አፋር፤ ኦሮሞ እያልን ዘር ቆጠራውን ስናሰላ ጀንበር ወጥታ ትጠልቃለች። ዘር መቁጠሩ ብቻውን በደል ባልሆነ ነበር። ችግሩ ከክልሌ ውጡ እያሉ ሰውን ማራወጥና መግደሉ ነው። የጠባብ ብሄርተኞች በሽታ አንድ እና አንድ ብቻ ነው። የበታችነት ስሜት። ይህን በሽታ ደግሞ የሚፈውስ የመርፌም ሆነ የሚዋጥ ፍቱን መድሃኒት የለም። ሰው ቋንቋውንና ብሄሩን አስልቶ ከኖረ እንስሳ እንጂ ሰው አይደለም። ለዚህ ነው የሃገሬ ገበሬ “በየዘርህ ቢሉት የመቶ አመት ቆዳ ገቢያ ሂዶ ቆመ” ያሉት። እንዴት የሰው ልጅ ዓለምና የዓለምን ሁኔታ ማየትና ሰውን በሰውነቱ ተቀብሎ ምድሪቱን በጋራ መጠቀም ይከብደዋል?
    ወያኔ ሃርነት ትግራይ የትግራይ ቀዳሚው መከራ አዝናቢ ሃይል ነው። ከበረሃ እስከ ከተማ የተቃመሱት ይህኑ የግፍ ቅምሻ ነው። የትግራይ ህዝብ ጠላት አማራው ወይም ኤርትራዊው አይደለም። የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ወያኔና ብልጽግና ናቸው። በ 27 ዓመት የስልጣን ዘመናቸው ዞር ብለው ያላዪት ያ የዋህና ፍሪሃ ፈጣሪን የተሞላ የትግራይ ህዝብ ከመከራ ላይ መከራ እየተደራረበ ይኸው አሁንም አልበቃ ብሎ ዛሬም ለጦርነት ህዝቡን መጋበዙ ወያኔ ምን ያህል የገፈኛ ስብስብ እንደሆነ ያሳያል። በእኔ እምነት ወልቃይት፤ መቀሌ፤ ሃረር፤ ወለጋ ወዘተ የመላው ኢትዮጵያዊያን ምድር እንጂ ለአንድ ብሄር የተሰጠ ሥፍራ የለም። ግን ያለ ጦርነትና እልቂት መኖር የማይቻላቸው ወያኔዎች ዛሬም ጦርነትን እንደ አማራጭ መምረጣቸው ምንም ያህል ለሰው ህይወት ቅንጣት እንደማያስቡ ያሳያል። እርቅ ማለት ጦረኝነትን መተው፤ በየስርቻው በትግራይ በረሃማ ክፍሎችን ያጎራቸውን ወታደሮችና የሲቪል ህብረተሰብ መፍታት፤ ብልጽግናማ በስመ የትግራይ ተወላጅ በእስር የሚያሰቃያቸውን መልቀቅና ውል ያለው ሰላም አውርዶ ህዝባችን ቀድሞ እንደነበረ ፍቅሩ እንደ ልቡ ተንቀሳቅሶና ሰርቶ እንዲኖር መንገድ ማመቻቸት ያለፈን ጥፋት ለመካስ ዋንኛ መንገድ ነው። ትላንትም ክራር፤ ዛሬም ቀረርቶ፤ ያኔም በለው አሁንም ያዘው ለምንም ለማንም አይጠቅምም። ጄ/ታደሰ ወረደና ሌሎችም የወያኔ አመራሮች ዝም ብለው የማይታመን ነገር ለሰው ሁሌ እየለፈፉ ጊዜአቸውን በከንቱ ከማባከን ይልቅ ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ጸጥታ እንዲሰፍን የጦርነት ታቡራቸውንና መጣን መጣን ማለቱን ቢተውት መልካም ነው። ጊዜው ተለውጧል። እሳት አቀባዪቻችን በዝተዋል። ሊያጫርሱን የሚሹ ብዙዎች ናቸው። ለዚህ ነው እኔ የጠ/ሚ መለስ ዜናዊን እልፈት በበሽታ ነው ብዬ የማልቀበለው። እንዲታመም ያደረገው ማን ነው? ለምን? በእውነትስ መለስ በህይወት ቢኖር ሃገሪቱ ዛሬ ባለችበት ሁኔታ ትገኝ ይሆን? መልሱ በጭራሽ ነው። ግን ምድሪቱ እንድትፍረከረክ ቀድመው እሱን ነው በሞት የሸኙት። የዓዞ እንባ የሚያፈሱልን ነጮችና አረቦች ሁሉ ለእኛ በጎ ነገር የሚመኙ አይደሉም። መንቃት እንዴት ያቅተናል። ዝንተ ዓለም ከመገዳደል ያለፈ የሃገሮችን መደርመስና አሁን ላይ በዓለም ዙሪያ የምናየውን የሽርክና ፓለቲካ መመዘን አስፈላጊ ነው። ምድሪቱ እንደ ሱዳን እንድትሆን ካማራቸው ወያኔዎች እንደ ለመድት ጦርነት ይክፈቱና የድሃ ልጅ ያስፈጅ/ይፍጅ። ትርፍ ግን በዚህም በዚያም አይኖርም። የሃበሻው የውሃ ወቀጣ ፓለቲካ ቅርጽና መልኩን እየቀያየረ የቆመውን እየዋጠ ይቀጥላል እንጂ ለውጥ ለማንም አይመጣም። ጦርነት ይብቃ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

190077
Previous Story

የወልቃይት አስተዳደር ለህወሃት ቁርጥ ያለ ምላሽ ሰጠ | “አብይን አህመድን ገርስሰን ጥለነዋል” ፋኖ ማርሸት | የመቀሌ – አዲስ አበባ መንገድ ፋኖ እጅ ገባ | ጀነራል አበባው ጀነራል ተገኝ አስቻለውን ገደለው | “ኢትዮጵያ ትፈርሳለች፤ ወልቃይትን እንይዛለን” ግምገማ | በአብይ ትዕዛዝ ሚ/ሩ በርካታ ሚሊዮን ብር ዘረፈ |

190097
Next Story

ዝናሽ ታያቸው ከአባቷ ጋር ተጣላች! | ዋናው ባለስልጣን ተገደለ ኮረኔሉም ተሸኘ | ፋኖ መርአዊን ተቆጣጠረ

Go toTop