April 5, 2024
1 min read

ጥያቄ፤ እንደገና ልማር – በላቸው ገላሁን

288358186 5211569042256804 2092752397205846827 n

288358186 5211569042256804 2092752397205846827 nፍዳ በአገር ሞልቶ
መከራ በርትቶ፤

ማስተዋል ተስኖኝ
ምፍቻው ቁልፍ ጠፍቶኝ

ባዝኜ ባዝኜ፤ ዋትቼ ዋትቼ
እራሴን መርምሬ ውስጤን ተመልክቼ፤

፟፟፟፟፟

አልኩ፤

የት አለ ማስተሬ
የት ሄደ ዶክተሬ

ወዴት ነው ማወቄ
የት ጠፋ መርቀቄ፤

የት አለ ደብተሬ
የት ሄድዋል ብዕሬ?

ያየቸከቸኩት በጠባ በነጋ ይታደገኝ ብዬ ከመከራ አለንጋ፤ ፌደል የቆጠርኩት ፈተና ያለፍኩት ያነበብኩ የጻፍኩት ያየሁ ያዳመጥኩት

ያሁሉ እውቀቴ ምጡቅ ምርምሬ ወዴት ተበተነ ትቢያ ሆነ ዛሬ፤ ብዬ ብመራመር አውጥቼና አውርጄ

ይህ እውቀት የምለው ከንቱው ልምምዴ ከህሊና ይልቅ ገባሪው ለሆዴ

ከቶ አልጎበኘኝም አልረገጠም ደጄ።

ዋ!

ይኸው በዚህ ምክንያት ይኸው በዚህ ሳንካ
ለእኔ ብዬ አልሰማ ወንድሜ ሲነካ፤

አልገለጥ አለኝ ተሳነኝ ነግ በኔ
የምቀጥል እኔ ተርተኛ መሆኔ።

እንግድያስ፤

ልከልስ ከጀልኩኝ እንደገና አስክዋላ
ሀ ብሎ መጀመር ክጥንቱ ከህዋላ

ምን አልባት ምን አልባት አቅሌ አደብ ገዝቶ
ሀ! ብዬ ከመማር ዋ! ብዬ ላይ ረግቶ

ይፈታ ይሆናል ይህ ሁሉ መከራ
ሰው ሰው ያላረገኝ ያወጣኝ ከተራ።

ፒትስበርግ

በላቸው ገላሁን
ሚያዝያ 2016

1 Comment

  1. ያሳዝናል የአላሙዲ ሃብት አልተወረሰም ትግሬዎቹም የዱጉማን ሃብት አልወረሱም የጻድቃንም ሆነ የሃግሪቱን አጥንት የጋጡ ትግሬዎች ሃብት አልተወረሰም የወርቁ አይተነው አገር መከራ ላይ በወደቀችበት ጊዜ እንደ አንድ የጦር ሰው ከጦሩ ጋር ሲዋጋ የነበረ ዜጋ አማራ ብቻ ስለሆነ ሃብቱ ተወርሷል፡፡ አማራ ያለው መንግስት ምን ያህል እንደሚጠላህ ከዚህ የተሻለ ማሳያ የለም ጉዳዩ በልተህ ተቀድስ ነው፡፡ አቶ ዳን ኤል ክብረት ነገር ሲለወጥ አንተን አያድርገኝ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

189638
Previous Story

“የግድያ ሙከራ መርዝ አበሉኝ” ክርስትያን | የሚኒሊክን ሃውልት እናፈርሳለን | ሚንስትሩ ላይ በአ.አ የግድያ ሙከራ |

189645
Next Story

ከግሸን ገዳም የተላከልኝ ቪዲዮ | የአብይ ወታደር አሳፋር ተግባር | ቆይ ምን ይሻላል ??

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop