April 5, 2024
4 mins read

ከግሸን ገዳም የተላከልኝ ቪዲዮ | የአብይ ወታደር አሳፋር ተግባር | ቆይ ምን ይሻላል ??

በግሸን ማርያም የሚሰማው እጅግ ይዘግንናል፡፡ የአብይ አህመድ ወታደሮች የቆረቡ መነኮሳት እንስቶችን በቡድን ሆነው መድፈራቸውን የአይን እማኞች ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ ይሄ በታሪክ እንዴት እንደሚመዘገብ አላውቅም፡፡በአህመድ ግራኝ ሳይሆን በአብይ አህመድ የተደጸመ ነው፡፡ ደብረ ኤልያስ ገዳም ከ600 መቶ በላይ መነኮሳት ሲታረዱ ዝም አልን፡፡ የኦሮምያ ቤተ ክህነት በሚል አያሌ ምዕመናን ሲታረዱና ቤተ ክርስትያናት ሲቃጠሉ ዝም፤ ዝቋላ ገዳም አባቶችን ጨምሮ በብዙ ገዳማትና የአብነት ት/ቤቶች አማኞች ሲገደሉ ዝም፤ ዛሬ ተራው የግሸን ማርያም ሆኗል፡፡ እስከመቼ ዝም?  በእውነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኝ ህዝብ እውነት አማኝ ክርስትያን ቢሆን በአንድ ቀን አመጽ በደሉ ይቆም ነበር፡፡ ህዝበ ክርስትያኒ ቢነሳ አብይ አህመድ አንድ ቀን በአራት ኪሎ አይውልም ነበር፡፡ ቤተ ክርስትያኒቱ የደለበ አቅም አላት፤ተቋማትም አሏት፤ በእውነት ቢሰራ ማህበረ ቅዱሳን የሚባለው ተቋም ብቻ ይበቃ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ አንድም የቤተ ክርስትያኒቱ ተቋማት ችግሩን በድፍረት ሲታገሉ አይታይም፡፡ ለምን?
ኦርቶዶክስ አማኝነት ነጣላ ለብሶ ቤተክርስትያን መሄድ ወይም ግዜው እንዳመጣው በተክሊል ሰርግ ማድረግ ወይም በበዓላት ቀን በሃበሻ ልብስ ደምቆ መታየት አይደለም፡፡ ኦርቶዶክስ እምነቷ ጸንቶ የኖረው በመራራ ትግል ነው፡፡ በስንፍና የሚገኝ ሃይማኖትም ይሁን እምነት አይኖርም፡፡ አባቶችም ጭምር ክርስትናው የገባቸው አይመስሉም፡፡
መፍትሄው ምን ይሁን? መንግስት መምራት ሲያቅተው የፋኖ ትግል እንደተጀመረ ሁሉ ሲኖዶስ ቤተክርትታኒቱን መምራት ስላልቻለ በካህናት የሚመራ የታችኛው መዋቅር መነሳት አለበት፡፡ ቤተ ክርትያኒቱን በትጋት የሚያገለግሉት ካህናትና ዲያቆናት አመራሩን ከጳጳሳት በመረከብ ለህዝቡ ቅርብ የሆኑት ካህናት፤ ዲያቆናትና የአብነት ተማሪዎች ህዝቡን ይዘው መታገለ አለባቸው፡፡ ጳጳሳቱ ከአዲስ አበባ ቁጭ ብለው ህዝቡን ሊታደጉት አልቻሉም፡፡ እንዴውም የችግሩ አካል ሆነዋል፡፡ታቦት ተወርውሮ ሲጣል ዝም የሚል ጳጳስ አባት አይደለም፡፡ አሁን የቀረው እንደተባለው ፓትርያርኩ መታረድ ብቻ ነው፡፡ አያድርገው እንጅ ፓትርያርኩን አንድ ቢያደርጓቸው የሚቆጣ የቤተክርስትያኒቱ ተቋም የለም፡፡ በቤተ ክርስትያኒቱና በአማኞች ላይ ያልተሰማ ግፍ የለም፡፡ አባቶች ለምን ዝም ይላሉ? የቤተ ክርስትያኒቱ ተቋማትስ የት አሉ? የቄርሎስና የዮሃንስ አፈወርቅ ልጆች የት አሉ? በበዓላት ላይ ደምቆ መታየት፤በጣዕመ ዜማ እየዘመሩ አምላክን ማመስገን የሚቻለው ቤተ ክርስትያኒቱ ስትኖር ብቻ ነው፡፡ ይሄ ትውልድ እመንቱን ከእጁ እየተነጠቀ መሆኑን ማወቅ፤ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡አማኝ የሆነ ሁሉ ሰይፉን ይዞ መታገል አለበት፡፡

Kaleb Menberu

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop